Ethiopian Consulate in Beirut, Lebanon የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄ/ጽ/ቤት ቤይሩት-ሊባኖስ

  • Home
  • Lebanon
  • Beirut
  • Ethiopian Consulate in Beirut, Lebanon የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄ/ጽ/ቤት ቤይሩት-ሊባኖስ

Ethiopian Consulate in Beirut, Lebanon የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄ/ጽ/ቤት ቤይሩት-ሊባኖስ በዚህ ገጽ ላይ በስርዓትና በጨዋነት እንዲሳተፉ ይጠየቃሉ፡፡ ማንኛውንም አይነት የስድብ ቃላት መጠቀም አይፈቀድም፡፡

This is the official Facebook address of the Consulate General of the Federal Democratic Republic of Ethiopia in Beirut, Lebanon,
it's responsible for Ethiopia Diaspora who are living in Lebanon, Syria and Jordan and to strengthen the diplomatic relation with Lebanon.

ታድሶ የመጣ ፓስፖርት!----------------------------ስማችሁ ከዚህ በታች የተጠቀሰው ዜጎቻችን፣ ፓስፖርታችሁ ታድሶ የመጣ ስለሆነ  በስራ ቀንና ሰዓት በቆንስላ ጽ/ቤታችን በአካል...
02/06/2026

ታድሶ የመጣ ፓስፖርት!
----------------------------
ስማችሁ ከዚህ በታች የተጠቀሰው ዜጎቻችን፣ ፓስፖርታችሁ ታድሶ የመጣ ስለሆነ በስራ ቀንና ሰዓት በቆንስላ ጽ/ቤታችን በአካል በመቅረብ ፓስፖርታችሁን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

አስቸኳይ!!======ከዚህ በታች ስማችሁ የተገለፀው ዜጎቻችን፣ ከዚህ በፊት ፓስፓርታችሁ ለማሳደስ ያመለከታችሁ ስሆን፣ ነገር ግን ፓስፖርታችሁ በልዩ ልዩ ጉድለት ስለተመለሰ በስራ ቀንና ሰዓት...
02/06/2026

አስቸኳይ!!
======
ከዚህ በታች ስማችሁ የተገለፀው ዜጎቻችን፣ ከዚህ በፊት ፓስፓርታችሁ ለማሳደስ ያመለከታችሁ ስሆን፣ ነገር ግን ፓስፖርታችሁ በልዩ ልዩ ጉድለት ስለተመለሰ በስራ ቀንና ሰዓት በቆንስላ ጽ/ቤታችን በአካል ቀርባችሁ ጉድለቱ እንድታስተካከሉ እናሳውቃለን።

01/06/2026



ዴሞክራሲያዊ ባህሏን እየገነባች የምትገኘው ኢትዮጵያ፣ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ እያካሄደች ነው። መራጮችም የበኩላቸውን ለመወጣት በማለዳው በየምርጫ ጣቢያዎቹ በመገኘት ድምፃቸውን መስጠት ጀምረዋል ።

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

በውጭ የምትኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን አካውንታችሁ ከፋይዳ መታወቂያ ጋር ባለመተሳስሩ የተዘጋባችሁ የባንኩ ደንበኞች ባንኩ በውጭ የምትኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን...
28/05/2026

በውጭ የምትኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን አካውንታችሁ ከፋይዳ መታወቂያ ጋር ባለመተሳስሩ የተዘጋባችሁ የባንኩ ደንበኞች ባንኩ በውጭ የምትኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በተለየ ሁኔታ ለማስተናገድ ባዘጋጀው አሰራር መስተናገድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን::

27/05/2026

እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል አድሐ በዓል አደረሰን፣ አደረሳችሁ!

