ANRS authority of labor affairs

ANRS authority of labor affairs Amhara National Regional State Authority Labor of affairs. Government Authority

29/10/2025
26/10/2025

ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ለክልል ተቋማት መሪዎች ሹመት ሰጡ።
**************
የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ከጥቅምት 15/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተለያዩ የክልል ተቋማት መሪዎች ሹመት ሰጥተዋል።

ሹመት የተሰጣቸው መሪዎች የአመራር ብቃት፣ የሥራ ልምድ፣ የትምህርት ዝግጅት እና ሥነ ምግባራቸውን መሰረት በማድረግ ነው።

በዚህም መሰረት :-

1. አማኑኤል ፈረደ (ዶ.ር) በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአሥተዳደር ክላስተር አስተባባሪ

2. አቶ ደረጀ ማንደፍሮ ዳመነ፡ የግብርና ቢሮ ኃላፊ

3. አቶ ጥላሁን ወርቅነህ ተክሌ፡ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ

4. አቶ አታላይ ጥላሁን፡ የገንዘብ ቢሮ ኃላፊ

5. ዳኝነት ፈንታ መኮነን (ዶ.ር)፡ የውኃና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ

6. ጋሻው ሙጨ (ዶ.ር)፡ እንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ

7. ሞላ መልካሙ (ዶ.ር)፡ የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ

8. መንገሻ ፈንታው (ዶ.ር)፡ የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ

9. አቶ ዓባይ መንግስቴ፡ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ

10. አቶ አሰፋ ሲሳይ ተሾመ፡ የኮንስትራክሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር

11. ማተቤ ታፈረ (ዶ.ር)፡ የአማራ ስቴት ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት

12. አቶ እሱባለው መሰለ ፀጋየ፡ የአማራ ስቴት ዩኒቨርስቲ ምክትል ፕሬዝዳንት

13. አቶ እርዚቅ ኢሳ፡ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የርእሰ መስተዳድሩ ሕዝብ ግንኙነት አማካሪ

14. አቶ ይትባረክ አወቀ፡ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የርእሰ መስተዳድሩ ልዩ አማካሪ

15. ዘላለም ልጃለም (ዶ.ር)፡ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የርእሰ መስተዳድሩ ጸጥታ ጉዳዮች አማካሪ

16. ፈንታየ ጥበቡ (ዶ.ር)፡ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የርዕሰ መስተዳድሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ

17. ወልደትንሣኤ መኮንን ፈለቀ (ዶ.ር)፡ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የውኃና ኢነርጂ ቢሮ አማካሪ

18. ሰይድ እሸቴ (ዶ.ር)፡ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የመሬት ቢሮ አማካሪ

19. አቶ አብይ አበባው ተስፋሁን፡ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የርእሰ መሥተዳድሩ ስትራቴጂክ ዘርፍ አማካሪ

20. ምትኩ አለማየሁ (ዶ.ር)፡ የፕላን ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር

21. አቶ ወርቁ ያየህ፡ የኅብረተሰብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ

22. አቶ አዲስ በየነ፡ የባሕል፣ ኪነ ጥበብና ዝክረ ታሪክ ጽ/ቤት ኃላፊ

23. አቶ አየልኝ መሳፍንት፡ የግብርና ቢሮ መስኖ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

24. ወ/ሮ መሰሉ ብርሃኑ ካሳው፡ የግብርና ቢሮ ተፈጥሮ ሀብት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

25. ወ/ሮ እታገኝ አደመ ገላው፡ የግብርና ቢሮ ምግብ ዋስትና ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

26. አቶ ዘውዱ ማለደ፡ የመንገድ፣ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

27. አቶ ጋሻው ተቀባ፡ የባሕል፣ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ የስፖርት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

28. አቶ ዘላለም አረጋ ፡ የሴቶች ሕጻናትና ወጣቶች ቢሮ ወጣት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

29. አቶ ነጋ ይስማው፡ እንስሳትና ዓሳ ሀብት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

30. ለዓለም ጥላሁን (ዶ.ር) ፡ የፕላንና ልማት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

31. ወ/ሮ ስመኝ ዋሴ፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

32. አቶ ጋሻው እሸቱ፡ በምክትል ቢሮ ኃላፊ ደረጃ የርእሰ መስተዳደሩ ሕዝብ ግንኙነት ረዳት አማካሪ

33. ተስፋሁን ተናኘ ፈሩህ (ዶ.ር)፡ የፕላን ኢኒስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር

34. አቶ ገ/ማርያም ይርጋ፡ የባሕል፣ ኪነ ጥበብ እና ዝክረ ታሪክ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ

35. ወ/ሮ የሺ ካሴ፡ የባሕል፣ ኪነ ጥበብና ዝክረ ታሪክ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ በመሆኑ ሹመት ተሰጥተዋል ።

አሚኮ

23/10/2025

የዘርፉን አዳዲስ እሳቤዎች እስከታችኛው መዋቅር ድረስ በማውረድ የክልሉን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ቢሮው አስታወቀ

