የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት-Ethiopian Political Parties Joint Council

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት-Ethiopian Political Parties Joint Council

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት-Ethiopian Political Parties Joint Council Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት-Ethiopian Political Parties Joint Council, Political organisation, Yeshi Building 7th floor, Addis Ababa.

05/12/2025
የኢትዮጵያ የፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት  ከ KrF ኖርዌይ  ጋር በመተባበር  የወጣቶች የፖለቲካ ተሳትፎን አስመልክቶ   የተካሄደውን  ውይይት በሚከተለው ማስፈንጠሪያ ገብተው ይከታተሉ...
29/11/2025

የኢትዮጵያ የፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ከ KrF ኖርዌይ ጋር በመተባበር የወጣቶች የፖለቲካ ተሳትፎን አስመልክቶ የተካሄደውን ውይይት በሚከተለው ማስፈንጠሪያ ገብተው ይከታተሉ ።

participation

የኢትዮጵያ የፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት  ከ KrF ኖርዌይ  ጋር በመተባበር  የአካል ጉዳተኞች የፖለቲካ ተሳትፎን  አስመልክቶ   የተካሄደውን  ውይይት በሚከለተው ማስፈንጠሪያ ገብተው...
29/11/2025

የኢትዮጵያ የፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ከ KrF ኖርዌይ ጋር በመተባበር የአካል ጉዳተኞች የፖለቲካ ተሳትፎን አስመልክቶ የተካሄደውን ውይይት በሚከለተው ማስፈንጠሪያ ገብተው ይከታተሉ ።

with disabilities participation

ጠንካራ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመትከልና ሰላምን ለማፅናት ሚናችንን እናጠናክራለን -የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አዲስ አበባ፤ሐምሌ 16/2017 (ኢዜአ):-በኢትዮጵያ ጠንካራ ዴሞክራሲያ...
23/07/2025

ጠንካራ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመትከልና ሰላምን ለማፅናት ሚናችንን እናጠናክራለን -የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት

አዲስ አበባ፤ሐምሌ 16/2017 (ኢዜአ):-በኢትዮጵያ ጠንካራ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመትከልና ሰላምን ለማፅናት በሚደረገው ጥረት ሚናቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን አየለ ገለጹ።

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት እና ሰላም ሚኒስቴር በጋራ "ሰላምን በማጽናት የፖለቲካ ፓርቲዎች ሚና" በሚል መሪ ሀሳብ ያዘጋጁት ሀገር አቀፍ የሰላም ኮንፍረንስ መካሄድ ጀምሯል።

በመድረኩ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የሰላም ሚኒስትር መሀመድ እድሪስ፣ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ሰለሞን አየለ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ታድመዋል።

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን አየለ፥ ሰላም ለግለሰብ፣ ለማህበረሰብና ለሀገር ደህንነት መጠበቅ መሰረታዊ ጉዳይ ነው ብለዋል።

ሀገር የምትጸናው በሰላም ነው ያሉት ሰብሳቢው፥ የዳበረ ዴሞክራሲያዊ ባህል፣ በዜጎች ቅቡልነት ላይ የተመሰረተ ሀገረ መንግስት ለመገንባትም ሆነ ለፖለቲካዊ መረጋጋት ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።

ነጻ፣ ፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊ የምርጫ ሂደት እና ስልጡን የፖለቲካ ምህዳር ለሀገር ልማት ቀጣይነትና ዘላቂ ሰላም ወሳኝ መሆኑንም አንስተዋል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሀገሪቱ በሁሉም መስክ ወደ እድገት ጎዳና የምታደርገውን ጉዞ ለማሳካት አስተማማኝ ሰላም በመገንባት ሂደት የበኩሉን እየተወጣ ይገኛል ብለዋል።

ግጭትን በዘላቂነት ለማስቀረት የፖለቲካ ፓርታዎች ሚና ከፍተኛ እንደሆነ በማስረዳት የፖለቲካ ፓርቲዎች የጠንካራ ዴሞክራሲ መሰረት ናቸው ሲሉም ተናግረዋል።

ሀገራዊ የፖለቲካ ሪፎርሙን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም በፓርቲዎች መካከል በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተቀራርቦ የመሥራት ባህል መጎልበቱንም ገልጸዋል።

የጋራ ምክር ቤቱም የሀገርን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለማዳበር የላቀ ሚና እየተወጣ መሆኑን ጠቅሰው፤ በቀጣይም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

#ኢዜአ

በኢትዮጵያ የዳበረ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት ለመገንባት የፖለቲካ ፓርቲ  አመራሮችን አቅም ለማጎልበት ትኩረት ተሰጥቷልአዲስ አበባ፤ሐምሌ 7/2017 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ የዳበረና የተረጋጋ የመድ...
20/07/2025

በኢትዮጵያ የዳበረ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት ለመገንባት የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችን አቅም ለማጎልበት ትኩረት ተሰጥቷል

አዲስ አበባ፤ሐምሌ 7/2017 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ የዳበረና የተረጋጋ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት ለመገንባት የፖለቲካ ፓርቲ አመራር አባላትን አቅም ማጎልበት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ።

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት፣የአፍሪካ አመራር ልዕቀት አካዳሚና የኔዘርላንድስ መልቲ ፓርቲ ዴሞክራሲ ኢንስቲትዩት በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የሦስትዮሽ ስምምነት ተፈራርመዋል።

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ሰለሞን አየለ በመግባቢያ ስምምነቱ ሥነ-ሥርዓት ወቅት እንደገለጹት፤ በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ሥርዓትን ለማዳበር በዕውቀት ላይ የተመሰረተ አመራርና አባላት አቅም መገንባት ያስፈልጋል።

ለዚህ ደግሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራር አባላትን አቅም ማጎልበት የሚያስችሉ ሥልጠናዎች ማዘጋጀት ወሳኝ ነው ብለዋል።

ምክር ቤቱ ከዚህ አኳያ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑን ጠቁመው፤ ከአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ጋርም መስራቱ በዕውቀት የሚመራ አመራር ለመገንባት ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል ብለዋል።

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚዳንት ዛዲግ አብርሃ እንደገለጹት፤ በኢትዮጵያ የዳበረ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ሂደት ውስጥ የፖለቲካ ፓርቲ አመራር አባላትን አቅም ማሳደግ ወሳኝ በመሆኑ የልህቀት አካዳሚው ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል።

ለዚህ ደግሞ አካዳሚው በአገር በቀል ዕውቀት የታገዘ የፖለቲካ ፓርቲዎች የስልጠና መመሪያና የአመራር ልማት ግንባታ እቅድና ስትራቴጂ ማዘጋጀቱንም ገልጸዋል።

የኔዘርላንድ መልቲ ፓርቲ ዴሞክራሲ ኢንስቲትዩት የኢትዮጵያ ተወካይ ይነበብ ንጋቱ (ዶ/ር) በበኩላቸው፥በኢትዮጵያ ጠንካራ የመድብለ-ፓርቲ ስርዓት ግንባታ ላይ የቴክኒክና የፋይናንስ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ አንስተዋል።

በመድብለ ፓርቲ ስርዓት ውስጥ እየተገነባ ላለው ዴሞክራሲ ስርዓት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ሲሰሩ መቆየታቸውን ገልጸው፥ከልህቀት አካዳሚው ጋርም በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት በዛሬው ዕለት መፈራረማቸውን ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ጠንካራ የመድበለ-ፓርቲ ሥርዓት በመገንባት ሂደት በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኑንም የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚዳንት ዛዲግ አብረሃ አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ሰለሞን አየለ በዚህ ረገድ ተቋማቱ በኢትዮጵያ የዳበረና የተረጋጋ የመድብለ-ፓርቲ ሥርዓት ለመገንባት የተፈራረሙትን ስምምነት ውጤታማ ለማድረግ አቅማቸውን አሟጠው እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

#ኢዜአ
#ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የሀገራዊ ምክክር አጀንዳዎችን ለኮሚሽኑ አስረከበህዳር 25 2017አዲስ አበባየኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ...
07/12/2024

