ዐቢይ ሚዲያ Abiy Media

  • Home
  • ዐቢይ ሚዲያ Abiy Media

ዐቢይ ሚዲያ Abiy  Media Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ዐቢይ ሚዲያ Abiy Media, Public & Government Service, addis abeba, .

አባቴ ጎበዝ ገበሬ ነበር። ምርቱም የሰመረለት እንበል። ችግሩ እሱ ብዙ ምርት ሰብስቤያለሁ እያለ ቢያወራም ልጆቹ እና ሚስቱ ግን በጠኔ ልናልቅ ሆነ። ይሄ ጉዳይ ያስጨነቀው ሀብታሙ ጎረቤታችን ...
13/03/2023

አባቴ ጎበዝ ገበሬ ነበር። ምርቱም የሰመረለት እንበል። ችግሩ እሱ ብዙ ምርት ሰብስቤያለሁ እያለ ቢያወራም ልጆቹ እና ሚስቱ ግን በጠኔ ልናልቅ ሆነ።

ይሄ ጉዳይ ያስጨነቀው ሀብታሙ ጎረቤታችን እነ እዚህ ሰዎች በረሀብ ሲያልቁ ዝም ብዬ አላይም ብሎ ቀለብ ልግዛላቸው ይላል።

ይሄን የሰማው አባቴም፣ ሀሳብህ ድንቅ ነው፣ ፈጣሪም ይወደዋል። ግን እህሉን ከሌላ ቦታ ከምትገዛ ከእኔ ግዛኝ እና ለቤተሰቦቼ ስጣቸው።

በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ መታህ ማለት ነው አለ እራሱን እንደ ብልህ እየቆጠረ።

አይ አባቴ!
Tewodros semere

"የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ካሸነፍኩ አልኮል እና አደንዛዥ እፅን ታቆማለህ" በማለት ክሪስቲያኖ በ2014 ከታላቅ ወንድሙ ሁጎ ጋር ስምምነት አደረገ። ሮናልዶ እንዳለው አሸንፎ ወዲያው ወደ ወን...
13/03/2023

"የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ካሸነፍኩ አልኮል እና አደንዛዥ እፅን ታቆማለህ" በማለት ክሪስቲያኖ በ2014 ከታላቅ ወንድሙ ሁጎ ጋር ስምምነት አደረገ። ሮናልዶ እንዳለው አሸንፎ ወዲያው ወደ ወንድሙ ሮጦ "ቃሌን ጠብቄአለሁ አሁን የአንተ ተራ ነው" አለው። የወንድሙን ሕይወት የለወጠው በዚህ መንገድ ነበር። ♥️👏🏻

መጽሐፍን በሽፋኑ ሰውን በአለባበሱ አይታችሁ አትፍረዱ።!በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቁ ተማሪዎች የመመረቂያ ጽሑፋቸውን በቅጡ አቅርበዋል።  ነገር ግን ከተማሪዎቹ መካከል አንዱ ተራ ልብሶችና የተቀ...
10/03/2023

መጽሐፍን በሽፋኑ ሰውን በአለባበሱ አይታችሁ አትፍረዱ።!

በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቁ ተማሪዎች የመመረቂያ ጽሑፋቸውን በቅጡ አቅርበዋል። ነገር ግን ከተማሪዎቹ መካከል አንዱ ተራ ልብሶችና የተቀደደ ስሊፐር አድርጎ ነበር። ያዘጋጀውን ጽሑፍ ለመስማት የተሰናዱ መምህራን በልጁ አለባበስ ተቆጥተው የትችት ናዳ አወረዱበት። ስድባቸውን ከጨረሱ በኋላ ተማሪው በእንባ ይናገር ጀመር....

