01/06/2026
የህብረተሰቡ ተሳትፎና ዝግጁነት ባህል እንዲጠናክር ይመከራል
***************************************************
እ.ኤ.አ ከጁን 1 እስከ 10/2026 (ግንቦት 24 እሰከ ሰኔ 3/2018 ዓ.ም) የሚኖረው የአየር ሁኔታ አዝማሚያ
//////////////////
በጁን የመጀመሪያዎቹ አስር ቀናት ለዝናብ መፈጠር አስዋጽኦ የሚያደርጉ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በተለይም በምዕራብ አጋማሽ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የተሻለ ጥንካሬ እንደሚኖራቸው የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ ። ከዚሁ ጋር በተያያዘም እርጥበታማው የአየር ሁኔታ ከቀን ወደ ቀን በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ በመጠንም ሆነ በሥርጭት እየተስፋፋ ከመሄዱ ጋር ተያይዞ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸዉ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
በሚቀጥሉት ቀናቶች ከሚጠናከሩት የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ላይ በመነሳት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች እና የደቡብ እና የደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ ቦታዎቻቸውን የሚሸፍን ከቀላል እስከ ከባድ (ከ1-30 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም አልፎ አልፎ በውሃ አካላትና በከባቢ አየር ውስጥ ከሚጠናከሩት የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ላይ በመነሳት በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብ እና በመካከለኛወ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ በ24 ሠዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
በጁን የመጀመሪያው አስር ቀናት ከሚኖረው ከፍተኛ የፀሐይ ሀይል ጋር በተያያዘ በተለይም የቀኑ ከፍተኛ ሙቀት በአፋር ክልል፣ በሰሜንና በደቡም ምዕራብ የሀገሪቱ ሥፍራዎች ሊይ ከ32 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ ትንበያዎች ያመላክታሉ፡፡