09/08/2022
በወሎ ሥም የሚቀነቀነው ክልላዊ ጩኸት‼️
አሳዬ ደርቤ
▬▬▬
➔ደቡብ ወሎ ላይ አዲስ ዞን በመመስረት ነባሩን ዞን በኦነግ ፖለቲካ የመሰልቀጥ ምኞት ያለው፤
➔በተመሳሳይ የፌስ ቡክ ሥም የተደራጀ የኦነግና የብልጽግና የሳይበር ጦር የሚያራግበው፤
➔ሕዝባዊ መሠረት የሌለው፤
➔አማራን ወደ ማይኖሪቲ አውርዶ ኦሮ፤ሚያን ብቸኛ ማጆሪቲ የማድረግ ሕልም ያለው ፤
➔የኃይማኖት ግጭት የመፍጠር ተልዕኮ የተሰጠው፤
➔የቤተ አማራዎች እትብት መቀበሪያ ምድር ወሎ መሆኗ የተዘነጋው፤
➔ትልቁን የአማራ ዞን አንዲት ወረዳ ከማታክል ልዩ ዞን ስር የማዋል እቅድ ያለው...
እናም እንላለን...
ብልጽግና ሆይ ያሰብከው ቅዠት በእኛና በፋኖዎች ዘመን ሊተገበር ስለማይችል በክልልነት ሥም ወሎን የመሰልቀጥ ምኞትህን ጥለህ ሕዝባዊ መሠረት ላለው የጉራጌ የክልልነት ጥያቄ አፋጣኝ መልስ ስጥ።
(ከአሳየህኝ ደርቢ)