Tachbet Woreda Court-ታችቤት ወረዳ ፍርድ ቤት

Tachbet Woreda Court-ታችቤት ወረዳ ፍርድ ቤት ይህ የፌስቡክ ገፅ የፍርድ ቤቱን አገልግሎት ለህብረተሰቡ ማሳወቅ እና ግንዛቤ ማስጨበጥ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው::

የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በስሩ ከሚገኙ ወረዳ ፍ/ቤች ጋር የ2015 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2016 በጀት ዓመት እቅድ ትውውቅ መድረክ በደብረ ብርሃን ከተማ አካ...
30/07/2023

የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በስሩ ከሚገኙ ወረዳ ፍ/ቤች ጋር የ2015 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2016 በጀት ዓመት እቅድ ትውውቅ መድረክ በደብረ ብርሃን ከተማ አካሄዷል ፡፡ በመድረኩም የ2015 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ሲካሄድ በ12 መመዘኛ ወረዳ ፍ/ቤቶችን አወዳድሯል፡፡ በዚህም የታች ቤት ንዑስ ወረዳ ፍ/ቤት አብዛኛውን መመዘኛ በማሟላት ከ32 ወረዳ ፍ/ቤቶች 89.8 በማስመዝገብ 1ኛ ደረጃን በመያዙ የወረደውን ህዝብ እና የፍ/ቤቱን ሰራተኞች እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እንወዳለን ፡፡
ለዚህ ስኬት የበቃነው በፍ/ቤቱ ዳኞች እና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ከፍተኛ ርብርብ እንዲሁም ትጋት በመሆኑ ከፍተኛ አፍፃፀማችን ወፊትም እንድናስቀጥል በማለት በድጋሚ እንኳን ደስ አለን እንኳን ደስ አላችሁ!!!
2ኛ ደረጃ ላገኘው ለአንፆኪያ ወረዳ ፍ/ቤት እና 3ኛ ደረጃ ላገኘው ለምንጃር ወረዳ ፍ/ቤትም በፍ/ቤታችን ስም እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እንወዳለን!!!
👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏

የታች ቤት ንዑስ ወረዳ ፍ/ቤት ያለበትን የቢሮ እና የችሎት ጥበት በጊዜያዊነት ለማቃለል ቀበሌውን ፣ ባለሃብት እና ልዩ ልዩ ተቋማትን በማስተባበር ግንባታ ማከናውን ችሏል፡፡ በዚህም የአንድ ...
18/07/2023

የታች ቤት ንዑስ ወረዳ ፍ/ቤት ያለበትን የቢሮ እና የችሎት ጥበት በጊዜያዊነት ለማቃለል ቀበሌውን ፣ ባለሃብት እና ልዩ ልዩ ተቋማትን በማስተባበር ግንባታ ማከናውን ችሏል፡፡ በዚህም የአንድ መስኮት አገልግሎት ለመስጠት እና ለሚመደብለት የዳኛ ቁጥር የዳኝነት አገልግሎቱን ለመስጠት በዝግጅት ላይ ይገኛል ፡፡
ሆኖም ይህ ግንባታ ችግሩን በዘለቄታ የማይፈታ በመሆኑ ፍ/ቤቱ ያለበትን የቢሮ ጥበት ወርዳው ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት ብርቱ የሆነ ርብርብ ሊያደርግ ይገባል ፡፡

የታች ቤት ንዑስ ወረዳ ፍ/ቤት የ2015 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም/*/*/*/*/*/*/*/*/*/*/*/*/*/*/*/*/መዝገብ አፈፃፀም=============== #የፍታብሄር ጉዳይካለፈው የተ...
09/07/2023

