17/09/2026
🌧️ በመሬ አለም ከተማ በረዶ በሽንኩርትና የተለያዩ የጓሮ አትክልት ላይ ጉዳት አደረሰ።
መስከረም 6/2019 ዓ.ም
በመሬ አለም ከተማ በመስከረም 6/2019 ዓ.ም በጣለው ዝናብ ተከትሎ የተከሰተው በረዶ በከተማዋ 03 ቀበሌ ኪዳነምህረት አካባቢ በሚገኙ የሽንኩርትና የተለያዩ የጓሮ አትክልቶች ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገለፀ።
በተለይም በአካባቢው የሚገኙ የሽንኩርት አዝመራዎች በበረዶው መጎዳታቸውና የአርሶ አደሩን የምርት ተስፋ መቀነሱ ታውቋል።
🌱 በረዶው በአዝመራው ላይ ያደረሰውን ጉዳት በመለየት በቀጣይ የሚወሰዱ የጉዳት ምርመራና የድጋፍ ርምጃዎች እንደሚኖሩ ይጠበቃል።