Addis Ketema Communication-አዲስ ከተማ

Addis Ketema Communication-አዲስ ከተማ This is Addis Ketema Sub-city Communication Office's Offical page,Come and join us!
(2)

ለዓለም ከተሞች ምሳሌ የሆነች ከተማ - አዲስ አበባ አዲስ አበባ  ዝቅተኛ የአደጋ ተጋላጭ የሆነች፥ ደህንነቷ የተጠበቀና የአየር ንብረት ለውጥን የምትቋቋም ከተማ በሚል  ከአፍሪካ ቀዳሚ ከዓለ...
17/09/2026

ለዓለም ከተሞች ምሳሌ የሆነች ከተማ - አዲስ አበባ

አዲስ አበባ ዝቅተኛ የአደጋ ተጋላጭ የሆነች፥ ደህንነቷ የተጠበቀና የአየር ንብረት ለውጥን የምትቋቋም ከተማ በሚል ከአፍሪካ ቀዳሚ ከዓለም ሁለተኛ ከተማ ሆና ተቀምጣለች።

የጂኦስፓሻል ኩባንያ አልፋ ጂኦ በዋነኝነት በሶስት መመዘኛዎች የአዲስ አበባ ከተማን የመዘነ ሲሆን አካላዊ የአየር ንብረት ለውጥ፥ አደጋ ተጋላጭነት፤ሊገጥሙ ለሚችሉ አደጋዎች አስተዳደር እና ፖሊሲ ምላሽ እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥ የማላመድ እርምጃዎች ላይ በማተኮር ነው ምዘናው የተካሄደው።

በእነዚህ መመዘኛዎች አዲስ አበባ ከተማ ከ72 ከተሞች ጋር ተወዳድራ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ለዓለም ከተሞች ምሳሌ ሆናለች፡፡

በዓለም የስልጣኔ ቁንጮ የተባሉትን እንደነ ፓሪስ እና ለንደን የመሳሰሉት ከተሞች አስከትላ በዓለም ላይ የአየር ንብረት ተጋላጭነት የምትቋቋም ከተማ በሚል ከአሜሪካዋ ቺካጎ ቀጥሎ በቁንጮ ላይ የተቀመጠችው አዲስ አበባ በኮሪደር እና የመንዝ ዳርቻ ልማት ያከናወነችው ስራዎች እና የዘረጋቻቸው ዘመናዊ መሰረተ ልማቶች በዚህ ደረጃ እንድትቀመጥ አስችሏታል፡፡

አዲስ አበባ የዓለም ቀልብ የምትስብ ለነዋሪዎቿ ምቹ ከተማ ብቻ አይደለችም ከምቹነት ባለፈ የአደጋ ተጋላጭነቷ ዝቅተኛ የሆነች፥ ደህንነቷ የተጠበቀ የአየር ንብረት ለውጥን የምትቋቋም ከተማ ናት ፡፡

በዓለምአቀፉ ጂኦስፓሻል ኩባንያ አልፋ ጂኦ (Alpha Geo) ለአዲስ አበባ የተሰጠው ማረጋገጫ ለፖሊሲ አውጪዎች፤ ኢንቬስተሮች እና የመሰረተ ልማት ባለቤቶች አዲስ አበባ ከተማ በተመለከተ የውሳኔ ሀሳቦች ለመስጠት እጅጉን ጠቃሚ ነው፡፡

በዓለም ላይ የሚገኙ ከተሞች ፈጣን የህዝብ ቁጥር ጭማሪን እያስተናገዱ ሲሆን ይህ የሕዝብ ቁጥር በፍጥነት ማደግ አዳዲስ ፍላጎቶችን ይዞ የሚመጣ ሲሆን በዚያው መጠን ደግሞ ከተሞች ለሚፈጠሩ አዳዲስ ፍላጎቶች ፈጣን ምላሽ መስጠት ይገባቸዋል፡፡