የታች ቤት ንዑስ ወረዳ ፍ/ቤት የ2015 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም
/*/*/*/*/*/*/*/*/*/*/*/*/*/*/*/*/
መዝገብ አፈፃፀም
===============
#የፍታብሄር ጉዳይ
ካለፈው የተላለፈ መዝገብ ብዛት=>72
አዲስ የቀረበ የመዝገብ ብዛት=>992
ከመዝገብ ቤት የተንቀሳቀሰ= >228
ድምር አቅርቦ=>1292
ክንውን=>1276
ወደ ቀጣይ ዓመት የተላለፈ=>16
ሰበር አዲስ የቀረበ=> 4
የተወሰነ=>4
እቅድ= >1244
ክንውን=>1280
ክንውን ከእቅድ=>103%
ክንውን ከአቅርቦት=>99%
የማጥራት አቅም=>105%
የመጨናነቅ መጠን=>1.01
የክምችት ቅነሳ=>0.01
#ወንጀል ጉዳይ
ካለፈው የተላለፈ መዝገብ ብዛት=>2
አዲስ የቀረበ የመዝገብ ብዛት=>212
ከመዝገብ ቤት የተንቀሳቀሰ=>55
ድምር አቅርቦት =>269
ክንውን=>269
ወደ ቀጣይ ዓመት የተላለፈ መዝገብ=>0
እቅድ=>258
ክንውን ከእቅድ=>104%
ክንውን ከአቅርቦት=>100%
የማጥራት አቅም=>101%
የመጨናነቅ መጠን=>1
# #ፍታብሔር እና ወንጀል ጉዳዮች
ካለፈው የተላለፈ መዝገብ=>74
አዲስ የቀረበ የመዝገብ ብዛት=>1208
ከመዝገብ ቤት የተንቀሳቀሰ=>283
ድምር አቅርቦት=>1502
እቅድ=>1502
ክንውን=>1549
ክንውን ከእቅድ=>103%
ክንውን ከአቅርቦት=>99%
የማጥራት አቅም=>104%
የክምችት ቅነሳ ጊዜ=>0.01
የክምችት መጠን=>1.01
ወደ ቀጣይ ዓመት የተላለፈ=>16
RTD የቀረበ=>15
የተወሰነ=>12
#ተዘዋዋሪ ችሎት
የተዘዋዋሪ ቀጠና=>4
በተዘዋዋሪ ችሎት ለመታየት የቀረበ=>55
በተዘዋዋሪ ችሎት የተዘጋ መዝገብ=>46
አገልግሎት ያገኙ ባለጉዳዮች
ወ-137 ሴ-66 ድምር->203
ለተገልጋዩ የቀረላቸው ወጪ ->30450ብር
ፍ/ቤቱ ለተዘዋዋሪ ችሎት ያወጣው ወጭ->4,823.45ብር
የተዘዋዋሪ ችሎት ወጭ በመዝገብ
- >88ብር
#ውሳኔ ያገኙ መዝገቦች ጊዜ ቆይታ
ከ30ቀን በታች=>1377/88.9%/
ከ1-2ወር=>134/9%/
ከ6ወር በላይ=>2/0.1%/
#ቀጠሮ ላይ ያሉ መዝገቦች የጊዜ ቆይታ
ከ30 ቀን በታች=>13/81%/
ከ1-2ወር=>3/19%/
#ይግባኝ
ለከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ይጠይቁ መዝገቦች=>74
ከፍተኛ ፍ/ቤት ደርሰው የመለሱ=>37 መዝገብ
የፀና=>25/67%/
የተሻረ=>8/21.6%/
የተሻሻለ=>4/10.8%/
#ገቢ
ከመቀጮ=>20100
ከዳኝነት=>171515ብር
በነፃ የታየ በገንዘብ ሲተመን=>6435.50
በደሃ ደንብ የመለሰ የዳኝነት ገንዘብ=>27318ብር
#እርቅ
ለእርቅ የተመራ መዝገብ->281
የተስተናገዱ ባለጉዳዮች ወ-386 ሴ-261 ድምር->647
በእርቅ የተዘጉ መዝገቦች ->195
የታራቂዎች ብዛት ወ-280 ሴ-177
ድምር->457
ቢከራከሩ ያወጡ የነበረው ወጪ->228500ብር
እስኪታረቁ ያወጡት ወጭ137100 ብር
በመታረቃቸው የቀረላቸው ወጪ -> 91400 ብር
#ልዩልዩ
#ቅድሚያ አገልግሎት
ለአካል ጉዳተኛ ወ-15 ሴ-7 ድምር ->22
ለአረጋውያን ወ-210 ሴ-122 ድምር->332
ለእምጫት ነፍሰጡር ሴቶች -118
#ፎርማት የተጠቀሙ ባለጉዳዮች
ወ-962 ሴ-835 ድምር->1797
ፎርማት በመቀማቸው የቀረላቸው ወጪ 157080 ብር
#የተገልጋይ እርካታ በዳሰሳ ጥናት 82.8%
#የምክክር መድረክ 4 ጊዜ ተካሄዷል
#የተላለፈ ዜና በሬዲዮ11 በምዲያ15
ዓመታዊ መፅሄት አንዴ ተዘጋጅቷል
#በጎ አድራጎት ወላጇን በHIV ላጣች ህፃን 2597 ብር ተሰብስቧል
ስልጠና ለሰራተኞች ፣ለማህበራዊ ፍ/ቤት ዳኞች፣ለመሬት ዴስክ ባለሞያዎች ተሰቷል፡፡
እውቅና ለሰራተኞች ና ለዳኛ ተሰቷል፡፡
ሰኔ 30/2015ዓ=ም ውይይቱ ተካሄዷል

