የቦሌ ሥራ፤ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ፅ-ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • የቦሌ ሥራ፤ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ፅ-ቤት

የቦሌ ሥራ፤ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ፅ-ቤት የቦሌ ሥራና ክህሎት ፅ-ቤት Official የፌስቡክ ገፅ ነው፤ እኛን የሚመለከት ጉዳይ ካለዎት ያግኙን።

 #እውቅናና ሽልማት ለላቀ ውጤታማነት !! ቦሌ 1ኛ !! የዘመናዊ መኪና ተሸላሚ !!የቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር በ2015 በጀት ዓመት በማህበራዊ ፣ በኢኮኖሚያዊና በሌሎች ዘርፈብዙ ስራዎች ተጨ...
02/11/2023

#እውቅናና ሽልማት ለላቀ ውጤታማነት !!
ቦሌ 1ኛ !! የዘመናዊ መኪና ተሸላሚ !!
የቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር በ2015 በጀት ዓመት በማህበራዊ ፣ በኢኮኖሚያዊና በሌሎች ዘርፈብዙ ስራዎች ተጨባጭ ውጤት አስመዝግቧል ።
ለውጤቱ መሳካት የአመራሩ ፣ የመንግስት ሰራተኞች ፣ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና የባለድርሻ አካላት ቅንጅት በእጅጉ ጎልቶ የታየበት ነበር ።
የክ/ከተማው አስተዳደር በበጀት ዓመቱ ባከናወናቸው ዘርፈብዙ ተግባራት የላቀ አስተዋጽኦ በማበርከቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተገቢውን እውቅናና ክብር መስጠቱ ለቀጣይ ስራዎች ስኬትና ውጤታማነት ትልቅ ሚና ይኖረዋል ።
እናመሰግናለን 🙏🙏🙏

01/07/2023

10 Books That Will Make You Mentally Tough

ስራ ስምሪት
30/10/2022

ስራ ስምሪት

ከዓለም ባንክ ግሩፕ ዋሽንግተን ቢሮ የስራ ኃላፊዎች ጋር የመንግስት ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማትን አቅም ገንብተን የሥራ ገበያው የሚፈልገውን በክህሎት የዳበረ የሠው ኃይል በማፍራት ጥራት ...
01/06/2022

ከዓለም ባንክ ግሩፕ ዋሽንግተን ቢሮ የስራ ኃላፊዎች ጋር የመንግስት ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማትን አቅም ገንብተን የሥራ ገበያው የሚፈልገውን በክህሎት የዳበረ የሠው ኃይል በማፍራት ጥራት ያለው የሥራ ዕድል ለመፍጠር የነደፍናቸው ስትራቴጂካዊ ሀሳቦች ላይ ተወያይተን ባንኩ የ200,000,000.00 ሁለት መቶ ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ከስራና ክህሎት ሚንስትር ጋስ ስምምነት ላይ መደረሱ ተገልጿል።

10,500 ወጣቶችን ወደ ተግባር ለማስገባት ከባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድርክ መካሄዱ ተገለፀ።የስራ ዕድልና ምግብ ዋስትና ዘርፍ "ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም" ውስጥ ...
27/05/2022

10,500 ወጣቶችን ወደ ተግባር ለማስገባት ከባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድርክ መካሄዱ ተገለፀ።

የስራ ዕድልና ምግብ ዋስትና ዘርፍ "ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም" ውስጥ የሚሳተፉ 10,500 ወጣቶችን ወደ ተግባር ለማስገባት ከባለድርሻ አካላት ጋር በትናንትናው ዕለት ውይይት አካሄደዋል።

የውይይቱ አለማ በአዲስ አበባ ከተማ ወስጥ ለሚገኙ በተለያየ ምክንያት ትምህርታቸውን ላቋረጡ ወጣቶች በተለያዩ ድርጅቶች ውስጥ በማሰገባት የስራ ላይ ልምምድ እንዲያደርጉ፤ የክህሎትና የሙያ ባለቤት እንዲሆኑ ማስቻል መሆኑን የስራ ስምሪት ማስፋፊያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰበሃዲን ሱልጣን ተናግረዋ።

የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም ለሀገራችን በአይነቱ ለየተ ያለ አሰራር ሲሆን ክህሎትና ሙያ ያላቸው ወጣቶችን ከማፍራት ባሻገር በድርጅቶች ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩበትን ዕድል የሚፈጥር እንደሆነ አቶ ሰበሃዲን ጨምረው ገልፀዋል።

ይሁንና በዚህ የወጣቶች ተጠቃሚነት ፕሮግራም ላይ የሀገራችን የስራ አጥ ችግር ለመቀነስ የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር በማጠናከር የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንደሚያበረክቱ ይጠበቃል።

ግንቦት 19-2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ አመራሮች የስልጠና መድረክ ተጠናቀቀ።ላለፉት ስድስት ቀናት "አዲስ ፖለቲካዊ ዕይታ አዲስ ሀገራዊ እምርታ" በሚል ለከተማዋ ከፍተኛ አመራር ሲሰጥ የነበረው የስልጠና...
26/05/2022

የአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ አመራሮች የስልጠና መድረክ ተጠናቀቀ።

ላለፉት ስድስት ቀናት "አዲስ ፖለቲካዊ ዕይታ አዲስ ሀገራዊ እምርታ" በሚል ለከተማዋ ከፍተኛ አመራር ሲሰጥ የነበረው የስልጠና መድረክ በዛሬው ዕለት ተጠናቋል።

በማጠቃለያ መድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ-ሮ አዳነች አቤቤ ሀገራዊ የለውጡ ሂደት ፈታኝ ቢሆንም ይሄንን ፈተና ለማለፍ በጥበብ እና ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ የአመራር ዘይቤ በመከተል ዛሬ ላይ መድረስ መቻሉን ከዚህ ስልጠና አመራሩ ግንዛቤ ማግኘቱን ተናግረዋል።

በለውጡ ሂደት ተስፋን የሚጭሩ ትላልቅ ስራዎች መሰራታቸው በተለይም የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የደህንነት፣ የሰላምና የጸጥታ ተቋሞቻችን ላይ የተደረጉ መሰረታዊ ሪፎርሞች በጊዜያዊነት ብቻ ሳይሆን ለሀገራዊ ግንባታው ወሳኝ የሆነ ሚና እንዲጫወቱ ማስቻል የተሰራውን ስራ ሰልጣኙ በተግባር ጭምር እየተመለከተ የሰለጠነበት ሁኔታ እንደነበር አንስተዋል።

አጠቃላይ ስልጠናው በአመራር የመሪነት ሚና ላይ ያተኮረ እንደነበር የገለጹት ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተቋም ግንባታ፣ ተቋማዊ አሰራሮች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸውና ሀገራዊ ለውጡ ተቋማዊ ሆኖ እንዲቀጥል ሁሉም ተባብሮ መስራት እንደሚገባው ተናግረዋል።

የፓርቲ ተቋማዊ ግንባታ ለመንግስትና ለሀገራዊ ጥንካሬ ወሳኝ ነው፤ ጠንካራ መንግስት የሚኖረን እና ጠንካራ ሀገር የምንገነባው በጠንካራ ፓርቲ ነውና አመራሩ ተግባራትን አቀናጅቶ መምራት እንደሚገባውም ከንቲባዋ አሳስበዋል።

የአምራች ኢንዱስትሪዎችን አቅም በመገንባት ኢኮኖሚውን የማነቃቃት ሥራ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ተጠቆመ ፡፡የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የሥራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ-ቤት “ኢት...
21/05/2022

የአምራች ኢንዱስትሪዎችን አቅም በመገንባት ኢኮኖሚውን የማነቃቃት ሥራ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ተጠቆመ ፡፡

የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የሥራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ-ቤት “ኢትዮጵያ ታምርት” በሚል መሪ ቃል በክፍለ ከተማው ከሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎች ጋር ባደረገው የምክክር መድረክ ላይ እንደተገለጸው ምቹ የሥራ ቦታና የገበያ ትስስር በመፍጠርና ጥራታቸውን የጠበቁ አገር በቀል ምርቶች ማምረት የኅብረተሰቡን በአገር ምርት የመጠቀም ልምድን ከማዳበር ባሻገር ኢኮኖሚውን ለማነቃቃት ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል።

