ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 03 ፐብሊክ ሠርቪስና የሠው ሀይል ሀብት አስተዳዳር ጽ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 03 ፐብሊክ ሠርቪስና የሠው ሀይል ሀብት አስተዳዳር ጽ/ቤት

ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 03 ፐብሊክ ሠርቪስና የሠው ሀይል ሀብት አስተዳዳር  ጽ/ቤት This is official page of Lemi Kura S/city worera 03 Public service and human resource manageme office

15/01/2024
ልምድ ልውውጥ ለተሻለ ለውጥ።የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ  የወረዳ 3 እና 2 የፐብሊክ ሰርቪና የሰው ሀብት ልማት ቤት  አስተዳደሮች በጋራ በመሆን በቦሌ ወረዳ 12 በመሄድ ልምድ ልውውጥ ለተሻለ ...
13/01/2024

ልምድ ልውውጥ ለተሻለ ለውጥ።

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ 3 እና 2 የፐብሊክ ሰርቪና የሰው ሀብት ልማት ቤት አስተዳደሮች በጋራ በመሆን በቦሌ ወረዳ 12 በመሄድ ልምድ ልውውጥ ለተሻለ ተሞክሮ በሚል መሪ ሀሳብ የጋራ ልምድ ልውውጥ አደረጉ።

በልምድ ልውውጡም በተሻ ሁኔታ የሰው ሀይሉን የማስተዳደርና የአሰራር ብቃት፣የሰራተኛውን መብትና ግዴታውን የማስጠበቅና የመወጣት ተግባር እንዲሁም ልዩ ልዩ ተሞክሮ እንዳገኙ የገለፁ ሲሆን በቀጣይም ከዚህ ተሞክሮና ልምድ ልውውጥ የአገኙትን እውቀትና ግንዛቤ በጽ/ቤታቸው ወስደው ተግባራዊ በማድረግ ለሌሎች አሪያ የመሆን ስራ እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

በተሰጠው የምዘና ፈተና 6 ሺሕ 517 ሰራተኞች የማለፊያ ነጥብ አስመዘገቡበአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተሰጠው የምዘና ፈተና ከ15 ሺሕ 151 ተፈታኞች 6 ሺሕ 517 የማለፊያ ነጥብ ማስመ...
11/01/2024

በተሰጠው የምዘና ፈተና 6 ሺሕ 517 ሰራተኞች የማለፊያ ነጥብ አስመዘገቡ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተሰጠው የምዘና ፈተና ከ15 ሺሕ 151 ተፈታኞች 6 ሺሕ 517 የማለፊያ ነጥብ ማስመዝገባቸው ተገለፀ።

ከተማ አስተዳደሩ በተለያዩ መዋቅሮች ለሚሰሩ ሰራተኞቹ የምዘና ፈተና መስጠቱ ይታወሳል።

በዚህም ፈተናውን ለመውሰድ የተመዘገቡ ሰራተኞችና አመራሮች 15 ሺሕ 592 ሲሆኑ ለፈተናው የቀረቡት 15 ሺሕ 151 ሰራተኞች መሆናቸውን የከተማ አስተዳደሩ ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ ጣሰው ገብሬ (ዶ/ር) እንደገለፁት በምዘና ፈተናው 4 ሺሕ 213 አመራሮች የተፈተኑ መሆኑንና 1 ሺሕ 422 ማለፋቸውን ገልፀዋል። ይህም ከተፈተኑት 34 በመቶ መሆኑንም አንስተዋል።

10 ሺሕ 257 ሰራተኞች በፈተናው መሳተፋቸውንና ከዚህም ውስጥ 5 ሺሕ 95 ማለፍ መቻላቸውንም አክለው ገልፀዋል።

በሰራተኞቹ በኩል 681 የሚሆኑት በተለያዩ የደንብ ጥሰቶች ምክንያት ፈተናውን ወስደው ያልታረመላቸው እንደሆኑም ተጠቅሷል።

ፈተናውን እንዲወስዱ ከተጠበቁ ሰራተኞች መካከል 441 ሰራተኞች እንዳልተገኙም ተገልጿል።

ፈተናው ፍፁም ደህንነቱንና ሚስጥራዊነቱን በጠበቀ መልኩ መካሄዱንም ፈተናውን ያስተናገዱት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና የኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ገልፀዋል።

Address

Ayat In Front Of Lemi Kura Sub City Zureyash Moll 5th Floor
Addis Ababa

Telephone

+251111123456

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 03 ፐብሊክ ሠርቪስና የሠው ሀይል ሀብት አስተዳዳር ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share