29/08/2026
በኑዌር ብሔረሰብ ዞን የጅካዎ ወረዳ ም/ቤት 3ኛ ምርጫ ጊዜ 14ኛ የሥራ ዘመን 25ኛ መደበኛ ጉባኤውን አጠናቋል።
በጂካዎ ወረዳ ባለፉት 12 ወራት የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ለማረጋገጥ አመራሩ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚጠበቅበት የጂካዎ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኮንግ ቱት ገለጹ።
የወረደ ዋና አስተዳዳሪ የአስፈጻሚ አካላትን የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የ12ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለጉባኤ አባላቱ አቅርበዉ በጉባኤ አባላት ዉይይት ተደርጓል።
ባለፉት 12ወራት በማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ዙሪያ አበረታች ዉጤቶች መሰራታቸዉን የጉባኤ አባላት ገልጸዋል።
ተጀምረው እስካሁን ያልተጠናቀቁ የመንገድና የመብራት መሰረተ ልማት አገልግሎት ችግር የተለያዩ ስራዎችን በተቀላጠፈ መንገድ ለማከናወን አስቸጋሪ መሆኑን አንስተዋል።
በትምህርት፣በግብርና በጤና ዘርፉ ላይም የግብዓት ችግሮች መኖራቸዉን ጠቁመዋል።
የጂካዎ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኮንግ ቱት ጂንግ ከጉባኤ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ የተቋረጡ መሰረተ ልማቶችን ለሟሟላት ከክልሉ መንግስት ጋር ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ ተናግረዋል።
በግብርናዉ ዘርፍ የጂካዎ ወረዳ ህዝብ ከተረጅነት ለማላቀቅ በዉሃ ሸሽ፣በመስኖ በመኸር እርሻ ኋላ ቀር አሰራርን በማዘመን በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል።
የጉባኤውን የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት የጂካዎ ወረዳ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ኩዮች ኛክ በቋሚ ኮሚቴዎች አማካኝነት የሚደረገው የክትትልና ቁጥጥር ስራ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።
ምክር ቤቱ ያከናወናቸው የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራት በማጎልበት ሊሻሻሉ የሚገባቸውም በማስተካከል የራሱን ድርሻ እንደሚወጣም አስረድተዋል።
አርሶ አደሩ የምግብ ዋስትናውን እንዲያረጋግጥ የእርሻ ስራውን በማዘመን ውጤታማ እንዲሆን በዘርፉ የተሰማሩ አመራሮችና ባለሙያዎች ጥረት ማድረግ እንደሚጠበቅባቸውም አፈ ጉባኤዋ አሳስበዋል።
በጂካዎ ያለውን እምቅ የተፈጥሮ ፀጋ በመጠቀምና ሀብቱን ወደ ልማት በመቀየር የህዝቡን የኑሮ ደረጃ ማሻሻል እንደሚገባም ገልፀዋል።