"በእግዚአብሔር ተአምር የምረቃውን ጥናቴን ለማቅረብ እዚህ ቆሜያለሁ። የቻልኩትን ያህል ለብሼአለሁ።

"ቤተሰቦቼ በጣም ሀብታም ነበሩ እናቴ እና አባቴ በመኪና አደጋ ሕይወታቸውን ያጡት የ9 ዓመቴ እና የ4ተኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ ነው። ብቻዬን ከሁለት እህቶቼ ጋር አጎታችን ንብረታችንን ዘርፎ በቤቱ ሲያኖረን ቆየ። ከጥቂት ዓመታት በኋላ የቤተሰባችንን ንብረት ወርሶ ከቤቱ አስወጣን፤ የማገኘውን ሁሉ ስራ እየሰራሁ፣ ሳልለምን እህቶቼን እና እራሴን መመገብ ጀመርኩ።

"በዚህ ሁኔታ እኔና እህቶቼ የተሻለ ትምህርት ወስደን ህይወታችንን እንድንለውጥ ለራሴ ቃል ገባሁ። ግማሹን ቀን እህቶቼን አበላለሁ ግማሹን ቀን ደግሞ እነሱን በማስተማር የግንባታ ስራ እሰራለሁ፣ እግዚአብሔር ይመስገን። እስከ ዛሬ ቃሌን ጠብቄ፡ ሁለቱንም እህቶቼን ኮሌጅ እያስተማርኩ ዲግሪዬን ልጨርስ ነው። እንደ ጓደኞቼ ዛሬ መልበስ አስቤ ነበር ነገር ግን ለሱፍ እና ለጫማ ያዘጋጀሁትን ገንዘብ ለእህቶች ለሴሚስተር የትምህርት ክፍያ ለመላክ ተገደድኩ... "

"ከፊቱ ተቀምጠው የሚሰድቡት መምህራን አንገታቸውን ደፍተው ነበር፤ ከአስተማሪዎቹ አንዱ:-

"እባክህ ከዚህ በላይ እንዳትናገር! ለመስማት የሚያስችል ጥንካሬ የለኝም" አለች እንባዋን እየጠረገች።

ተማሪው የመመረቂያ ፅሑፉን በጥሩ ሁኔታ አሳካ! እሱን ያልተረዱት መምህራን ተነስተው አጨበጨቡለት። መጽሐፍን በሽፋኑ ሰውን በአለባበሱ አይታችሁ አትፍረዱ።

  ❷(በቅርቡ ከሚታተመው መፅሀፌ የተቀነጨበ)የጉራጌ አባቶች አንፀው ለትውልድ ካስተላለፏቸው ባህሎች መሀከል በጣም የምገረመው የውይይት ና የንግግር ባህሉ ይጠቀሳል።እስኪ እንበልተው..በጉራጌ ...
10/03/2023



(በቅርቡ ከሚታተመው መፅሀፌ የተቀነጨበ)

የጉራጌ አባቶች አንፀው ለትውልድ ካስተላለፏቸው ባህሎች መሀከል በጣም የምገረመው የውይይት ና የንግግር ባህሉ ይጠቀሳል።

እስኪ እንበልተው..

በጉራጌ ባህል ሠርክ ምሽት ለ #ዊከር (ሸንጎ) የተለቀቀ ነው። አግብተህ ከቤት የወጣህ እንደሆነ ሁል ጊዜ ማታ ማታ አባትህ ቤት ትገኛለህ። መላው ቤተሰቡ ይሰባሰብና ቡና ይፈላል።

ቡና ለማህበረሰቡ ያለው ትርጓሜ ደግሞ ብዙ ነው። በቡና ይደሰታል..ያፅናናል..ይወያያል..ማህበረሰባዊ የእውቀት ሽግግር ያደርጋል..ሌላም ሌላም..