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የሀገራዊ ምክክር አጀንዳዎችን ለኮሚሽኑ አስረከበ
ህዳር 25 2017
አዲስ አበባ
የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ጽ/ቤት በመገኘት የጋራ ምክር ቤቱ ለሀገራዊ ምክክሩ ያዘጋጀውን የምክክር አጀንዳዎች ለኮሚሽኑ አስረክበዋል።
በጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ በአቶ ሰለሞን አየለ የተመራው የጋራ ምክር ቤቱ የልኡካን ቡድን ከተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሰብስበው በቅርቡ በጋራ ምክር ቤቱ ጠቅላላ ጉባኤ የጸደቁ አጀንዳዎችን ለኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ለፕ/ር መስፍን አርአያ አስረክበዋል።
በአጀንዳ ማስረከብ ስነ ስርአቱ ላይ የጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን አየለ ሀገራዊ ምክክር እና መግባባት የሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ቁልፍ አጀንዳ መሆኑን ገልጸው፣ ባለፉት በርካታ አመታት የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተናጠል እና በጋራ በመሆን በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር እንዲካሄድ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ መቆየታቸውን አስታውሰዋል። አቶ ሰለሞን የጋራ ምክር ቤቱም ሆነ አባል የፖለቲካ ፓርቲዎች ማናቸውም የፖለቲካ ልዩነት በጠረጴዛ ዙሪያ እና በምክክር ሊፈቱ ይገባል ብለው በጽኑ እንደሚያምኑ አመልክተዋል።
አቶ ሰለሙን በሀገራችን ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው የሀገራዊ ምክክር የፖለቲካ ፓርቲዎች ዋነኛ ባለድርሻ አካላት መሆናቸውን ጠቅሰው፣ ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን የጋራ ምክር ቤቱ የበኩሉን አስተዋጾ እንደሚያበረክት ገልጸዋል።
በስነስርአቱ ላይ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕ/ር መስፈን አርአያ ኮሚሽኑ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ፣ በኢትዮጵያ አካታች ሀገራዊ ምክክር ለማካሄድ ከፍተኛ ዝግጅት ሲያካሂድ መቆየቱን አውስተው፣ በበርካታ ክልሎች የምክክር አጀንዳ ልየታ እና የተሳታፊዎች መረጣ መካሄዱን ገልጽዋል። ኮሚሽኑ የምክክር ሂደቱን በገለልተኝነት እና በታማኝነት ለማካሄድ በቂ ዝግጅት ማድረጉን የገለጹት ዋና ኮሚሽነሩ፣ ሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ይሳካ ዘንድ የባለድርሻ አካላት በተለይም የፖለቲካ ፓርቲዎች ንቁ ተሳትፎ እጅግ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
ፕ/ር መስፍን ኮሚሽኑ ባለፉት አመታት ሲያከናውናቸው በነበሩ የዝግጅት ስራዎች የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤቱ ከፍተኛ ድጋፍ እና ትብብር ማድረጉን ገልጸው፣ የጋራ ምክር ቤቱ እና አባል የፖለቲካ ፓርቲዎች በተናጠል እስከ አሁን ላደረጉት ድግፍ እና ትብብር በኮሚሽኑ ስም ምስጋና አቅርበዋል።
በስነስርአቱ መጨረሻ የጋር ምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን እና ዋና ኮሚሽነር ፕ/ር መስፍን አርአያ በፕሮግራሙ ላይ ከተገኙ ጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄዎች መልስ በመስጠት ተጠናቋል።
የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት
ህዳር 25፣ 2017

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አመራሮች ጋር ተወያዩ።ህዳር 24 2017አዲስ አበባ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ...
06/12/2024

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አመራሮች ጋር ተወያዩ።
ህዳር 24 2017
አዲስ አበባ

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ጽ/ቤት በመገኘት ከቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ከክብርት ወ/ሮ ሚላትወርቅ ኃይሉ እና ከቦርዱ ም/ሰብሳቢ ከአቶ ውብሸት አየለ ጋር ውይይት አካሂደዋል።
በውይይቱ መጀመሪያ የቦርዱ ሰብሳቢ ክብርት ወ/ሮ ሜላትወርቅ አጭር የእንኳን መጣችሁ መልእክት እና አዲስ ለተመረጡ የጋራ ምክር ቤቱ አባላት መልካም የስራ ጊዜ ተመኝተዋል።

