Kolfe Food and Drug Administration ኮልፌ ምግብና መድኃኒት

Kolfe Food and Drug Administration ኮልፌ ምግብና መድኃኒት The official page of kolfe keranyo sub city Food and Drug Administration

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ  ሎጎ መቀየሩን አስታወቀ።***********************************የአዲስ አበባ ከተማ የምግብና መድሀኒት ባለስልጣን ከተቋቋመበት አላማና ከሚያከናውናቸው...
07/03/2024

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሎጎ መቀየሩን አስታወቀ።
***********************************
የአዲስ አበባ ከተማ የምግብና መድሀኒት ባለስልጣን ከተቋቋመበት አላማና ከሚያከናውናቸው ተግባራት እንዲሁም ከተሰጠው ተግባርና ሀላፊነት አንጻር ባለስልጣኑን ሊወክለው የሚችል ሎጎ መቀየሩን አስታውቋል።
ሎጎው በሶስት ቀለማት ማለትም በሰማያዊ ፣ቀይ እና ነጭ ቀለሞች የተዋቀረ ሲሆን ባለስልጣኑን ወካይ ምልክቶችንም አጠቃሎ ይዟል። በሎጎው የተቀመጡ ምልክቶችም የማረጋገጫ ምልክት የሎጎው አብዛኛው ክፍል በእንግሊዘኛ ሲ (C) ቁጥጥርን /control/የሚለውን የሚወክል ( Check marks/ / approval ቁጥጥር የሚያደርግባቸው ተቋማትና የሙያ ብቃት ትክክለኛቱን አረጋጋጭ መሆኑን ሲያመላክት በማረጋገጫ ምልክት ውስጥ ያለው በክብ የተቀመጠው ደግሞ የሚሠጠው አገልግሎት በእኩልነትና ከእድልዎ የፀዳ መሆኑን የሚያንጸባርቅ ነው፡፡ የመጨረሻው ምልክት እጁ የዘረጋ ሰው ምልክት ሲሆን ጤናውና ደህንነቱ የተረጋገጠለት ማህበረሰብ መፈጠሩን የሚያመለክት ወካይ ተምሳሌት እንደሆነም ተብራርቷል፡፡
የሎጎው ይዘትም በሎጎ እሳቤና ፍልስፍና መሰረት ሰማያዊ ቀለም የዓለም አቀፍ ጤና ድርጅት በመውሰድ የባለስልጣኑ ተልእኮና ስምሪት እንዲሁም መርህ ከዓለም አቀፍ ጤና መርሆዎችና ደረጃዎች ላይ የተመሰረተ እንደሆነ ፤ ከዚህ በተጨማሪም ይህ ቀለም ከኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴርና ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን መ/ቤቶች የተቆራኘ የህብረቀለም ይዘት እንዲኖረው ተደርጎ የተዘጋጀ ሲሆን ተቆጣጣሪና እርምጃ የመውሰድ ስልጣን ያለው መሆኑና የራሱ መለያ እንዲኖረው በማሰብ ደግሞ በቀጭኑ ቀይ ቀለም እንዲኖረው ተደርጎ ተዘጋጅቷል፡፡ የቀለማት ምርጫችንና የሎጎው ቅርፆች የባለስልጣኑ መርሆዎችና ዓለም አቀፍ የጤና እና የሃይጅን መርሆዎችን የሚገልፁ ናቸው፡፡

06/09/2023
06/09/2023
03/08/2023

"ዐሻራችን ለትውልዳችን- ለትውልድ እንሰራለን ለኢትዮጲያ እንትከል፡፡"   በሚል መሪ ቃል በቀን 10/11/2015ዓ.ም የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የምግብና መድሐኒት አስተዳደርና ቁጥጥር ጽ/...
17/07/2023

"ዐሻራችን ለትውልዳችን- ለትውልድ እንሰራለን ለኢትዮጲያ እንትከል፡፡"
በሚል መሪ ቃል በቀን 10/11/2015ዓ.ም የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የምግብና መድሐኒት አስተዳደርና ቁጥጥር ጽ/ቤት ከባለስልጣን መስሪያ ቤት ጋር በጋራ በመሆን በቂሊንጦ ኢንዱስትሪያል ፓርክ በመገኘት በአገር ደረጃ የታቀደውን የችግኝ ተከላ እቅድ እውን ለማድረግ የበኩላችንን ድርሻ ማሳካት ተችሏል፡፡ በችግኝ ተከላው ወቅትም የተለያዪ የፍራፍሬ ችግኞች እንዲሁም የዛፍ ችግኞችን መትከል የተቻለ ሲሆን ይህም እንዲሳካ ለተሳተፉ ሁሉ የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ እንጋ እርቀታ በጽ/ቤታችን ስም የላቀ ምስጋና በማቅረብ የተተከሉ ችግኞችን በመንከባከብ የዜግነት ግዴታችንን እንድንወጣ አሳስበዋል፡፡

My leader 💜 ❤️ ♥️ 💙 💕
17/07/2023

My leader 💜 ❤️ ♥️ 💙 💕

24/03/2023
የኮልፌ ቀራኒዮ ከፍለ ከተማ የምግብ መድኃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደር ቁጥጥር ጽ/ቤት ኃላፊ የሰራ ሂደቶችና ባለሞያዎች  የ2015 ዓ.ም የስድስት ወር የእቅድ አፈፃፀምና የእውቅና ፕሮግራም ...
23/03/2023

የኮልፌ ቀራኒዮ ከፍለ ከተማ የምግብ መድኃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደር ቁጥጥር ጽ/ቤት ኃላፊ የሰራ ሂደቶችና ባለሞያዎች የ2015 ዓ.ም የስድስት ወር የእቅድ አፈፃፀምና የእውቅና ፕሮግራም ከሁሉም ወረዳ አመራሮች ስራ ሂደቶችና ከባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ ተደረገ ።

Address

Betel
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kolfe Food and Drug Administration ኮልፌ ምግብና መድኃኒት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share