በስልጤ ዞን የጦራ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን

  • Casa
  • Italia
  • Tora
  • በስልጤ ዞን የጦራ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን

በስልጤ ዞን የጦራ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን ጠንካራ ኢንስፔክሽን ለጠንካራ ፓርቲ !

07/06/2026
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የብልጽግና የኢንስፔክሽንና የሥነ ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ከዞንና ከልዩ ወረዳ ቅ/ጽ/ቤቶች ጋር የግንቦት ወር የኮሚሽኑን እቅድ ክንውን አፈፃፀም ግምገማ በበይነ ...
07/06/2026

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የብልጽግና የኢንስፔክሽንና የሥነ ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ከዞንና ከልዩ ወረዳ ቅ/ጽ/ቤቶች ጋር የግንቦት ወር የኮሚሽኑን እቅድ ክንውን አፈፃፀም ግምገማ በበይነ መረብ በማካሄድ በቀጣይ አንድ ወር በሚከናወኑ ተግባራት ላይ የጋራ መግባባት ፈጠረ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ግንቦት 30/2018 ዓ.ም

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የብልጽግና የኢንስፔክሽንና የሥነ ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ከዞንና ከልዩ ወረዳ ቅ/ጽ/ቤቶች ጋር የግንቦት ወር የኮሚሽኑን እቅድ ክንውን አፈፃፀም ግምገማ በበይነ መረብ በማካሄድ በቀጣይ አንድ ወር በሚከናወኑ ተግባራት ላይ የጋራ መግባባት በመፍጠር ዝግጁነት ተፈጥሮዋል።

በበየነ መረብ ግምገማው የኢንስፔክሽንና የሥነ ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዱልዋሪስ ጀማልና ም/ኃላፊ ወ/ሮ ሂሩት ተሾመ እንዲሁም የዞንና የልዩ ወረዳ የብልጽግና የኢንስፔክሽንና የሥነ ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ዋናና ምክትል ሀላፊዎች ተገኝተዋል ።

''ጠንካራ ኢንስፔክሽን ፤ ለጠንካራ ፓርቲ''

05/06/2026
03/06/2026

የስልጤ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ነኢማ ሙኒር 7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ በሆነ መልኩ በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት በሙሉ የምስጋና መልዕክት አስተላለፉ።

ግንቦት 26/ 2018 ዓ.ም
የስልጤ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የህዝብ ግንኙነት
____________________________________________


‎7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ በሆነ መልኩ እንዲጠናቀቅ የላቀ ሚና ለተጫወቱ ከክልልና ከዞን ማዕከል ጀምሮ በየደረጃው ያላችሁ አመራሮች፣ አባላት ፣ ደጋፊዎች፣የፀጥታ አካላት፣ሴቶች ፣በጎ ወጣቶች እንዲሁም መላው መራጭ ህዝብ በነቂስ ወጥታችሁ ምርጫው ላይ የተሳተፋችሁ አካላት በሙሉ ከልብ የመነጨ ክብርና ምስጋና ይገባችሀል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፏል ።

‎ምርጫ በማንኛውም ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ውስጥ የሕዝብ ሉዓላዊ ፈቃድ የሚገለጽበት፣ የዜጎች እውነተኛ የፖለቲካ ተሳትፎ የሚረጋገጥበት እና የሀገር የጋራ ራዕይ፣ ዕድልና አቅጣጫ የሚወሰንበት ታላቅ ሀገራዊ ሂደት ነው።

‎ይህ ታላቅ ሂደት በሰላምና በስኬት እንዲጠናቀቅ የተደረገው ጥረት የአንድ ተቋም ወይም የአንድ አካል ብቻ ድካም ውጤት አይደለም ይልቁንም የብዙኃኑ ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ልፋት፣ የማይናወጥ ትብብር እና የጋራ ቁርጠኝነት የታየበት ስኬት ነው።

‎የዘንድሮዉ የምርጫው ሂደት በሕግና በሥርዓት እንዲመራ፣ የመራጮች መብት እንዲከበር፣ የምርጫ ጣቢያዎች ፍጹም ሰላማዊ አገልግሎት እንዲሰጡና የሕዝቡ ንቁ ተሳትፎ በተሟላ ሁኔታ እንዲረጋገጥ ሌት ተቀን በትጋት ለደከሙ አካላት በሙሉ የላቀና ልዩ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

‎‎በተጨማሪም በቅድመ-ምርጫ፣ በምርጫው ዕለትና በድህረ-ምርጫ ሂደቶች ሁሉ ሰላምና መረጋጋት ሳይናጋ እንዲቀጥል የዜጎች ደህንነት አስተማማኝ እንዲሆን እና የሕግ የበላይነት እንዲከበር የማይተካ ሚና ለተጫወቱት የጸጥታ ኃይሎቻችን የላቀ አክብሮትና ታላቅ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።

የመቻቻል ባህልን በማሳደግና የሰላም እሴቶችን በማክበር፣ በሕጋዊና ሰላማዊ መንገድ ብቻ ለተወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ዕጩዎችና ደጋፊዎቻቸው በሙሉ ላበረከቱት አስተዋፅኦ ታላቅ አክብሮታቸውን ገልፀዋል።

