OBN አማርኛ

OBN አማርኛ Oromia Broadcasting Network (OBN)
Voice of the People!
(2)

OBN አማርኛ page is a part of Oromia Broadcasting Network (OBN), producing news, documentary and programs in Amharic language to reach our audiences in all over the world. Join us:
www.obnoromia.com
www.youtube.com/OBNoromiyaa
www.twitter.com/OBNoromiyaa
www.facebook.com/OBNAfaanoromo
www.facebook.com/OBNEnglish

01/09/2026

የምሽት 1፡00 ሰዓት አማርኛ ዜና
OBN ነሐሴ 26፣ 2018

ባርሴሎና ጋብሬል ጄሱስን ከአርሰናል አስፈረመ ኦቢኤን ሣይበር ሚዲያ ነሐሴ 26/ 2018የስፔኑ ክለብ ባርሴሎና ብራዚላዊውን የፊት መስመር ተጫዋች ጋብሬል ጄሱስን ከአርሰናል ማስፈረሙን ይፋ አ...
01/09/2026

ባርሴሎና ጋብሬል ጄሱስን ከአርሰናል አስፈረመ

ኦቢኤን ሣይበር ሚዲያ ነሐሴ 26/ 2018

የስፔኑ ክለብ ባርሴሎና ብራዚላዊውን የፊት መስመር ተጫዋች ጋብሬል ጄሱስን ከአርሰናል ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል፡፡

ባርሴሎና ለተጨዋቹ ዝውውር 8 ነጥብ 6 ሚሊየን ፓውንድ ወጪ አድርጓል፡፡

ጋብሬል ጄሱስ በስፔኑ ክለብ እስከ ፈረንጆቹ 2029 ድረስ የሚያቆየውን ውል ተፈራርሟል፡፡

የ29 ዓመቱ ተጫዋች ለአርሰናል 123 ጨዋታዎችን አድርጎ 32 ግቦችን አስቆጥሯል፡፡BBCSport

የወርሀ ሐምሌ እና ነሐሴ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቁልፍ ተግባራት ቅኝትየአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር፦የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ስምንተኛ ዓመቱን በያዘበት በዚህ ዓመት፤ የኮፕ32 (C...
01/09/2026

የወርሀ ሐምሌ እና ነሐሴ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቁልፍ ተግባራት ቅኝት

የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር፦

የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ስምንተኛ ዓመቱን በያዘበት በዚህ ዓመት፤ የኮፕ32 (COP32) ሰብሳቢ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)፣ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና የኮፕ32 ብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት ዓመታዊውንና የአንድ ጀምበር ሀገር አቀፍ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብርን መርተዋል።

ዘመቻው በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በአንድ ቀን ውስጥ 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ታላቅ ግብን የሰነቀ ሲሆን በዚህም ከተቀመጠው እቅድ በላይ ማሳካት የቻለ ዘመቻ ነበር። ይህ ጥረት በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተከናወነ ሲሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ተሳታፊዎች የታሪክ፣ የአንድነት እና የጽናት ድል ያስመዘገቡ መሆናቸውን በመግለጽ ለሁሉም ምስጋና አቅርበዋል።
ፕሮጀክቶች ጉብኝት እና ምረቃ፦

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በባሕር ዳር የሚገኘውን የደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አዲስ ተርሚናል መርቀው ከፍተዋል። ይህ ፕሮጀክት ለኢትዮጵያ ቁልፍ ከሆኑ መግቢያ በሮች አንዱ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከተማዋ በቅርቡ ባጋጠሟት ፈተናዎች ሳትበገር የጽናት፣ የማገገም እና የቀጣይ ኢንቨስትመንት ማዕከልነት ማረጋገጫ መሆኑን አስገንዝበዋል።

አዲሱ ተርሚናል ዘመናዊ የአውሮፕላን ማረፊያ መሠረተ ልማቶችን፣ የተሻሻሉ የመዳረሻ መንገዶችን እና ሰፊ አገልግሎቶችን በማካተት የአውሮፕላን ማረፊያውን አቅም የሚያሰፋና የመንገደኞችን ምቾት የሚያሻሽል ሲሆን፤ ይህም ከከተማዋ ሰፊ የከተማ ትራንስፎርሜሽን ጋር ተዳምሮ ባሕር ዳርን ለዓለም አቀፍ እና ለሀገር ውስጥ በረራዎች ማዕከል ያደርጋታል።