የአማራ ክልል ለሚገኙ የክልል፣ የዞንና የወረዳ የዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች
በተሻሻሉ የዘርፉ ማስፈፀሚያ ሰነዶች ላይ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።

በአማራ ክልል ሥራና ስልጠና ቢሮ ኃላፊ ስቡህ ገበያው (ዶ/ር )እንደገለፁት፤ ክልሉ በፈታኝ ሁኔታ ውስጥ ሆኖም ለዜጎች የሥራ ዕድል የመፍጠር ሥራ በትኩረት እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር በክልሉ የዘርፉን ኃላፊዎችና ባለሙያዎች አቅም ለማጎልበት እያደረገ ለሚገኘው ጥረት አመስግነው የዘርፉን አዳዲስ እሳቤዎች እስከታችኛው መዋቅር ድረስ በማውረድ የክልሉን ነዋሪዎች ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ቢሮው እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በመድረኩ በተሸሻለው የጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ፖሊሲ ፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ መመሪያ፣ በቤተሰብና ማህበረሰብ ንግድ አደረጃጀት፣ በሥራ ማዕከላት ሪፎርምና የዕሴት ሰንሰለትን መሰረት ባደረገ ሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ ( ፌደራል ሥራና ክህሎት ሚኒስትር ነው)

“ በስራ ቦታ የኤች.አይቪ.ኤድስን መከላከል የግንዛቤ ማስጠጨበጫ ውይይት ተደረገ ”                             ጥቅምት 6/2018 ዓ.ም የአብክመ አሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ባለስ...
16/10/2025

“ በስራ ቦታ የኤች.አይቪ.ኤድስን መከላከል የግንዛቤ ማስጠጨበጫ ውይይት ተደረገ ”
ጥቅምት 6/2018 ዓ.ም
የአብክመ አሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ባለስልጣን ሠራተኛች እና የሚመለከታቸው አካላት ጋር በወቅታዊ ኤች.አይቪ.ኤድስ መከላከል ዙሪያ የማህበረሰብ አቀፍ ውይይት የተደረገ ሲሆን የመወያያ መነሻ ፁሁፍ በመ/ቤቱ ሥርዓተ-ፆታ ባለሙያ የሆኑት አቶ አብርሀም ምትኬ ሰነዱን አቅርበዋል፡፡

በውይይቱም ወቅት የኤች.አይቪ ኤድስ የመከላከል ግንዛቤ ከመስጠት አኳያ እየተረሳ እና ትኩረት እየተነፈገው የመጣ በመሆኑ መሰጠት ያለበትና ለተተኪ ትውልድ ግንዛቤ ከመስጠት አኳያ እያንዳንዳችን ድርሻ እንዳለበት ተገልፃል፡፡

በመጨረሻም የባለስልጣን መ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ስመኝ ዋሴ በሥራ ቦታዎች በኤች.አይቪ.ኤድስን መከላከል በትኩረት ተይዞ መሠራት እንዳለበት አሣስበው እንዲሁም በውይይቱ የተነሱ ጥያቄዎችን በመመለስና አስተያየቶችን በመቀበል እንዲሁም የማጠቃለያ ሃሣባቸው እያንዳንዳችን እንደሃገር እንደ መ/ቤት ትኩረት ሰጠን መስራት እንዳለበት በመጨመር መድረኩ ተጠናቋል፡፡

ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ባለስልጣን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ፡፡
በቴሌግራም አድራሻችን
https://t.me/ANRSALOA
በኤክስ (በትዊተር)አድራሻችን
https://twitter.com/
በፊስቡክ አድራሻችን(
https://www.facebook.com/Amharalaboraffairs
መስከረም 6/2018 ዓ.ም
ባህር ዳር

የአብክመ አሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ባለስልጣን ዓለም አቀፉ የአረጋውያን ቀን በዓል አክብሮ ዋል፡===========================================                   ...
08/10/2025

የአብክመ አሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ባለስልጣን ዓለም አቀፉ የአረጋውያን ቀን በዓል አክብሮ ዋል፡===========================================

መስከረም 28/2018 ዓ.ም

በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ35ኛ ጊዜ በአገራችን በኢትዮጵያ ለ34ኛ ጊዜ “ለአረጋውያን ደኅንነት እና መብቶች መጠበቅ ሁለንተናዊ ኃላፊነታችንን እንወጣ” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ነው።

የአብክመ አሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ባለስልጣን ሠራተኛች ፣ ኃላፊዎች በአረጋዊያን ቀን አስመልክቶ የመወያያ ጽሁፍ የቀረበ ሲሆን ሰነዱ አለም አቀፋ የህግ ማዕቀፎች፣ አረጋዊያንን በተመለከተ ያሉ አለም አቀፋ ዘላቂ የልማት ግቦች እንዲሁም የፖሊሲ ማዕቀፎች ቀርበው ውይይት ተደርጓል፡፡

በውይይቱም ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ጉዳዮች የተነሱ ሲሆን እንደችግር እየታዩ ያሉ የማህበራዊ ስብራቶች ፣ መንስኤዎች የሚመለከተው አካል በዘላቂነት ለመፍታት በጥናት መለየት እንዳለባቸው ተመላክቷል፡፡