‎የምርጫው ሂደት ግልጽና ታማኝ እንዲሆን የሕዝብ ዓይንና ጆሮ በመሆን ያገለገሉትን የሚዲያ ተቋማትና ጋዜጠኞች ያመሰገኑት ክብርት ነኢማ ሙኒር ሚዲያው እውነተኛና ሚዛናዊ መረጃዎችን በወቅቱ በማድረስና ሂደቱን በኃላፊነት በመዘገብ ላሳዩት የላቀ ሚና ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።

በተለይ የህብረተሰቡ ምሰሶ ለሆኑት የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች ልዩ አክብሮታቸውን የገለጹት ክብርት ወ/ሮ ነኢማ የሕዝብን አንድነት በማጥበቅና የምርጫው ሂደት በአዎንታዊ መንፈስ እንዲሳካ በማድረግ ረገድ ላበረከቱት የማይተካ አስተዋጽኦ ታላቅ ምስጋና ይገባቸዋል ሲሉም ገልፀዋል ።

ከሁሉም በላይ የክብሩ መደብና የታሪኩ ባለቤት ለሆነው ለተከበረው የስልጤ ዞን ሕዝብ ልዩና የላቀ ምስጋና ያቀረቡት ክብርት ወ/ሮ ነኢማ በምርጫው ዕለት የዜግነት ኃላፊነቱን ለመወጣት ካለሊቱ 11:30 ጀምሮ እስከ ምሽት 6:00 ድረስ ሳይሰለች፣ ብርድና ንፋስ፣ ፀሐይና ሙቀት እየተፈራረቁበት በሰላማዊና በሥርዓታማ ሰልፍ በመቆም፣ የዴሞክራሲ መብቱን በከፍተኛ ኃላፊነት በመጠቀም ለምርጫው ስኬት የላቀ ታሪክ የጻፈው ውዱ ሕዝባችን ከምንም በላይ ታላቅ ምስጋና እና ክብር ይገባዋል ብለዋል።

‎የሕዝባችን የማይናወጥ ሰላም ፍቅር፣ የጸና የአንድነት መንፈስ እና ልባዊ የሕግ አክባሪነት ለዚህ ታሪካዊ ስኬት ዋነኛውና የማይናጋው መሠረት ነው።

‎ይህ ምርጫ በሰላም መጠናቀቁ የዞናችን ሕዝብ የዴሞክራሲ ባሕልን እያዳበረና እያጠናከረ መምጣቱን፣ ለዘላቂ ሰላም ያለውን ፍጹም ቁርጠኝነት እና ለሀገር ግንባታ ያለውን ንቁ ተሳትፎ በግልጽ ያሳየበት ታላቅ ማረጋገጫ መሆኑን ገልፀዋል።

ይህንን ያገኘነውን በጎ ተሞክሮ እና መልካም ልምድ ይበልጥ በማስቀጠል ለላቀ ሰላም፣ ለተፋጠነ ልማትና ለአጠቃላይ ብልጽግና በጋራ እንደምንሠራ ያለን እምነት ፍጹም ጽኑ ነው።

በመጨረሻም ይህ 7ኛው አጠቃላይ ምርጫ በሙሉ ሰላምና በላቀ ስኬት እንዲጠናቀቅ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ አሻራችሁን ላሳረፋችሁ በሙሉ በድጋሚ ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
በቀጣይም ለሕዝባችን ጽኑ ሰላም፣ ለዞናችን ሁለንተናዊ ዕድገት እና ለሀገራችን የጋራ ብልጽግና በትጋት በአንድነት እንድንቆም በፓርቲያችን ስም ጥሪዬን አስተላልፋለሁ ብለዋል።

25/05/2026

ለምርጫው 7 ቀናት ብቻ ቀርተውታል!

በሀገራችን አዲስ የዕድገት ምዕራፍ ታሪካዊ አሻራዎን ለማሳረፉ ከወዲሁ ይዘጋጁ!

አቶ ደኑር ኮሪ የጦራ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ

ግንቦት 24፣ 2018
ምርጫችን ብልፅግና ይሁን!

23/05/2026
22/05/2026

#ለምርጫው 10 ቀናት ብቻ ቀርተውታል! በድምፅዎ ዴሞክራሲን በማፅናት የብልፅግና ጉዟችን ላይ ጉልህ አሻራዎን ያሳርፉ !

አቶ ደኑር ኮሪ የጦራ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ

#ምርጫችን ብልጽግና
#ምልክታችን የስንዴ ነዶ
#መልዕክታችን ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር

የጦራ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት

Indirizzo

Tora

Telefono

+251916573025

Sito Web

Notifiche

Lasciando la tua email puoi essere il primo a sapere quando በስልጤ ዞን የጦራ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን pubblica notizie e promozioni. Il tuo indirizzo email non verrà utilizzato per nessun altro scopo e potrai annullare l'iscrizione in qualsiasi momento.

Contatta L'organizzazione

Invia un messaggio a በስልጤ ዞን የጦራ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን:

Condividi