Wolkite City Administration Government Communication Affairs Office

Wolkite City Administration Government Communication Affairs Office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Wolkite City Administration Government Communication Affairs Office, Wolkite.

‎በሊዝ ጨረታ ለመኖሪያ ፣ለንግድ እና ለልማት የተላለፉ ቦታዎችን የወሰዱ ተጠቃሚዎች በውሉ መሠረት በፍጥነት ወደ ልማት ስራ እንዲገቡ የወልቂጤ ከተማ ማዘጋጃ ቤት አሳሰበ።‎‎ግንቦት 28/201...
05/06/2026

‎በሊዝ ጨረታ ለመኖሪያ ፣ለንግድ እና ለልማት የተላለፉ ቦታዎችን የወሰዱ ተጠቃሚዎች በውሉ መሠረት በፍጥነት ወደ ልማት ስራ እንዲገቡ የወልቂጤ ከተማ ማዘጋጃ ቤት አሳሰበ።

‎ግንቦት 28/2018ዓ.ም [ወልቂጤ ]

‎በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ለ5ኛ ዙር ያወጣውን የመኖሪያ ቦታ የሊዝ ጨረታ በይፋ ተከፈተ።

‎ ለ5ኛ ዙር የወጣው ግልፅ የሊዝ ጨረታ ለመኖሪያ ቤት 54 ፕሎቶች ለከተማው ነዋሪው የማቅረብ ስራ መሰራቱን ማዘጋጃ ቤቱ ገልጿል ።


‎የወልቂጤ ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ቶፊቅ ሱልጣ እንደተናገሩት በ2018 በጀት አመት የከተማ መሬት ጨረታ ስራ በህግ፣በግልፅነትና በተወዳዳሪነት ለተጠቃሚዎች በሊዝ ለማስተላለፍ ከምንም ጊዜ በተሻለ በትኩረት መሠራቱን ገልጸዋል ።

‎ለ5ኛ ዙር የወጣውን ግልፅ የመኖሪያ ቦታ የሊዝ ጨረታ ኮሚቴዎችና ስነምግባሮች በተገኙበት ጨረታው መከፈቱንም አስረድተዋል ።

‎በዚህ ዙር ለመኖሪያ ቤት 54 ፕሎቶች ለከተማው ነዋሪው የማቅረብ ስራ መሰራቱን ዋና ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል።

ለማህበረሰቡ በፍትሀዊነት የመኖሪያ እና የንግድ ቦታ በሊዝ ጨረታ በማስተላለፍና ፋላጎቶችን በሟሟላት የከተማዋን ገቢ በማሳደግ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገትን ላይ መሠረት ያደረጉ የልማት ስራዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል።


‎ቀጣይ ጨረታውን ያሸኑፉ የህብረተሰብ ክፍሎች ተለይተው የሊዝ ውል ማስፈፀምና የመሬት ርክክብ ስራ እንደሚሰራ ገልፀው ከዚህ በፊት በሊዝ ቦታ አግኝተው የተረከቡ አካላትም ፈጥነው ወደ ልማት መግባት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

‎እንዲሁም ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤቱ አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅት በማድረግና የተላለፉ ቦታዎች የመሠረተ ልማት ምቹ በማድረግና ህዝቡን በማሳተፍ በልዩ ትኩረት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

‎የከተማችን ማህበረሰብ ለልማት ለእድገት እያደረገው ያለውን ንቁ ተሳትፎ በማጠናገር ከተማዋ ውብ ማራኪ እና ለዜጎቿ ምቹ እንድትሆን በጋራ እንስራ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ  ሀገራዊ ልማትን ለማፋጠን እያከናወናቸው የሚገኙ የጥናትና ምርምር ስራዎች ይበልጥ አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበት ተገለፀ።‎ግንቦት 28/2018 (ወልቂጤ) የወልቂጤ ዩኒቨርሲ...
05/06/2026

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሀገራዊ ልማትን ለማፋጠን እያከናወናቸው የሚገኙ የጥናትና ምርምር ስራዎች ይበልጥ አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበት ተገለፀ።

ግንቦት 28/2018 (ወልቂጤ) የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሁለተኛው ዓለም አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ "በጥንካሬ በመቋቋም ወደ ዘላቂ ዕድገት ለመሻገር የሚረዱ መዋቅራዊ የለውጥ መንገዶች" በሚል መሪ ሃሳብ አካሄደ፡፡

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አብዱልሙህሲን ሀሰን እንደገለፁት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመማር ማስተማር፣ የማህበረሰብ አገልግሎት እና ችግር ፈቺ የጥናትና ምርምር ስራዎች በማከናወን አለም አቀፋዊነት ይዘት ያላቸው ተግባራት እያከናወኑ ይገኛሉ።