ስለዒድ አል-አድሐ “ዐረፋ” በዓል ስናስብ ሦስት ነገሮች ቀድመው ይታወሱናል። መስዕዋትነት፣ መታዘዝ እና መተጋገዝ። አባት ልጁን ለመስዕዋት ያቀረበበት፤ ልጅ የአባቱን ትዕዛዝ የፈጸመበት፤ ሙስሊሞች የመተጋገዝን እሴት ለዓለም የገለጡበት በዓል ስለሆነ “ዐረፋ” በሕዝበ-ሙስሊሙ ዘንድ ትልቅ ትርጉም አለው።

እስማኤል ለነብዩ ኢብራሂም የመጀመሪያ እና ተወዳጅ ልጃቸው ነው። አላህ (ሱ.ወ.) ይሄን ተወዳጅና የመጀመሪያ ልጅ እንዲሠዉለት ሲጠይቃቸው ታዘዙ እንጂ ወደኋላ አላሉም። ለመታዘዝ የሞከሩት ነገሩ ቀላል ሆኖ አይደለም። ልጅን ያህል ነገር መስዕዋት ማድረግ ምኑ ይቀላል? የአባትነት ስሜት ይተናነቃል። የሰይጣን ሹክሹክታ ይፈታተናል። የቤተዘመድን ወቀሳ እና የጎረቤትን አስተያየት መቋቋምም ይከብዳል። ነብዩ ኢብራሒም፥ በዚህ ሁሉ አጣብቂኝ ውስጥ አንድ ሐቅ ተገልጦላቸዋል። ከራስ ስሜት፣ ከሰው ሐሜት እና ከወዳጅ ፍላጎት የሚልቅ ታላቅ ዓላማ እንዳለ አምነዋል። ስለዚህም በፈተና ውስጥ ጸንተው ቆሙ፤ ቆራጥነታቸውም በተግባር ታየ።

ሀገር የምትገነባው ከራስ ጥቅም በላይ በሚያስቡ እና ከግላዊ ፍላጎታቸው በላይ ለመፈጸም በቆረጡ ዜጎች ነው። የሚወዱትን ነገር እንኳን ሳይቀር ለመሠዋት ዝግጁ የሆኑ ዜጎች ሲበዙላት ሀገር ትበረታለች። እስማኤላቸውን ለመስጠት የማያመነቱ ዜጎች የሞሉባት ሀገር ጽኑ ናት።

የለመድናቸው፣ የምንወዳቸው፣ የራሳችን ገንዘብ ያደረግናቸው ብዙ ነገሮች ይኖራሉ። ከእነዚህ የሚበልጥ ዓላማ ግን አለ፤ እሱም “ሀገርነት እና ሉአላዊነት” ይሰኛል። ሀገርነት የሚገነባው ከመውሰድ ይልቅ በመስጠት ነው። ሉአላዊነት የሚጸናው በፈተና ሳይወድቁ በመቆም፤ በወጀብ ሳይናወጡ መጓዝ በመቻል ነው።

የእውነት ኢትዮጵያ ሲያልፍላት ማየት የምንሻ ከሆነ ምኞታችን በተግባር ይገለጥ። የሀገር ኩስመና ካሳሰበን ለግዝፈቷ እንድከም። ያጎበጣትን የድህነት ቋጥኝ ለመሸከም ትከሻችንን እናመቻች። ጎተራዋ እንዲሞላ እጃችን አፈር ይንካ። የጠየመ ገጽዋ እንዲፈካ በሥራ ሌት-ተቀን እንሰለፍ። የተቀማ ክብሯ እስኪመለስ ድርሻችንን እንወጣ። ሀገር መውደዳችን ከልብ ከሆነ መስዕዋት ለመሆን አናመንታ።

የዐረፋ በዓል የመታዘዝና የመስዕዋት ብቻ ሳይሆን የመደጋገፍና የመተጋገዝ በዓል ጭምር ነው። በዐረፋ ከሚከናወነው እርድ አንድ ሦስተኛው ለምስኪኖች እንዲሰጥ የእስልምና አስተምህሮ ያዛል። በዐረፋ ሕዝበ-ሙስሊሙ ደስታና ሐዘኑን እየተጋራ በዓሉን ያከብራል። የዐረፋ እለት አንድም ሰው ተከፍቶ አያሳልፍም፤ በዐረፋ ሰሞን ማንም ሰው ተርቦና ተጠምቶ አያድርም። በዓሉ ትርጉም የሚሰጠው ሕዝበ-ሙስሊሙ ያለውን ተካፍሎ ሲያከብረው ነው። ሰዎች አስቸጋሪ ሁኔታን የሚሻገሩበት መፍትሄው መተሳሰብና መተጋገዝ እንደሆነ ከዐረፋ እንማራለን። ሀገርም ከፈተናዎችዋ በላይ እንድትሆን እኒህ እሴቶች ወሳኝ ናቸው።