በእኛ በኩልም ለተደረገልን አቀባበል የቦርዱን ኃላፊዎች በማመስገን ፣ የጋራ ምክር ቤቱ ሲመሰረትም ሆነ ከተመሰረተ በኃላ ቦርዱ ለጋራ ምክር ቤቱ ያደረገው ሁለንተናዊ እና ያላሰለሰ ድጋፍ የጋራ ምክር ቤቱ አሁን ላይ ለደረሰበት ደረጃ ትልቅ አስተዋጾ ማበርከቱን ገልጸናል:: በተለይም ቦርዱ ለጋራ ምክር ቤቱ ላደረገው የፋይናንስ፣ የቴክኒክ፣ የሰው ኃይል ድጋፍ በምክር ቤቱ ስም የላቀ ምስጋና አቅርበናል።

የጋራ ምክር ቤቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ ልምድ እያካበተ እና በአደረጃጀት እና በአሰራር እየጠነከረ መምጣቱን በመጥቀስ፣ ም/ቤቱ በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ካሉ ቁልፍ ተዋናዮች አንዱ እና ዋነኛው ሊሆን መቻሉን በማመልከት በቅርቡ የጸደቀው የጋራ ምክር ቤቱ የመተዳደሪያ ደንብ፣ የጋራ ምክር ቤቱን ድርጅታዊ አቅም ከመገንባት አንጻር ትልቅ አስተዋጾ እንደሚኖረው አመልክተናል። በመጨረሻም የጋራ ምክር ቤቱ እና አዲስ የተመረጠው የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በቀጣይ ለሚያደርጉት እንቅስቃሴ የቦርዱ ድጋፍ እና ትብብር በተሻለ መልኩ እንደሚቀጠል ያለንን ጽኑ እምነታችን መሆኑን ገልጸናል።

በመቀጠል የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ውብሸት አየለ የጋራ ምክር ቤቱ እንዲመሰረት ሀሳቡን ከማመንጨት ጀምሮ፣ አስፈላጊውን የቴክኒክ፣ የፋይናንስ እና የሎጂስቲክ ድጋፍ በማድረግ፣ ለጋራ ምክር ቤቱ መቋቋም፣ ማደግ እና መጠንከር ቦርዱ የሚችለውን ሁሉ ሳይሰስት ማድረጉን አውስተው፣ ቦርዱ ወደፊትም ለጋራ ም/ቤቱ በተሻለ ሁኔታ ድጋፍ ለማድረግ እና ለማገዝ ፍቃደኛ መሆኑን ገልጸዋል። አቶ ውብሸት ቦርዱ የጋራ ምክር ቤቱ እንዲመሰረትም ሆነ እንዲጠነክር ያደረገው ድጋፍ፣ የጋራ ምክር ቤቱ ለአባል የፖለቲካ ፓርቲዎችም ሆነ ለሀገራችን የመድብለ ፓርቲ ስርአት መገንባት አይተኬ ሚና እንዳለው ካለው ጽኑ እምነት የተነሳ መሆኑን ተናግረዋል። አቶ ውብሸት አዲስ ለተመረጡ የጋራ ምክር ቤቱ አመራሮች መልካም የስራ ጊዜ ተመኝተዋል::