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በየአመቱ በሚያካሄዳቸው ኮንፈረንሶች በርካታ የጥናትና ምርምር ስራዎች የሚቀርቡ ሲሆን ኮንፈረንሱ የምርምር ስራዎች ውጤታማ ለማድረግ፣ ተመራማሪዎች ልምድ እንዲለዋወጡ ለማስቻልና በአለም አቀፍ ደረጃ የሚካሄዱ የጥናትና ምርምር ስራዎች በሀገሪቱ ከሚከናወኑ የምርምር ስራዎች ውጤት ጋር ያላቸውን ቁርኝት ለመለየት ያስችላል ብለዋል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አለም አቀፋዊ ይዘታቸውን ለማስፋፋት መሰል አለም አቀፍ ኮንፈረንሶች ሚናቸው ከፍተኛ ሲሆን የዩኒቨርሲቲው ተመራማሪዎች በጥናታቸው የሚያገኟቸው ውጤቶች ከተለያዩ የአለም ሀገራት ከተገኙ የምርምር ውጤቶች ምን ያህል ቁርኝት እንዳላቸው ለመፈተሽ እና የተሻለ የምርምር ርዕሶችን ለመምረጥ የሚያስችል ልምድ ያስገኝላቸዋል።

በዩኒቨርሲቲው የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዮሀንስ ገብሩ በኮንፈረንሱ ሁለንተናዊ ብልጽግና የሚያረጋግጡ 19 አለም አቀፍ የምርምር ውጤቶች የቀረቡ መሆናቸውን ገልፀዋል።

በምርምር ስራዎቹ ሰባት የውጭ ሀገር፣ አምስት ከተለያዩ የሀገር ውስጥ እንዲሁም ሰባት የምርምር ስራዎች በዩኒቨርሱቲው ተመራማሪዎች የተዘጋጁ የምርምር ስራዎች መቅረባቸውን አውስተዋል።
ይህ ደግሞ ወልቂጤ ዩኒቨርሱቲ አያከናወናቸው የሚገኙ ስራዎች ይበልጥ ለማስተዋወቅ እንደሚያስችል ዶ/ር ዮሀንስ ገልፀዋል።

የምርምር ስራዎቹ በግብርና፣ በማህበራዊ ሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ ያተኮሩ እንደሆነም አብራርተዋል።

ዶ/ር ፈቀደ ምኑታ፣ ዶ/ር አዲሰአለም መብራቱ እና ዶ/ር አለማየሁ ስፍር የኮንፈረንሱ ተሳታፊዎችና የምርምር ውጤቶች ካቀረቡ ተመራማሪዎች መካከል ተጠቃሾች ሲሆኑ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት ተመራማሪዎች የቀረቡ የምርምር ውጤቶች የማህበረሰቡን ችግር የሚቀርፉ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰቡን ችግር የሚፈቱ፣ ለፖሊሲ አውጪዎች ግብአት የሚሆኑና የአገርን ልማት የሚያፋጥኑ የጥናትና ምርምር ውጤቶችን ማበርከቱን ጠቅሰዋል።

በተለይ በግብርና፣ በአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ መቋቋም፣ በጤና ልማት፣ በምጣኔ ሀብት፣ በብዝሃ ሕይወት ጥበቃ፣ በሀገር በቀል እውቀቶች ማበልፀግ እና በሌሎች የምርምር መስኮች መፍትሔ አመላካችና ችግር ፈቺ የምርምር ሥራዎች ያከናወነ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው ሀገራዊ ልማትን ለማፋጠን እያከናወናቸው የሚገኙ የጥናትና ምርምር ስራዎች ይበልጥ አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበት ገልፀዋል።

ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የተሰጠ መግለጫ**********************ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ማለዳ ላይ፤ የመጀመሪያው የወገግታ ጭላንጭል ...
05/06/2026

ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የተሰጠ መግለጫ
**********************

ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ማለዳ ላይ፤ የመጀመሪያው የወገግታ ጭላንጭል በከፍታማዎቹ የኢትዮጵያ ተራሮች ላይ ፈንጥቆ ጨለማውን ሳይቀድ በፊት ኢትዮጵያውያን ረጃጅም ሰልፍ ተሰልፈዋል። በጅማ፣ በድሬዳዋ፣ በሐዋሳ፣ በባሕር ዳር እንዲሁም ስማቸው በዓለም አቀፍ የዜና ጋዜጣዎች ላይ ፈጽሞ ሊወጣ በማይችሉ ከተሞችና መንደሮች ውስጥ ያሉ ወንዶችና ሴቶች፤ ወሳኝ ተግባር ለመፈጸም በሰልፍ ቆሙ። ድምፅ ሰጡ! ይህንን ታሪካዊ ኃላፊነት ለመወጣት ከሃምሳ አራት ሚልዮን በላይ የሚሆኑ ዜጎች ተመዝግበው ነበር። ይህ ቁጥር ከአንዳንድ ሀገሮች አጠቃላይ ሕዝብ ቁጥር በላይ ነው። ይህ ምርጫ እውነተኛ ስለመሆኑ ጥያቄ ለሚያነሣ ለማንኛውም አካል ግልጽ እና የማያሻማ ምላሽ ሰጥቷል!