በዚህ መርህ የተቃኘው የአዲስ አበባ ከተማ የወንዝ እና የኮሪደር ልማት ስራ ከተማዋ በዓለማቀፍ ደረጃ እውቅና እንዲቸራት እያደረገ ሲሆን በ8 ወንዞች 59 ኪሎ ሚትር ርዝመት ያለው የአዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻ ልማት ለበርካታ ችግሮች ሁሉን አቀፍ ምላሽ የሰጠ ነው፡፡

ወንዞችን ማልማት ከመዋብ ባለፈ ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች አሉት፤ የወንዞችን መበከል ይከላከላል፣ የጎርፍ አደጋን ይቀንሳል፣ የከተማዋን የሙቀት መጠን ይቀንሳል፥ ነዋሪዎች ንጹህ አየር የሚያገኙበትን፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የሚያደርጉበትን እና አዕምሮአቸውን የሚያድሱበትን ዕድል ይፈጥራል።

በመላው ሀገራችን ለሚገኙ ተማሪዎቻችን አዲሱ የትምህርት ዘመን ስኬታማ እንዲሆን እንመኛለን! ‎‎ወጣቱ ትውልድ ለኢትዮጵያ ትልቁ ሀብቷ በመሆኑ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጅማሮን ተከትሎ፤...
16/09/2026

በመላው ሀገራችን ለሚገኙ ተማሪዎቻችን አዲሱ የትምህርት ዘመን ስኬታማ እንዲሆን እንመኛለን!

‎ወጣቱ ትውልድ ለኢትዮጵያ ትልቁ ሀብቷ በመሆኑ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጅማሮን ተከትሎ፤ እያንዳንዱ ተማሪ ለላቀ እውቀት በትጋትና ጉጉት ትምህርቱን እንዲከታተል፣ ለጥሩ ውጤት በጽናት እንዲተጋ፣ እንዲሁም የሀገራችንን የወደፊት ዕድል መቅረጽ በሚያስችሉ ክህሎቶች እንዲገነባ አበረታታለሁ።

‎ ዛሬ እየተገበርነው ያለው በርካታ የልማት ሥራዎች የነገን ትውልድ ታሳቢ ያደረጉ በመሆናቸው፣ የዚህ ቀጣይ ዕድል ተጠቃሚ እና ባለአደራ እንደመሆናችሁ መጠን፣ የኢትዮጵያን ታላቅ የስልጣኔ ታሪክ ወደፊት ለማስቀጠል የእናንተ ቁርጠኝነት መሠረት እንደሆነ ሙሉ እምነቴ ነው።

‎ብቁ እና በራሱ የሚተማመን ትውልድ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ውስጥ የመምህራኖቻችን ትጋትና መሰጠት መሰረታዊ ምሰሶ ነው። ተማሪዎቻችንን ማነቃቃት፣ አቅማቸውን ማውጣት፣ እንዲሁም ነገ ተፎካካሪ ሆነው እንዲወጡ የሚያስችሏቸውን ዕውቀት፣ ክህሎትና እሴቶችን የማስታጠቅ አደራን ቀጥሉበት ስል በትህትና አሳስባለው።

‎በትምህርት ዘርፉ ውስጥ ለምትገኙ ባለድርሻ አካላት በሙሉ፤ ስኬታማ እና ፍሬያማ የትምህርት ዘመን እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

የዛሬን ኑሮ እያሻሻሉ የነገን ትውልድ የመገንባት ስትራቴጂ በአዲስ አበባየኢትዮጵያ የልብ ምት የሆነችው አዲስ አበባ ባለፉት አምስት ዓመታት የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባሻገር፣ የነዋሪዎችን የ...
15/09/2026

የዛሬን ኑሮ እያሻሻሉ የነገን ትውልድ የመገንባት ስትራቴጂ በአዲስ አበባ

የኢትዮጵያ የልብ ምት የሆነችው አዲስ አበባ ባለፉት አምስት ዓመታት የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባሻገር፣ የነዋሪዎችን የኑሮ ጥራት እና አስተሳሰብ በማሻሻል ወደ አዲስ የብልጽግና ምዕራፍ እየተሸጋገረች ትገኛለች።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተደጋጋሚ እንደሚያነሱት ከተማዋ የምትከተለው የልማት ስትራቴጂ ትውልድ ግንባታን ማጠንጠኛ ያደረገ "ሰው-ተኮር" ተግባር ነው።

የዚህ የለውጥ ጉዞ መሠረት አስተሳሰብን መለወጥ በመሆኑ ይህንኑ መርህ ከትምህርት ቤቶች ጀምሮ በተግባር እየተረጎሙት ይገኛሉ።

"ትልልቅ ፕሮጀክቶችን ስንገነባ ልጆቻችን የሚረሱባት ከተማ ልትሆን አይገባም" በሚል ጽኑ አንድ ሚሊዮን ገደማ ለሚሆኑ ተማሪዎች በቀን ሁለት ጊዜ የምገባ መርሐ ግብር መተግበሩ የዚሁ ስኬት ማሳያ ነው።

ከዚህ ቀደም በከተማዋ የመንግሥት የሕጻናት መዋያ አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ያልነበረ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ቁጥራቸውን ከ1 ሺህ 100 በላይ ማድረስ ተችሏል።

በተጨማሪም የሕጻናት መጫወቻ ስፍራዎች ከ20 ወደ 5 ሺህ 500 ከፍ መደረጋቸው አስተዳደሩ ለትውልድ ግንባታ የሰጠውን ልዩ ትኩረት በጉልህ ያሳያል።

ይህ ሰው-ተኮር የልማት አቅጣጫ በትምህርት ዘርፍ ብቻ የተገደበ አይደለም። አቅመ ደካሞችን ታሳቢ ያደረጉ የቤት እድሳት እና ግንባታ ፕሮጀክቶች፣ ለነዋሪው ምቹ የሆኑ ዘመናዊ መዝናኛ ስፍራዎች እና ፓርኮች ግንባታ፣ እንዲሁም የጤና ተቋማት ማስፋፊያ ስራዎች የዚሁ ትውልድን የመቅረጽ እና የዜጎችን ክብር ከፍ የማድረግ የተቀናጀ ራዕይ አካል ናቸው።

አስተዳደሩ በቀጣይ ዓመታት የትምህርት ዘርፉን ይበልጥ ለማዘመን ተደራሽነትን፣ ጥራትን እና ፍትሃዊነትን በዋና ምሰሶነት ነድፎ እየሠራ ነው።

ከንቲባዋ እንደገለጹት የስኬት መለኪያው በፈተና የሚያልፉ ተማሪዎች ውጤት ብቻ ሳይሆን፣ የተማሪዎችን እውነተኛ "ልቀት" ማረጋገጥ ነው።

ዘንድሮ በ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና የተመዘገበው የ96 በመቶ የማለፍ ምጣኔ እጅግ አበረታች ቢሆንም፣ የከተማ አስተዳደሩ ዋነኛ ግብ ከዚህ የዘለለ መሠረታዊ እና ዘላቂ የጥራት ለውጥ ማምጣት ነው።

ትምህርት ቤቶችን ከአዋኪ ድርጊቶች ሙሉ ለሙሉ ነጻ በማድረግ ጤናማ የመማር ማስተማር አካባቢን በመፍጠር ረገድ የተከናወነው ተግባር ሌላው ስኬት ነው።

ተማሪዎች በስጋት ሳይሆን በተረጋጋ መንፈስ እንዲማሩ የትምህርት ቁሳቁስና የደንብ ልብስ አቅርቦትን በነጻ ማሟላት ተችሏል።

በተጨማሪም ተማሪዎች በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የሚያሳልፉትን ጊዜ በመገደብ ትኩረታቸውን በትምህርታቸው ላይ ብቻ እንዲያደርጉ ከወላጆች ጋር በቅንጅት እየተሠራ ነው።