ዐረፋ ማኅበረሰባዊ በዓል የሚባለው ለዚህ ነው። ሰዎች በግላቸው የሚያከብሩት አይደለም። ቤተሰቡ፣ ጎረቤቱ፣ ሠፈሩ፣ ከተማው የሚያከብረው በዓል ነው። ያላቸውና የሌላቸው፤ የሚችሉና የማይችሉ፤ ታላላቆችና ታናናሾች፤ ባለ ሥልጣናትና ተራ ዜጎች፣ በአንድነት የሚያከብሩት በዓል ነው። ሰው የሚኖረው በቤቱ ውስጥ አይደለም። በማኅበረሰቡ ውስጥ ነው።

ማኅበረሰባዊ ትሥሥርና ትብብር ለዜጎች እና ለሀገር ደኅንነት ወሳኝ ናቸው። ማኅበረሰባዊ ትሥሥር ስለሌሎች እንድናስብ፣ ስለሌሎች እንድንሠራ እና ስለ ሌሎች ዋጋ እንድንከፍል ያደርገናል። ራሳችንን በሌሎች ጫማ ላይ አቁመን እንድናይ ያስችለናል። የሁላችንም ሰላም፣ የሁላችንም ደኅንነት እና የሁላችንም ጥቅም ካልተከበረ በቀር የግላችንን ብቻ ልናስከብር እንደማንችል ያስገነዝበናል። ስለዚህም ማኅበራዊ ግዴታን እንደ ዜግነት ግዴታ ወስደን እንድንሠራ ያደርገናል።

ምርጫ ማኅበራዊና ዜግነታዊ ግዴታዎችን ከምንወጣባቸው የዴሞክራሲ መገንቢያ መሳሪያዎች መካከል ዋነኛው ነው። ያለ ሕዝብ ተሳትፎ ዴሞክራሲ አይሳካም። ያለ ምርጫም የሕዝብ ተሳትፎ ምሉዕ አይሆንም። የዴሞክራሲያችን መሰረት ጥንካሬው የሚለካው በተሳትፎአችን መጠን ነው።

የዘንድሮ ሀገራዊ ምርጫ ሀገረ-መንግሥታዊ ሥርዓታችን የሚጠነክርበት መሰረት ነው። የዴሞክራሲ ልምምዳችን አንድ ደረጃ ከፍ የሚልበት፤ የቀጣይ ዓመታት የሀገራችንን እጣ-ፈንታ የምንበይንበት፤ ከምንም በላይ ብዝሃ-ድምጽ የሚሰማበት የሕግ መወሰኛ ምክርቤት የምንመሰርትበት ወሳኝ አጋጣሚ ነው። በመሆኑም በዓሉን ስናከብር ዜግነታዊ ግዴታችንን ለመወጣት ብቻ ሳይሆን በካርዳችን ዴሞክራሲያዊ መብታችንን ለማረጋገጥ እየተዘጋጀን እንዲሆን ጥሪዬን አቀርባለሁ።

በድጋሚ መልካም የዐረፋ በዓል እንዲሆን እመኛለሁ!
ዒድ ሙባረክ!!

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ግንቦት 18፣ 2018 ዓ.ም

ማስታወቂያ (ስማችሁ ለተዘረዘረ የመጀመሪያ ዙር ተሳፋሪዎች)=======በማስ ትራቭል ፕሮግራም ወደ አገር ቤት ለመሳፈር ተመዝግባችሁ ስማችሁ ከዚህ በታች የተዘረዘረ ዜጎቻችን ወደ ሀገር ቤት መ...
26/05/2026

ማስታወቂያ (ስማችሁ ለተዘረዘረ የመጀመሪያ ዙር ተሳፋሪዎች)
=======
በማስ ትራቭል ፕሮግራም ወደ አገር ቤት ለመሳፈር ተመዝግባችሁ ስማችሁ ከዚህ በታች የተዘረዘረ ዜጎቻችን ወደ ሀገር ቤት መመለሻ የጉዞ ትኬት ከታች ባለው ፕሮግራም መሰረት የተቆረጠላችሁ ስለሆነ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ራፊቅ ሐረሪ አውሮፕላን ማረፊያ እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡
1. ከተራ ቁጥር 1 - 41 ያላችሁት እሮብ ምሽት እ.ኤ.አ ጁን 3 ቀን 2026 በሊባኖስ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 11፡00pm (በኢትዮጵያ አቆጣጠር እሮብ ግንቦት 26 ቀን 2018 ከምሽቱ 5፡00 ሰዓት)፤