በመጨረሻም የባለስልጣን መ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ስመኝ ዋሴ ጥያቄዎችን በመመለስና አስተያየቶችን በመቀበል እንዲሁም የማጠቃለያ ሃሣባቸውን በመጨመር መድረኩን አጠናቀዋል፡፡

ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ባለስልጣን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ፡፡
በቴሌግራም አድራሻችን
https://t.me/ANRSALOA
በኤክስ (በትዊተር)አድራሻችን
https://twitter.com/
በፊስቡክ አድራሻችን(
https://www.facebook.com/Amharalaboraffairs
መስከረም 28/2018 ዓ.ም
ባህር ዳር

02/10/2025
26/09/2025
ለመላው የኦርቶዶክስ የክርስትና እምነት ተከታዮች!!እንኳን ለ2018 ዓ.ም ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ!! ለሰው ልጆች ቤዛ፣መድሀኒት እና ሀይል ነውና በዓሉ የምህረትና የእርስ በእርስ ፍቅር ...
26/09/2025

ለመላው የኦርቶዶክስ የክርስትና እምነት ተከታዮች!!
እንኳን ለ2018 ዓ.ም ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ!!

ለሰው ልጆች ቤዛ፣መድሀኒት እና ሀይል ነውና በዓሉ የምህረትና የእርስ በእርስ ፍቅር መሰረት በመሆኑ ፍቅራችንን የምናፀናበት የአንድነታችን ማጥበቂያ መስቀል ነው።

ቅዱስ መስቀል ከተቀበረበት መሬት በንግስት እሌኒ አማካኝነት መገኘቱን ስናስብ በአሁኑ ዘመን ከብዙዎቻችን የራቀንን ፍቅርና አንድነት እንዲገለጥልን ተስፋ በማድረግ ነው።

በዓሉን ስናከብር የወደቁትን በማንሳት፣የተራቡትን በማብላት፣የታመሙትን በመጠየቅ፣የተጣሉትን በማስታረቅ እንደሚሆን በማመን ነው።

መልካም በዓል!!
የአብክመ አሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ባለስልጣን፡

ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ባለስልጣን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ፡፡
በቴሌግራም አድራሻችን
https://t.me/ANRSALOA
በኤክስ (በትዊተር)አድራሻችን
https://twitter.com/
በፊስቡክ አድራሻችን(
https://www.facebook.com/Amharalaboraffairs
መስከረም 16/2018 ዓ.ም
ባህር ዳር

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መመረቁን አስመልክቶ የአብክመ አሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ባለስልጣን ሠራተኞች እና አመራሮች  በባህር ዳር ከተማ በተዘጋጀው  የሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ላይ በመገኘት ድ...
16/09/2025

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መመረቁን አስመልክቶ የአብክመ አሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ባለስልጣን ሠራተኞች እና አመራሮች በባህር ዳር ከተማ በተዘጋጀው የሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ላይ በመገኘት ድጋፍቸውን ገልፀዋል፡፡
06/1/2018 ዓ.ም
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ባለስልጣን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ፡፡
በቴሌግራም አድራሻችን
https://t.me/ANRSALOA
በኤክስ (በትዊተር)አድራሻችን
https://twitter.com/
በፊስቡክ አድራሻችን(
https://www.facebook.com/Amharalaboraffairs
መስከረም /2018 ዓ.ም
ባህር ዳር

እንኳን ለ2018 አዲስ ዓመት በሠላም አደረሳችሁ!!     "አብክመ አሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ባለስልጣን "በዓሉ የሰለም የጤና የመተሳሰብ ዘመን እንዲሆን ምኞቱን ይገልፃል።            መል...
10/09/2025

እንኳን ለ2018 አዲስ ዓመት በሠላም አደረሳችሁ!!
"አብክመ አሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ባለስልጣን "

በዓሉ የሰለም የጤና የመተሳሰብ ዘመን እንዲሆን ምኞቱን ይገልፃል።
መልካም በዓል!!

09/09/2025
"እንኳን  ለ1ሺ500ኛው የመውሊድ በዓል   በሰላም አደረሳችሁ " ።ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች  በሙሉ ነገ ነሐሴ 29 ቀን 2017 ዓ.ም  ለሚከበረዉ ለ1ሺ 500ኛው  የነቢዩ መሐመ...
03/09/2025

"እንኳን ለ1ሺ500ኛው የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ " ።

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ ነገ ነሐሴ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ለሚከበረዉ ለ1ሺ 500ኛው የነቢዩ መሐመ የመውሊድ (ልደት) በዓል በሰላም አደረሳችሁ። በአሉ የሰላም ፣ የፍቅር እና የመተሳሰብ እንዲሆን እንመኛለን::

"መልካም የመውሊድ በዓል ።"

የአማራ ክልል አሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ባለስልጣን

Address

Bahir Dar
Abba
461

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ANRS authority of labor affairs posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to ANRS authority of labor affairs:

Share