02/09/2026
ጤናማና አምራች ማህበረሰብን ለመገንባት አከባቢን ከአር ፁዱ በማድረግ ለነዋሪዎች ሚቹ አከባቢ መፈጠር ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ ።
በዳዉሮ ዞን ቶጫ ወረዳ መ/ዓለም እና ሹሹር ቀበሌዎች ከአር የፀዱ በመሆናቸዉ በማብሰር የምረቃ ስነ-ሰርዓት ተካሄዷል ።
በመረሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት የቶጫ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አንድነት ቡንጉዶ እንደጠቆሙት፦ ነዋርዎቹ አከባቢያቸዉን ፅዱና ንፁሁ በማድረጊ ለኑሮ ሚቹ ማድረጋቸዉ እንዳስደሰተቸዉ በመግለጽ አከባቢን ከብክለት ነፃ ማድረጊ የፓርቲያችን ኢኒሼቲቭ መሆኑን በማንሳት የተመዘገበው ስኬት የህዝብን አቅም አስተባብሮ በመስራት ረገድ የተገኘ ትልቅ ድል መሆኑን ገልጸዋል።
አክለዉ አቶ አንድነት፦ቀበሌዎቹ ከአር የፀዱ መሆናቸዉ የነዋሪዎችን ጤናማነት ከማረጋገጥ ባለፈ ለልማት ስራዎች ሚቹ መደላደል ለመፍጠር ጽኑ መሰረት የጣለ ተግባር መሆኑንም አንስተዋል። የቀበሌው ህብረተሰብ ለውጤቱ መመዝገብ ያሳዩት ቁርጠኝነት የሚበረታታ በመሆኑ፣ የተገኘውን ድል ለማስቀጠል እና ወደ ተሻለ የልማት ምዕራፍ ለመሸጋገር የሁሉም ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ርብርብ ማድረግ እንዳለበት አሳስበዋል።
የቶጫ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ተወካይና የበሽታ መከላከል ቡድን አስተባባሪ አቶ መላኩ መኩሪያ በበኩላቸው፦ ተቋሙ የህብረተሰቡን ጤና ከበሽታ ቀድሞ ለመከላከል በልዩ ትኩረት እየራ በሆኑ በዛሬዉ ዕለት የክልልና የዞን የጤና ቡድን በተለያዩት ጊዜያት ዞሬዉ በመመልከት በሰጡት ግብረ-መልስ መነሻ ሁለቱ ቀበሌዎች ከአር የፀዱ የሆናቸዉን አብስረዋል።
አክለዉ አቶ መላኩ፦አር/የሰገራ አጠቃቀም በህብረተሰቡ ላይ ያስከትል የነበረውን ከባድ የጤና ጫና በማስታወስ፣ አሁን የተደረሰው ስኬት በውሃ ወለድ እና ተላላፊ በሽታዎች የሚደርሰውን ጉዳት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀንሰው አመላክተዋል።
በመረሃ-ግብሩ ላይ ጤናማና አምራች ማህበረሰብን ለመገንባት አከባቢን ከአር ፁዱ በማድረግ እንዲህ አይነት የመሰረታዊ ንጽህና ዘመቻዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸውም ተጠቁሟል።
ዘገባዉ፦የቶጫ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነዉ።