11/04/2026
በ23 ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል
በደቡብ ወሎ ዞን ኩታበር ወረዳ ልዩ ስሙ "አምቦ" ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በደረሰ የትራፊክ አደጋ በሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን የኩታበር ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
አደጋው የደረሰው ሚያዝያ 2 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡20 ሰዓት ላይ ሲሆን፣ ከደሴ ወደ ማሻ 85 ሰዎችን አሳፍሮ ይጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮ-3-አማ 34510 የሆነ የ"ታታ" የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ኩታበር ወረዳ 06 ቀበሌ ላይ ተገልብጧል።
እስከ አሁን ባለው መረጃ መሠረት በ12 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰ ሲሆን በሌሎች 11 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል። በአደጋው የጠፋ የሰው ህይወት የሌለ ሲሆን ተጎጂዎቹም በአሁኑ ወቅት አስፈላጊው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል።
የተሽከርካሪው አሽከርካሪ ከአደጋው በኋላ ከአካባቢው ያመለጠ ሲሆን የፖሊስ ሃይል አደጋው የተከሰተበትን ትክክለኛ መንስኤ ለማወቅ ምርመራ እያደረገ መሆኑ ተገልጿል።
© Kutaber/ኩታበር/