AAWSA Nifas Selk Branch

AAWSA Nifas Selk Branch የንፁህ ውሃ አቅርቦትና የዘመናዊ የፍሳሽ ማስወገድ አገልግሎት መስጠት፡፡
Provide clean water supply and modern sewerage services

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ንፋስ ስልክ ቅ/ጽ/ቤት በቀን 14/05/2014 የደንበኞች ፎረም ጠቅላላ አባላት የውይይት  መድረክ ተካሂዷል፡፡ የውይይቱ ዋና ዋና አጀንዳዎች፡-• የ20...
25/01/2022

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ንፋስ ስልክ ቅ/ጽ/ቤት በቀን 14/05/2014 የደንበኞች ፎረም ጠቅላላ አባላት የውይይት መድረክ ተካሂዷል፡፡
የውይይቱ ዋና ዋና አጀንዳዎች፡-
• የ2014 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም
• የአገልግሎት አሰጣጥ እና መልካም አስተዳደር ስራዎችን በተመለከተ እንዲሁም ከውይይቱ ተሳታፊዎች አስተያየቶችና ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን በአጠቃላይ በተነሱት አስተያየቶችና ጥቆማዎች ላይ የሚመለከታቸው የስራ ሀላፊዎች ማብራሪያና የመፍትሄ አቅጣጫዎች በማስቀመጥ የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ የእለቱ የውይይት መድረክ በጥሩ ሁኔታ ተጠኗቋል፡፡

03/01/2022

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የንፋስ ስልክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቀን 22/04/2014 ዓ.ም
በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በደንበኞች አገልግሎት በራስ ሀይል የተዘጋጀ አጭር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ለሁሉም የውሃ አገልግሎት ደንበኞች ሰራተኞች ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
የስልጠናው ዋና ዋና ይዘቶች፡-
•መልካም አስተዳደር
•አገልግሎት አሰጣጥ
•ገቢ አሰባሰብ
•የቆጣሪ ንባብ ጥራት
•ስታንዳርድ አገልግሎትና አመዘጋገብ
•MRT (የሞባይል ቴክኖሎጂ ቆጣሪ ማንበቢያ ሲስተም)
ስልጠናውን የሰጡት የቅ/ጽ/ቤቱ ሰራተኞች
1. አቶ መኮንን ቦጋለ(ከቆጣሪ ጋር የተገናኙ ቴክኒካዊ ጉዳዮች)
2. አቶ ብሩክ ጎሹ( የቆጣሪ ንባብ ጥራት፤ መልካም አስተዳደር፤ አገልግሎት አሰጣጥና ገቢ አሰባሰብ)
3. አቶ አማረ ትዛዙ( MRT የሞባይል ቴክኖሎጂ ቆጣሪ ማንበቢያ ሲስተም)
4. አቶ ፍቃዱ ሀብታሙ (ስታንዳርድ አገልግሎትና አመዘጋገብ)

03/01/2022

ታህሳስ 22/ 2014 ዓ.ም
ቅርንጫፉ የውሃ አገልግሎት ክፍያን በዘመቻ እያሰባሰበ መሆኑን ገለፀ

የንፋስ ስልክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በታህሳስ ወር መጀመሪያ ባደረገው ዘመቻ ከ3 ወር በላይ የውሃ አገልግሎት ክፍያ ያልፈፀሙ ደንበኞችን ቆጣሪ በማንሳትና አገልግሎት በቋረጥ ከ3.9 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ሰብስቧል፡፡

በተደረገው ዘመቻ የአገልግሎት ክፍያ ባለመክፈል ግዴታቸውን ያልተወጡ 1 ሺህ 981 ደንበኞችን የውሃ ቆጣሪ በማንሳት ውዝፍ ክፍያቸውን እንዲከፍሉ አድርጓል፡፡

ቅርንጫፉ በሁለት ዙር ለሁለት ሳምንት ባደረገው ዘመቻ 2 ሚሊየን 951 ሺህ 85 ብር የውሃ አገልግሎት ክፍያ ከማስከፈሉም በላይ 893 ሺህ 280 ብር የማስቀጠያ እንዲሁም 70 ሺህ 806 ብር የወለድ ቅጣት በማስከፈል በአጠቃላይ 3 ሚሊየን 915 ሺህ 117 ብር ገቢ ማሰባሰብ ችሏል፡፡