የታች ቤት ንዑስ ወረዳ ፍ/ቤት ንብረት ክፍል ኦፊሰር በመሆን ህዝባቸውን በታማኝነት እና በታታሪነት ሲያገለግሉ የነበሩትን አቶ ወንዲራድ ገስጥ ጡረታ መውጣታቸውን በማስመልከት በስራ ባልደረቦቻ...
09/05/2023

የታች ቤት ንዑስ ወረዳ ፍ/ቤት ንብረት ክፍል ኦፊሰር በመሆን ህዝባቸውን በታማኝነት እና በታታሪነት ሲያገለግሉ የነበሩትን አቶ ወንዲራድ ገስጥ ጡረታ መውጣታቸውን በማስመልከት በስራ ባልደረቦቻቸው ግንቦት1 ቀን2015ዓ.ም ደማቅ የሽኝት ፕሮግራም ተካሄደ፡፡ በእለቱም በፍ/ቤቱ በነብራቸው ቆይታ ብስራቸው ለነበራቸው ትጋት እንዲሁም መልካም ስነ-ምግባር ምስጋና ተችሯቸዋል፡፡ በመጨረሻም መልካም የእርፍት ጊዜ እንዲሆንላቸው በመመኘት ከስራ ባልደርቦቻቸው ፣ ከዳኞች እና ቀድሞ የፍ/ቤቱ ዳኞች በነበሩ ጭምር ማስታወሻ ይሆናቸው ዘንድ ስጦታ ተበርክቶላቸዋል፡፡

08/04/2023

ጎረቤቶችን እንቅልፍ በመንሳት የተከሰሰው አውራ ዶሮ እንዲታረድ የናይጄሪያ ፍርድ ቤት ወሰነ

ናይጄሪያ ውስጥ ጉዳዩ ፍርድ ቤት የደረሰው ጩኸቱ ጎረቤቶችን ሰላም የነሳው አውራ ዶሮ በድምጽ ብክለት ምክንያት እንዲታረድ ተፈረደበት።

በአንድ አውራ ዶሮ ምክንያት እንቅልፍ አጣን ያሉት ናይጄሪያውያን ለፍርድ ቤት ባቀረቡት አቤቱታ ነው ባለቤቱ አውራ ዶሮውን እስከ መጪው አርብ ድረስ እንዲያርደው መወሰኑን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን የዘገቡት።

በሰሜናዊ ናይጄሪያ ካኖ ግዛት ውስጥ የሚገኘው ፍርድ ቤት ሁለት ሰዎች የአውራ ዶሮው የማይቋረጥ ጩኽት ሰላም አሳጣን፣ እንቅልፍ ነሳን በማለት ነበር የቀረበለትን ክስ ተከትሎ ነው ብይን የሰጠው።