በውይይቱ የተሳተፉ አምራች ኢንዱስትሪዎች ተወካዮች በሰጡት አስተያየት የብድር አገልግሎት የመሥሪያ ቦታዎች፣ የመሠረተ ልማት እንዲሁም የጥሬ ዕቃ ውድነት ለሥራቸው ማነቆ እንደሆነባቸው በመግለጽ በአሠራር ሂደት ላይ ያሉ ችግሮችን አስተዳደሩ ትኩረት ሰጥቶ ሊፈታ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ውይይቱን የመሩት የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጽ-ቤት ኃላፊ አቶ አብነት ባልቻ በአምራች ኢንዱስትሪዎች የተነሱትን ችግሮች አስተዳደሩ ለመፍታት በትኩረት እንደሚሠራ ገልጸው፣ ከቀጣዩ ሳምንት ጀምሮ የክፍለ ከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራር በአምራች ኢንዱስትሪዎቹ በአካል በመገኘት ችግሮቹን ለመፍታት የመፍትሄ አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥ አክለው አስታውቀዋል።

በስራ ቦታና አካባቢዎች የሥራ ላይ አደጋና በስራ ምክንያት ሊከሰት የሚችል በሽታን ለመከላከል በትኩረት እንሰራለን።አቶ ዩሃንስ ምትኩ የአሰሪና ሰራኛ ጉዳይ ዘርፍ ኃላፊ የሥራ፣ኢንተርፕራይዝና ...
19/05/2022

በስራ ቦታና አካባቢዎች የሥራ ላይ አደጋና በስራ ምክንያት ሊከሰት የሚችል በሽታን ለመከላከል በትኩረት እንሰራለን።

አቶ ዩሃንስ ምትኩ የአሰሪና ሰራኛ ጉዳይ ዘርፍ ኃላፊ
የሥራ፣ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በሀገራችን ለ19ኛ ጊዜ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ ጊዜ የሚከበረውን የሙያና ደህንነት ጤንነት ቀን "የሙያ ደህነንነት ጤንነት ባህልን ተባብረን እንገንባ!" በሚል መሪ ቃል ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በድምቀት ተከብሯል፡፡

በውይይቱ የኢትዮጵያ አሰሪ ፌዴሬሽኖች ኮንፌዴሬሽን፣ የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን፣ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካለት የተሳተፉ ሲሆን በሀገራችን የሙያ ደህንትና ጤንነት ለመገንባት ያለው ምቹ ሁኔታ፣የሙያ ደህንነት አጠባበቅ አመራር ስርዓት እንዲሁም የኮንስትራክሽን ሴፍቲን አስመልክቶ ጽሁፎች ቀርበው ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

በከተማዋ በስራ ላይ በተሰማሩ አምራች ዜጋ በስራ ቦታ ላይ የሚከሰቱ አደጋዎችን ለመከላከል የግንዛቤ ማስጨበጫ በስፋት መስጠት፣ የህግ ተፈፃሚነትን ማጠናከር፣ የሥራ ላይ መመሪያዎችን መፈጸም እንዲሁም ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ አቶ አሰግድ ተስፋዬ ተናግረዋል፡፡

በከተማችን በርካታ የማምረቻ ኢንዱስትሪዎችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በመኖሩ ከሁለት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ዜጎች በስራ ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዩሃንስ ምትኩ ጠቁመው፤ በስራ ቦታና አካባቢዎች የሥራ ላይ አደጋን እና በስራ ምክያት ሊከሰት የሚችል በሽታን ለመከላከል ቢሮው በትኩረት እየሰራ መሆኑን አቶ ዩሀንስ ተናግረዋል፡፡

ግንቦት 10 ቀን 2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ

Address

Addis Ababa

Telephone

+251913858489

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የቦሌ ሥራ፤ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ፅ-ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share