‎ማኅበራዊ ጉዳይ፦

በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ (OBN) ጋር ቃለ መጠይቅ ያደረጉ ሲሆን በቆይታቸውም ከሀገራዊ ጥቅም ይልቅ ግላዊ ጥቅምን ያስበለጡ በኦሮሚያ፣ በአማራ እና በትግራይ የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ቡድኖች መንግሥትን ለብቻቸው ማሸነፍ እንደማይችሉ ከተገነዘቡ በኋላ ህብረት መፍጠራቸውን ገልጸዋል።

በተጨማሪም ጊዜው ባለፈበት የፖለቲካ አስተሳሰብ እና የአመራር ዘይቤ እነዚህ ቡድኖች ኢትዮጵያን ለማዳከም እና ለመበታተን ለሚፈልጉ ታሪካዊ የውጭ ጠላቶች እንደ መጠቀሚያ መሣሪያ እያገለገሉ የመሆናቸውን ታሪካዊ ግድፈት አብራርተዋል። አክለውም እውነተኛ ዲሞክራሲ ከተራ የፖለቲካ ግልጽነት ባለፈ የሕግ የበላይነትን ወደሚያረጋግጥ እውነተኛ ብሔራዊ ውይይት መሸጋገር እንዳለበት አፅንዖት ሰጥተዋል።

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለሀገር ሰላም እና አብሮነት ያበረከተው አስተዋጽኦ የላቀ ነው፦ የሰላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ (ዶ/ር) ኦቢኤን ሣይበር ሚዲያ ነሐሴ 26/ 2018 የኢት...
01/09/2026

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለሀገር ሰላም እና አብሮነት ያበረከተው አስተዋጽኦ የላቀ ነው፦ የሰላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ (ዶ/ር)

ኦቢኤን ሣይበር ሚዲያ ነሐሴ 26/ 2018

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ 15ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል እና 18ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በዛሬው ዕለት እየተካሄደ ይገኛል።
በጉባኤው ላይ ንግግር ያደረጉት የሰላም ሚኒስትሩ መሐመድ እድሪስ (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ባለፉት 15 ዓመታት ውስጥ የሃይማኖት ተቋማትን በማስተባበር በሀራችን አብሮነትን ለመገንባት እና ሰላምን ለማፅናት እጅግ አበረታች ተግባራትን ማከናወኑን ገልጸዋል።
የሕዝብን አንድነት፣ አጋርነት እና ወዳጅነት ለማጠናከር በተደረጉ ጥረቶች ውስጥ ጉባኤው የተጫወተው አዎንታዊ ሚና እጅግ የላቀ መሆኑን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤታቸው እውቅና እንደሚሰጥም አስታውቀዋል።
ጉባኤው በሰላም እና በአብሮነት ችግሮችን በጋራ በማለፍ ታሪካዊ ድሎችን በአንድነት ማስመዝገቡን የጠቆሙት ሚኒስትሩ፣ በተለይም በቅርብ ጊዜ እየተከናወነ ያለውን ሀገራዊ የምክክር ሂደት ጨምሮ በሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ ያበረከተው አስተዋጽኦ ለሀገር እና ለሕዝብ አለኝታነቱን የሚያሳይ እና ለብዙዎች ምሳሌ የሆነ መሆኑን አንሥተዋል።
በቀጣዩ የአገልግሎት ዘመን ይበልጥ ውጤvታማ ለመሆን ያለፈውን ጉዞ በጋራ በመገምገም ጉድለቶችን መሙላት እና ጠንካራ ጎኖችን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚያስፈልግ ነው ያሳሰቡት።
በአሁኑ ወቅት ከእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የሚጠበቀው በትብብር እና በአንድነት በመቆም ሀገርን ማበልጸብ እና የበለጸገች ኢትዮጵያን ለትውልድ ማስተላለፍ መሆኑን የመደመር መንግሥት ያምናል ብለዋል።
በመሆኑም ከልዩነት ይልቅ በጋራ ጉዳዮች ላይ በሰፊው በማተኮር፣ ከሁሉም በላይ ለሰላም፣ ለእውነት እና ለፍትሕ ምሳሌ የሆነ ማንነት በመገንባት ሕዝቡን ከቃል ባለፈ በተግባር መምራት እንደሚያስፈልግ ዶክተር መሐመድ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።ebc