‎የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍላጎት
‎የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከ52,000 ምርጫ ጣቢያዎች መካከል ከ50,188 በላይ የሚሆኑት በሰዓቱ ተከፍተው ቀኑን ሙሉ መራጮችን ሲያስተናግዱ እንደነበር አረጋግጧል። ከ42 የፖለቲካ ፓርቲዎች የተወጣጡ ከ10,438 በላይ ዕጩዎች እና 80 የግል እጩዎች በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የክልል ምክር ቤት ወንበሮችን ለማሸነፍ ተወዳድረዋል። ይህ በማንኛውም ሊለካ በሚችል መሥፈርት በኢትዮጵያ ታሪክ ትልቁ እና በውሳኔ አሰጣጥም ሆነ በአስተዳደራዊ ረገድ እጅግ በረቀቀ ሁኔታ ተግባራዊ የተደረገ ዴሞክራሲያዊ ተሳትፎ የታየበት ኩነት ነበር።

የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ክቡር ኡሁሩ ኬንያታ የሚመሩትና ከ37 የአፍሪካ ሀገሮች የተወጣጡ 83 ታዛቢዎችን ያቀፈው የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን ምርጫውን “ዴሞክራሲያዊ አስተዳደርን በሰፊው በሚደግፍ ሕጋዊና ተቋማዊ ማዕቀፍ ውስጥ የተካሄደ” ሲል ገምግሞታል። በቀድሞዋ የኡጋንዳ ምክትል ፕሬዚዳንት ክብርት ዶክተር ስፔሲዮዛ ዋንዲራ ካዚብዌ የሚመራው የኢጋድ የምርጫ ታዛቢ ቡድን ባወጣው የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት፥ በታዘቡባቸው ጣቢያዎች ሁሉ የምርጫ ሳጥኖች በትክክል የታሸጉ መሆናቸውን፣ የፓርቲ ወኪሎች በሂደቱ በሙሉ መገኘታቸውን እንዲሁም ምርጫው አስደናቂ ተቋማዊ፣ አስተዳደራዊና የቴክኖሎጂ ዕድገትን ያሳየ መሆኑን አረጋግጧል። የኢጋድ የምርጫ ታዛቢ ልዑክ ይሄንን ምርጫ «የበርካታ አዳዲስ ምዕራፎች ምርጫ» ሲል ሰይሞታል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በድምፅ መስጠት ሂደት ውስጥ ምንም ዓይነት የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዳልተመለከተ አረጋግጧል። የሲቪክ ማኅበረሰብ ታዛቢዎች ጥምረት በምርጫ ቦርድ እውቅና ከተሰጣቸው 55 ድርጅቶች 65,299 የታዛቢዎችን በመላ ሀገሪቱ ያሠማራ ሲሆን፥ 99 በመቶ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ያለምንም ዕንቅፋት የመታዘብ ዕድል ማግኘቱን አረጋግጧል። እነዚህ ተዓማኒነት ያላቸው ሀገራዊ እና አኅጉራዊ ተቋማት ያደረጓቸው ግምገማዎችና የሰጧቸው እውነተኛ ፍርዶች ናቸው። እነዚህ ለአፍሪካ ጥላቻ ካላቸው ወይም የአፍሪካን ዴሞክራሲ በውጫዊ መሥፈርቶች ከሚለኩ ተቋማት የተደመጡ ድምፆች አይደሉም።

‎አንዳንድ ዓለም አቀፍ ተንታኞች ይሄንን ምርጫ እንደ ንግሥና በዓል አድርገው ያቆሸሹት ሲሆን ውጤቱም አስቀድሞ የተወሰነ ድራማ እንደነበር አድርገው ሊያቀርቡት ሞክረዋል። እነዚህን መግለጫዎች ከእውነታው ፈጽሞ የራቁ፣ በጥናትና ትንተና ላይ ያልተመሰረቱ እንዲሁም ነፃና የታሰበበት ዴሞክራሲያዊ ምርጫቸውን በኩራት ላደረጉ በሚልዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ክብር የማይሰጡ በመሆናቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሙሉ በሙሉ የማይቀበላቸው መሆኑን ያረጋግጣል። አስቀድሞ የተወሰነ ውጤት ቢኖር ኖሮ፤ ከ37 የአፍሪካ ሀገሮች የተወጣጡ 83 ገለልተኛ ታዛቢዎችን፣ 65,299 የሀገር ውስጥ የሲቪል ማኅበረሰብ ታዛቢዎችን ወይም 1,100 ዕውቅና የተሰጣቸውን ዓለም አቀፍ ጋዜጠኞች መጋበዝ ባላስፈለገ ነበር።

‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዚህ ሀገራዊ ምርጫ ለተሳተፉ የኢትዮጵያ ዜጎች፣ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና ላሠማራቸው ከ350,000 በላይ ኃላፊዎች፣ ሂደቱን ለጠበቁት የጸጥታ ኃይሎች እንዲሁም ኢትዮጵያ ለዴሞክራሲ ግንባታ መጎልበት እና ለሂደቱ መሳካት ያላትን ቁርጠኝነት ላረጋገጡት የአፍሪካ እና ቀጣናዊ የታዛቢ ቡድኖች ምስጋናቸውን ያቀርባሉ!

