የሳንኩራ ወረዳ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ፅ/ቤት

የሳንኩራ ወረዳ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ፅ/ቤት የተሻሻሉ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን እና አሰራሮችን በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን መጨመር

05/12/2025
29/06/2022
 #መደበኛ ተምች African Army worm አጭር ማብራሪያ:- :- የስብስብ/አጀባ ቅርጽ (Gregarious phase) ትሎች በወረርሽኝ  በከፍተኛ ቁጥር አንድ ጋር ሆነው የሚመገቡ፣ ሰብሉ...
13/06/2022

#መደበኛ ተምች African Army worm አጭር ማብራሪያ:-

:- የስብስብ/አጀባ ቅርጽ (Gregarious phase) ትሎች በወረርሽኝ በከፍተኛ ቁጥር አንድ ጋር ሆነው የሚመገቡ፣ ሰብሉን አውድመው ምግብ ፍለጋ ወይም ወደ ኩብኩባ (ሙሽሬ) ለመለወጥ አመቺ ቦታ ፍለጋ በአንድነት የሚጓዙ የትሎች መንጋ ናቸው፡፡
የሰውነት ቀለማቸው #ጥቁር አረንጓዴ ሆኖ በግራና ቀኝ ጎኖቻቸው ላይ ነጭ ቀለም ያላቸው ሁለት መስመሮች አላቸው፡፡


የአገዳ ሰብሎች (በቆሎ፣ ማሽላ፣ ስንዴ፣ ገብስ፣ ጤፍ፣ ዳጉሳና ሩዝ) ላይ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ውድመት በማድረስ የምግብ እህል እጥረትና ረሃብ እንዲከሰት ምክንያት ይሆናል፡፡
በተጨማሪ የግጦሽ ሳርን በመብላት የመኖ እጥረትና የቤት እንሰሳት ጤና መታወክና ሞት ያስከትላል፡፡

#ባህላዊ መቆጣጠሪያ

የተባዩን ትል መጨፍጨፍ፣ በማሳ ዙሪያ ቦይ መቆፈርና የተምች ትሎች ወደ ማሳ እንዳይገቡ መከላከል

#ኬሚካላዊ መቆጣጠሪያ
_ማላታዮን 50% ኢሲ¼ በውኃ የሚበጠበጥ ፈሳሽ 1.00 ሊትር በሄ/ር
_ዲያዚኖን 60% ኢሲ¼ በውኃ የሚበጠበጥ ፈሳሽ 1.00 ሊትር በሄ/ር
_ካራቴ ፈሳሽ 1ሊትር በሄ/ር
ኢትዩፓይፎረስ ፈሳሽ 1ሊትር በሄ/ር ከላይ የተጠቀሱ ፀረ-ነፍሳት ኬሚካል በ200-400 ሊትር ውኃ በጥብጦ በአንድ ሄክታር ላይ መርጨት ።

በበልግ በለሙ ሰብሎች ላይ  #የመደበኛ ተመች መከሰቱን ፅ/ቤቱ ገለጿል።በወረዳችን በበልግ በለሙ ሰብሎች እንድሁም ሳር መሰል የእንስሳት መኖዎች ላይ የመደበኛ ተምች(African army war...
13/06/2022

