22/11/2025
ማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ ለአሰልጣኞች ሲሰጥ የቆየውን የማመጣጠን ስልጠና አጠናቀቀ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ኀዳር 13 ቀን 2018 ዓ.ም
አሰልጣኞች ለሁለት ወር ያህል የእግረኛ ተዋጊ የሰልጥኖ ማሰልጠን ስልጠና በሚገባ ሲከታተሉ ቆይተው የብቃት ማረጋገጫ ተሰጥቷቸው አጠናቅቀዋል።
የማሰልጠኛ ትምህርት ቤት አዛዥ ብርጋዲየር ጀኔራል አዲሱ ተርፍሳ አሰልጣኞች ተለዋዋጭ የውጊያ ስልቶችን በፍጥነት ተረድተው ድል ማምጣት የሚችሉ ሰልጣኞችን በዕውቀት እና በክህሎት ለማሰልጠን እንደሚያግዛቸው ታሥቦ የተሠጠ ሥልጠና መሆኑን ገልፀዋል።
ዘመኑ የሚጠይቀውን የውጊያ ቴክኒክ አቅም የሚገለጽ ተፈጥሯዊ መልክዓ ምድር አቀማመጥ መቋቋም የሚችል አይበገሬ ሠራዊት ለማሰልጠን ማሰልጠኛው የተሟላ ዝግጁነት በሁሉም ዘንድ እያጠናከረ እንዳለም ተናግረዋል።
አሰልጣኞች በስልጠና ሂደት በተለያዩ ጊዜያት ያገኟቸውን ወታደራዊ ልምድና ችሎታ በመቀመርና ታሳቢ በማድረግ አሃዳዊ ትስስር ፈጥረው የተቋሙን ተልዕኮ ለማስፈፀም ራሳቸውን በማንኛውም ሁኔታ ማዘጋጀት እንደሚጠበቅባቸውም አሥገንዝበዋል።
ዘጋበ ተስፋዬ ያረጋል
ፎቶግራፍ አበበ እያሱ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/-9629...
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official