26/10/2021
ለትራፊክ ፖሊሶች እና የመንገድ ደህንነት ቁጥጥር አመራሮች የትራፊክ ማኔጅመንት ስልጠና ተሰጠ።
*********
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ኤንቲዪ (NTU) ከተባለው የዴንማርክ ድርጅት ጋር በመተባበር በአምስት የመንገድ ኮሪደሮች ላይ በፓይለት ደረጃ የቁጥጥር ስራንና ከአደጋ በኃላ አፋጣኝ የህክምና አገልግሎት በማሻሻል ላይ ትኩረት አድርጎ በመስራት ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ በተመረጡ ክልሎች እና ከተማ አስተዳደር የትራፊክ ቁጥጥር ተቋማት መሪዎችና ለትራፊክ ፖሊሶች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል።
ስልጠናዉንም የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ምክትል ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አሰፋ ሐዲስ ያስጀመሩት ሲሆን፣ በሀገራችን የትራፊክ ግጭት የበርካታ ዜጎችን ህይወት እየቀጠፈ እንዲሁም ከፍተኛ የሆነ የአካል እና የንብረት ጉዳት እያደረሰ ይገኛል በማለት ይህ በቅንጅት የሚሰጥ ሰልጠና ችግሩን ለመቅረፍ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ገልፅዋል ።
የኤንቲዪ(NTU) አማካሪ ድርጅት ቡድን መሪዉ ድርጅቱ በመንገድ ደህንነት እና በትራፊክ የሚደርሱ አደጋዎች እንዲቀንስ የሚሠራ መሆኑን ገልጸው አደጋው በዓለም አቀፍ ያለበትን ደረጃ ገልፀዋል።
የትራፊክ ማኔጅመንት ሥልጠናው ለሁለት ቀን የተሰጠ ሲሆን የብሔራዊ መንገድ ደህንነት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ዮናስ በለጠ በማጠናቀቂያ መርሀ ግብር በመገኘት ለተሳታፊዎች ሰርተፍኬት አበርክተዋል፡፡