Dessie City Sport Mekrbet

Dessie City Sport Mekrbet ጠንክረን በመስራት ምርጥ ስፖርተኞች በማፍራት ስፖርት በማህበራዊ እና በኢኮኖሚው ዘርፍ የላቀ አስተዋጽኦ እድያበረክት እንሰራለን።

31/05/2026
የምስራቅ አፍሪካ ካራቴ ሻምፒዮና ውድድር ከግንቦት 22 -26/2018 ዓ.ም በኬንያ ናይሮቢ የሚካሄድ ይሆናል። በዚህ ውድድር የሚሳተፈው የኢትዮጲያ ቡድን ዛሬ ማታ አመሻሽ ላይ ወደ ስፍራው አ...
28/05/2026

የምስራቅ አፍሪካ ካራቴ ሻምፒዮና ውድድር ከግንቦት 22 -26/2018 ዓ.ም በኬንያ ናይሮቢ የሚካሄድ ይሆናል። በዚህ ውድድር የሚሳተፈው የኢትዮጲያ ቡድን ዛሬ ማታ አመሻሽ ላይ ወደ ስፍራው አቅንቷል። ለልዑኩ መልካም እድል እንመኛለን።ስፖርተኞችን እንድሳተፉ ያገዛችሁ የደሴ ከተማ ባለሃብቶች ከልብ እናመሰግናለን።

ርእሰ መሥተዳድር የተከበሩ አቶ  አረጋ ከበደ በደሴ ከተማ የተሠሩ የልማት ሥራዎችን መርቀው ሥራ አስጀመሩ። ደሴ: ግንቦት 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ርእሰ መሥተዳድሩ የደሴ ከተማን ገጽታ የ...
26/05/2026

ርእሰ መሥተዳድር የተከበሩ አቶ አረጋ ከበደ በደሴ ከተማ የተሠሩ የልማት ሥራዎችን መርቀው ሥራ አስጀመሩ።

ደሴ: ግንቦት 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ርእሰ መሥተዳድሩ የደሴ ከተማን ገጽታ የቀየሩ የኮሪደር ልማት፣ የአስፓልት መንገድ ሥራዎችን እና ሌሎች የልማት ሥራዎችን ነው መርቀው ሥራ ያስጀመሩ። በኮሪደር ልማቱ ሚኒ የእግርኳስ ሜዳ አብሮ ተመርቋል።

የልማት ሥራዎችም የደሴ ከተማ ዕድገትን ወደ ተሻለ ደረጃ የሚያሸጋግ፣ ለነዋሪዎችም ምቾትን የሚሰጡ መኾናቸው ተገልጿል።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ከርእሰ መሥተዳድሩ በተጨማሪ የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን ( ዶ.ር)፣ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ ዘሪሁን ፍቅሩ (ዶ.ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

በደሴ ከተማ "ስፖርት ለሁሉም-ሁሉም ለሰላም" በሚል መሪ ቃል በ5ቱም ክፍለከተማ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሂዷል። የፌስቲቫሉ ዋና አለማ ሁሉንም ማህበረሰብ በአካል ብቃት እንቅስቃሴ በመሳተ...
24/05/2026

በደሴ ከተማ "ስፖርት ለሁሉም-ሁሉም ለሰላም" በሚል መሪ ቃል በ5ቱም ክፍለከተማ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሂዷል። የፌስቲቫሉ ዋና አለማ ሁሉንም ማህበረሰብ በአካል ብቃት እንቅስቃሴ በመሳተፍ ጤንነቱን እንድጠብቅ እና አንድነቱን እንድያጠናክር ማስቻል ነው።

"የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የሁሉም ስፖርት ዘርፎች መሰረት ነው" ዛሬ ግንቦት 11/2018 ዓ.ም በደሴ  ከተማ መምሪያችን ከአማራ ክልል ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር የ1ኛ ደ...
19/05/2026

"የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የሁሉም ስፖርት ዘርፎች መሰረት ነው"