ከዚህ ጎን ለጎንም ያለ መምህራን ብቃት የታለመውን ልቀት ማምጣት ስለማይቻል የመምህራንን አቅም መገንባት እና ጥቅማጥቅሞችን ማሻሻል ቀዳሚ ተግባር ሆኖ በመተግበር ላይ ይገኛል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እያካሄደ ያለው የለውጥ ጉዞ በመንግስትና በሕዝብ መካከል በተፈጠረ ጠንካራ የጋራ መተማመን ላይ የተመሠረተ ነው።

ከተማዋ በትምህርት፣ በጤና፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ እና መሰረተ ልማት ዝርጋታ እያስመዘገበች ያለው ስኬት በቀጣይ ዓመታት ለኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ ትልቅ አቅም የሚፈጥርና በአፍሪካ ደረጃም የከተማነት ተምሳሌት ሆኖ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

በ2019 የትምህርት ዘመን ተማሪዎች በስነምግባር ታንፀውና በእውቀት ዳብረው እንዲወጡ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ::************መስከረም  5-2019ዓምበአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በሚ...
15/09/2026

በ2019 የትምህርት ዘመን ተማሪዎች በስነምግባር ታንፀውና በእውቀት ዳብረው እንዲወጡ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ::
************
መስከረም 5-2019ዓም
በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በሚገኙ ሁሉም የመንግስትና የግል ት/ቤቶች የ2019 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሂደት በይፋ ተጀምሯል፡፡

በተያዘው የ2019 የትምህርት ዘመን የትምህርት ጥራትን ከማረጋገጥ በተጨማሪ ተማሪዎች በስነምግባር ታንፀውና በእውቀት ዳብረው እንዲወጡ ማድረግ የሁሉም ሃላፊነት በመሆኑ በቅንጅት እየተሰራ ነው::

መንግሥት ለትምህርት ጥራትና ትውልድ ግንባታ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ሲሆን ብቁ ትውልድ ለመገንባት ለተማሪዎች ምቹና ዘመናዊ የመማሪያ አካባቢን በመፍጠር የትምህርት ቤቶች ማስፋፊያና አዳዲስ ግንባታ፣ ደረጃቸውን የጠበቁ የመመገቢያ ክፍሎች መገንባት እንዲሁም ቤተ-መጻሕፍትና ቤተ-ሙከራዎችን ማስፋፋትና ማዘመን ስራዎች ተሰርተዋል::

በተጨማሪም የተማሪዎች የተመጣጠነ ምገባ ፕሮግራም እና የትምህርት ግብአት አቅርቦት ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ተማሪዎችም በደስታና በከፍተኛ ተነሳሽነት ትምህርታቸውን መጀመራቸውን ለመታዘብ ችለናል።

በእሸት ት/ቤት በተካሄደው የትምህርት ማስጀመሪያ መልዕክት ያስተላለፉት የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ብሩክ ተ/ማርያም የ2019 የትምህርት ዘመን የመመር ማስተማር ሂደት በክፍለ ከተማው በሚገኙ ሁሉም የመንግስትና የግል ት/ቤቶች በጀመሩን ገልፀው ለተማሪዎች ውጤት መሻሻል ከዘርፉ ባለድርሻች ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

አዲስ ከተማ ኮሙኒኬሽን ለሁሉም ተማሪዎች መልካም የትምህርት ዘመን ይመኛል!!

