30/08/2026
ነሀሴ 24/2018 ዓ.ም
በእኖር ኤነር መገር ወረዳ "አንድም ተማሪ በትምህርት ቁሳቁስ እጥረት ከትምህርት ገበታው ውጭ አይሆንም!" በሚል መሪ ቃል በክረምት በጎ ፈቃድ የተሰበሰበውን የተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል።
በወረዳው ለጓረባ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለ40 አቅመ ውስንነት ያለባቸው ተማሪዎች የአካባቢው ተወላጅ በሆኑት በአቶ ግርማ ተክሌ እና በወይዘሮ ውድነሽ ታደሰ እንዲሁም በቤተሰቦቻቸው 40 ደርዘን ደብተር ፣ እስክሪብቶ እርሳስ ፣ ላፒስ፣ መቅረጫ እና የስዕል ደብተር ተበርክቶላቸዋል።
በድጋፍ ርክክቡ ላይ የተገኙት የእኖር ኤነር መገር ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ኤሊያስ ሸምሱ የትምህርት ቁሳቁስ እርዳታው ህፃናትን በትምህርት ቁሳቁስ ችግር ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው እንዳይስተጓጎሉ እና ትምህርታቸውን በእኩልነት መከታተል እንዲችሉ በማሰብ ነው ብለዋል።
የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በማህበረሰቡ የድጋፍ መስክ አገልግሎት የተማሪዎች የመማሪያ ቁቁሳቁስ የደብተር እስክሪብቶ አሰባሰብ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ አቶ ኤሊያስ ተናግረዋል።
የተደረጉት የትምህርት ቁሳቁሶቹ ለተማሪዎች በወቅቱ እንዲደርሱና በትምህርት ጉዟቸው የሚያጋጥማቸውን የመማሪያ ቁሳቁስ እጥረት ለማቃለል የሚያግዙ ናቸው ብለዋል።
እንደዚህ ያሉ የበጎ አድራጎት ተግባራት በማህበረሰቡ ውስጥ የእርዳታ ባህልን ለማጎልበት እና ተማሪዎችን ለትምህርት ለማበረታታት ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለው ገልፀዋል።
በመሆኑም ይህ በጎ ተግባር ሊበረታታ የሚገባና ትልቅ የህሊና እርካታን የሚሰጥ በመሆኑ ለዚህ ሰናይ ተግባር ላበረከቱ አካላት በትምህርት ጽ/ቤት ስም አቶ ኤሊያስ አመስግነዋል።