Finote selam 02 kebele youth league office

Finote selam 02 kebele youth league office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Finote selam 02 kebele youth league office, UAS, Labo.

28/09/2025

ሰው እንሁን

19/06/2025

#ለአሽከርካሪዎቻችን

አደጋን ተከላክሎ የማሽከርከር ስልት ማለት ምን ማለት ነው?

አደጋን ተከላክሎ ማሽከርከር ማለት አሽከርካሪዎች ከእንቅስቃሴ በፊት፤በእንቅስቃሴ ወቅት እና ከእንቅስቃሴ በኋላ በሚያደርጉት ዝግጁነት ከአደጋ ራሳቸውንና ሌሎችን እንዲጠብቁ በመንገድ ላይ አንዱ የሌላውን የመንቀሳቀስ መብትና የእንቅስቃሴ ሁኔታ መረዳት የሚያስችል ጉዳይ ነው::

በተጨማሪም አደጋን ተከላክሎ ማሽከርከር ሲባል የመንገድ ሕግ እና ደንብ እንዲሁም መሰረታዊ የማሽከርከር እውቀት እንዲሁም ክህሎት ከማወቅና ከመተግበር ባሻገር፤ ከእንቅስቃሴ በፊት የሚያደርጉት ዝግጁነት እና የሌሎች አሽከርካሪዎች ሁኔታን ማጤን ወይ ማገናዘብን ጨምሮ በመንገዱ የሚስተዋሉ ሁኔታዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት በጥንቃቄ ማሽከርከርን ያመለክታል፡፡

አደጋን ተከላክሎ የማሽከርከር ስንል

√ በተገቢው የአሽከርካሪ ቦታ ላይ መቀመጥና በስነ-ልቦና ዝግጁ መሆን፤
√ ለችግሮች ተገቢውን መፍትሄ ለመስጠት ሁልጊዜ ዝግጁ መሆን
√ ንቁ ና አስተዋይ መሆን፣
√ ቀበቶ መጠቀም፤
√ ከየትኛውም አቅጣጫ የሚመጡ አሽከርካሪዎች ሊሳሳቱ ወይም ያልተጠበቁ ክስተቶች ሊያጋጥሙ እንደሚችል መገመትና ጥንቃቄ ማድረግ ፤
√ አቅጣጫ ለመቀየር በቅድሚያ የአቅጣጫ ምልክቶችን ማሳየት፣
√ ከፊት፣ ከግራና ከቀኝ በቂ ርቀትን መጠበቅ፤
√ ከትራፊክ ህጉ ጋር የተጣጣመ ፍጥነት መጠቀም፤
√ ተገቢውን እርምጃ በወቅቱ ለመውሰድ መዘጋጀት ፤
√ ከጠጡ በኋላ፣ ድካም ወይም የሚያደክም መድሃኒት ወስዶ አለማሽከርከር፤
√ ለተሽከርካሪው ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግና ማሽከርከር ከመጀራችን በፊት ተሽከርካሪዉን መፈተሽ፤

እነዚህንና መሰል የጥንቃቄ ተግባራትና ስልቶችን ዘወትር በመተግበር የትራፊክ አደጋን እንከላከል ።

የትራፊክ አደጋ በሚከሰት ወቅት የተሽከርካሪ ጉዳትን ጨምሮ ሌሎችን ጉዳቶች ከኢንሹራንስ ጋር ለማያያዝ መሟላት ያለባቸው መረጃዎች:-1. የተሽከርካሪው ባለቤትነት ማረጋገጫ (ሊብሬ)2.አሽከርካሪ...
19/06/2025

የትራፊክ አደጋ በሚከሰት ወቅት የተሽከርካሪ ጉዳትን ጨምሮ ሌሎችን ጉዳቶች ከኢንሹራንስ ጋር ለማያያዝ መሟላት ያለባቸው መረጃዎች:-

1. የተሽከርካሪው ባለቤትነት ማረጋገጫ (ሊብሬ)
2.አሽከርካሪው ከባለቤቱ ውጪ ከሆነ የስራ ቅጥር ውል
3.የታደሰ 3ኛ ወገን
4.ቦሎና
5.አደጋው በተከሰተበት ቅጽበት በሚመለከተው የህግ አካል ስለአደጋው የተመዘገበ ዳታ እና መሰል መረጃዎች ሊሟሉ ይገባል።

የአደጋ መከሰት ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩም በአጋጣሚ የሚከሰት መሆኑን በመረዳት አደጋው ከደረሰ በኋላ ጉዳቱን ሊያካከስ የሚችል ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ጤናማ እና ከላይ የተጠቃቀሱት ሰነዶች የተሟላለትን አሽከርካሪ እያሽከረከርን ስለመሆናችን እርግጠኛ መሆንና ሙያዊ ሀላፊነታችንን መወጣት አለብን ።

Finote Selam City Transport Office

15/06/2025

የመንገድ አጠቃቀማችንን በማሻሻልና በማዘመን የትራፊክ አደጋን በጋራ እንከላከል።

ሁልጊዜም በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ብንሆንም ተሽከርካሪ በሚያዘወትርባቸው አካባቢዎች መንገድን ስንጠቀም ወይንም ስንንቀሳቅስ ግራ መስመራችንን በመያዝ እንዲሁም ስናቋርጥ የዜብራ ምልክቱን በመጠቀም ሊሆን ይገባል።

የፍ/ሰላም ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ተጠሪ ጽ/ቤት

Address

UAS
Labo
121314

Telephone

+251900223456

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Finote selam 02 kebele youth league office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share