# # # # # # # # # # # # # #
መረጃን ከምንጭ በተለያየ አማራጭ
https://linktr.ee/Addis_Ketema_Communication

አዲስ አበባ የእህትማማች ከተሞች ትስስርን በማስፋት ከዓለም ከተሞች ጋር ያላትን ግንኙነት እያሳደገች ነው፡፡አዲስ አበባ በተለያዩ ዘርፎች የጋራ ትብብርን ለማጠናከር በምታደርገው ጥረት ባለፉት...
15/09/2026

አዲስ አበባ የእህትማማች ከተሞች ትስስርን በማስፋት ከዓለም ከተሞች ጋር ያላትን ግንኙነት እያሳደገች ነው፡፡

አዲስ አበባ በተለያዩ ዘርፎች የጋራ ትብብርን ለማጠናከር በምታደርገው ጥረት ባለፉት አምስት ዓመታት የከተማዋ የእህትማማች ከተሞች ትስስር ከ20 ወደ 30 ከተሞች አድጓል፡፡
አዲስ አበባ ባላት ታሪክ እና አሁን ላይ እያስመዘገበችው ባለው ሁለንተናዊ ለውጥ በርካታ የዓለም ከተሞች የእህትማማችነት ግንኙነቱን እያሳደጉ ይገኛሉ፡፡

ይህ ከከተሞች ጋር የሚኖር ስትራቴጂካዊ ግንኙነት አዲስ አበባ ከዓለም አቀፍ ከተሞች ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስርን ያሳድጋል፡፡

በተጨማሪም ዘመናዊ የከተማ ልማት ልምዶችን እና ምርጥ ተሞክሮዎችን ለመለዋወጥ እጅግ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል፡፡
የአዲስ አበባ ለውጥ ዛሬ በሁሉም መልኩ የእይታ ማዕከል እንድትሆን አድርጓታል፡፡

ዓለምዓቀፍ ተቋማቶች ስብሰባዎቻቸውን አዲስ አበባ ላይ ለማድረግ ቀዳሚ ምርጫቸውን አድርገዋል፡፡

በ2018 በጀት ዓመት ብቻ 221 ዓለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ ኮንፈረንሶች በአዲስ አበባ ተካሂደዋል።

አዲስ አበባ ወደ ስማርት ሲቲ (ዘመናዊ ከተማ) ለመቀየር በምታደርገው ተከታታይ ጥረትና በምታስመዘግባቸው ስኬቶች በርካታ ዓለም አቀፍ ሽልማቶችንና እውቅናዎችንም አግኝታለች።

ከእነዚህ እውቅናዎች መካከልም በሪዮዲጀነሪዮ የተቀበለችው የምገባ ኘሮግራም ሽልማት፡ በደቡብ ኮሪያ የተበረከተውና ለከተማዋ አመራር እውቅና የሰጠው የሴኡል ስማርት ከተማ ሽልማት (2024)፡ ለቆሻሻ አወጋገድ ስርዓት መሻሻል በቦነስአይረስ የተሰጠው እውቅና፡ የC40 ከተሞች የብሉምበርግ ሽልማት፡ በናይሮቢ ኬንያ በተካሄደው የአፍሪካ ስማርት ከተሞች ኢንቨስትመንት ሰሚት የተሰጠው የአፍሪካ ምርጥ ስማርት ከተማ ሽልማት (2024)፡ አዲስ አበባ በመንገድ ደህንነትና ፍጥነት ማስተዳደር ላይ ባስመዘገበችው ውጤት በዓለም አቀፍ የከተሞች የዘርፉ ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ የሆነችባቸው ተጠቃሽ ናቸው፡፡

እነዚህ ዓለም አቀፍ እውቅናዎች የከተማዋን ሁለንተናዊ መልካም ገጽታ በዓለም መድረክ ላይ በግልጽ ያሳዩ ታላላቅ ስኬቶች ናቸው።

18ተኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ የሁለተኛ ቀናት ቆይታ፦‎‎የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ልዑካቸው ከመስከረም 2 /2019ዓ.ም ጀምሮ በተካሔደው 18ተኛው የብሪ...
14/09/2026

18ተኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ የሁለተኛ ቀናት ቆይታ፦

‎የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ልዑካቸው ከመስከረም 2 /2019ዓ.ም ጀምሮ በተካሔደው 18ተኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ ላይ መሳተፋቸው ይታወሳል፤

