Fitsum Arega

Fitsum Arega DG Eth. Diaspora Service, FMR Amb. of to US & Canada. Inst: fitsum.aregaa X:
(343)

የኢትዮዽያ ህዝብ በሌሊት ወጥቶ ከምርጫ ውጪ አገርን ሊመራ የሚችል ተወካይ መሰየም አይቻልም በሚል ጽኑ እምነት ድምጹን በሰላማዊ መንገድ በመስጠት ላይ ይገኛል። እኔም በ5 ዓመት አንዴ በሚመጣ...
06/01/2026

የኢትዮዽያ ህዝብ በሌሊት ወጥቶ ከምርጫ ውጪ አገርን ሊመራ የሚችል ተወካይ መሰየም አይቻልም በሚል ጽኑ እምነት ድምጹን በሰላማዊ መንገድ በመስጠት ላይ ይገኛል። እኔም በ5 ዓመት አንዴ በሚመጣ በዚህ ታላቅ ታሪካዊ ዕድል ላይ ለመሳተፍ በመቻሌ ታላቅ ደስታ ተሰምቶኛል። በህይወት ኖሮ፣ በዲሞክራሲያዊ ምርጫ ድምጽ በመስጠት የኢትዮዽያን መዳረሻ በጋራ ማቃናት እንዴት መታደል ነው!

Today, June 1st, Ethiopians are voting peacefully since morning, exercising our democratic right to choose representatives and form a government. I’m truly excited to participate in this historic national moment, a chance that comes only once every 5 years. Being alive and able to contribute to ‘s future is a great honor!
Let’s shape our destiny together.

05/26/2026

በአገር ቤት እና በዳያስፖራ ለምትገኙ የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቼ፣ እንኳን ለዒድ አል አድሐ (ለዐረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ። በዓሉ የጤና እና እርስ በርስ የመረዳጃ እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ። Eid Mubarak!

ዛሬ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በሌሊት ተመው ወደ መስቀል አደባባይ በመውጣት ዲሞክራሲን ለማጽናት፣ ብልጽግናን ለማስቀጠል ድምጻቸውን በአንድነት አሰምተዋል። ዛሬ በአደባባይ ድምጽዎን በጋራ እንዳ...
05/26/2026

ዛሬ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በሌሊት ተመው ወደ መስቀል አደባባይ በመውጣት ዲሞክራሲን ለማጽናት፣ ብልጽግናን ለማስቀጠል ድምጻቸውን በአንድነት አሰምተዋል።

ዛሬ በአደባባይ ድምጽዎን በጋራ እንዳሰሙት በመጪው ሰኞ፣ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. በተመዘገቡበት የምርጫ ጣቢያ፣ የተመዘገቡበትን የምርጫ ካርድ ይዘው ድምጽዎን በመስጠት ስልጣን በምርጫ ብቻ እንደሚገኝ ያስረግጡ፣ ዲሞክራሲን ያጎልብቱ፣ ብልጽግናን ያስቀጥሉ።

ብልጽግና ለኢትዮዽያ፣ ብልጽግና ለመላ ህዝቧ!

Today, the people of have spoken with one powerful voice!

At this final Prosperity Party rally before the June 1st General Election, they have decided loud and clear, it is Prosperity Party that is leading forward!

Lighting the way, paving the path, walking with the people, delivering real progress including a clean and beautiful city, and igniting real hope for a brighter, prosperous future! Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ

Prosperity to Ethiopia and its people!

63 years ago our forefathers gathered in   and dreamed of a free, united Africa, the dream is still alive. From North Af...
05/25/2026

63 years ago our forefathers gathered in and dreamed of a free, united Africa, the dream is still alive. From North Africa to the South, from East Africa to the West, we celebrate our rich heritage, resilience, and unbreakable spirit. Today we honor our past, embrace our diversity, and commit to a bright future. Together we rise, together we thrive. The world is watching, let’s show them what can do! African Union

! May 25,2026!

