23/03/2026
😭😭😭
#የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ ም/ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አዱኛ አዛዥ መጋቢት 9/2018 ዓ.ም ወደ አርባምንጭ በሚጓዙበት ጊዜ፣ በጋርዱላ ዞን ሆልቴና ሽላሌ አካባቢ በታጣቂዎች በተከፈተባቸው ድንገተኛ ተኩስ ተመትተው ሆስፒታል ገብተው ነበር።
በቀን 09/07/2018 ዓ.ም በአርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ረጅም ሰዓታት የፈጀ ቀዶ ጥገና ከተደረገላቸው በኋላ፣ መጋቢት 10/2018 ዓ.ም ከቀኑ 6:00 ሰዓት አካባቢ እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ ህይወታቸው ማለፉ ተረጋግጧል።
በዚህም የአርባ ምንጭ ከተማ ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ጽ/ቤት በከፍተኛ አመራሩ ድንገተኛ ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልጻል።ለቤተሰባቸውና ለወዳጆቻቸው እንዲሁም ለሥራ ባልደረቦቻቸው ከልብ መፅናናትን ይመኛል😭