በዶሮው እና በባለቤቱ ላይ ክስ ካቀረቡት ግለሰቦች መካከል አንዱ የሆነው ግለሰብ ዩሱፍ ሙሐመድ፣ የአውራ ዶሮው ጩኽት በቤቱ ውስጥ የሰላም እንቅልፍ የማግኘት እና የማረፍ መብቱን እንደጣሰበት ለፍርድ ቤቱ ተናግሯል።

የአውራ ዶሮው ባለቤት ኢሲያኩ ሹይቡ የቀረበውን ክስ ተከትሎ ለፍርድ ቤቱ እንዳስረዳው ዶሮውን በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር ነገ አርብ ለሚከበረው የስቅለት በዓል ለቤተሰቦቹ እንደገዛው እና ብዙ ጊዜ አለመቆየቱን ተናግሯል።

የአውራ ዶሮው ጩኽት ሰላም አሳጣን ያሉት ጎረቤቶቹም ዶሮው ለበዓሉ አርብ ዕለት የሚታረድ በመሆኑ ጥቂት ቀናት ብቻ እንዲታገሱት ጠይቋል።
https://bbc.in/3ZONkxY ተገባው የቢቢሲ አማርኛ ነው።

መጋቢት 25 ቀን 2015ዓ.ም በታች ቤት ንዑስ ወረዳ ፍ/ቤት ለባለ ጉዳዮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ሲሰጥ፡፡
03/04/2023

መጋቢት 25 ቀን 2015ዓ.ም በታች ቤት ንዑስ ወረዳ ፍ/ቤት ለባለ ጉዳዮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ሲሰጥ፡፡

የታች ቤት ንዑስ ወረዳ ፍ/ቤት በገጠር መሬቶች ላይ ለሚነሱ ክርክሮች የመሬት አስተዳደር መረጃ በአግባቡ  አጣርቶ መላክ ስለሚችሉበት ሁኔታ ላይ ለታች ቤት ንዑስ ወረዳ ቀበሌ የገጠር መሬት ባ...
01/04/2023

የታች ቤት ንዑስ ወረዳ ፍ/ቤት በገጠር መሬቶች ላይ ለሚነሱ ክርክሮች የመሬት አስተዳደር መረጃ በአግባቡ አጣርቶ መላክ ስለሚችሉበት ሁኔታ ላይ ለታች ቤት ንዑስ ወረዳ ቀበሌ የገጠር መሬት ባለሞያዎች ስልጠና መጋቢት 23ቀን 2015ዓ.ም ሰጥቷል፡፡

የመርሃቤቴ ቀጠና ፍ/ቤት እና ፍትሕ ጽ/ቤት በዛሬው እለት መጋቢት 16/2015ዓ.ም በወረሞ ዋጀቱ ንዑስ ወረዳ ፍ/ቤት አዘጋጅነት ለሁለተኛ ጊዜ በሬማ ከተማ ተካሄደ፡፡
25/03/2023

የመርሃቤቴ ቀጠና ፍ/ቤት እና ፍትሕ ጽ/ቤት በዛሬው እለት መጋቢት 16/2015ዓ.ም በወረሞ ዋጀቱ ንዑስ ወረዳ ፍ/ቤት አዘጋጅነት ለሁለተኛ ጊዜ በሬማ ከተማ ተካሄደ፡፡