በመጨረሻም ክብርት ወ/ሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ ለጋራ ምክር ቤቱ አዲስ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ጋር በመገናኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው፣ ቦርዱ ባለፉት አመታት ያከናወናቸውን ስራዎች፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና መልካም ተሞክሮዎች በአጭሩ አውስተዋል። ክብርት ሰብሳቢዋ ቦርዱ በርካታ ውስጣዊ እና ውጫዊ ተግዳሮቶች ውስጥም ሆኖ በጥቂት አመታት ውስጥ በርካታ ስራዎችን ማከናወኑን እና ትልልቅ ስኬቶችን ማስመዝገቡን ገልጸው፣ በዚሁ ሁሉ ቦርዱ እንደ አንድ አጋር እና ባለድርሻ አካል ከጋራ ምክር ቤቱ ጋር በትብብር እና በቅርበት መስራቱ እጀግ የሚያስመሰግን ተግባር መሆኑን አመልክተዋል።
ወ/ሮ ሜላት ቦርዱ ለጋራ ምክር ቤቱ ትልቅ ክብር እና ቦታ የሚሰጥ መሆኑን ገልጸው፣ ቦርዱ በነበሩበት በርካታ ውስንነቶች ምክንያት ለጋራ ምክር ቤቱ የሚገባውን ድጋፍ ማድረግ እንዳልቻለ ገልጸው፣ በቀጣይ የተሻለ ድጋፍ ለማድረግ እና ከጋራ ምክር ቤቱ ጋር በትብብር ለመስራት ቦርዱ ያለውን ፍላጎት አመልክተዋል። በሀገራችን ጠንካራ የዴሞክራሲ እና የመድብለ ፓርቲ ስርአት እንዲገነባ ቦርዱ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እና በጋራ ለመስራት ሁሌም ዝግጁ መሆኑን የገለጹት ወ/ሮ ሜላትወርቅ፣ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት እና በየደረጃው ያሉ የጋራ ም/ቤቱ አደረጃጀቶች መጠንከር ለዚህ ዓላማ መሳካት ከፍተኛ አስተዋጾ ያደርጋል ብለው በጽኑ እንደሚያምኑ ተናግረዋል። ወ/ሮ ሚላትወርቅ ኢትዮጵያውያን ያለችን አንድ ሀገር በመሆኗ የተለያየ አመለካከት እና ሀሳብ ቢኖረንም ተመካክሮ፣ ተከባብሮ እና ተባብሮ መስራት እጅግ አስፈላጊ መሆኑ ገልጸዋል።
በመጨረሻማ የጋራ ምክር ቤቱ በቅርቡ የጸደቀውን የጋራ ምክር ቤቱን መተዳደሪያ ደንብ፣ ለቦዱ ሰብሳቢ ለክብርት ሜላትወርቅ ኃይሉ በማስረከብ፣ የትውውቅ ፕሮግራሙ ተጠናቋል፣
ህዳር 24፣ 2017
የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር
አዲስ አበባ

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ስራ ስፈጻሚ ኮሚቴ አንደኛ መደበኛ ስብሰባ ተካሄደኮሚቴው በተለያዩ በአጀንዳዎች ላይ ውሳኔ አስተላልፏል። ህዳር 23 2017አዲስ አበባህዳር 8 ...
05/12/2024

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ስራ ስፈጻሚ ኮሚቴ አንደኛ መደበኛ ስብሰባ ተካሄደ
ኮሚቴው በተለያዩ በአጀንዳዎች ላይ ውሳኔ አስተላልፏል።
ህዳር 23 2017
አዲስ አበባ
ህዳር 8 በተካሄደው የጋራ ምክር ቤት ስብሰባ አዲስ የተመረጠው የጋራ ምክር ቤቱ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ህዳር 23 የመጀመሪያ መደበኛ ስብሰባውን በማካሄድ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል።
የስራ አስፈርጻሚ ኮሚቴ የተወያየባቸው አጀንዳዎች እና ውሳኔዎች የሚከተሉት ናቸው፣
ከቀድሞ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ሪፖርት እና የስራ ርክክብ ተከናውኗል። በዚህም ባለፈው አንድ አመት የተሰሩ ስራዎች፣ ታቅደው ያልተከናወኑ ስራዎች፣ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የተሰሩ ስራዎች እና ያሉበት ደረጃ፣ ያጋጠሙ ዋና ዋና ተግዳሮቶች እና የመፍትሄ አቅጣጫዎች ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ፣ የ2017 እቅድ ያለፈው አመት ተሞክሮን ታሳቢ በማድረግ እንዲዘጋጅ ከስምምነት ላይ ተደርሷል።

