Adama Customs Branch Office የአዳማ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Adama
  • Adama Customs Branch Office የአዳማ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ ቤት

Adama Customs Branch Office የአዳማ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ ቤት Adama Customs Branch Office
የአዳማ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ ቤት

04/06/2026
04/06/2026

የሀርሞናይዝድ ሲስተም ታሪፍ የአተረጓጎም አጠቃላይ ደንቦች

 የሀርሞናይዝድ ሲስተም አተረጓጎም አጠቃላይ ደንቦች 6 ናቸው፣

 በሕግ ፊት ተቀባይነት አላቸዉ፣

 የታሪፍ መጽሐፉን እንዴት አድርገን እንደምንጠቀምበት ያስረዱናል
ወይም ያዙናል፣

 የዕቃዎች ምደባ ወጥ (Uniform) እንዲሆን የሚያስችሉ ደንቦች ናቸው፣

 ከደንብ ቁጥር 1 እስከ ደንብ ቁጥር 4 ድረስ ያሉትን የምንጠቀምባቸው
በቅደም ተከተል ነው

 ደንቦቹ አንድ ዕቃ የሚመደብበትን የታሪፍ አንቀጽን ለይቶ ለመወሰን
የሚያገለግሉ ናቸው፣

 ደንብ ቁጥር 1 የሚያዘውን በሚገባ ሳንፈጽም ወደ ደንብ ቁጥር 2
ብንሻገር የታሪፍ ምደባው የተሳሳተ ሊሆን ይችላል፣

 ደንብ ቁጥር 5 እና 6 የሚታዩት በየራሳቸው ነው እንጂ ከላይ እንዳሉት
ህጎች በቅደም ተከተል አይደለም፣

 ደንብ ቁጥር 5 የሚገልጽልን የዕቃ መጠቅለያዎችን፣ ማሸጊያዎችንና
መያዣዎችን እንዴት አድረገን እንደምንመድባቸው ነዉ፣

 ከደንብ ቁጥር 1 እስከ 5 እስከ በባለአራት ዲጂት አንቀጽ ድረስ
አመዳደቡን ይወስናሉ፣

 ደንብ ቁጥር 6 ደግሞ አንድ ዕቃ የሚመደብብትን ንዑስ አንቀጽ ወይም
ኤች. ኤስ ኮድን የሚመለከት ነው፡፡

ይቀጥላል----------

03/06/2026

የጉምሩክ አስተላላፊነት ሥልጠና የሚያካትታቸው የሥልጠና ዓይነቶች

በኮሚሽኑ ለጉምሩክ አስተላላፊዎች የሚሰጥ ስልጠና ይዘት የሚከተሉትን ያካትታል፡-

 የዕቃ ስያሜ ፣ የታሪፍ አመዳደብና አተረጓጎም ፣
 የዋጋ አተማመንና የቀረጥና ታክስ ስሌት ፣
 የስሪት አገር ማረጋገጫ እና አሠራር ፣
 የዕቃ ዲክላራሲዮን አሞላል ፣
 የጉምሩክ የመረጃ ቴክኖሎጂ ሥርዓት አጠቃቀም ፣
 የትራንዚት ዕቃዎች የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ፣
 የገቢና ወጪ ዕቃዎች አወጣጥ ሥነ-ሥርዓት ፣
 የመጋዘን አሠራር ሥርዓት ፣
 የወጪ ንግድ ማበረታቻ ሥርዓት ፣
 ስለቀረጥ ተመላሽ ፣
 ስለቀሪ ቀረጥና ታክስ አከፋፈል ፣
 አቤቱታ እና ይግባኝ አቀራረብ ሥነ-ሥርዓት ፣
 የድህረ-ዕቃ አወጣጥ ኦዲት የአሠራር ሥርዓት ፣
 ስለጉምሩክ ሕጎች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎችና የአሠራር መርሆች ፣
 ስለጉምሩክ አስተላላፊነት ሥነ-ምግባር ፣
 ዓለም አቀፍ የዕቃ ግዥ፣ ሽያጭና የባንክ አሠራር ፣
 የወደብ ሥራ ክንውን ጽንሰ ሀሳብ ፣
 የደንበኞች አያያዝና አገልግሎት አሠጣጥ እና ፣
 እንደ አስፈላጊነቱ ሌሎች በኮሚሽኑ የሚካተቱ የሥልጠና ዓይነቶች ናቸው፡፡

02/06/2026
ለመላው የአዳማ ጉምሩክ የእስልምና እምነት ተከታይ ሰራተኞች ፣ አስመጪና ላኪዎች፣ ጉምሩክ አስተላላፊዎች እና ተጓዳኝ ተቋማት በሙሉ እንኳን ለ1447 ኛው ታላቁ የዒድ አል አደሃ የአረፋ  በዓ...
26/05/2026

ለመላው የአዳማ ጉምሩክ የእስልምና እምነት ተከታይ ሰራተኞች ፣ አስመጪና ላኪዎች፣ ጉምሩክ አስተላላፊዎች እና ተጓዳኝ ተቋማት በሙሉ እንኳን ለ1447 ኛው ታላቁ የዒድ አል አደሃ የአረፋ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። አደረሰን!!
በዓሉ አብሮነትን አጠንክረን ለጋራ ራዕይ የምንተጋበት በእምነቱ አስተምሮ መሰረት ድጋፍ ለሚሹ ወገኖቻችን መአድ አጋርተን የምንውልበት የደስታ በዓል እንዲሆን የአዳማ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ከልብ ይመኛል፡፡
መልካም በዓል
ኢድ ሙባረክ!!

Address

Adama

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Adama Customs Branch Office የአዳማ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Adama Customs Branch Office የአዳማ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ ቤት:

Share