ከዘመቻው በተጨማሪ በቆጣሪ አንባቢዎች፣ በፎረም አባላት እና በደብዳቤ ለደንበኞች ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ በመሠራቱ ቅርንጫፉ ከሉት 78 ሺህ ደንበኞች መካከል 52 ሺህ የሚሆኑት ክፍያቸውን በወቅቱ መፈፀማቸውን የቅርንጫፉ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዮሴፍ አርጋው ገልፀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ንፋስ ስልክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የ3ኛው ዙር ጠቅላላ የደንበኞች ፎረም የምክክር መድረክ በ16/08/2013 የተዘጋጀ ሲሆን በዚህም መድረክ ላይ የተለያዩ ጉ...
28/04/2021

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ንፋስ ስልክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የ3ኛው ዙር ጠቅላላ የደንበኞች ፎረም የምክክር መድረክ በ16/08/2013 የተዘጋጀ ሲሆን በዚህም መድረክ ላይ የተለያዩ ጉዳዮች ተነስተዋል፡፡
የውይይቱ አጀንዳዎች
1. የ 2013 በጀት ዓመት የ9 ወር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርትና የውሃ ስርጭትን በተመለከተ በተለይ በፈረቃ መዛባትና መሰረተ ልማት ስርዓትን በተመለከተ ለፎረሙ አባላት አጭር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ተከናውኗል፡፡
ከደንበኞች ፎረም አባላት የተነሱት ጥያቄዎችና አስተያየቶች መካከል፡-
• በቀረበው የ 9ወር ዕቅድ ክንውን መልካም የሚባልና እየተሰሩ ያሉትን ስራዎችና ችግሮችን በግልፅነት ያሳየ ሪፖርት መሆኑን በመናገር በዚሁ ይቀጥል የሚል አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
• በወረዳዎች የውሃ አቅርቦት ችግር ያጋጠመ ሲሆን ይህንን ችግር ለመፍታት ጥረት እተደረገ መሆኑና በቀጣይ የውሃ ስርጭቱን የበለጠ ፍትሃዊ ለማድረግ የተለያዩ አማራጭ ስራዎች እተሰሩ ነው፡፡
• ባጠቃላይ በተነሱት ጥያቄዎችና አስተያየቶች በቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ እና በሚመለከታቸው የስራ ሀላፊዎች ምላሽና ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ችግሮችን ለመፍታት የተቻለውን ያህል ጥረት እየተደረገ መሆኑን በዚህም ላይ የህብረተሰቡ ተሳትፎና የፎረሙ አባላት ትልቅ ሚና ያላቸው ስለሆነ እገዛችሁን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ የሚል ሀሳብ የቀረበ ሲሆን ባጠቃላይ የነበረው የምክክር መድረክ በመልካም ሁኔታ ተፈፅሟል፡፡

በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የንፋስ ስልክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት  በቀን 06/06/2013 ዓ.ም የደንበኞች የመወያያ መድረክ የተዘጋጀ ሲሆን ከሀምሌ 1/2012 እስከ ታህሳስ 30/ 201...
15/02/2021

በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የንፋስ ስልክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቀን 06/06/2013 ዓ.ም የደንበኞች የመወያያ መድረክ የተዘጋጀ ሲሆን ከሀምሌ 1/2012 እስከ ታህሳስ 30/ 2013 የ ስድስት ወር የእቅድ አፈጻጸም ክንውን ሪፖርት የተመለከተ ነበር፡- በውይይቱ ላይ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት፤ ከ ወረዳዎች ና ከክፍለ ከተማ የተገኙ ሲሆን ከተነሱ ሀሳቦች መካከል
• በቀረበው ሪፖርት ላይ ደስተኛ መሆናቸውንና ማህበረሰቡን በ ቅንነት ለማገልገል የሚያደርገውን ጥረት አድንቀዋል፡፡
• የቀረበው ሪፖርት ግልጽና ሚዛናዊ መሆኑ
• የውሃ ስርጭት ፈረቃው ፍትሃዊነት እንደሚጎድለውና ይህንንም ለመፍታት እየሰተሰራ መሆኑ
• በከተማው ያለውን የውሃ እጥረት መኖሩን እንደሚገነዘቡና መ/ቤቱም ካለው የ ከተማ እድገት ጋር የሚሄድ የውሃ አቅርቦት መፍትሄዎችን ቢያመቻች
• የገቢ አሰባሰብ ስርዓቱን የተሻለ ለማድረግ የተለያዩ አሰራሮች እየተተገበሩ መሆኑና የክፍያ አማራጮችን መኖሩን ደንበኞች ይህንን በመረዳት ክፍያቸውን በወቅቱ እንዲከፍሉ እየተደረገ እንደሆነና በቀጣይም ክትትል ተደርጎ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አቅጣጫ ተቀምጣል፡፡
ባጠቃላይ በዚህ የመወያያ መድረክ ላይ አበረታች ሀሳቦች የተነሱ ሲሆን ለተነሱ የተለያዩ ጥያቄዎች የስራ ሀላፊዎች ምላሽ የሰጡ ሲሆን የተነሱትን ሀሳቦች በቀጣይ ማስተካከያ በሚስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራም ታውቋል፡፡

በቀን 22/05/2013 ዓ.ም በተደረገ የንፋስ ስልክ ቅ/ጽ/ቤት ሰራተኞች ጉብኝት በአዲስ አበባ የሚገኘውን የአንድነት ፓርክ መንፈስ የሚያድስ፤ ለስራ የሚያነሳሳ እና በአጭር ጊዜ የሚያስደምም...
03/02/2021

በቀን 22/05/2013 ዓ.ም በተደረገ የንፋስ ስልክ ቅ/ጽ/ቤት ሰራተኞች ጉብኝት በአዲስ አበባ የሚገኘውን የአንድነት ፓርክ መንፈስ የሚያድስ፤ ለስራ የሚያነሳሳ እና በአጭር ጊዜ የሚያስደምም ስራ መስራት እንደሚቻል ያሳየ ፓርክ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን የንፋስ ስልክ ቅ/ጽ/ቤት ሰራተኞች ገለጹ፡፡ በነበረው ጉብኝትም ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ሰራተኞቹ ይህን ያሉት ፓርኩን ተዘዋውረው በጎበኙበት ወቅት ነው፡፡
የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ባለራዕይ በመባል የሚታወቀው የሰራተኞች መረዳጃ ማህበር በየአመቱ ከሰራተኞቹ ጋር የሚያደርገውን አመታዊ ክብረ-በዓል ወደ ጉብኝት በመቀየር ነው በፓርኩ ቆይታ ያደረገው፡፡
ሰራተኞቹም ከመብላት መጠጣት ባሻገር ይህን መሰል ጉብኝት ማድረግ አዕምሮን ከማደስ ባለፈ ከፍተኛ የስራ ተነሳሽነትን ይፈጥራል ብለዋል፡፡ ማህበሩም ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ አመራሮች ጋር በመሆን በየጊዜው የሰራተኛውን ማህበራዊ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያደርገው ጥረትም አድንቀዋል፡፡ ይህም ለሌሎች ቅ/ጽ/ቤቶች መልካም ተሞክሮ ይሆናል ተብሎ ይታሰባል፡፡

በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ንፋስ ስልክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የነጭ ሪቫን ቀንና የኤች.አይ.ቪ ቀንን በማስመልከት ታህሳስ 23 2013 ዓ.ም በተዘጋጀ ፕሮግራም ላይ ሰራተኞች ተሳትፈዋል...
04/01/2021

በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ንፋስ ስልክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የነጭ ሪቫን ቀንና የኤች.አይ.ቪ ቀንን በማስመልከት ታህሳስ 23 2013 ዓ.ም በተዘጋጀ ፕሮግራም ላይ ሰራተኞች ተሳትፈዋል፡፡ በዚህ ፕሮግራም ላይ ከ ዋና መስሪያ ቤት ከመጡ አሰልጣኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ የተሰጠ ሲሆን ከተሰጡት መካከል በጥቂቱ በ ሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በጋራ መከላከል እና አሁን አሳሳቢ ደረጃ ላይ ስለደረሰው የኤች.አይ.ቪ ቫይረስ መደረግ ስላለበት ጥንቃቄ ሲሆን በዚህ ፕሮግራም ላይ ከተሳታፊዎች የተለያዩ መወያያ ሀሳቦች ተነስተው ፕሮግራሙ በጥሩ ሁኔታ ተፈፅሟል፡፡