‎ስለ ኢትዮጵያ ልማት
‎ኢትዮጵያውያን ግንቦት 24 2018 ዓ.ም ውሳኔያቸውን ሲያስቀምጡ፣ ሀገራቸውን በፍጹም የዴሞክራሲ ባህል ውስጥ ለማንበር ነው። በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ባላት ጸጋ ልክ የሚያስፈልጋትን ሁለንተናዊ ልማት በፍጥነት እውን የማድረግ ባህል እንዲቀጥል ሕዝባችን ተናግሯል።

‎ባለፉት ዓመታት የታየው እውነት እንደሚያሳየን የኢፌዴሪ መንግሥት የተስፋ ቃል መንግሥት አልነበረም። ይልቁንም በተጨባጭ የሚታዩ ውጤቶች የተመዘገቡበት ውጤት ተኮር መንግሥት ሲሆን፤ እነዚህም ውጤቶች በግልጽ የሚታዩ ናቸው። የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ2017 በጀት ዓመት የ9.2 በመቶ ዕድገት ያስመዘገበ ሲሆን፥ ይሄም በዓለም ላይ ፈጣን ዕድገት ካስመዘገቡ ኢኮኖሚዎች አንዱ ያደርገዋል። ይሄንን መነቃቃት መሠረት በማድረግ በ2018 በጀት ዓመት የኢኮኖሚ ዕድገቱ 10.2 በመቶ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል። ዕድገቱ ግብርናን፣ ኢንዱስትሪንና የአገልግሎት ዘርፎችን በከፍተኛ ደረጃ ያካተተ ሰፊ መሠረት ያለው ቢሆንም፥ ከጊዜ ወደ ጊዜ ግን ኢንዱስትሪው ለዕድገቱ ዋነኛ አንቀሳቃሽ ኃይል ሆኖ እየመጣ ይገኛል። ይሄም መንግሥት ለማኑፋክቸሪንግ፣ ለኢንዱስትሪ ልማት፣ ለዕሴት ጭማሪና ለውጭ ገበያ ተኮር ምርቶች የሰጠውን ቀጣይነት ያለው ትኩረት ያሳያል።

‎እነዚህ ውጤቶች እንዲሁ ግምቶች ብቻ ሳይሆኑ፥ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የ100 ቀናት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ሥርዓት አማካኝነት ክትትል የሚደረግባቸው የተጠያቂነትና የታቀደ አመራር ፍሬዎች ናቸው። አጠቃላይ የወጪ ንግድ ገቢ 20 ቢልዮን የአሜሪካ ዶላር ይደርሳል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፥ ይህም ከ2016 ዓ.ም. ወዲህ የ100 በመቶ ገደማ ጭማሪ አሳይቷል። የዋጋ ግሽበትም ወደ ታች ማሽቆልቆሉን በመቀጠል አሁን ላይ ወደ አንድ አሐዝ ደረጃ እየተቃረበ ይገኛል፤ ይሄም በቅርብ ዓመታት ውስጥ በቤተሰቦችና በንግዶች ላይ ከባድ ጫና ፈጥሮ ከነበረው ባለ ሁለት አሐዝ የዋጋ ግሽበት አንጻር ትልቅ መሻሻል ነው። ይህ ስኬት የተመዘገበው ዓለም አቀፍ የኃይል አቅርቦትና ሌሎች ስትራቴጂካዊ ቁሳቁሶችን ገበያ ያናጋው የመካከለኛው ምስራቅ ወቅታዊ ጂኦፖለቲካዊ ውጥረት ጨምሮ፣ ውጫዊ ጫናዎች በነበሩበት ወቅት ነው።
‎የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ከተጀመረ ወዲህ መንግሥት ከውጭ ምንጮች ምንም ዓይነት አዲስ የንግድ ብድር ስምምነት ያላደረገ ሲሆን፥ ይሄም የሀገሪቱን የብድር ዕዳ ጫና በከፍተኛ ሁኔታ አቅልሎታል። ከእነዚህ ቁጥሮች በስተጀርባ ኢትዮጵያውያን በዓይናቸው የሚያዩትና በእጃቸው የሚዳስሱት ተጨባጭ ለውጥ አለ። ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለመኖሪያ ቤቶች፣ ለንግድ ተቋማትና ለጎረቤት ሀገራት የኤሌክትሪክ ኃይል እያመነጨ ይገኛል። ይህ ግድብ በራሳቸው በኢትዮጵያውያን የተደገፈ፣ በኢትዮጵያውያን መሐንዲሶች የተገነባና ቀጣይነት የነበረውን ውጫዊ ጫናዎችን ተቋቁሞ የተጠናቀቀ ነው። ከሃይድሮ ፓወር ጎን ለጎን፥ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የሚገኘውን የአይሻ ሁለት የንፋስ ኃይል ማመንጫ እና በአርሲ ዞን የሚገኘውን የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች፤ በመሳሰሉ ሥራዎች የታዳሽ ኃይል አቅርቦቷን እያሰፋች ሲሆን፥ ይህም የቀጣናዊ ኢነርጂ ትብብርን እያሳደገ የብሔራዊ ኃይል አቅርቦት መረቡን የመቋቋም ዐቅም ያጠናክራል። በአፍሪካ አህጉር ታሪክ ውስጥ ትልቁ የመሠረተ ልማት ኢንቨስትመንት አንዱ የሆነው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት የመሠረት ድንጋይ ተጥሎ ግንባታው ተጀምሯል። እነዚህ ምኞቶች አይደሉም፤ ተጨባጭ ሐቆች ናቸው።