‎ መስከረም 3 ቀን፣ 2019 ዓ.ም የጉባዔው ሁለተኛ ቀን ‘‘ጽናትን፣ ፈጠራን፣ ትብብርን እና ዘላቂነትን መገንባት’’ በሚል መሪ ቃል የብሪክስ አባል እና አጋር ሀገራት መሪዎች እንዲሁም የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች በተሳተፉበት የተካሔደ ሲሆን፣ ጥምረቱ 140 የጋራ አቋሞችን የያዘ (የኒው ዴልሂ መግለጫ) በማውጣትም የመሪዎቹ ጉባኤ ተጠናቋል።

‎የብሪክስ ኒው ዴልሂ የአቋም መግለጫ የዓለም አቀፍ አስተዳደር ማሻሻያ፣ ዓለም አቀፍ እና ቀጣናዊ ሰላም፣ ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት እንዲሁም የህዝብ ለህዝብ ትሥሥርን ያካተቱ ዐበይት ጉዳዮች ላይ የአባል ሀገራቱን የጋራ አቋም ያንጸባረቀ ሲሆን ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉን የንግድ ድርጅት ለመቀላቀል የምታደርገውን ጥረት ጥምረቱ በጽኑ እንደሚደግፍ በድጋሚ አረጋግጧል፤ በዓለም አቀፍ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ምክር ቤት ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት ብቸኛ እጩ በመሆን ተጨማሪ መቀመጫ እንድታገኝ የሚደረገውን ጥረት በጽኑ እንደሚደግፍም አመላክቷል። በተጨማሪም ሀገሪቱ የዓለም አቀፉን የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ኮፕ 32 ለማዘጋጀት የጀመረችውን ተነሳሽነትና ዝግጅት እንደሚደግፉ በጋራ መግለጫቸው አረጋግጠዋል። ጥምረቱ 19ኛውን የብሪክስ ጉባኤ በቻይና አስተባባሪነት እንዲዘጋጅም በጋራ አጽድቋል።

‎ከመሪዎቹ ጉባኤ ጎን ለጎን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከአባልና አጋር ሀገራት መሪዎች ጋር በሁለትዮሽ የሀገራቱ ትብብር ዙሪያ ፍሬያማ ውይይቶችን ያካሄዱ ሲሆን፤ በንግድና ኢንቨስትመንት፣ በመከላከያ መስኮች ትብብር፣ በዲጂታላይዜሽን ዙሪያ ሊኖሩ ስለሚችሉ ትብብሮች በጥልቀት ተወያይተዋል።

‎በድኅረ ጉባኤ ለመሪዎች በተደረገው የእራት ግብዣ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከተለያዩ የብሪክስ አባል እና አጋር ሀገራት መሪዎች ጋር የታደሙ ሲሆን፤ የሁለት ቀናት የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤን አጠናቅቀው ተመልሰዋል።

14/09/2026

ከሱስ የፀዳ ትውልድ እንፍጠር በሚል የተካሄደው የኒኮላ ካፕ ውድድር የማጠቃለያ ድባብ

ከሱስ የፀዳ ትውልድ እንፍጠር በሚል መሪ ሐሳብ ለተከታታይ 12 ሳምንታት ሲካሄድ የቆየው 2ኛው የኒኮላ ሰመር ካፕ እግር ኳስ ጨዋታ ተጠናቀቀ::****************መስከረም  3-2019ዓ...
13/09/2026

ከሱስ የፀዳ ትውልድ እንፍጠር በሚል መሪ ሐሳብ ለተከታታይ 12 ሳምንታት ሲካሄድ የቆየው 2ኛው የኒኮላ ሰመር ካፕ እግር ኳስ ጨዋታ ተጠናቀቀ::
****************
መስከረም 3-2019ዓም

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት አዘጋጅነት ላለፉት 12 ሳምንታት ሲካሄድ የቆየው የ2018ዓም 2ኛው የኒኮላ ሰመር ካፕ ውድድር በጉለሌ ኒኮላ ቡድን አሸናፊነት ተጠናቀቀ።

