Ethiopian Embassy - UAE / AbuDhabi

Ethiopian Embassy - UAE / AbuDhabi Embassy of the Federal Democratic Republic of Ethiopia in Abu Dhabi.
(1)

08/09/2026

ክቡር የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ በ15ኛው የዱባይ ዓመታዊ የኢንቨስትመንት ጉባኤ ያስተላለፋት መልዕክት

ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ክፍት እና ዝግጁ ናት- ክቡር የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ———ክቡር የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ በዓመታዊ የዱባይ ዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ጉባኤ ...
07/09/2026

ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ክፍት እና ዝግጁ ናት- ክቡር የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ
———
ክቡር የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ በዓመታዊ የዱባይ ዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ጉባኤ የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል።

ፕሬዝዳንቱ አገሪቱ በአገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ለዓለም አቀፍ ኢንቨስተሮች ምቹ የሆኑ በርካታ አማራጮችን እያዘጋጀች መሆኑን በመጠቆም በተለይም በኢኮኖሚው ውስጥ ትኩረት የተሰጣቸውን አምስት ዋና ዋና የኢንቨስትመንት ዘርፎችን ለይተው አብራርተዋል።

የመጀመሪያው የታዳሽ ኃይል ዘርፍ ሲሆን ኢትዮጵያ በዚህ ረገድ ከፍተኛ አቅም እንዳላት የጠቆሙት ክቡር ፕሬዝዳንቱ በንፋስ፣ በፀሐይ፣ በጂኦተርማል እና በውሃ ኃይል ማመንጨት ላይ መሰማራት ለሚፈልጉ አልሚዎች በሀገሪቱ ምቹ ሁኔታዎች እና ሰፊ አማራጮች መኖራቸውን ገልጸዋል።

በሁለተኛነት የግብርና እና አግሮ-ፕሮሰሲንግ ዘርፍን ያነሱ ሲሆን ኢትዮጵያ የበጋ መስኖን እና ሌሎች ቴክኒኮችን በመጠቀም ከስንዴ አስመጪነት ወደ ላኪነት መሸጋገሯን ገልጸዋል። ሀገሪቱ በአፍሪካ ትልቋ የስንዴ አምራች ለመሆን የበቃችበትን ስኬት እንደ አቮካዶ፣ ሰሊጥ እና ሌሎች የሰብል ዓይነቶች ባሉ የግብርና ምርቶች ላይ ለመድገም ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገች እንደሚገኝ ገልጸዋል። በመሆኑም ኢንቨስተሮች በዚህ ዘርፍ እሴት በሚጨምሩ ስራዎች ላይ እንዲሰማሩ ጥሪ አቅርበዋል።

በትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ክቡር ፕሬዝዳንቱ መንግስት በ12.5 ቢሊዮን ዶላር ወጪ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቢሾፍቱ አቪዬሽን ከተማ ግንባታን እያከናወነ እንደሚገኝ አንስተዋል። ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት አፍሪካን ከተቀረው ዓለም ጋር የበለጠ የሚያስተሳስር ከመሆኑም በላይ ሀገሪቱን የአፍሪካ የሎጂስቲክስ ማዕከል ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት የሚያፋጥን መሆኑን ጠቁመዋል።

በማዕድን ዘርፍ ኢትዮጵያ በወርቅ ምርት ብቻ ሳይሆን ለዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ እና ኢንዱስትሪ ዕድገት ወሳኝ የሆኑ በርካታ Critical Minerals ባለቤት መሆኗን ገልጸዋል። በዘርፉ ሰፊ ያልተነካ አቅም በመኖሩ ኢንቨስተሮች ይህንን እድል እንዲጠቀሙበት ጋብዘዋል።

በመጨረሻም የሰው ኃይል አቅምን በተመለከተ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ቁጥር ያለው አምራች የወጣት ህብረተሰብ ባለቤት መሆኗን አንስተው ይህንን አቅም በመጠቀም ከመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ጋር በሰው ኃይል ልማት፣ በክህሎት ሽግግር እና በጋራ ልማት ዙሪያ ያለውን ትስስር አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ክቡር ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ በመክፈቻ ከዋናው መርሃ ግብር ጎን ለጎን ከዓለም አቀፍ ተቋማት እና የሀገራት ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር የሁለትዮሽ ውይይቶችን በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

የዱባይ ዓመታዊ የኢንቨስትመንት ጉባኤ እስከ ሴፕቴምበር 9 ቀን 2026 የሚቀጥል ይሆናል።

ክቡር ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በዓለም ኢንቨስትመንት ጉባኤ ላይ ለመታደም ዱባይ ገቡ--------በክቡር የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን AIM በተሰኘ...
06/09/2026

ክቡር ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በዓለም ኢንቨስትመንት ጉባኤ ላይ ለመታደም ዱባይ ገቡ
--------
በክቡር የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን AIM በተሰኘውና በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች አዘጋጅነት በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ጉባኤ ለመሳተፍ ዛሬ ዱባይ ገብቷል።

ክቡር ፕሬዝዳንቱ ዱባይ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የንግድ ሚኒስትር ዶ/ር ታኒ አል ዘዩዲ ደማቅ አቀባበል አድርገዉላቸዋል። በአቀባበሉ ላይ የአቡዳቢ እና ዱባይ የኢፌዲሪ ሚሲዮን አመራሮች እና ዲፕሎማቶችም ታድመዋል።

እ.ኤ.አ ከሴፕቴምበር 7-9 በሚካሄደው ጉባኤ ላይ ክቡር ፕሬዝዳንቱ መልዕክት የሚያስተላልፋ ሲሆን ከተለያዩ አገራት መሪዎችና የቢዝነስ አመራሮች ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በጉባኤ ላይ በርካታ የአገር መሪዎችና የመንግሥታት ልዑካን፣ የቢዝነስ መሪዎች እንዲሁም የዓለም አቀፍና ቀጠናዊ ድርጅቶች አመራሮች ይታደማሉ።

አስቸኳይ ማሳሰቢያ!ትክክለኛውን የኢ-ፓስፖርት ማመልከቻ ፖርታል በማስመሰል የሐሰት URL (ድህረ-ገጽ) እየተሰራጨ መሆኑ ተደርሶበታል። ይህ ፌክ ድረ-ገጽ የኤምባሲዎችን ትክክለኛ ገጾች በቅርበ...
05/09/2026

አስቸኳይ ማሳሰቢያ!

ትክክለኛውን የኢ-ፓስፖርት ማመልከቻ ፖርታል በማስመሰል የሐሰት URL (ድህረ-ገጽ) እየተሰራጨ መሆኑ ተደርሶበታል። ይህ ፌክ ድረ-ገጽ የኤምባሲዎችን ትክክለኛ ገጾች በቅርበት በማስመሰል የተሰራ በመሆኑ፣ አመልካቾችን ለፋይናንስ ብዝበዛና ለእንግልት እያጋለጠ ይገኛል።

ለኢ-ፓስፖርት ማመልከቻ ብቸኛውና ትክክለኛው ይፋዊ ፖርታል የሚከተለው ብቻ ነው፦

https://immigration.gov.et

እባካችሁ ይህንን መረጃ ለአመልካቾችና ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ በማጋራት የድርሻዎን ይወጡ።

ማስታወቂያ!በ “Young Future Energy Leaders” ሥልጠና ፕሮግራም ዕድል መሳተፍ ለምትፈልጉ በሙሉበተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች ታዋቂ የሆነው የካሊፋ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ...
26/08/2026

ማስታወቂያ!

በ “Young Future Energy Leaders” ሥልጠና ፕሮግራም ዕድል መሳተፍ ለምትፈልጉ በሙሉ

በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች ታዋቂ የሆነው የካሊፋ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በታዳሽ ኃይል፣ በአካባቢ ጥበቃ እና በዘላቂ ልማት ዘርፍ ላይ ትኩረት የሚያደርገውን የ2027 Young Future Energy Leaders የአንድ ዓመት ሥልጠና ፕሮግራም አዘጋጅቷል። ዩኒቨርሲቲ በዚህ ፕሮግራም ላይ የሚሳተፉ ኢትዮጵያውያንን በመመልመል ሂደት ድጋፍ እንድናደርግ ጥያቄ አቅርቦልናል፡፡

የፕሮግራሙ ዋና ዋና ጥቅሞች
• የአንድ ዓመት ሙሉ ሥልጠና፦ የምርምር ፕሮጀክቶች፣ የአመራርነት ሥልጠናዎች እና ከዘርፉ ባለሙያዎች ጋር የሚደረጉ የልምድ ልውውጦች።
• ልዩ የሥራ ዕድል፦ ከጥር 12 እስከ 14 ቀን 2027 (እ.ኤ.አ) በአቡዳቢ በሚካሄደው World Future Energy Summit (WFES) ላይ በመገኘት ከዓለም አቀፍ መሪዎች ጋር የመገናኘት ዕድል።
• ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች፦ የታዳሽ ኃይል፣ የውኃ ደህንነት፣ የቆሻሻ አወጋገድ፣ ዘላቂ ከተሞች እና የአካባቢ አየር ለውጥ እርምጃዎች።

የአመልካቾች መስፈርት
• ዕድሜ፦ ከ20 እስከ 25 ዓመት
• የትምህርት ውጤት (GPA)፦ 3.50 እና ከዚያ በላይ
• የትምህርት ደረጃ፦ የመጀመሪያ ዲግሪ/ማስተርስ በመከታተል ላይ ያለ፣ በቅርቡ የተመረቀ ወይም በዘርፉ የመጀመሪያ ደረጃ የሥራ ልምድ ያለው
• ሌሎች፦ በታዳሽ ኃይል እና ዘላቂ ልማት ላይ ከፍተኛ ፍላጎት ያለው እና እንግሊዝኛ ቋንቋ መናገር/መፃፍ የሚችል።

የማመልከቻ ሂደት

ሙሉ መረጃችሁን ማለትም (ሙሉ ስም፣ የትምህርት ማስረጃ እና ሰርቴፊኬቶች ካሉ፣ ስልክ ቁጥር) ከዛሬ ጀምሮ እስከ ኦገስት 29 ቀን 2026 ድረስ በኤምባሲው ኦፊሴላዊ ኢሜይል አድራሻ [email protected] ይላኩ።

ማስታወሻ፦ ኤምባሲው በተቀመጠው መስፈርት መሰረት ብቁ የሆነ ዕጩዎችን ዝርዝር ለዩኒቨርሲቲው የሚያስተላልፍ ሲሆን የመጨረሻ ተሳታፊዎችን የሚመረጥው ዩኒቨርሲቲው እንደሆነ ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡

የጋብቻ ማስታወቂያ
24/08/2026

የጋብቻ ማስታወቂያ

ማስታወቂያ!
19/08/2026

ማስታወቂያ!

AUCTION NOTICE
18/08/2026

AUCTION NOTICE

ማስታወቂያ
16/08/2026

ማስታወቂያ

Address

Villa19 Ahl Alma'rifa St/Al Nahyan/Abu Dhabi
Abu Dhabi

Opening Hours

Monday 08:30 - 15:30
Tuesday 08:30 - 15:30
Wednesday 08:30 - 15:30
Thursday 08:30 - 15:30
Friday 08:30 - 12:30

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Embassy - UAE / AbuDhabi posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Ethiopian Embassy - UAE / AbuDhabi:

Share