18/03/2023

⚖ዜና ችሎት⚖
ሞባይል የሰረቀው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ!
# # # # # # # # # # # # # # # # # # #
ነዋሪነቱ በታች ቤት ንዑስ ወረዳ ሰባጌ ሃሮገንዳ ቀበሌ የሆነው አቡየ ጌታሁን ብ1996ዓ.ም የወጣውን የኢፌዴሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ665/1/ ተላልፎ የማይገባውን ጥቅም ለማግኘት በማሰብ መጋቢት 2 ቀን 2015ዓ.ም ከምሽቱ በግምት2፡00ሰዓት ሲሆን ፌጥራ01 ቀበሌ ልዩ ቦታው ብቅታ ከተባለው ቦታ ንብርትነቱ የአቶ ደምስ ክፍሉ የሆነውን አንድ ዳንጎቴ ሞባይል ግምቱ 1600ብር የሆነውን ከእጁ ላይ ነጥቆ በመስርቅ መጋቢት ቀን 2015ዓ.ም ከጠዋቱ በግምት 1፡00ሰዓት ላይ በፌጥራ 01 ክብር ለወ/ሮ ፀዱሴት አይፎክሩ በ800ብር /ስምንት መቶ/ ብር የሸጠ ሲሆን በፈፀመው የስርቆት ወንጀል የታ/ን/ወ/ ፖሊስ ጽ/ቤት ምርመራውን አጣርቶ ለታች ቤት ንዑስ ወረዳ ዐ/ህግ ጽ/ቤት አቅርቧል፡፡
ዐ/ህግ ጽ/ቤትም ክፖሊስ የቀርበለትን የምርመራ ውጤት እና ማስርጃዎቹን አጠናቅሮ ክሱን አቅርቧል፡፡
ፍ/ቤቱም የቀረበለትን ክስ ትብብር ለግራ ቀኙ ሲያሰማቸው ተከሳሽ ክሱን ያመነ በመሆኑ ባመነው መሰረት ጥፋተኛ ብሎታል፡፡ መጋቢት 5 ቀን2015 በዋለው ችሎት ተከሳሹ ከዚህ ቀደም የወንጅል ሪከርድ ያልቀረበበት መሆኑ፣ ወንጀሉን በማመኑ እና የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆኑን ሶስት ጠቅላላ የቅጣት ማቅለያዎችን በመያዝ ተከሳሹን ያሰተምራል ሌሎች ወንጀል ፈፃሚዎችን ያስጠነቅቃል በሚለው በ1ዓመት ከ4ወር ቀላል እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
የታ/ን/ወረዳ ህዝብ ግንኙነት ክፍል

08/03/2023
አለም አቀፍ የሴቶች ቀን በታች ቤት ንዑስ ወረዳ ፍ/ቤት በድምቀት ተከበረ🌺🌹🌺🌹🌺🌹🌺🌹🌺🌹🌺    በእለቱም በዓሉን በአለም አቀፍ ደረጃ ለማክበር ምክንያት የሆነውን ሁኔታ እና ከበዓሉ ጋር ተያ...
08/03/2023

አለም አቀፍ የሴቶች ቀን በታች ቤት ንዑስ ወረዳ ፍ/ቤት በድምቀት ተከበረ
🌺🌹🌺🌹🌺🌹🌺🌹🌺🌹🌺
በእለቱም በዓሉን በአለም አቀፍ ደረጃ ለማክበር ምክንያት የሆነውን ሁኔታ እና ከበዓሉ ጋር ተያያዝነት ያላቸውን ሃሳቦችን በማንሳት ውይይት በማድርግ የፍ/ቤቱ ዳኞች እና ሰራተኞች አክብረዋል፡፡
ስለሷ
✨✨✨✨✨✨
የሴትነት ክብር
ከእውነታው ድግስ
በሃቅ እንዲታደም
ከሴቶች ቀን በፊት
ሴትን ማክበር ይቅደም፡፡
✍️ኢዛና መስፍን

የታች ቤት ንዑስ ወረዳ ፍ/ቤት ህዝብ ግንኙነት

127ኛው የዓደዋ የድል በዓል በታች ቤት ንዑስ ወረዳ ፍ/ቤት በድምቀት ተከበር፡፡✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨በዕለቱ በዓሉን አስመልክቶ ውይይት እና ልዩ ልዩ ፕሮግራሞች ቀርበው ጀግኖች ተዘክረዋል...
02/03/2023

127ኛው የዓደዋ የድል በዓል በታች ቤት ንዑስ ወረዳ ፍ/ቤት በድምቀት ተከበር፡፡
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
በዕለቱ በዓሉን አስመልክቶ ውይይት እና ልዩ ልዩ ፕሮግራሞች ቀርበው ጀግኖች ተዘክረዋል፡፡ አሁን ላይ እንደ ሃገር ካጋጠመን የዘረኝነት ጎጠኝነት እርስበርስ መተላለቅ ችግር ለመወጣት ሃገራዊ አንድነት ለማምጣት በዓደዋ ጦርነት ጀግኖች አባቶቻችን የነበራቸውን አንድነት ፅናት በመድገም ወደ ከፍታ ማማ መውጣት ይገናል፡፡ ታሪካችንን መዘከር ይገባናል፡፡