20 የእግር ኳስ ቡድኖች የተሳተፉበት ጨዋታ ዛሬ ፍፃሜውን ሲያገኝ በወጣቶች ቡድን ጉለሌ ኒኮላ እግር ኳስ ቡድን ብራዚል ሰፈር ቡድን 2ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሻምፒዮን መሆን የቻለ ሲሆን እንዲሁም በጤና ቡድን አዲሱ ገበያ ቡድን ሻምፒዮን ሆኗል::

በፍፃሜ ጨዋታው የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ በአዕምሮና በአካል የዳበረ ጤናማ ትውልድ ለመፍጠር እንደዚህ አይነት ውድድሮች ሚናቸው የጎላ በመሆኑ አዲስ ከተማ አርዓያነት ያለው ተግባር ፈፅሟል ብለዋል::

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሮ ፋኪያ ሸሪፍ በበኩላቸው ከሱስ የፀዳ ጤናማና አምራች ትውልድ ለመገንባት መሰል ውድድሮች አስፈላጊ መሆናቸውን ገልጸዋል::

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ታደሰ ወርቁ በበኩላቸው ውድድሩ ስፖርታዊ ጨዋነትን በተላበሰ መልኩ እጅግ ባማረና በደመቀ ድባብ ተጠናቋል ብለዋል::

የወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት የስፖርት ውድድር ቡድን አስተባባሪ አቶ ዳኝነት አበበ በበኩላቸው 2ኛው የኒኮላ ሰመር ካፕ እግር ኳስ ውድድር ፍጻሜውን ሲያገኝ ለውድድሩ ኮከብ ጎል አስቆጥምሪዎች፣ ለኮከብ ተጨዋቾች እንዲሁም ለዳኞች ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ሲሉ ገልፀዋል ::

# # # # # # # # # # # # # #
መረጃን ከምንጭ በተለያየ አማራጭ
https://linktr.ee/Addis_Ketema_Communication

13/09/2026

"Economic uncertainty is testing our countries. BRICS has already reshaped
the global conversation. Our responsibility now is to help shape a fairer international system and widen economic opportunity."

Prime Minister Abiy Ahmed (PhD)

አባልና አጋር ሀገራትን ባሳተፈው የብሪክስ ፕላስ የምክክር መድረክ ላይ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጠንካራ የአፍሪካ ውክልና እንዲኖር፣ የፋይናንስ እና የገበያ ተደራሽነት ይበልጥ እንዲሰ...
13/09/2026

አባልና አጋር ሀገራትን ባሳተፈው የብሪክስ ፕላስ የምክክር መድረክ ላይ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጠንካራ የአፍሪካ ውክልና እንዲኖር፣ የፋይናንስ እና የገበያ ተደራሽነት ይበልጥ እንዲሰፋ እንዲሁም ንግድ፣ ኢንቨስትመንት እና ትስስርን ለማሳደግ ተግባራዊ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ጥሪ አቅርበዋል።

‎በዚህ አውድም፣ የኒው ዴቨሎፕመንት ባንክ አድማሱን በመላው አፍሪካ እንዲያስፋፋ የባንኩን ቢሮ በአዲስ አበባ ለማስተናገድ ኢትዮጵያ በሙሉ አቅም ዝግጁ መሆኗን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

‎በተጨማሪም በአዲስ አበባ የሚካሄደው ኮፕ 32 በብሪክስ ሙሉ ድጋፍ ለአየር ንብረት ጥበቃ ሥራዎች እና ለዘላቂ ልማት መፋጠን ሁሉንም ድምፆች የሚያሰባስብ ሁሉን አቀፍ መድረክ ሆኖ ማገልገል እንደሚችል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አስገንዝበዋል።

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis Ketema Communication-አዲስ ከተማ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Addis Ketema Communication-አዲስ ከተማ:

Shortcuts

Share