01/03/2026
♦"ግዛዋ ካለ ከደጅሽ፣ለምን ታመመ ልጅሽ?” ♦
``````````````````````````````````````````
#ግዛዋ (ጊዜዋ) በኢትዮጵያ የባህል ህክምና ውስጥ “ሁለገብ”
ከሚባሉት ውስጥ አንዱ ነው፡፡ ሁለገብ ማለት ለሁሉ ሰው፣ ለሁሉ
በሽታ አገልግሎት ይሰጣል እንደ ማለት ነው፡፡ እንዲሁም መላ የተክሉ
ክፍል ሥሩ፣ ቅጠሉ ወዘተ ለመድኃኒት ይውላሉ፡፡ ለዚህ ነው “ ጊዜዋ
ካለ ከደጅሽ፣ ለምን ታመመ ልጅሽ?” የሚባለው ተረት የሚነገረው፡፡
ይህ ማለት ግዛዋ በደጃፍሽ እያለ ከቅጠሉ ወይ ከሥሩ፣ ማጠጣት
ስትችይ ምን ነክቶሽ ነው ልጅሽ እንዲህ የሚታመምብሽ? ብሎ
እናትየዋን እንደመውቀስ፣ ስንፍና ይዟት እንደሆን ለማጎበዝ
ይመስላል፡፡ ይህን የጥንት ተረት ወደ ዛሬ ኢትዮጵያ አምጥተን እንዲህ
እንላለን፤ “ግዛዋ ሞልቶ በዱርሽ፣ ምነው ሰብሳቢ ሰው አጣሽ?!”
ሌላው ቀርቶ የህንድ ጊንሰንግ (Indian ginseng.) ተብሎም
ይጠራል፡፡ “የኢትዮጵያ ጊዜዋ” እንዳይባል ወይ ተረስቷል ወይ
ተዘሏል፡፡ አልያም ህንዶች በአግባብ ስለተጠቀሙ በስማቸው ተጠርቶ
ይሆናል፡፡
፴ግዛዋ በሳይንሳዊ መጠሪያው ዊታኒያ ሶምኒፌራ ( Withania
somnifera) በእንግሊዘኛ አሽዋጋንዳ (Ashwagandha
Withania, Indian ginseng.) ) ይባላል፡፡ በግዕዝ፣ ዕፀ ግዕዝ፤
በኦሮሚፋ ግዛዋ ወይም ዋሃሌ (Gizawwa, Wahalle) ይባላል፡፡
በብዙ የጭሳጭስ ነጋዴዎች ዘንድ በጣም ይታወቃል፡፡ ሥሩ
ተቆራርጦ፣ ደርቆ ከነ ቀበርቾ እና ሌሎች የጭሳጭስ ሥራሥሮች
ወዘተ ጋር አብሮ ለገበያ ይቀርባል፡፡ በተለምዶ ጭሱ ተውሳክ
ያስወግዳል ይባላል፡፡
በባሕል ሐኪሞች ዘንድ ብቻውን ወይም ከሌሎች ዕፀ መድኃኒት
ተክሎች ጋር ተቀምሞ ሥሩ እና ቅጠሉ ለብዙ ሕመም መድኃኒትነት
ይሰጣል፡፡
ይህም ሆኖ ጊዜዋ የሚፈለገውን ያህል በአገራችን ለልማት
አልዋለም፤ ለጠቀሜታም አልዋለም፣ ተሻሽሎ አልቀረበም፤ ከቶውንም
ሥሩ እየተነቀለ ማንም ባልገመተው መንገድ ወደ ውጭ እየተሸጠ
ነው፡፡ ምናልባትም በጥሬ ዕቃ ደረጃ ሲሸጥ በጭራሮ ዋጋ ይሸጥ
ይሆናል፡፡ የገዙት ብዙ ሙያ ይሰሩበታል፡፡ በፋብሪካ ከተቀናበረ በኋላ
በውድ ዋጋ ለዓለም ገበያ ያቀርቡታል፡፡
ሀ/ ጊዜዋ በሌሎች አገራት
ጊዜዋ በሌሎች አገራት ምን ይቀጠሙበታል?
በዚህ https://www.healthline.com/nutrition/12-proven-
ashwagandha-benefits #1 መረጃ መረብ ላይ እንዲህ
ይነበባል፡፡ ከጊዜዋ የሚዘጋጅ ንጥረ መድኃኒት 12 ያህል የጤና
ጠቀሜታዎች አሉት፡፡
1. በህንድ ከ ሶስት ሺ አመታት በላይ ጠቀሜታ ላይ ውሏል፡፡
ጭንቀት ለማስወገድ፣ ኃይል ለመስጠት እና የሰው ትኩረት
ለማሻሻል የታወቀ ነው፤
2. ለዓይነት 2 የስኳር ታማሚዎች የደም ስኳር መጠንን ለመቀነስ
ይረዳል፤
3. የዕጢ ዕብጠት ሴሎችን ( tumor cells) ለመግደል እና ብዙ
የነቀርሳ ዓይነትን (several types of cancer) ለማስወገድ
ይረዳል፤
4. በከፍተኛ ጭንቀት ወይም ውጥረት ውስጥ ያሉ ታማሚዎችን
የኮርቲሶል መጠን በመቀነስ (lower cortisol levels ) ይረዳል፤
5. በእንስሳትም ሆነ በሰው ላይ የተደረጉ ብዙ ጥናቶች ጊዜዋ
ጭንቀትን እንደሚቀንስ ታውቋል፤
6. ድብርትን ይቀንሳል፤
7. የወንድን ቴስቶስትሮን በመጨመር ( increase testosterone )
የዘር ፍሬን ያሻሽላል፤
8. የጡንቻን ይዘት በማጎልበት፣ የሰውነትን ስብ በመቀነስ፣
የወንዶችን ጥንካሬ ይጨምራል፤
9. የበሽታ ገዳይ ሴሎችን ሥራ በማጎልበት፣ የሰውነት ብግነትን
ወይም መቆጣት ይቀንሳል፤
10. ከፀረ ብግነት ብቃቱ በተጨማሪ የልብን ጤና ያሻሽላል