Shukare /ሹካሬ/

Shukare /ሹካሬ/ Providing facts from all over the world! your No #1 information choice!

14/08/2026
09/08/2026
09/08/2026

ምክክር - አዲስና ታሪካዊ ምዕራፍ
++++++++++++

ጋዜጣ ፕላስ፦ ለዓመታት የመሣሪያ ድምፅና የፖለቲካ ውጥረት በነገሠባት ሀገራችን፣ ዛሬ ዘላቂ የሰላም አየር ሊነፍስ አዲስ አቅጣጫ ተይዟል። በኃይል የታፈኑ ልዩነቶች አሁን በውይይት ጠረጴዛ ላይ እየቀረቡ ይገኛሉ። ይህ ሀገራዊ የምክክር ሒደት ከስሜታዊነት ምክንያታዊነትን አስቀድሟል።

ሒደቱ የፖለቲካ ተቃርኖዎችን ለማጥበብና ሕገ-መንግሥታዊ ማሻሻያዎችን ለማምጣት ተስፋ ፈንጥቋል። በሴራ የተሞላውን ኋላቀር የፖለቲካ ባሕል በሠለጠነ ውይይት ለመተካት አልሟል።

ቀደም ሲል በመሣሪያ ትግል ሲያደርጉ የነበሩ አካላት ወደዚህ የሰላም መድረክ መጥተዋል። የያዙትን የተሳሳተ የትግል አማራጭ ትተው ለውይይት መዘጋጀታቸው ትልቅ ማሳያ ሆኗል። በኢትዮጵያዊ ጨዋነትና በሰከነ መንፈስ እየተከናወነ ያለው ታሪካዊ ሒደት፤ የቀደመውን በኃይል የተሞላ የፖለቲካ ባሕል በመቀየር ለነገዋ ኢትዮጵያ አዲስ ተስፋን ሰንቋል።

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ ተስፋሁን ዓለምነህ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደሚገልጹት፣ ይህ ምክክር በየአምስት ዓመቱ የሚደገም መደበኛ ክስተት አይደለም። ይልቁንም በርካታ ዝግጅቶችን፣ ውይይቶችንና አጀንዳ ማሰባሰቦችን አልፎ እዚህ የደረሰ የረጅም ጊዜ የትግል ውጤት ነው።

ሒደቱ ሁሉንም የማኅበረሰብ ክፍሎች ያካተተ በመሆኑ ያልተወከለ አካል የለም። ቀደም ሲል በሰላማዊም ሆነ በትጥቅ ትግል ሲነሱ የነበሩ አጀንዳዎችም ሙሉ በሙሉ ተካተዋል ያሉት አቶ ተስፋሁን፤ ቀደም ሲል እርሳቸውና ፓርቲያቸው በትጥቅ ትግል ጭምር ይንቀሳቀሱ እንደነበር ገልጸዋል።

አሁን ያንን መንገድ በመተው ወደ ሰላማዊ የምክክር መድረክ መምጣታቸው በልዩነት ውስጥ ሆኖ ሀገርን ማዳንና የፖለቲካ ልዩነቶችን በንግግር መፍታት እንደሚቻል ያሳየ የሠለጠነ አካሄድ .....

ሙሉውን መረጃውን አስተያየት መሰጫ ሳጥን ውስጥ ያገኙታል

08/08/2026
25/05/2026
21/04/2026

ዛሬ በኢትዮጵያ ስፖርት ዕድገት ታሪክ ውስጥ፣ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ስፖርት ልማትና አስተዳደር አዋጅ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ በሙሉ ድምፅ ጸድቋል።

እንኳን ደስ አለን/አላችሁ!

ይህ አዋጅ ዘርፉን በማዘመን፣የአሰራርና የህግ ስርዓቶችን በመዘርጋትና ተጠያቂነትን በማስፈን ለኢትዮጵያ ስፖርት ልማት ዕድገት ቁልፍ ሚና ይጫወታል።

አዋጅን በማዘጋጅት ህደት ውስጥ፣ ሀሳብ በመሰጠትና የበለጠ እንድዳብር በማድረግ የተሳተፋችሁ ሙሁራን፣የህግና የስፖርት ባለሙያዎች፣ጋዜጠኞችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በሙሉ በራሴና በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ስም ላቅ ያለ ምስጋና ላቀርብ እወዳለሁ።

12/01/2026

Address

Belay Zeleke Street, Pissa Road
Addis Ababa
251,56

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Shukare /ሹካሬ/ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share