ዓደዋ
✨✨✨

ዋ ! . . . . . . .ያቺ ዓድዋ
ዓድዋ ሩቅዋ
የዓለት ምሰሶ አድማስ ጥግዋ
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ
ዓድዋ . . . . .
ባንቺ ብቻ ህልውና
በትዝታሽ ብፅዕና
በመስዋዕት ክንድሽ ዜና
አበው ታደሙ እንደገና . . . .
ዋ !
ዓድዋ የዘር ዐፅመ ርስትዋ
የደም ትቢያ መቀነትዋ
በሞት ከባርነት ሥርየት
በደም ለነፃነት ስለት
አበው የተሰውብሽ ለት ፤
ዓድዋ
የኩሩ ትውልድ ቅርስዋ
የኢትዮጲያዊነት ምስክርዋ
ዓድዋ
የኩሩ ደም ባንቺ ጽዋ
ታድማ በመዘንበልዋ
ዐፅምሽ በትንሳኤ ነፋስ
ደምሽ በነፃነት ሕዋስ
ሲቀሰቀስ ትንሳኤዋ
ተግ ሲል ሲንር ጥሪዋ
ድው - እልም ሲል ጋሻዋ
ሲያስተጋባ ከበሮዋ
ሲያስገመግም ዳኘው መድፍዋ
ያባ መቻል ያባ ዳኘው
ያባ ነፍሶ ያባ ቃኘው
ያባ በለው በለው ሲለው
በለው - በለው - በለው - በለው !
ዋ ! . . . . ዓድዋ . . . .
ያንቺን ጽዋ ያንቺን አይጣል
ማስቻል ያለው አባ መቻል
በዳኘው ልብ በአባ መላው
በገበየሁ በአባ ጎራው
በአባ ነፍሶ በአባ ቃኘው
በለው ብሎ ፥ በለው - በለው !
ዋ ! . . . . ዓድዋ . . . .
ዓድዋ የትላንትዋ
ይኸው ባንቺ ህልውና
በትዝታሽ ብፅዕና
በመስዋዕት ክንድሽ ዝና
በነፃነት ቅርስሽ ዜና
አበው ተነሱ እንደገና ። . . . . ዋ ! . . . . .ያቺ ዓድዋ
ዓድዋ ሩቅዋ
የአለት ምሰሶ አድማስ ጥግዋ
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ
ዓድዋ . . . . . . . .

(((✍️ ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን ))
( ዓድዋ )

ዓድዋን ጥሯት ዓድዋን ጥሯት
ያቺን የድል ችቦ ለኩሳችሁ አብሯት
ደማቅ ታሪካችን ጋርደው ሳይሰውሯት
አንድነት ፍቅራችን አጥብቃችሁ ቋጥሯት
በገና በረመዳን በአርባፆም ምህላት
ሙስሊም ክርስቲያኑ ስንቶች የሞቱላት
ዓድዋ አርማ ናት በደምና ባጥት ደምቃ የተሳለች
ክብር ጀግንነቷን በአዋጅ ያሳዎቀች
ከህዝብ የራቁ ጀግኖችን ከንጉስ ጋር ያስታረቀች
ዓድዋ ሰንደቃችን ናት የአድነታችን ሚስጥር
የጥቁር ህዝብ ሀጉራት የክብር አጥር
አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ሰንደቋን
ከላይ ከፍ አድርጋ እያስመራሽ
የጥቁርን ህዝብ ጨለማ በድል
ለኩሳ ያበራሽ
በነጭ ወራሪ ጠላቷ ተገፍታ ያልተሸነፈች
ዘላለም አዊ ስሟን

✍ሃብትሽ

የታ/ን/ፍ/ቤት ህዝብ ግንኙነት

Address

Fetira
`Alem Ketema

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tachbet Woreda Court-ታችቤት ወረዳ ፍርድ ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share