01/09/2026

#ኢትዮጵያ 🇪🇹 በአኒሜሽን ጥበብ፤
‎ እጅግ ማራኪ ውበት፣ የማይደበዝዝ የታሪክ ትውፊት እና ድንቅ ብዝሃነት ያላት ምድር።

‎''የሀገሬ ልጆች የኢትዮጵያን ድንቅ የብዝሃነት ውበት ትጎበኙ ዘንድ ጥሪዬን አቀርባለሁ!''- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

"ኢትዮጵያ ሀገራችን በአስደናቂ የለውጥ ጉዞ ላይ ትገኛለች፤ ለውጡን እየመራን፣ ለውጡን እየሰራን ያለን ሰዎች በየቀኑ እንደመማለን። በአንድ ዓመት ከስድስት ወር ማዕከል ተገንብቶ እናያለን፣ ከ...
01/09/2026

"ኢትዮጵያ ሀገራችን በአስደናቂ የለውጥ ጉዞ ላይ ትገኛለች፤ ለውጡን እየመራን፣ ለውጡን እየሰራን ያለን ሰዎች በየቀኑ እንደመማለን። በአንድ ዓመት ከስድስት ወር ማዕከል ተገንብቶ እናያለን፣ ከተማ ሲገነባ እናያለን፣ አካባቢ ሲቀየር እናያለን፣ ተቋም ሲቀየር እናያለን።የእኛ ቀጣይ ሥራችን ይህንን ማየት እና መገንዘብ ያልቻሉ ዜጎችን በተደጋጋሚ አዳዲስ ታሪኮች እያስመዘገብን እነሱን በንግግር ሳይሆን በተግባር ማሳመን ነው፤ አሁንም በኮሪደር ልማት ያላመኑ ዜጎች አሉ፣ ደጋግመን አዳዲስ ከተሞችን ሰርተን እናሳምናቸዋለን።ተቆጥተን አይደለም፣ ተናግረን አይደለም፣ ሰርተን እናሳምናቸዋለን፤ ተቋማት ገንብተን እናሳያቸዋለን። የኢትዮጵያ ብልጽግና አይቀሬ ጉዳይ ነው፤ አትጠራጠሩ ልጆቻችን የበለፀገችና የጠነከረች ኢትዮጵያን ይረከባሉ። አሁን ያለው ትውልድ እንደ ሻማ ይቀልጣል፤ ልጆቻችን ግን በዚያ ሻማ ብርሃን ለአፍሪካ ኩራት፣ ለአፍሪካ ምሳሌ፣ ለአፍሪካ ክፉ ቀን ደራሽ የሆነች ኢትዮጵያን ይረከባሉ።"-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
'ከመስከረም እስከ መስከረም'' መጽሐፍ 8ተኛ ቅጽ ገፅ 17

በአውሮፓ ኅብረት ‘ግሎባል ጌትዌይ’ ኢኒሼቲቭ እና በኢትዮጵያ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ መካከል ባለው መጣጣም ዙሪያ የፖሊሲ ውይይት እየተካሄደ ነው ኦቢኤን ሣይበር ሚዲያ ነሐሴ 26/ 20...
01/09/2026

በአውሮፓ ኅብረት ‘ግሎባል ጌትዌይ’ ኢኒሼቲቭ እና በኢትዮጵያ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ መካከል ባለው መጣጣም ዙሪያ የፖሊሲ ውይይት እየተካሄደ ነው