‎ግብርና፣ አምራች ኢንደስትሪና ቴክኖሎጂ
‎በግብርናው ዘርፍ፣ የመንግሥት የምግብ ሉዓላዊነት አጀንዳ ወቅታዊ ለውጦችን ሳይሆን መዋቅራዊ ውጤቶችን እያስገኘ ቀጥሏል። በሶማሌ ክልል የጎዴ ዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካን ለመገንባት ከአሊኮ ዳንጎቴ ግሩፕ ጋር የተፈረመው አጋርነት የዘመኑ ጉልህ የኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንቶች አንዱ ማረጋገጫ ነው። ፋብሪካው በዓመት 3 ሚልዮን ሜትሪክ ቶን ዩሪያ የማምረት አቅም እንዲኖረው ታቅዶ እየተገነባ ሲሆን፥ ይሄም ኢትዮጵያን በዓለም ትላልቅ ማዳበሪያ አምራች ሀገራት ተርታ ያሰልፋታል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግንቦት 9 ቀን 2018 ዓ.ም. የፕሮጀክቱን የግንባታ ሂደት በጎበኙበት ወቅት እንደገለጹት፤ “ይህ ፕሮጀክት በግብርና ትራንስፎርሜሽን፣ በምግብ ዋስትና፣ በኢንዱስትሪ ዕድገትና በኢኮኖሚ ራስን መቻል ላይ የተደረገ ስትራቴጂካዊ ኢንቨስትመንት ነው” ብለዋል። አስተማማኝ ባልሆነና ውድ በሆነ የማዳበሪያ አቅርቦት ለረጅም ጊዜ ለተገደቡት ኢትዮጵያውያን አምራቾች የዚህ ፕሮጀክት ፋይዳ ፈጣንና ተጨባጭ ነው።

ከዚህ ምርጫ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግንቦት 19 ቀን 2018 ዓ.ም. በነገሌ ቦረና ገዳ አውሮፕላን ማረፊያ ምርቃት ላይ ሲገኙ የታየው ተምሳሌትነት ለቦረና ሕዝብ ትልቅ ትርጉም ነበረው። ይህ ዞን በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቅበት ስም የሀገርን አንገት ያስደፋ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታ ሲሆን፤ እርሱም ድርቅ ነው። ለሦስት ተከታታይ ዓመታት የዝናብ መጥፋት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ከብቶችን የገደለ፣ ቤተሰቦች ለውኃ ፍለጋ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮችን እንዲጓዙ ያስገደደ፣ እንዲሁም በእነዚህ የግጦሽ መሬቶች ላይ ለዘመናት ራሳቸውን ችለው የኖሩ ማኅበረሰቦችን ለአስቸኳይ የምግብ እርዳታ እጅ እንዲዘረጉ አድርጎ ነበር። ዓለም የሚያውቃት ቦረና እርሷ ነበረች። የጠቅላይ ሚኒስትሩ የግንቦት ወር ጉብኝት ግን የተለየ ታሪክ አሳይቷል። አሁን ላይ ለአርብቶ አደር ማኅበረሰቦችና ለከብቶቻቸው ንጹሕ ውኃ እያቀረቡ ያሉትን የውኃና የመስኖ መሠረተ ልማቶችን የገመገሙ ሲሆን፥ ከጥቂት ዓመታት በፊት አቧራ ብቻ በነበረው መሬት ላይ የክላስተር እርሻዎችን ጎብኝተዋል፤ በያቤሎ የባህል ማዕከል መርቀዋል፤ እንዲሁም በአየር ንብረት ሁኔታዎች ምክንያት ቀድሞ ተገልሎ ለነበረው ቀጣና ዓመቱን ሙሉ ትስስር የሚፈጥር አውሮፕላን ማረፊያ መርቀው ከፍተዋል።