እናልህ ቤተሰቡ በሙሉ ለዊከር ተሠብስቦ የቀን ውሎውን ያወጋል። ታድያ ከቤተሠቡ ሽማግሌ እስከ ህፃናት ድረስ ተሰብስበዋልና መንጫጫት ይኖራል። ሳይደማመጡ ያወሩ ይሆናል ብለህ ከገመትክ በጣም ተሳስተሀል።

በማህበረሰቡ ውስጥ ሁሉም የት ፣ እንዴት ና ምን ማውራት እንዳለበት ጠንቅቆ ያውቃል። እንኳን አወራሩ አቀማመጡ ራሱ ህግ አለው። ወደ ጎጆ ቤቱ እንደገባህ በስተግራህ የመጀመርያው ተለቅ የሚለው ወንበር የቤቱ አባወራ ሲሆን በስተቀኝ ያለው ደሞ የቤቱ የመጀመርያ ል (የእንግዳም) መቀመጫ ነው። በተርታ እንደማህበራዊ እርከን ..ወንዶች..ሴቶችና ህፃናት..ይቀመጣሉ። ከነሱ ፊት ለፊት ደግሞ ከብቶች ይኖራሉ።

ይግረምህና ከብቶችም በተርታ እንጂ በዘፈቀደ አይታሠሩም። ..ፈረስ..በቅሎ..በሬ..ላም..ወይፈን..ጊደር..ጥጃ.. ቋሚ አሠላለፋቸው ነው።

ስለአቀማመጥ ህግ ና ስለ ክብ ፍልስፍና በቀጣዩ ፅሁፌ ስለምመለስ ወደ ንግግሩ ልመለስ ..እንግዲህ በየማታው ውይይት ሲደረግ አባቶችና እናቶች የማውራት እድሉን በቀዳሚነት ይወስዳሉ። አንዱ እያወራ ሌላው ሲደረብ አትሰማም የሚሰማህ ብቸኛው ድምፅ የቡናው መንቆርቆር ነው።

ዘመነኛ ነን ባዮች እንዳሉት ቡና መጠጣቱ የሀሜት ነው ብለህ እንዳታስብ

አባቶች የቀደመ ታሪክን ያወሩበታል።

ችግር ለገጠመው ሰው መፍትሄ ይፈለግበታል። ሥነልቦናዊ ቴራፒም አለው።

ወጣቶች ና ህፃናት በዝምታ ውክጥ ከአባቶቻቸው ህይወትን ይማራሉ። እንደዛሬ ወጣት ስለትዳር ወይም ሌላ የአዋቂ ተግባር ለማወቅ መፅሀፍ መግለጥ አይጠበቅባቸውም አባቶቻቸው ከመፅሀፍ በላይ ናቸውና።

ሴት ሙሽሪትም አጠገቧ ያሉ እናቶች የትዳርን ኮርስ ያስተምሯታል።

የመረጃ መለዋወጫም ነው። በቀየው ሲሆን የዋለው ከሩቅም የተሠማውን መረጃ ይለዋወጡበታል።
. ብዙ ነገር ነው ቡና...ቃዋ..

ታድያ በዚህ ማህበረሰብ መሀል ስታድግ አውርቶ የማሣመን በምክንያታዊነት የመከራከር ልምድን ሌላውን የማዳመጥም አቅምህን ታሣድጋለህ።ላትደማመጥ አትንጫጫም ይልቅስ በአይን ንቅናቄ ብቻ ትግባባለህ ። በአብዛኛው የገጠር አባወራ ለሚስቱ የንግግር ትዕዛዝ ሲሰጣት አታይም ግን አንዴ ዞር ብሎ ያያታል። በቃ 'በቂ መግለጫ' ሰጥቷታል። ተግባብተዋል።

ወጣት ሆነህ ይህንን ባህል እንድትለማመድ ደግሞ እድሉን አይከለክሉህም። በሰርግና በአላት የምሽት ጭፈራዎች ላይ አባቶችና እናቶች 'እንዴ ተጮጅዋ - እስቲ ተጫወቱ' ብለው ዘወር ሲሉላችሁ ከመሠሎችህ ጋር በነፃነት መድረኩን ትቆጣጠራለህ። 'ፕራክቲስ ' ወጣህ ማለት ነው።