ኦቢኤን ሣይበር ሚዲያ ነሐሴ 26/ 2018

በአውሮፓ ኅብረት ‘ግሎባል ጌትዌይ’ ኢኒሼቲቭ እና በኢትዮጵያ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ መካከል ያለው መጣጣም ዙሪያ ትኩረቱን ያደረገ የፖሊሲ ውይይት በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና ሰላም ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዲማ ኖጎ (ዶ/ር)፣ በኢትዮጵያ እና በአውሮፓ ኅብረት መካከል ያለው ግንኙነት ከቀድሞው የተለመደ የልማት ዕርዳታ አሰጣጥ ወጥቶ፣ አሁን ይበልጥ በኢንቨስትመንት ላይ ወደተመሠረተ አጋርነት መሸጋገሩን አብራርተዋል።

ኢትዮጵያ በመንግሥት ከሚመራ የኢኮኖሚ ሞዴል ወደ የግሉ ዘርፍ የባለቤትነት ድርሻ በሰፊው ወደሚሰፍንበት የገበያ ኢኮኖሚ እየተሸጋገረች መሆኗን የጠቆሙት ዶክተር ዲማ፣ በዚህም ሂደት በርካታ ዘርፎች ለግሉ ዘርፍ ክፍት መደረጋቸውን ጠቁመዋል።

የአውሮፓ ኅብረት ተወካይ ዳንኤል ሀቼዝ በበኩላቸው፣ የኅብረቱ ኢኒሼቲቭ የሆነው ‘ግሎባል ጌትዌይ’ መሠረተ ልማትን፣ ንግድን፣ መልካም አስተዳደርን እና መዋቅራዊ ማነቆዎችን ለመፍታት የመንግሥት እና የግል ተቋማትን ድጋፍ እንደሚያጠናክር ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ እና የአውሮፓ ኅብረት ‘ግሎባል ጌትዌይ’ በጋራ ከሚሠሩባቸው ዋና ዋና ሴክተሮች መካከል የኤሌክትሪክ ግሪድን ማዘመን፣ የገጠር ኤሌክትሪክ አቅርቦትን ማስፋፋት፣ እንዲሁም ዝቅተኛ የካርቦን ልቀት ወደሚያመነጭ እና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ መሸጋገር ዋና ዋናዎቹ መሆናቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም በንግድ እና ሎጅስቲክስ ዘርፍ፤ በኤክስፖርት ላይ የተመሠረተ ዕድገትን ማሳካት፣ መዋቅራዊ የንግድ ትሥሥር መፍጠር እና የሎጅስቲክስ ተወዳዳሪነትን ማሻሻል ከኅብረቱ ጋር በቅርበት የሚሠራባቸው ቁልፍ የትብብር መስኮች መሆናቸው በመድረኩ ተመላክቷል።

በፖሊሲ ውይይቱ ላይ አምባሳደሮች፣ ፖሊሲ አውጪውች እና ከፍተኛ ዲፕሎማቶች እየተሳተፋ ይገኛሉ።

የህዳሴ ግድብ በሀብታችን የመጠቀም ጅማሮ እንጂ መጨረሻ አይደለም ሲሉ የውሃ ምህንድስና ተመራማሪው ገለጹኦቢኤን ሣይበር ሚዲያ ነሐሴ 26/ 2018ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ የገነባችው ግድብ ...
01/09/2026

የህዳሴ ግድብ በሀብታችን የመጠቀም ጅማሮ እንጂ መጨረሻ አይደለም ሲሉ የውሃ ምህንድስና ተመራማሪው ገለጹ

ኦቢኤን ሣይበር ሚዲያ ነሐሴ 26/ 2018

ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ የገነባችው ግድብ ጅማሮ መሆኑንና ገና በርካታ ሥራዎች ሊከናወኑ እንደሚችሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የውኃ ምሕንድስና መምህሩ ፕሮፌሰር ይልማ ስለሺ ገለጹ።

የውኃ ምሕንድስና መምህሩ ፕሮፌሰር ይልማ ስለሺ ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ከዓባይ ወንዝ ገና መጠቀም ጀመረች እንጂ የማንንም ጥቅም አልነካችም። ኢትዮጵያ የራሷን የተፈጥሮ ሀብት ተጠቅማ የሕዳሴ ግድብን በመገንባቷ ምንም ዓይነት ቅሬታ የሚያስነሳባት ጉዳይ እንደሌለም ተናግረዋል።