‎የአምራች ዘርፉም ተመሳሳይ የለውጥ ታሪክ አለው። በግንቦት 2018 ዓ.ም. በተካሄደው 4ኛው ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ላይ፤ መንግሥት ለአራት ዓመታት የተመዘገበውን ቀጣይነት ያለው የኢንዱስትሪ መስፋፋት ውጤቶች አቅርቧል። የአምራች ዘርፉ የግብአት አቅርቦት በዓመት 9 ሚልዮን ቶን ወደ 15 ሚልዮን ቶን አድጓል። የምርት አቅም አጠቃቀም ከ47 በመቶ ወደ 67 በመቶ ከፍ ማለቱን፣ የማኑፋክቸሪንግ ዕድገት ከ4.8 በመቶ ወደ 10.7 በመቶ ማደጉን፣ እንዲሁም ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሚቀርበው ፋይናንስ ከ8.1 ቢልዮን ብር ወደ 50 ቢሊዮን ብር ማደጉን ያሳያል። እነዚህ ስኬቶች በሀገር ውስጥ ምርት ላይ በከፍተኛ ሁኔታ እየተንጸባረቁ ይገኛሉ። ኤክስፖው በተጠናቀቀ በሃያ ቀናት ውስጥ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዘጠኝ ወራት ውስጥ ብቻ ተጠናቆ ከ80 በመቶ በላይ ጥሬ ዕቃውን ከሀገር ውስጥ የሚያገኘውን ግዙፍ የኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንት «ግራንዲዩር የሴራሚክ ማኑፋክቸሪንግ» ፋብሪካን በሞጆ ከተማ መርቀዋል። ቀደም ሲል በገቢ የሴራሚክ ምርቶች ላይ ጥገኛ የነበረችው ኢትዮጵያ አሁን ላይ የሴራሚክ ምርቶችን ከውጭ ማስገባት ሙሉ በሙሉ ለማቆምና ለውጭ ገበያ የሚሆን ምርት ለማስፋፋት እየተዘጋጀች ትገኛለች።

‎በቴክኖሎጂው ዘርፍም፥ ዘመናዊ ልማት ከጊዜ ወደ ጊዜ በዳታ፣ በፈጠራና በዲጂታል ሥርዓቶች የሚወሰን መሆኑን በመገንዘብ፥ መንግሥት ኢትዮጵያን ሰው ሠራሽ አስተውሎት እና የኢንዱስትሪ 5.0 ማሕቀፎችን ቀድመው ከተገበሩ ሀገራት ተርታ እያሰለፋት ይገኛል።

‎የጽንፈኝነትን ፖለቲካ ውድቅ ማድረግ
‎በኦነግ ሸኔ ዐማጽያን በንጹሐን ዜጎች ላይ በተለይም በሃይማኖት ተቋማት ውስጥ ዒላማ ተደርገው የተፈጸሙ ጥቃቶችን ተከትሎ፤ የቤተሰብ እና የወዳጆቻቸውን ሕይወት ላጡ፣ የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው እና የቤት ንብረታቸው ለወደመባቸው በአርሲ ዞን ለሚገኙ ወገኖቻችን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ መንግሥት ስም የተሰማቸውን ጥልቅ ኀዘን ይገልጻሉ።

እነዚህ ጥቃቶች የሀገሪቱን ብሔራዊ ዕድገት ለማደናቀፍ ከሚሹ አካላት፣ በአማራ ክልል ከሚንቀሳቀሱ የሀገር ውስጥ አማፂ ቡድኖች እና ለሀገሪቱ ሁለንተናዊ ዕድገት ጥላቻ ካላቸው የውጭ ኃይሎች ጋር በጥምረት የተከናወኑ ሲሆኑ፤ ዓላማቸውም በኢትዮጵያ አለመረጋጋትንና የምርጫ መስተጓጎልን ለመፍጠር ሲደረግ የነበረ የጥፋት ውጥን ተከታይ ነው። መንግሥት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ያለ አንዳች የፀጥታ ችግር ፍትሐዊና አሳታፊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ከአንድ ዓመት በላይ የዘለቀ ልዩ ትኩረትና ዝግጅት በማድረግ በቁርጠኝነት ሲሠራ ቆይቷል። በሌላ በኩል የጥፋት ኃይሎች ከባዕዳን ጋር 'ፅምዶ' የሚል ቁርኝት በመፍጠር ዕኩይ ዓላማቸውን ለማሳካት ሰፊ የጥፋት ዝግጅት ሲያድርጉ ቆይተዋል፣ ሀገራዊ ምርጫው እንዳይከናወን ሰፊ ርብርብ አድርገዋል። በተጨባጭም በቅድመ ምርጫ እና በምርጫ ወቅት የዜጎችን የመምረጥ መብትና ነጻነት ለመጋፋትና ለማደናቀፍ አለን የሚሉትን የጥፋት እጅ ዘርግተዋል።
‎እነዚህ የጠላት ኃይሎች በመደጋገፍና በመናበብ ዐመፅና ሁከት ለማነሳሳት፣ ከተሞችን በሽብር ጥቃት ለማወክ፣ በመንገዶች የደፈጣ ጥቃት በመፈጸም እንቅስቃሴ ለመገደብ እና በተወሰኑ አካባቢዎች ዒላማ አድርገው ነጥሎ ለማጥቃት ተንቀሳቅሰዋል። እንደ ማሳያ የጦር መሣሪያ፣ ተተኳሾችንና ሌሎች ሎጀስቲክሶችን በድጋፍ በማቅረብ በደቡባዊ ትግራይ በሚገኙ አዋሳኝ የአማራ ክልል አንዳንድ ቦታዎች ላይ ትንኮሳ ፈጽመዋል፣ በአማራ ክልል ባሕር ዳር፣ ጎንደር፣ ደብረ ብርሃን እና ወልድያ ከተሞችን ጨምሮ በክልሉ ዋና ዋና ከተሞች እና ሲቪሎች ላይ ዒላማ በማድረግ ያካሄደው የሽብር እንቅስቃሴና ዝግጅት፣ በአዲስ አበባ ከተማ ባደራጃቸው የኅቡዕ ሴሎች አማካኝነት በተመረጡ አከባቢዎች ላይ ጥቃት እንዲፈጸም ተንቀሳቅሰው የነበረ ቢሆንም ይሄን የጥፋት ሴራ እና ድርጊት እንዲከሽፍ ማድረግ ተችሏል።