በበልግ በለሙ ሰብሎች ላይ #የመደበኛ ተመች መከሰቱን ፅ/ቤቱ ገለጿል።

በወረዳችን በበልግ በለሙ ሰብሎች እንድሁም ሳር መሰል የእንስሳት መኖዎች ላይ የመደበኛ ተምች(African army warm) በተለያዩ ቀበሌዎች በወረርሽኝ መልክ የተከሰተ ሲሆን እስካሁን ባለዉ ቆሬ፣ ጀ/ሰያቶ፣ እ/ጉጣንቾ፣ ገተም፣ ጉጣንቾ ቀበሌዎች ክስተቱ የታየባቸዉ ናቸዉ ።
የዘርፉ ባለሙያወች ከቀበሌ አመራሩ በመቀናጀት በዞን ድጋፍ በገቡ ኬሚካሎች የርጭት ስራዉ ተጠናክሮ ቀጥሏል። ሆኖም ሌሎች ቀበሌወችም ላይ ክስተቱ ስለሚኖር ኮሚቴ በማዋቀር ከአጋዥ ሀይሎች ጋር ርብርብ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ አሰሳ በማድረግና የተከሰተበት ላይ ሳይስፋፋ ፈጥነን መከላከል ካልቻልን ጉዳቱ የከፋ ይሆናል።

 #የ2014 በልግ ልማት የዘነበዉን ርጥበት በመጠቀም ልማቱን ፈጥኖ የማጠናቀቅ ስር በስፋት እየተከናወነ መሆኑ ተገለፀ ። #የም/ዘመኑ የበልግ ልማት ስራችን በበጋ መራዘምና ዝናብ መቆራረጥ ም...
04/06/2022

#የ2014 በልግ ልማት የዘነበዉን ርጥበት በመጠቀም ልማቱን ፈጥኖ የማጠናቀቅ ስር በስፋት እየተከናወነ መሆኑ ተገለፀ ።

#የም/ዘመኑ የበልግ ልማት ስራችን በበጋ መራዘምና ዝናብ መቆራረጥ ምክነያት ፋርም ካላንደሩን ጠብቆ እንዳይለማ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሰደረበትና የአ/አደሩ ዘር በማጎተት ዝናብ ዘግይቶ መግባትና ከለማም በኋላ ፈጥኖ የመዉጣት ችግር በምርትና ምርታማነት ላይ የሚያደርሰዉ ተፅዕኖ የጎላ ነዉ።

በመሆኑም የዘነበዉን ዝናብ በመጠቀም ርጥበትን ተከትሎ ፈጥኖ ዘር የመሸፈን ስራ አስፈላጊ ሲሆን ዝናብ በዘነበባቸዉ ቀበሌወች አ/አደሩ በክላስተር በስፋት በዘር ማሳዉን እሸፈነ የሚገኝ ሲሆን የተሻሻሉና ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድጉ ቴክኖሎጅወች ላይ ትኩረት በማድረግ ቴክኒካል ፓርቱ ላይ የድጋፍና ክትትል ስራወች ተጠናክሮ ይቀጥላል። በገተምና ረግድና ክሳስተር የዘር ሽፋን እንቅስቃሴ በከፊል ገፅታ...

 #ጥንቃቄና ቅንጅታዊ አሰሳ ይደረግ !
03/06/2022

#ጥንቃቄና ቅንጅታዊ አሰሳ ይደረግ !

23/05/2022

*** #ግብርና ከማምረትም በላይ ነዉ !!

👉 ግብርና ምግብ ነዉ !!
👉 ግብርና ቤት ነዉ !! መጠለያ ነዉ!!
👉 ግብርና ልብስ ነዉ !!
👉 ግብርና ጤና ነዉ !!
👉 ግብርና ስራ ዕድል ነዉ !!
👉 ግብርና ደን ነዉ !! ደን የዉሀ ምንጭ ነዉ !!
👉 ግብርና ዝናብ ነዉ !!
👉 ግብርና ወተት ነዉ !!
👉 ግብርና ማር ነዉ!!
👉 ግብርና ትምህርት ነዉ!! ምክንያቱም መቀንጨር የትምህርት ፀር ስለሆነ ነዉ!!
👉 ግብርና ቱሪዝም ነዉ!! አረንጓዴ አካባቢ የቱሪዝም ራስ ነዉና !!
👉 ግብርና በአፈር፣ በዉሀ፣ በእፅዋት እና በእንስሳት ላይ መሰልጠን ማለት ነዉ !!
***ግብርና ከማምረትም በላይ ነዉ!!

Address

`Alem Gebeya

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የሳንኩራ ወረዳ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ፅ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share