ሁሉም የማህበረሰቡ አባል የታላቆቹ የመናገር እድልን ሲሰጥ 'እኔ ብቻ ነኝ አዋቂ' ከሚል ተዐብዮ ሊነፃ ነውኮ። ለዚህ ትህትናው ደግሞ በየመሀሉ ተከባሪው ሽማግሌ ልጆቻቸውን ይመርቃሉ ለአካባቢያቸው ሰላምን ይመኛሉ። ምርቃቱን ካዥጎደጎዱት በኋላ ግን የቤቱ ራስ እኔ ነኝ በሚል ምርቃቱን በራሳቸው አይጨርሱትም። አሃ የሠው ትልቅ ቢሆንም ለፈጣሪያቸው ግን ትንሽ ናቸዋ።

"ቢያ የቀፐረ ጎይታ ኧመንኣኩ" ብለው ምርቃቱን ይዘጉታል "ከኔ የቀረውን ፈጣሪ ይሙላው" ማለት ነው።

አሜን አትሉም?

💚💛❤

© Tesfa Neda

" ሰልፉ ተራዝሟል "********ቅዱስ ሲኖዶስ ምንም እንኳን የአቋም ለውጥ ባያደርግም ትላንት በነበረው ውይይት መንግስት የቤተክርስቲያኗን ጥሪ በመቀበል የቤተክርስቲያኗን ችግር ለመፍታት በመ...
11/02/2023

" ሰልፉ ተራዝሟል "
********
ቅዱስ ሲኖዶስ ምንም እንኳን የአቋም ለውጥ ባያደርግም ትላንት በነበረው ውይይት መንግስት የቤተክርስቲያኗን ጥሪ በመቀበል የቤተክርስቲያኗን ችግር ለመፍታት በመስማማቱ ነገ ሊደረግ የታሰበው ሰላማዊ ሰልፍ መራዘሙን አሳውቋል።

🙄🤔🙄🤔
07/02/2023

🙄🤔🙄🤔

አንድን ህዝብ ለአንድ ጊዜ " ኮንፊውዝ" ልታደርገው ትችላለህ:: ሁልጊዜ "ኮንፊውዝ" እያደረኩት እኖራለሁ ብለህ የምታስብ ከሆነ ግን "ኮንፊውዝድ" የምትሆነው አንተ እንጅ ህዝቡ አይደለም:: ...
06/02/2023



አንድን ህዝብ ለአንድ ጊዜ " ኮንፊውዝ" ልታደርገው ትችላለህ:: ሁልጊዜ "ኮንፊውዝ" እያደረኩት እኖራለሁ ብለህ የምታስብ ከሆነ ግን "ኮንፊውዝድ" የምትሆነው አንተ እንጅ ህዝቡ አይደለም:: "ኮንቪንስና ኮንፊውዝድ" የማድረግ አቅም ሲዳከም; የክላሽ አፍ ይከፈታል::

ታሪክ እንደሚነግረን ለሃይማኖቱ የሚታገልን ሰው: የክላሽ አፍ አያቆመውም ምክንያቱም ብሞትም ጽድቅ ይጠብቀኛል ብሎ ስለሚያስብ:: ሞቴ ዘላለማዊ ትርፍ እንጅ ዘላለማዊ ኪሳራ አያመጣም ብሎ ስለሚያምን: የታንክ አፍ ለመጨበጥ ወደ ሁዋላ አይልም:: ኮንፊውዝድ ስትሆን ይህን ቀላል እውነት እንኳን መረዳት ይከብድሃል::

06/02/2023

ደሀ ሀገራት ግን ህዝባቸውን ለመርዳት ያጡትን ገንዘብ ለጦርነት ሲሆን ከየት ነው የሚያገኙት!?🙄🤔

01/02/2023

ጳጳስነት
የፓርላማ ወንበር አይደለም በብሔር ተዋጽኦ የሚወከለው

Address

Addis Abeba

Telephone

+251909951013

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ዐቢይ ሚዲያ Abiy Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to ዐቢይ ሚዲያ Abiy Media:

  • Want your organization to be the top-listed Government Service?

Share