ዛሬ ግንቦት 11/2018 ዓ.ም በደሴ ከተማ መምሪያችን ከአማራ ክልል ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር የ1ኛ ደረጃ የአካል ብቃት የአሰልጣኞች ስልጠና ማሰጠት ጀምረናል።
በስልጠናው ከደሴ ከተማና አካባቢው የተውጣጡ ከ70 በላይ ሰልጣኞች እየተሳተፉ የሚገኙ ይገኛሉ።

ስልጠናው በሁሉም የስፖርት ዘርፍ ያሉ ባለውያዎችን እንደየዘርፉና እንደየማህበረሰቡ ፍላጎትና አላማ እንዴት ሳይንሳዊ የሆነ የአካል ብቃት ስልጠና እንድሚሰጡ አቅም እንዲፈጥሩ ያስችላል። በሂደቱም የአካል ብቃት እንቅስቃሴን በማስፋፋት የማህበረሰቡን ጤና ለማስጠበቅ ብሎም ኢሌት ስፖርተኞችን ለማፍራት ያግዛል።

በከተማችን በአካል ብቃት እንቅስቃሴ የሚሳተፉ የማህበረሰብ ክፍል ቁጥር እየጨመረ የመጣ በመሆኑ ይህንን ፍላጎት ሊሸከም የሚችል በዘርፉ ብቁና ተወዳዳሪ የሆኑ አሰልጣኞችን ለማብቃ ታስቦ የተዘጋጀ ስልጠና ነው።

የስለልጠናው መርሃግብር የንድፈ ሃሳብና የተግባር ትምህርት አካቶ በቀን ሁለት ጊዜ ለተከታታይ አስር ቀናት የሚቆይ ይሆናል።

በደሴ ከተማ ሲሰጥ የነበረው የካራቴ ስፖርት የ3ኛ ደረጃ የአሰልጣኝነት እና የዳኝነት ስልጠና ተጠናቀቀ። በደሴ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ከአማራ ክልል ካራቴ ፌዴሬሽን...
18/05/2026

በደሴ ከተማ ሲሰጥ የነበረው የካራቴ ስፖርት የ3ኛ ደረጃ የአሰልጣኝነት እና የዳኝነት ስልጠና ተጠናቀቀ።

በደሴ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ከአማራ ክልል ካራቴ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የ3ኛ ደረጃ የአሰልጣኝነት እና የዳኝነት ስልጠና የተጠናቀቀ ሲሆን ከ50 በላይ ሰልጣኞች ተሳትፈው ስልጠናው በብቃት ያጠናቀቁ ሰልጣኞች ከክልሉ የተዘጋጀላቸውን የምስክር ወረቀት ተቀብለዋል። ስልጠናው በዘርፉ የአሰለጣጠን ዘደውን ሳይንሳይ ስልጠና ለመስጠትና በስፖርቱ የነበረውን የዳኝነት ችግሩን ለመቅረፍ በትልቁ ያግዛል።

በደሴ ከተማ አስተዳደር  ሲካሄድ የቆየው የትምህርት ቤት የተማሪዎች ስፖርት ውድድር ተጠናቀቀ ።ባለፉት ሶስት ወራቶች ከክፍል ለክፍል ጀምሮ፣ በጉድኝትና በክላስተር ተካሂዶ በየካላስተሩ አሸናፊ...
17/05/2026