‎በተመሳሳይ በኦሮሚያ ክልል የሸኔ ሽብር ቡድን ከጽንፈኛው ፋኖ ታጣቂ ቡድን ጋር በመናበብ በአንዳንድ አካባቢዎች መንገዶችን በመዝጋት እንቅስቃሴ ለማስቆምና ለማስተጓጎል ፍላጎት የተንቀሳቀሰ ቢሆንም በጸጥታ ኃይሉ በተወሰደበት የተጠናከረ እርምጃ ፍላጎቱን ማሳካት አልቻለም። ቡድኑ በፀጥታ ኃይሉ የተወሰደበትን ርምጃ መቋቋም ባለመቻሉ እና ፍላጎቱን ማሳካት ባለመቻሉ ስስ ዒላማዎች ላይ ያተኮረ ርምጃ በመውሰድ የሃይማኖት እና የብሔር ግጭት ለመቀስቀስ በማለም በአርሲ ዞን አሰኮ እና አካባቢው ጥቃት በመፈጸም ሁሉን አይነት የጥፋት ርብርብ ያደረገ ቢሆንም ሁኔታውን በመቆጣጠር ፀጥታ ኃይላችን በእነዚህ ኃይሎች ላይ የተቀናጀ ርምጃ እየወሰደ ይገኛል።

መንግሥት መሰል ሥጋቶችን በንቃት በመከታተል ላይ ሲሆን፣ በምርጫው ወቅትም በብዙ የሀገሪቱ አካባቢዎች የተቀነባበሩ ተመሳሳይ ዕቅዶችን በስኬት ማክሸፍ ችሏል። በንጹሐን ዜጎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን፤ ፍርሃትና ክፍፍልን ከሚያጎሉ የሚዲያ ዘመቻዎች ጋር በማስተሣሠር የተቀነባበረው ይህ እኩይ ተግባር፤ በመንግሥት የደኅንነት መዋቅርና ኦፕሬሽኖች አማካኝነት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲስተጓጎል ተደርጓል። ብሔራዊ እና ሃይማኖታዊ ክፍፍልን ለመዝራት የኃይል ጥቃትን እና ውድመትን እንደ መሣሪያ የሚጠቀሙ አካላት በሁሉም ኢትዮጵያውያን ዘንድ በግልጽ ሊወገዙ ይገባል። መሰል ተግባሮች በኢትዮጵያ ውስጥ ምንም ዓይነት የወደፊት ዕድል እንደሌላቸው ለማሳየት የተቀናጀ ብሔራዊ ምላሽ በመስጠት ወሳኝ ርምጃዎችን ይቀጥላል።

‎በንጹሐን ዜጎች ላይ ጥቃት የሚፈጽሙ አካላት፣ ድርጊታቸውን ምክንያታዊ ለማስመሰል ምንም ዓይነት የፖለቲካ ንግግር ቢጠቀሙ፤ ወሳኝ ዓላማን እያሳኩ ሳይሆን ወንጀል እየፈጸሙ ነው። የፖለቲካ ቅሬታዎች በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት፣ በብሔራዊ ምክክር ሂደት እና በዴሞክራሲያዊ ተቋማት አማካኝነት መፍትሔ ሊያገኙ የሚችሉ እና ሊያገኙ የሚገባቸው ናቸው።

‎ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም!

በዞኑ በቀጣይ በሚሰጠው የ8ኛና የ12ኛ ክፍል ክልልና ሀገር አቀፍ ፈተና የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ሁሉም ተማሪዎች ሳይዘናጉ በቂ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ተሸላሚ ተማሪዎች መከሩ። ግንቦት ...
05/06/2026

በዞኑ በቀጣይ በሚሰጠው የ8ኛና የ12ኛ ክፍል ክልልና ሀገር አቀፍ ፈተና የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ሁሉም ተማሪዎች ሳይዘናጉ በቂ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ተሸላሚ ተማሪዎች መከሩ።

ግንቦት 28/2018ዓ.ም(ወልቂጤ) የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ የ2018 ዓ.ም ዞን አቀፍ የ8ኛና የ12ኛ ክፍል አመታዊ የአሸናፊዎች አሸናፊ የጥያቄና መልስ ውድድር በወልቂጤ ከተማ አካሂዷል።

በዞን አቀፍ የ8ኛና የ12ኛ ክፍል አመታዊ የአሸናፊዎች አሸናፊ የጥያቄና መልስ ውድድር ላይ አንደኛ በመሆን ካጠናቀቁ ተሸላሚ ከሆኑ ተማሪዎች መካከል ተማሪ ብሩክ ሰንብት ከጉንችሬ፣ ተማሪ የሺወርቅ አበበ ከወልቂጤና ተማሪ ሪሃና ሹሜ ከእምድብር ከተማ ይገኙበታል።