በዳያስፖራ ዘርፍ የ10 ወር አፈጻጸም አስመልክቶ ከመላው አምባሳደሮች፣ የዳያስፖራ እና የፋይናንስ ዘርፍ ዲፕሎማቶች ጋር ውጤታማ የቨርቹዋል ውይይት አድርገናል። በረሚታንስ፣ በዳያስፖራ ቱሪዝም...
05/21/2026

በዳያስፖራ ዘርፍ የ10 ወር አፈጻጸም አስመልክቶ ከመላው አምባሳደሮች፣ የዳያስፖራ እና የፋይናንስ ዘርፍ ዲፕሎማቶች ጋር ውጤታማ የቨርቹዋል ውይይት አድርገናል።

በረሚታንስ፣ በዳያስፖራ ቱሪዝም፣ በኢንቨስትመንት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በበጎ አድራጎትና በምክክር እንዲሁም በህዳሴ ግድብ የገንዘብ ድጋፍ ዙሪያ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።

እስከ ሰኔ 30/2018 ከዳያስፖራው በቦንድ ሽያጭና በስጦታ 3 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ፣ የዓመቱን እቅድ በ10 ወር ማሳካት ተችሏል። በዚህ በጎ ተግባር ለተሳተፋችሁ ለሚሲዮን መሪዎች፣ ለዲፕሎማቶች እና ለዳያሰፖራዎች የከበረ ምስጋናችን ይድረሳችሁ።

እቅዳቸውን ያላሳኩ ሚሲዮኖች በቀሪ 2 ወራት አካክሰው እንዲሰሩ መግባባት ላይ ደርሰናል።

የኢትዮዽያ ንግድ ባንክ ከፍተኛ የስራ ኃላፊም በመድረኩ ላይ ተገኝተው ባንኩ ለዳያስፖራው ባለው አገልግሎት ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በኢትዮዽያ 10 ቀን ብቻ የቀረው የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በአገር ቤት መላ ህዝቡ ተግቶ እየሰራ መሆኑን፣ ስለሆነም ዳያስፖራው ካለበት ሆኖ ወገኑን ለመደገፍ በማህበራዊ ሚዲያ አዎንታዊ ሚና እንዲጫወት ጥሪ ቀርቧል።

Very pleased today visiting the Ethiopian Statistical Service’s exhibition at the Addis Ababa Convention Center. Thank y...
05/20/2026

Very pleased today visiting the Ethiopian Statistical Service’s exhibition at the Addis Ababa Convention Center.

Thank you to Dr. Beker Shale (DG), Dr. Meron Kifelew (DDG), and the entire team for the excellent exhibition and for driving this impressive transformation.

From Manual process to a fully digitized, real-time system, powered by CAPI, GIS, remote sensing, cloud storage and tracking platforms and AI-powered survey dashboard with highly professional staff. This is real progress!

PM Abiy Ahmed Ali is right: Ethiopia is advancing fast toward data & statistical sovereignty. Data is a key pillar of national sovereignty & policy independence. We are now proudly collecting and analyzing our own data. Well done !

በደቡብ ኦሞ ዞን፣ በበና ጸማይ ወረዳ፣ ቦሪ ቀበሌ 50 ሚሊዮን ብር በሚጠጋ ወጪ ከ11,500 በላይ ለሆኑ ነዋሪዎች የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ሲመረቅ በመታደሜ ደስታ ተሰምቶኛል። ፕሮጄክቱ ...
05/17/2026

በደቡብ ኦሞ ዞን፣ በበና ጸማይ ወረዳ፣ ቦሪ ቀበሌ 50 ሚሊዮን ብር በሚጠጋ ወጪ ከ11,500 በላይ ለሆኑ ነዋሪዎች የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ሲመረቅ በመታደሜ ደስታ ተሰምቶኛል።

ፕሮጄክቱ 150 ሜትር ጥልቅ ጉድጓድ፣ 20 ኪሎ ሜትር የቧንቧ ዝርጋታ፣ 100 ሜ.ኪ የውሃ ማጠራቀሚያ፣ 22 ኪ.ዋ. የጸሃይ ኃይል፣ 9 የውሃ ቦኖዎች፣ 6 የእንሰሳት ማጠጫ ገንዳዎች እና መጸዳጃ ቤቶች ያጠቃልላል።

ይህንን ፕሮጄክት በገንዘብ ለደገፉ አሜሪካን አገር ለሚገኙ የ‘CRS’ የግል ለጋሾችን እንዲሁም በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን የሶዶ/ጂንካ ሀገረ ስብከት ፕሮጀክቱ በፍጥነት እና በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲጠናቀቅ ላደረጉት ድጋፍ የከበረ ምስጋናችን ይድረሳቸው።

የአካባቢው አስተዳደርም ከመንግስት የሚፈለገውን ድጋፍ በማድረግና ህብረተሰቡን በማስተባበር 2 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ነጻ የጉልበት ዋጋ አንዲያበረክቱ በማድረግ የፕሮጄክቱ ባለቤትና ጠባቂ እንዲሆኑ አድርጓል።