በደሴ ከተማ አስተዳደር ሲካሄድ የቆየው የትምህርት ቤት የተማሪዎች ስፖርት ውድድር ተጠናቀቀ ።
ባለፉት ሶስት ወራቶች ከክፍል ለክፍል ጀምሮ፣ በጉድኝትና በክላስተር ተካሂዶ በየካላስተሩ አሸናፊ የሆኑት በከተማ ደረጃ በሆጤ ስታድየም ውድድሩን በማካሄድ ውድድሩ ተጠናቋል።
በዚህ ውድድር ሁሉም የ1ኛ፣ ሁለተኛና መሰናዶ ትምህርት ቤቶች በ4 የስፖርት አይነት ማለትም በእግርኳስ፣ በመረብኳስ፣ በቅርጫት ኳስና በአትሌቲክስ ስፖርት ውድድራቸውን ሲያካሂዱ ቆይተው ዛሬ ለፍጻሜ በቅቷል።
በመዝጊያ ስፖርት ውድድሩ ላይ ንግግር ያደረጉት አቶ ፍቅር አበበ የደሴ ከተማ አስ/ትምህርት መምሪያ ሃላፊ ትምህርት ቤቶች የተተኪ ስፖርተኞች መፍለቂያ መሆናቸውን በመግለጽ ውድድሩ ተተኪ ስፖርተኞችን ከማፍራት ባለፈ በተማሪዎች መካከል አንድንትን፣ ፍቅርና ወዳጅነትን ለማጠናከር የጎላ ፋይዳ አለው ብለወዋል።
በሌላ በኩል የባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ሃላፊ አቶ ሰይድ አራጋው ይህ የትምህርት ቤት ውድድር እንደዚህ በተደራጀ አግባብ መካሄዱ ፋይዳው ከፍ ያለ እንደሆነ አስረድተው ተወዳዳሪ ተማሪዎች ከማሸነፍና ማሸነፍ በዘለለ ራሳቸውን በስፖርት በማዝናናት ትምህርት የመቀበል አቅማቸውን ከፍ እንደሚያደርገው በመግለጽ በደሴ ከተማ የሚገኙ ሁሉም ተማሪዎች በአንድ መድረክ የተሰባሰቡበት እርስበእር እንድተዋወቁ ያደረገ የተማሪዎችን አንድነት ያጠናከረ ከዚያም ከፍ ሲል ምርጥ ተተኪ ስፖርተኞች የታዩበት ነው ትልቅ መድረክ ነው ብለዋል። ለዚህ አላማ ስኬት ትምህርት መምሪያውን አመስግነዋል። ውድድሩ በቀጣይ አመትም ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን ጥንካሬዎችን አስቀጥሎ የታዩ ክፍተቶች ታርመው ለስፖርቱ እድገት ተተኪን በማፍራት አይነተኛ መሳሪያ ሆኖ ይቀጥላል ብለዋል።

በዚህ ውድድር በወንዶች እግርኳስ ስፖርት አዝናኝና ማራኪ ጨዋታ በታየበት ለፍጻሜ የደረሱት ሆጤ ጉድኝት ከመምህር አካል ወልድ ጉድኝት ሲሆን መደበኛውን ጨዋታ 3 እኩል ጨርሰው አሸናፊውን ለመለየት በተሰጠው የመለያ ምት ሆጤ ጉድኝት 5ለ4 በሆነ ውጤት አሸንፎ የዋንጫ ባለቤት ሆኗል። በሌሎች ስፖርቶች ከ2ኛ ደረጃ ት/ቤት ጉድኝት
🥍በቅርጫት ኳስ ወንዶች -ሆጤ ጉድኝት
🥍በመረብኳስ ወንዶች - መምህር አካልወልድ ጉድኝት
🥍 በእግርኳስ ሴቶች -ሆጤ ጉድኝት የዋንጫ አሸናፊ ሲሆኑ
ከ1ኛ ደረጃ ት/ቤት ጉድኝት
🎯በመረብኳስ ወንድ - ጡንጅት አምባ ጉድኝት
🎯በመረብኳስ ሴት- ቁርቁር ጉድኝት
🎯በእግርኳስ ሴት- ሮቢት ጉድኝት
🎯በእግርኳስ ወንድ-ሰኞ ገበያ ጉድኝት
🎯በአትሌቲክስ አጠቃላይ አካልወልድ ጉድኝት የዋንጫ ባለቤት በመሆን ያጠናቀቁ ሲሆን የተዘጋጀላቸውን ዋንጫ ከእለቱ የክብር እንግዶች እጅ ተቀብለዋል።
በመጨረሻም ውድድሩ በስኬት እንድጠናቀቅ ለተሳተፉ ሁሉም ትምህርቤቶች፣ ዳኞች፣ የጸጥታ አካላት፣ የትምህርትና የባህልና ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ሰራተኞች እና ላገዙ ሁሉ ምስጋና ቀርቧል።