07/12/2020

በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን መ/ቤት የንፋስ ስልክ ቅርንጫፍ የመጀመሪያ ሩብ አመት የአካል ግምገማ ህዳር 24 2013 ዓ.ም የተከናወነ ሲሆን በዚህም ምልከታ የተነሱ የተለያዩ ሀሳቦች ሲሆኑ የታዩ አበረታች ስራዎችና እና ሊስተካከሉ የሚገቡ ጉዳዮችን በጋራ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
በ ውይይቱ ከተነሱ ሀሳቦች መካከል በጥቂቱ…
• የ2013 በጀት ዓመት ዕቅድ ዝግጅት
• የስታንዳርድ ስራዎች አፈጻጸም
• የለውጥና ሪፎርም ስራዎች ዝግጅት
• የመልካም አስተዳደር ስራዎች አፈጻጸም

በዋናው መ/ቤት የክትትልና ድጋፍ ባለሙያዎች ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የክትትልና ድጋፍ ባለሙያዎች ከሚያገኙት ወቅታዊ የክትትልና ድጋፍ መረጃ በተጨማሪ የእይታ ምልከታ በማከናወን አጠቃላይ በተገኘው የሱፐርቪዥን ግኝት ዙሪያ በጋራ ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ስራ አመራር እና የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት ውይይት ተደርጓል፡፡

በ አዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የንፋስ ስልክ ቅርንጫፍ  ጽ/ቤት  ሰራተኞች በህዳር 25 2013ዓ.ም ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት ደም የመለገስ ፕሮግራም በ ጽ/ቤቱ  ግቢ ያደረገ ሲሆን...
07/12/2020

በ አዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የንፋስ ስልክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሰራተኞች በህዳር 25 2013ዓ.ም ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት ደም የመለገስ ፕሮግራም በ ጽ/ቤቱ ግቢ ያደረገ ሲሆን በዚህም ሰራተኞቹ ከመከላከያ ጉን መኖናቸውን አስመስክረዋል፡፡ በዚህም ለተሳተፋችሁ ሰራተኞች መስሪያ ቤቱ ምስጋና ያቀርባል፡፡

08/10/2020
በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የንፋስ ስልክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የዉሃ ስርጭት በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ የ  የውሃ ስርጭት የፈረቃ ፕሮግራም
05/10/2020

በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የንፋስ ስልክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
የዉሃ ስርጭት በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ የ የውሃ ስርጭት የፈረቃ ፕሮግራም

24/09/2020

ባለስልጣኑ በ2012 በጀት ዓመት 1.3 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ፡፡

ገቢውም ከውሃ ፍጆታ ክፍያ እና የተለያዩ የገቢ ርእሶች የተሰበሰበ ነው፡፡ በበጀት ዓመቱ ከተያዘው ዕቅድ አኳያም 86 % ማሳካት ተችሏል፡፡

የተሰበሰበው ገቢ ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከአራት መቶ ሰባ ሚሊዮን ብር (470,000, 000) ብር በላይ ብልጫ አለው፡፡

ለገቢ አሰባሰብ ማደግ ዋነኛ ምክንያቶችም የክፍያ ስርዓት ተደራሽነት እና ዘመናዊነት በማሳደግ ከለሁሉ ክፍያ ጣቢያ ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመዘዋወሩ ፣የቆጣሪ ንባብ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ መታገዝ እንዲሁም፤

ለበርካታ ጊዜያት ውዝፍ ያለባቸው ተቋማት እና ግለሰቦች እዳቸውን እንዲከፍሉ ከፍተኛ የዘመቻ ስራ በመሰራቱ ነው፡፡

Address

Nifas Silk
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when AAWSA Nifas Selk Branch posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to AAWSA Nifas Selk Branch:

Share