ህብረተሰቡም ለመጀመሪያ ግዜ ንጹህ የመጠጥ ውሃ በማግኘቱ፣ እናቶችና ወጣት ሴቶች ግዜና ጉልበት መቆጠብ በመቻላቸው፣ በአጠቃላይ ጤናቸውን በመጠበቅ ትምህርታቸውን በተሻለ መከታተል ስለሚያስችላቸው፣ በድርቅ ወቅትም ውሃ ፍለጋ መንከራተት ስለቀረላቸው፣ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል።

የመንግስት፣ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና የማህበረሰብ የተቀናጀ ትብብር እንዲህ ለተሻለ ውጤት ያበቃል። ይበል የሚያሰኝ ነው። የበና ብሔረሰብም በአስደናቂ የባህላዊ ጭፈራው ላደረገልን አቀባበል ምስጋናችን የበዛ ነው።

Pleased to join the inauguration of the Bori Clean Water Project in Bori Kebele, Bena-Tsemay Woreda, South Omo Zone, South Region, implemented at a total cost of nearly 50 million ETB.

Our sincere appreciation goes to (Catholic Relief Service) and its private donors based in the U.S. for funding this impactful initiative, as well as to CCE (catholic Caritas Ethiopia) teams from S**o and Jinka for supporting its implementation in close collaboration with the local administration and community.

We also appreciated the warm welcome and beautify traditional dance by the Benna Community.

This transformative initiative now provides safe, reliable, and climate-resilient water access to more than 11, 500 people and over 90,000 livestock across five villages that for years faced severe water shortages.

Women and girls previously travelled 7-14 km daily in search of water, while communities depended on unsafe and seasonal sources.

The project includes 150m deep borehole, solar-powered pumping and energy system, a 100 mc reservoir, 20 km of pipeline installation, 9 water distribution points, cattle troughs, and community WASH and hygiene training.

Beyond water access, the project will improve health, education, livelihood, and community resilience while reducing conflict and easing the burden on women and girls.

Access to safe water is more than a basic necessity; it is dignity, opportunity and hope for a better future. 🇪🇹

05/16/2026

Congratulations! Gelan Gura Industrial Park (in ) is now open on 43 hectares! This major milestone creates a great investment for SMEs, delivers thousands of New jobs for youth, & boasts ‘s industrialization. Investing in SMEs means more jobs, resilience & shared prosperity!

Ethiopia warmly welcomes President Emmanuel Macron! We are proud of the excellent relations between   &  , spanning more...
05/13/2026

Ethiopia warmly welcomes President Emmanuel Macron!

We are proud of the excellent relations between & , spanning more than 125 years.

Our strong partnership continues to grow in key areas including cultural & heritage restoration (Lalibela & National Palace), economic development, trade, security cooperation, education - the historic Lycee Guebre Maria (over 80 years), and political dialogue on issues in the Horn & the

France is a strategic partner, and we look forward to deepening ties even further. Thank you, Mr. President for your friendship and continued support! Abiy Ahmed Ali

በኬንያ ናይሮቢ በመካሄድ ላይ ባለው መድረክ ላይ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር Abiy Ahmed Ali  የሚከተለውን አጋርተዋል:- “የአረንጓዴ ኢንዱስትሪ ልማት እና የኃይል ሽግግርን በተመለ...
05/12/2026

በኬንያ ናይሮቢ በመካሄድ ላይ ባለው መድረክ ላይ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር Abiy Ahmed Ali የሚከተለውን አጋርተዋል:-

“የአረንጓዴ ኢንዱስትሪ ልማት እና የኃይል ሽግግርን በተመለከተው ውይይት መድረክ ላይ ከተሞክሯችን የተቀዱ ከፍ ያሉ ሀሳቦች ተነስተዋል። ኢትዮጵያ በተነሱት ሁለት ዘርፎች የጀመረችውን ስራ በማጠናከር የላቀ ሚና መጫወቷን ትቀጥላለች።” …

Address

575 Island Park Crescent
Ottawa, ON
K1Y3P2

Opening Hours

Monday 9am - 5pm
Tuesday 9am - 5pm
Wednesday 9am - 5pm
Thursday 9am - 5pm
Friday 9am - 5pm

Telephone

+12023641200

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Fitsum Arega posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share