2. ከተራ ቁጥር 42 -76 ያላችሁት ሀሙስ እ.ኤ.አ ጁን 4 ቀን 2026 በሊባኖስ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 11፡00pm (በኢትዮጵያ አቆጣጠር ሀሙስ ግንቦት 27 ቀን 2018 ከምሽቱ 5፡00 ሰዓት) ፤

3. ከተራ ቁጥር 77- 111 ያላችሁት አርብ እ.ኤ.አ ጁን 5 ቀን 2026 በሊባኖስ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 11፡00pm (በኢትዮጵያ አቆጣጠር አርብ ግንቦት 28 ቀን 2018 ከምሽቱ 5፡00 ሰዓት) ፤

4. ከተራ ቁጥር 112 -146 ያላችሁት ቅዳሜ እ.ኤ.አ ጁን 6 ቀን 2026 በሊባኖስ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 11፡00pm (በኢትዮጵያ አቆጣጠር ቅዳሜ ግንቦት 29 ቀን 2018 ከምሽቱ 5፡00 ሰዓት) ፤

5. ከተራ ቁጥር 147 -180 ያላችሁት እሁድ እ.ኤ.አ ጁን 7 ቀን 2026 በሊባኖስ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 11፡00pm (በኢትዮጵያ አቆጣጠር እሁድ ግንቦት 30 ቀን 2018 ከምሽቱ 5፡00 ሰዓት) ፤

6. ከተራ ቁጥር 181 -215 ያላችሁት ሰኞ እ.ኤ.አ ጁን 8 ቀን 2026 በሊባኖስ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 11፡00pm (በኢትዮጵያ አቆጣጠር ሰኞ ሰኔ 1 ቀን 2018 ከምሽቱ 5፡00 ሰዓት) ፤

*** ጥብቅ ማሳሰቢያ
 የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ሰዓቱን አሁን በሚበርበት የቀን በረራ የሚቀጥል ከሆነ ኤርፓርት የምትገኙበት ሰዓትና ቀን ለውጥ(ሽግሽግ) ሊኖረው ስለሚችል በቆንስላው የሚተላለፉ መረጃዎችን እንድትከታተሉ እናሳስባለን፡፡
 ወደ አገር ቤት የምትሳፈሩ ዜጎቻችን በምትሳፈሩበት ወቅት መያዝ የምትችሉት 2 ሻንጣ (እያንዳንዱ ከ23 ኪሎ መብለጥ የለበትም) እና አንድ ተጎታች(ከ7 ኪሎ መብለጥ የለበትም) መሆኑን አውቃችሁ የተፈቀደዉን ኪሎ ብቻ ይዛችሁ እንድትመጡ እያሳሰብን፡ ከተፈቀደው ኪሎ በላይ ይዞ የሚመጣ ሰው የማይስተናገድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

በሊባኖስ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቆንስል ጄኔራል ጽ/ቤት በዛህሌ ከተማ እና አካባቢው ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር ውይይት አካሄደ፤===========================(ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ...
25/05/2026

በሊባኖስ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቆንስል ጄኔራል ጽ/ቤት በዛህሌ ከተማ እና አካባቢው ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር ውይይት አካሄደ፤
===========================
(ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም.) በሊባኖስ (ቤይሩት) የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤታችን በአገሪቱ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር እና ከማህበሩ የዛህሌ ከተማ ቅርንጫፍ ጋር በመተባበር በዛህሌ ከተማ እና አካባቢው ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡

በመድረኩ የኢፌዲሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤቱ ተወካይ እና የዲያስፖራ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ጌታቸው ኡታ የቆንስላ ጄነራል ጽ/ቤቱ የ2018 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ስኬቶች፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች፣ የተወሰዱ መፍትሔዎች እና በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን አቅርበው ውይይት ተደርጓል። በዚህም የዜጎች መብትና ጥቅም የማስጠበቅ ሥራዎች፣ የዜጎች ሕገ-ወጥ ፍልሰት እያስከተለ ያለው ጫና እና ይህንን ሕጋዊ መስመር ለማስያዝ የተፈረመው የሁለትዮሽ የሥራ ሥምሪት ስምምነት ያለበት ደረጃ በተመለከተ ከተሳታፊዎች ጥያቄዎች እንዲሁም ሃሳቦች ቀርበው ሰፊ ውይይትና ማብራሪያ ተደርጎባቸዋል፡፡ በመድረኩ ከቆንስላ ጽ/ቤቱ የተለያዩ ዘርፎች የተውጣጡ ዲፕሎማቶች እና የኮሚኒቲ ማህበር አመራሮች ከተሳታፊዎች ለቀረቡ ለጥያቄዎችና ሐሳቦች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በዛህሌ ከተማ እና አካባቢው ቅርንጫፍ የኮሚኒቲ ማህበር የተጓደሉ አመራሮች የማሟላት ሥራም ተከናውኗል፡፡

በመጨረሻም የማህበረሰብ አባላት በውይይት ወቅት ላደረጉት ንቁ ተሳትፎ እና ገንቢ አስተያየቶች በማመስገን በቀጣይም ጽ/ቤቱ የዜጎችን መብትና ጥቅም ለማስከበር የኮሚኒቲ አደረጃጀቶችን ጨምሮ ከባለድርሻ አካላት ጋር ይበልጥ በቅርበት እንደሚሰራ በማረጋገጥ ውይይቱ ተቋጭቷል።

Prime Minister Abiy Ahmed Ali "Happy Africa Day to all Our African Brothers and Sisters!================================...
25/05/2026

Prime Minister Abiy Ahmed Ali "Happy Africa Day to all Our African Brothers and Sisters!
=================================
63 years ago, our forefathers gathered here in Addis Ababa and dared to dream of a free, united Africa-a Vision that remains as vibrant today as it was at its inception.

As the proud host of the African Union, Ethiopia stands in steadfast solidarity with our sister nations in the pursuit of this shared ideal. While we celebrate our progress, we acknowledge that our work continues. Let us build upon our shared heritage, fostering a renewed spirit of collaboration that accelerates our collective prosperity and drives us toward meaningful, sustainable growth.

Africa's greatest resource has always been her people; together, in unity and shared resolve, we rise."

ማስታወቂያ!=======
22/05/2026

ማስታወቂያ!
=======

Today, Mr. Getachew Uta, Charge' d'Affaires of the Consulate General of the Federal Democratic Republic of Ethiopia in L...
21/05/2026

Today, Mr. Getachew Uta, Charge' d'Affaires of the Consulate General of the Federal Democratic Republic of Ethiopia in Lebanon and the Head of the Diaspora Affairs, held productive discussion with H.E. Ambassador Abdel Sattar Issa, Secretary General of the Ministry of Foreign Affairs and Emigrants of the Republic of Lebanon.

The discussion focused on Strengthening cooperation and partnerships in bilateral, regional and international issues of common concern including matters of national and regional peace, security, and development.

During the discussion, Mr. Getachew highlighted the state building endeavors as well as the stabilizing roles of the Federal Democratic Republic of Ethiopia in the Horn of Africa through its active bilateral and multilateral diplomatic engagements, conflict resolutions, economic integration, and people to people relations.

H.E. Ambassador Issa on his part expressed appreciation to the continued excellent relations between the two countries and commended Ethiopia's contributions to regional peace and stability, and reaffirmed Lebanon's firm support for a peaceful and prosperous Ethiopia.

Both officials concluded the meeting by committing to expanded cooperation.
They firmly emphasized that inclusive diplomatic dialogue remains the viable path forward for the peaceful resolution of differences.

Address

Beirut

Opening Hours

Monday 08:00 - 15:00
Tuesday 08:00 - 15:00
Wednesday 08:00 - 15:00
Thursday 08:00 - 15:00
Friday 08:00 - 15:00

Telephone

+9615467166

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Consulate in Beirut, Lebanon የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄ/ጽ/ቤት ቤይሩት-ሊባኖስ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Ethiopian Consulate in Beirut, Lebanon የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄ/ጽ/ቤት ቤይሩት-ሊባኖስ:

Share