በደሴ ከተማ የካራቴ የ3ኛ ደረጃ የአሰልጣኝነት እና የዳኝነት ስልጠና ማሰጠት ጀምረናል።የደሴ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት መምሪያ ከአማራ ክልል ካራቴ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበ...
12/05/2026

በደሴ ከተማ የካራቴ የ3ኛ ደረጃ የአሰልጣኝነት እና የዳኝነት ስልጠና ማሰጠት ጀምረናል።

የደሴ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት መምሪያ ከአማራ ክልል ካራቴ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የ3ኛ ደረጃ የአሰልጣኝነት እና የዳኝነት ስልጠና በደሴ ከተማ ስልጠና እየተሠጠ ነው።

ስልጠናውን በይፋ ያስጀመሩት የመምሪያው የስፖርት ቡድን መሪ አቶ ተፈሪ አሰፋ እንደገለጹት መርሃ ግብሩ በከተማዋ ያለውን የስፖርት እንቅስቃሴ ለማነቃቃትና ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት ያለመ ነው።

አክለውም በዘርፉ ብቁና ተወዳዳሪ የሆኑ ስፖርተኞችን ሳይንሳዊ የሆኑ ስልጠና በመስጠት አሰልጣኞችን ለማብቃት እንዲህ ያሉ ስልጠናዎች ወሳኝ መሆናቸውን ገልጸዋል።

​ከደሴ ከተማ እና ከተለያዩ የክልሉ ዞኖች የተውጣጡ ከ50 በላይ ሰልጣኞች በዚሁ መርሃ ግብር ላይ እየተሳተፉ ሲሆን፤ ስልጠናው ለቀጣይ ሰባት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ይሆናል።

የወዳጅነት እግርኳስ ጨዋታ በውቢቷ ደሴ ከተማ 👉 የቀድሞ የደሴ ከተማ ምርጥ እግርኳስ ተጨዋቾች  Vs  ከድሬዳዋ የቀድሞ ምርጥ እግርኳስ ተጨዋቾች 👉ቅዳሜ ሚያዚያ 24/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:...
30/04/2026

የወዳጅነት እግርኳስ ጨዋታ በውቢቷ ደሴ ከተማ

👉 የቀድሞ የደሴ ከተማ ምርጥ እግርኳስ ተጨዋቾች Vs ከድሬዳዋ የቀድሞ ምርጥ እግርኳስ ተጨዋቾች
👉ቅዳሜ ሚያዚያ 24/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 በሆጤ ስታድየም
🤝የደሴና የድሬ ወዳጅነት ይበልጥ በእግርኳስ ጠበብቶች የሚጠናከርበትን ትልቅ የፍቅር መድረክ 🤝 ከእነዚህ አንጋፋ ተጨዋቾች በተጨማሪ ከፍተኛ አመራሮች የሚሳተፉበት የእግርኳስ ጨዋታ ነው።
ሁላችሁም ተጋብዛችኋል !!

ድሬዎች እንኳን የሰላም፣የፍቅና የውበት አንባ ወደሆነችው ደሴ ከተማ በሰላም መጣችሁ!!

እኛ ደሴዎች አርሂቡ ብለናል!!

የዋንጫ  ጨዋታ 'Dessie  Cup 'የደሴ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ምክርቤት ከሚያካሄቸው ውድድሮች  አንዱ  'የደሴ ዋንጫ' የፍጻሜ ውድድር ቅዳሜ የካቲት 14/2018 ዓ.ም  በሆጤ ስታድየ...
20/02/2026

የዋንጫ ጨዋታ
'Dessie Cup '
የደሴ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ምክርቤት ከሚያካሄቸው ውድድሮች አንዱ 'የደሴ ዋንጫ' የፍጻሜ ውድድር ቅዳሜ የካቲት 14/2018 ዓ.ም በሆጤ ስታድየም
⚽️ ቧንቧውሃ ክፍለከተማ ከ ደሴ ከነማ ''B'' ከቀኑ 9 :00 ሰዓት
በሰዓቱ ተገኝታችሁ እንድትከታተሉ የአክብሮት ግብዣችን ነው።

Address

Dessie

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dessie City Sport Mekrbet posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share