የዓባይ ወንዝ 45 ሺህ ጊጋ ዋት ኃይል ማመንጨት የሚያስችል አቅም እንዳለው የጠቆሙት ፕሮፌሰር ይልማ፤ ኢትዮጵያ በሕዳሴ ግድብ ላይ የምታከናውናቸው ሥራዎች የተደበቁ ሳይሆኑ በግልጽ ለሁሉም በሚታይ መልኩ የሰፈሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የዓባይ ወንዝ ከኢትዮያ የሚነሳ ሀብቷ ቢሆንም የታችኛውም ሆነ የላይኛው ተፋሰስ ሀገራትን በሚጠቅምና ምክንያታዊ በሆነ መንገድ መጠቀም ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ያስቀመጠችው እውነታ እንደሆነም አብራርተዋል።

ኢትዮጵያ ዓለም አቀፉን ሕግ የተላለፈችበት ጊዜ እንደሌለ የገለጹት ፕሮፌሰር ይልማ፤ አሁንም ቢሆን ፍትሐዊና ምክንያታዊ በሆነ መንገድ ወንዙን ለሌሎች አገልግሎቶች የመጠቀም ሙሉ መብት እንዳላት አስረድተዋል።

የግብፅ ጩኸት የውኃ መጠን ቀንሶባት ሳይሆን ቀደም ሲል በበላይነት የመጠቀም አሠራሯ እንዳያበቃ ከመስጋት የመነጨ መሆኑንም ፕሮፌሰሩ አክለው ገልጸዋል።

የህዳሴ ግድብ ጳጉሜ 4 ቀን 2017 ዓ.ም ተመርቆ ወደ ሥራ መግባቱና ኃይል ማመንጨት መጀመሩ ይታወሳል።

01/09/2026

የኢትዮጵያ የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት በራስ አቅም የተቀናጀ ተቋማዊ የለውጥ እርምጃም ተትቶ የቆየውን የሥራ ቦታ ወደ ማራኪ የሥራ ከባቢነት ለመቀየር አስችሎታል-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

"የ21ኛው ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ኅብረ-ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር ለዘላቂ ሰላም እና ለኢኮኖሚ ዕድገታችን ጉልህ አበርክቶ ይኖረዋል" -አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገርኦቢኤ...
01/09/2026

"የ21ኛው ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ኅብረ-ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር ለዘላቂ ሰላም እና ለኢኮኖሚ ዕድገታችን ጉልህ አበርክቶ ይኖረዋል" -አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር

ኦቢኤን ሣይበር ሚዲያ ነሐሴ 26/ 2018

የኢፌዲሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤና የበዓሉ አስተባባሪ ዐቢይ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አገኘሁ ተሻገር በ21ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ላቅ ያለ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ውጤት እንዲመዘገብ ከወዲሁ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን ገለጹ።

አፈ ጉባኤው እንዳመለከቱት በዓሉ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ባህልና ልምዳቸውን በመለዋወጥ ኅብረ-ብሔራዊና ዲሞክራሲያዊ አንድነታቸውን እንዲያጠናክሩ እንዲሁም ለሀገራችን ዘላቂ ሰላምና ዘርፈ-ብዙ የኢኮኖሚ እድገት በጋራ እንዲቆሙ ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል።

በዓሉ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ እና ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ተጠናቅቆ አዲስ መንግሥት በተመሰረተበት፣ ሀገራዊ ችግሮችን በምክክር ለመፍታት መሠረት በተጣለበት እንዲሁም የዲሞክራሲ ባህልን የሚያጎለብቱ በርካታ አገራዊ ሁነቶች በተከናወኑበት ማግሥት የሚከበር በመሆኑ የተለየ ትርጉምና ገጽታ ይኖረዋል።

የገዳ ሥርዓትን ጨምሮ የበርካታ ታሪካዊና ባህላዊ ሀብቶች ባለቤት በሆነችው ታሪካዊቷ የጅማ ከተማ በሚካሄደው በዚህ በዓል፣ የሕዝቦች ወንድማማችነትና አብሮነት ከፍ ብሎ እንደሚንፀባረቅ ተጠቅሷል።

Address

Bole
Adama
2919

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when OBN አማርኛ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to OBN አማርኛ:

Shortcuts

Share