13/10/2025
የዳኝነት እና የፍትህ ጥመርታ ፍትህን ለማስፈን የሚሰጠው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው:- ክቡር ፕረዚዳንት አምሳሉ አበራ
❇❇❇❇❇❇❇❇❇❇❇❇❇
ቦምቤ:-ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም በወላይታ ዞን ቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ፍርድ ቤት የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም የወረዳ እና ከተማ ፍትህ ተቋማት ጋር ግምገማ አካሄደዋል።
መድረኩን የመሩት የቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ፍርድ ቤት ፕረዚዳንት ክቡር አምሳሉ አበራ የዳኝነት እና የፍትህ ጥመርታ ፍትህን ለማስፈን የሚሰጠው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል።
ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት መስጠት የህዝቦችን መብት ማስከበር እንደሆነ የገለፁት ክቡር ፕረዚዳንት ባለድርሻዎች ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመግባባት መሥራት ይገባል ሲሉ አብራርተዋል።
በ2018 በጀት ዓመት በ1ኛ ሩብ ዓመት ፍትህን ለማስፈን በተደረገው ጥረት ብዙ መሻሻሎች ቢኖሩም የህዝባችንን ተጠቃሚነት እና ፍትህን ከማረጋገጥ ጋር በተያዜ በሚደረገው ጉዞ ላይ በትኩረት መስራት ያስፈልጋል።
ዳኞችና ዓቃቢያን ፍትህን ለማስፈን አቅምን ከፍ አድርገው መንቀሳቀስ ግድ ይለዋል ያሉት ክቡር ፕረዚዳንት አምሳሉ በፍርድ ቤት ውስጥ የሚሰሩ ዳኞች በሕግ አተረጓጎም ረገድ ያላቸውን እውቀት እርስ በርስ በመረዳዳት አቅማቸውን የሚያጎለብቱበት ሁኔታ ተፈጥሯል ብለዋል።
በወረዳ እና ከተማ አስተዳደር ደረጃ በየጊዜው የሚፈጸመው ወንጀል እና ወንጀል ነክ ጉዳዮች በመርመር እና ፍትሃዊ ዉሳኔ መስጠት ጋር በተያዘው መርማሪ ፖሊስ ቀልጣፋና ውጤታማ ሥራ በማድረግ ተገቢ ዉሳኔ መስጠት ይገባል።
የዳኞች እና የፍትህ ተቋማት ጥመርታ ለቀልጣፋና አስተማማኝ ፍትህ ማረጋገጥ የሚሰጠው ሚና ወሳኝ እንደሆነ በመገንዘብ ሁሉም ባለድርሻዎች ከሚመለከታቸው ጋር በቅንጅትና በመግባባት መሥራት ያስፈልጋል ተብለዋል።
በወረዳና ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ተቋማት ዉስጥ የነበረው አለመግባባት የህዝቦችን መብትና ፍትህን ለማረጋገጥ ሲል ቅሬታቸውን በዕርቅ እንድያልቅ ተደርጓል።
በመድረክ ላይ የቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ፍርድ ቤት ፕረዚዳንት የተከበሩ አምሳሉ አበራ፣ የወረዳ ፍርድ ቤት ዳኞች፣ የወረዳና ከተማ አስተዳደር ፍትህ ተቋማት ኃላፊዎች፣ የሁለቱ መዋቅር ፖሊስ አዛዦች፣ ዓቃቢያን እና ሌሎች አካላት ተሳትፈዋል።
ምንጭ:- #የቦሎሶ-ቦምቤ-ወረዳ-ፍርድ-ቤት-ነው