የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት

የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት, Political Party, omedla streat, Addis Ababa.

10/09/2026
ጳጉሜን 5 "የነገው ቀን" በሲያደብርና ዋዩ ወረዳ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን አቅምን ለማሳደግ ያለመ ስልጠና ተሰጠ፡፡ "የኢትዮጵያ መንሰራራት" በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከበሩ ...
10/09/2026

ጳጉሜን 5 "የነገው ቀን" በሲያደብርና ዋዩ ወረዳ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን አቅምን ለማሳደግ ያለመ ስልጠና ተሰጠ፡፡

"የኢትዮጵያ መንሰራራት" በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከበሩ ከሚገኙት የጳጉሜን ቀናት መካከል ጳጉሜን 5 "የነገው ቀንን" ምክንያት በማድረግ በሲያደብርና ዋዩ ወረዳ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን ለማፋጠን ያለመ ስልጠና ተሰጥቷል።
በሰሜን ሸዋ ዞን የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ አስተዳደር ኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ቡድን ከደነባ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ጋር በመተባበር በአዘጋጁት በዚህ መድረክ የመንግስት ሰራተኞች ከወቅቱ የቴክኖሎጂ እድገት ጋር እኩል መራመድ የሚያስችላቸው ግንዛቤ ተፈጥሮላቸዋል።
በስልጠናው ላይ የኢትዮ ኮደርስ (Ethio Coders) ፕሮግራም የኮዲንግ ጥቅም የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችና የመፍትሔ አቅጣጫዎች ዙሪያ በወረዳው ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቡድን መሪ በአቶ ሄኖክ በቀለ ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቷል።

የዲጂታል አማራ (Digital Amhara) ስራዎች የቴክኖሎጂ ሽግግርን ለማፋጠን፣ አሰራርን ለማዘመንና መረጃዎችን በፍጥነት ተደራሽ ለማድረግ ያለውን ሚና የደነባ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ አይሲቲ ኢንስትራክተር ከበደ ወግደረስ አብራርተዋል።
ሰልጣኞች የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመቋቋም ስልጠናውን በአግባቡ በመውሰድ የቴክኖሎጂ እውቀታቸውን ማሳደግ እንዳለባቸው በስልጠናው ወቅት ተመልሷል።



#ጳጉሜን5 #ነገውቀን
#ሲያደብርናዋዩ

የነገው ቀንሀገራዊ የቴክኖሎጂ ሽግግርከወረቀት ወደ ዲጂታል፤ ከተጠቃሚነት ወደ ፈጣሪነት! ትናንትን በመማርና በማረም ዛሬን በላቀ ትጋት በመገንባት ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የዕለት ተዕለት ባህላ...
10/09/2026

የነገው ቀን
ሀገራዊ የቴክኖሎጂ ሽግግር
ከወረቀት ወደ ዲጂታል፤ ከተጠቃሚነት ወደ ፈጣሪነት! ትናንትን በመማርና በማረም ዛሬን በላቀ ትጋት በመገንባት ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የዕለት ተዕለት ባህላችን እየሆነ ነው። ንግድና አገልግሎትን ያቀላጥፋል፣ መረጃዎችን ተደራሽ ያደርጋል፣ ዘርፎችንም ያዘምናል! የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያ ኮደሮች ንቅናቄ ወጣቶችን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፈጣሪ በማድረግ ወደ 7 ሚሊዮን ግባችን እያመራ ሲሆን የዲጂታል አገልግሎት ተደራሽነትና ጥራትን አረጋግጧል። በሀገር በቀል አቅም የበለጸገው የሳይበር ሉዓላዊነታችን ደግሞ የማንቆጣጠራቸው ቴክኖሎጂዎችን ጥገኝነት አላቆ በዲጂታል ኢኮኖሚ በራስ አቅሟ የምትቆም አዲሷ ኢትዮጵያ በታላቅ ምዕራፍ ላይ መሆኗን በኩራ ነው።

የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ገቢዎች ጽሕፈት ቤት የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸሙን በመገምገም የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ አካሄደ።የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ገቢዎች ጽሕፈት ቤት የ201...
09/09/2026

የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ገቢዎች ጽሕፈት ቤት የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸሙን በመገምገም የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ አካሄደ።

የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ገቢዎች ጽሕፈት ቤት የ2018 በጀት ዓመት የገቢ ሰብሰባ ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት የገቢ ዕቅድ ትውውቅ ከባለድርሻና ከአጋር አካላት ጋር አካሂደዋል።

በመድረኩ የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ አብነት ጥላዬ እንደገለጹት፤ በ2018 በጀት ዓመት ከ156 ሚሊዮን ብር በላይ በመሰብሰብ የዕቅዱን 96 በመቶ ማሳካት ተችሏል ብለዋል።

ኃላፊው አክለውም በ2019 በጀት ዓመት 288.8 ሚሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ ታቅዶ ወደ ሥራ መገባቱን ጠቁመው፤ የተጣለውን የገቢ ዕቅድ ለማሳካት አጋርና ባለድርሻ አካላት ልዩ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ም/አስተዳዳሪ አቶ ተፈሪ በሱፍቃድ የወረዳውን ፀጋ አውቆ በትኩረት መምራትና መስራት ያስፈልጋል ያሉ ሲሆን የወረዳችንን አጠቃላይ የልማት እንቅስቃሴና የሕዝባችንን ተጠቃሚነት ለማሳለጥ የገቢ አሰባሰብ ስርዓቱን ማጠናከርና የድርሻችንን መወጣት ወሳኝ መሆኑም በአፅንኦት ገልፀዋል።

የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተገኝወርቅ ሸዋዬ የ2018 በጀት ዓመት የገቢ አሰባሰብ በትኩረት በስራትና የተሰጠን እቅድ በአግባቡ መፈፀምና በ2019 በጀት ዓመት የታቀደውን የገቢ ግብ ለማሳካት የሚያስችሉ ስልቶችና የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ትኩረት አድርጎ መሰራት አለበት ብለዋል ።

በመጨረሻም በ2018 በጀት ዓመት የገቢ አሰባሰብ ሂደቱ ስኬታማ እንዲሆን የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አጋርና ባለድርሻ አካላት፣ ለንግዱ ማህበረሰብ ተወካዮችና ለምስጉን ግብር ከፋዮች የዕውቅና የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።

ጳጉሜን 4 "የህብር ቀን" በሲያደብርና ዋዩ ወረዳ በደማቅ ሁኔታ በተለያዩ ተግባራት ተከበረ፡፡"ብዝሃነታችን የውበታችንና የጥንካሬያችን ምስጢር ነው!"የተለያዩ ባህሎች፣ ቋንቋዎችና ማህበራዊ እ...
09/09/2026

ጳጉሜን 4 "የህብር ቀን" በሲያደብርና ዋዩ ወረዳ በደማቅ ሁኔታ በተለያዩ ተግባራት ተከበረ፡፡

"ብዝሃነታችን የውበታችንና የጥንካሬያችን ምስጢር ነው!"

የተለያዩ ባህሎች፣ ቋንቋዎችና ማህበራዊ እሴቶች ባለቤት የሆንን የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች የብዝሃነታችንን ጌጥ የምንገልጽበትና አብሮነታችንን የምናጠናክርበት ጳጉሜን 4 "የህብር ቀን" በወረዳችን በርካታ ሰው ተኮርና ማህበራዊ ተግባራትን በማከናወን በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል።

በፕሮግራሙ ላይ የወረዳው አመራሮች፤ የመንግስት ሰራተኞችና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት የወንድማማችነትና የጤናማ ህይወት መግለጫ የሆነ የጋራ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ እንዲሁም ብሔር ብሔረሰቦች ውብ ባህላዊ ውዝዋዜዎች ቀርበው የእለቱን ዓላማ የሚያጎላ ውይይት ተካሂዷል።

ለተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ስርጭት፣ ለተቸገሩ ወገኖችም የአልባሳት ድጋፍ ፣ ነጻ የህክምና አገልግሎት ለአቅመ-ደካሞችና ድጋፍ ለሚሹ ወገኖችም በነጻ የተሰጠ ሲሆን ለችግረኛ ወገኖች በክረምት በጎፍቃድ አገልግሎት እየተገነቡ ያሉ መኖሪያ ቤቶችም በመገኘት በዓሉ በድምቀት ተከብሯል፡፡

የህብር ቀን የልዩነትን ውበት በመጠበቅ፤ አብሮነትን፣ መተባበርንና የጋራ ኃይልን ለማጠናከር የሚያስችል ትልቅ መልዕክት ያለው ሲሆን፣ በእለቱ የተከናወኑት ተግባራት ማህበራዊ ትስስርን ያጠናከሩና ለተማሪዎቻችን ትልቅ አለኝታነትን ያሳዩ እንደነበሩ ተገልፃል።

"በአንድነትና በህብር አብሮነታችን ይጎልብት!" 🇪🇹

#የህብርቀን #ጳጉሜ4 #ብዝሃነት
#ሲያደብርናዋዩ #አብሮነት
#ኢትዮጵያ

ጳጉሜን 3 — የፅናት ቀን፤ ሀገራዊ ፅናት ለሕዝብ ሰላምና ለሁለንተናዊ ዕድገት መሠረት ነው በሲያደብርና ዋዩ ወረዳ የህዝባችንን ሰላም በማረጋገጥ  የልማት ስራዎቻችን በማሳለጥ የህዝባችንን ተ...
08/09/2026

ጳጉሜን 3 — የፅናት ቀን፤ ሀገራዊ ፅናት ለሕዝብ ሰላምና ለሁለንተናዊ ዕድገት መሠረት ነው

በሲያደብርና ዋዩ ወረዳ የህዝባችንን ሰላም በማረጋገጥ የልማት ስራዎቻችን በማሳለጥ የህዝባችንን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ያስፈልጋል።

"የኢትዮጵያ መንሰራራት" በሚል መሪ ቃል እንደ ሀገር እየተከበረ የሚገኘውን የጳጉሜን ቀናቶች የጳጉሜን 3 «የፅናት ቀን» ምክንያት በማድረግ በሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ሀገራዊ ፅናት ለሕዝብ ሰላምና ለሁለንተናዊ ዕድገት መሠረት ነው በማለት በተለያዩ ወታደራዊ ትርኢቶችና ውይይትች ተከብራል።

በአሉን በሲያደብርና ዋዩ ወረዳ በአንጭቆረር ከተማ ከሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ ከወረዳው ፖሊስ አባላት፣ ከሰላም አስከባሪዎችና ከሚሊሻ አባላት ጋር ተከብሯል።

በፕሮግራሙላይም የወረዳው አመራሮች ተገኝተው አበረታተዋል። የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ እንኳን ለፅናት ቀን አደረሳችሁ በማለት የሀገር መከላከያ ሰራዊትና፣ ፖሊሳችን ሰላም አስከባሪያችን እንዲሁም ሚሊሻችን ለሀገር ሰላምና ለህዝባችን የከፈለውንና እየከፈላ ያለውን ዋጋ አንስተው አወያይተዋል።

የቀጠናው አስተባባሪ መቶ አለቃ ኤፍሬም ጌታቸው ሀገርን የመጠበቅና የመከላከል ጽኑ ዓቅማችንን የምንዘክርበት፣ ለሀገረ-መንግሥታችን ዘላቂነትና ለሉዓላዊነታችን ሲሉ ውድ ሕይወታቸውን የገበሩ የጀግኖቻችንን መስዋዕትነት በከፍተኛ ክብር የምናስብበት ልዩ ቀን ነው ብለዋል።