2017 እቅድ፡ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው የጋራ ምክር ቤቱን የቃል ኪዳን ሰነድ እንዲሁም የጠቅላላ ጉባኤው ያጸደቀውን የእቅድ ማእቀፍ መነሻ በማድረግ በተዘጋጀው የ2017 ረቂቅ እቅድ ዙሪያ ሰፊ ውይይት አድርጓል። ረቂቅ እቅዱ 6 ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች እና በርካታ ዝርዝር ተግባራትን አካቷል። የጋራ ምክር ቤቱን እና የፖለቲካ ፓርቲዎችን አቅም መገንባት፣ ሰላም ግንባታ፣ ሀገራዊ ምክክር፣ አካባቢያዊ እና 7ኛ ጠቅላላ ምርጫ ቅድመ ዝግጅት፣ እንዲሁም ዴሞክራሲያዊ ስርአት፣ መልካም አስተዳደር እና የህግ የበላይነት መከበር የ2017 ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች ተደርገው ተለይተዋል።

የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት የስራ ክፍፍል። የጋራ ምክር ቤቱ ያሉበትን ኃላፊነቶች በንቃት እና በጥራት መወጣት ይችል ዘንድ፣ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት የስራ ክፍፍል ማድረግ አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበታል። በመሆኑም የጋራ ምክር ቤቱን ተቋማዊ አደረጃጀት ታሳቢ በማድረግ የቋሚ ኮሚቴ አባላት እና የክንፎች የስራ ክፍፍል ተካሂዷል። በዚሁ መስረት፣
አቶ ሰለሞን አየለ ብሄራዊ መግባባት እና የምርጫ ቋሚ ኮሚቴ አስተባባሪ
ዶ/ር አብዱልቃድር አደም ጥናት፣ ምርምር እና ፖሊሲ ቋሚ ኮሚቴ አስተባባሪ
አቶ መለሰ አለሙ የአደረጃጀት ቋሚ ኮሚቴ አስተባባሪ
አቶ አውግቼው ማለደ የአቅም ግንባታ ቋሚ ኮሚቴ አስተባባሪ
አቶ ደስታ ዲንቃ የህግ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አስተባባሪ
ወ/ሮ ሂንዲያ ሻፊ አስተዳደር እና ፋይናንስ ቋሚ ኮሚቴ አስተባባሪ ሆነው የተመደቡ ሲሆን፣
ከዚህ በተጨማሪ፡
አቶ ካህሳይ የአካል ጉዳተኞች ክንፍ አስተባባሪ
አቶ አውግቼው ማለደ የወጣቶች ክንፍ አስተባባሪ
ወ/ሮ ሂንዲያ ሻፊ የሴቶች ክንፍ አስተባባሪ ሆነው ተመድበዋል።

የመተዳደሪያ ደንብ ማሻሻያ፡ የጋራ ምክር ቤቱ መተዳደሪያ ደንብ በቅርቡ በጠቅላላ ጉባኤ ለውይይት በቀረበበት ወቅት፣ በደንቡ ላይ የተለያዩ አስተያያቶች ተሰጥተዋል። የህግ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ የተሰጡ አስተያያቶችን በመተዳደሪያ ደንቡ በማካተት ለስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ለውይይት ቀርቧል። የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በጠቅላላ ጉባኤው የተሰጡ አስተያያቶች በአግባቡ መካተታቸውን አንቀጽ በአንቀጽ በመመልከት አረጋግጧል። ኮሚቴው የመተዳደሪያ ደንቡ የመጨረሻው ረቂቅ በባለሙያ ተዘጋጅቶ እንዲታተም እና ለባለ ድርሻ አካላት እንዲሰራጭ ውሳኔ አስተላልፏል።

የስራ ርክክብ፡ በስብሰባው መጨረሻ የጋራ ምክር ቤቱ አዲስ ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን አየለ ከምክር ቤቱ የቀድሞ ሰብሳቢ ከአቶ ደስታ ዲንቃ ርክክብ በማድረግ የእለቱ ስብሰባ ተጠናቋል።
የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት
ህዳር 23፣ 2017

19/11/2024

Address

Yeshi Building 7th Floor
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት-Ethiopian Political Parties Joint Council posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት-Ethiopian Political Parties Joint Council:

Share