መቶ አለቃ ዳኛቸው አይደም በበኩላቸው የፅናት ቀንን ስናስብ የሉዓላዊነታችንና የሀገራዊ ፅናታችን ምስክር ነው ለህዝባችን የሚከፈለውን የህይወት ዋጋ የተሻለ ነገን በማሰብ ሰላምን ለማረጋገጥና የህዝባችንን ሰላም ለማስፈን በሀገር ደረጃም ለሁለንተናዊ ዕድገትና ልማትን ለማምጣት ነው ሲሉ ገልፀዋል።

07/09/2026
በሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ጳጉሜን 2  “የመንሰራራት ቀን” በታላቅ ድምቀት ተከበረ።በሰሜን ሸዋ ዞን በሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ጳጉሜን 2 — የመንሰራራት ቀን— የተለያዩ አበይት የልማት እንቅስቃሴ...
07/09/2026

በሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ጳጉሜን 2 “የመንሰራራት ቀን” በታላቅ ድምቀት ተከበረ።

በሰሜን ሸዋ ዞን በሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ጳጉሜን 2 — የመንሰራራት ቀን— የተለያዩ አበይት የልማት እንቅስቃሴዎችን በመጎብኘት በታላቅ ድምቀት ተከብሯል።

የ2018 ዓ.ም የጳጉሜን ቀናት ሀገራዊ መሪ ሐሳብ በሆነው “የኢትዮጵያ ማንሠራራት” በሚል እየተከበረ ይገኛል ይህን ምክንያት በማድረግ ጳጉሜን 2 የማንሰራራት ቀን በድምቀት ተከብሯል።

በወረዳችን እየተከናወኑ ያሉ አበይት የልማት ስራዎች የተጎበኙ ሲሆን የወረዳችንን የኢኮኖሚ ምሶሶ የሚያጠናክሩና የህዝባችንን የኑሮ ደረጃ ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋገሩ ተስፋ ሰጪ ፕሮጀክቶች ተጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ከተቃኙ ዋና ዋና የልማት ፕሮጀክቶች የአቶ ነዋይ ተሾመ የዱቄት ፋብሪካ ሲሆን ግንባታው ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ወደ ምርት ሂደት ለመግባት በዝግጅት ላይ የሚገኘው ይህ ፋብሪካ በስፋት ተጎብኝቷል። ወረዳችን በስንዴ ምርታማነቱ የሚታወቅ እንደመሆኑ መጠን፣ ፋብሪካው ወደ ሥራ መግባቱ ለወረዳችንና ለዞናችን አግራሮ-ኢንዱስትሪ ዕድገት ትልቅ አቅም የሚፈጥር፤ ለበርካታ ዜጎችም የሥራ ዕድል በማስገኘት በዕለታዊ ሕይወታቸው ላይ ጉልህ ሚና የሚያመጣ ነው።

የደነባ ከተማን የውሃ እጥረት በዘላቂነት ለመፍታት ከ17 ሚሊዮን ብር በላይ የተገነባው የጠዴ የውሃ ፕሮጀክት ሌላው የጉብኝቱ አቢይ አካል የነበረ ሲሆን፣ የህዝባችንን የመሠረተ ልማት ጥያቄ የሚመልስ አዎንታዊ እርምጃ እንደሆነ ተነስቷል።

አንድ ከተማ ለአንድ ፕሮጄክት በኢኔሸቲፍ ተግባር የተገነባውን የመዋለ ህፃናት ግንባታም በጉብኝቱ ተካቷል።

እነዚህ መሰል ፕሮጀክቶች መጠናቀቃቸውና የልማት እንቅስቃሴዎች መስፋፋታቸው የወረዳችንና የሀገራችን የማንሰራራት ጉዞ እውነተኛ ማሳያዎች መሆናቸው ተመላክቷል።

የአካባቢያችንን እምቅ የተፈጥሮና የግብርና ሀብት ወደ ተጨባጭ የኢኮኖሚ አቅም የሚቀይሩ የልማት ስራዎቻችን በላቀ ትጋት ይቀጥላሉ።

መልካም የመንሰራራት ቀን!


#ጳጉሜን2
#ደነባ

Address

Omedla Streat
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share