ተማሪዎቹ በጋራ በሰጡት አስተያየት በዞን አቀፍ የአሸናፊዎች አሸናፊ የጥያቄና መልስ ውድድር ላይ ከአጠቃላይ ተማሪዎች የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ ተሸላሚ በመሆናቸው ደስታ እንደተሰማቸው አንስተዋል።

ለዚህ ውድድር አሸናፊ የመሆናቸው ሚስጥር ከመምህራኖቻቸው በቅርበት በመሆን የሚሰጣቸው ትምህርት በተገቢው ከመከታተል ባለፈ በራሳቸው ጥረት በቂ ዝግጅት እያደረጉ በመሆናቸው ስለመሆኑንም ገልጸዋል።

ከዚህም ባሻገር ፕሮግራም በማውጣት ጊዜያቸውን በአግባቡ እንደሚያነቡ አንስተው ከዚህም ባለፈ ለትምህርታቸው አጋዥ የሆኑ ቪዲዮዎችን በማየትና ወርክ ሺቶችን እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

ጎበዝ የመሆናቸው ሚስጥር ተማሪዎች የሚሰጣቸው መደበኛና የድጋፍ ትምህርት በተገቢው ከመከታተል ባሻገር በራሳቸው የተለያዩ ጥረቶችን እንደሚያደርጉም አውስተዋል።

ቀጣይ የ8ኛና 12ኛ ክፍል ክልልና ሀገር አቀፍ ፈተናዎች መቃረቡን ተከትሎ ከሌሎች ተማሪዎች ለመወዳደርና የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በቂ ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን ያነሱት ተማሪዎቹ ሌሎችም ተማሪዎች ሳይዘናጉ ለትምህርታቸው ትኩረት በመስጠት በቀሪ ጊዜያት ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉም መክረዋል።
የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ነው

በተካሄደው የ2018 ዓ.ም ዞን አቀፍ የ8ኛና የ12ኛ ክፍል አመታዊ የአሸናፊዎች አሸናፊ የጥያቄና መልስ ውድድር. አጠቃላይ ውጤት ከከተማ አስተዳደሮች ወልቂጤና ከወረዳዎች ምሁር አክሊል ወረዳ...
05/06/2026

በተካሄደው የ2018 ዓ.ም ዞን አቀፍ የ8ኛና የ12ኛ ክፍል አመታዊ የአሸናፊዎች አሸናፊ የጥያቄና መልስ ውድድር. አጠቃላይ ውጤት ከከተማ አስተዳደሮች ወልቂጤና ከወረዳዎች ምሁር አክሊል ወረዳ አሸናፊ ሆኑ።

ግንቦት 28/2018ዓ.ም(ወልቂጤ) የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ የ2018 ዓ.ም ዞን አቀፍ የ8ኛና የ12ኛ ክፍል አመታዊ የአሸናፊዎች አሸናፊ የጥያቄና መልስ ውድድር በወልቂጤ ከተማ አካሂዷል።

በተካሄደው የ2018 ዓ.ም ዞን አቀፍ የ8ኛና የ12ኛ ክፍል አመታዊ የአሸናፊዎች አሸናፊ የጥያቄና መልስ ውድድር. አጠቃላይ ውጤት ከከተማ አስተዳደር ወልቂጤና ከወረዳዎች ምሁር አክሊል ወረዳ አሸናፊ ሲሆኑ

ከከተማ አስተዳደሮች ጉንችሬ 2ኛ ደረጃ ሲወጣ ከወረዳዎች ደግሞ ጌታ 2ኛና አበሽጌ 3ኛ ደረጃ በመውጣት እውቅናና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ከተማሪዎች ጠቅላላ ውጤት
ከ8ኛ ክፍል 1ኛ, ተማሪ ሪሃና ሹሜ ከእምድብር ከተማ፣ 2ኛ ተማሪ መካሪ አ/ኸኒን ከወልቂጤና 3ኛ, ተማሪ ሳሙኤል ጠንክር ከምሁር አክሊል ወረዳ አሸናፊ ሲሆኑ

ከ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ 1ኛ, ተማሪ የሺወርቅ አበበ ከወልቂጤ ከተማ፣ ተማሪ ማትዮስ ጦርበዛ ከጉንችሬ ከተማና 3ኛ, ተማሪ ታረቀኝ መንጂየ ከአገና ከተማ እንዲሁም

ከ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ ብሩክ ሰንብት ከጉንችሬ ከተማ፣ 2ኛ, ተማሪ ያሬድ ሰክቱ ከቸሃ ወረዳና ተማሪ ቃልኪዳን ገ/ጻዲቅ ከእንደጋኝ ወረዳ አሸናፊ በመሆን የሰርተፊኬትና የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

የጥያቄና መልስ ውድድሩ በተማሪዎች መካከል ከፍተኛ ትንቅንቅ የታየበት እንደነበር ተገልጿል።
የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ነው

የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ የ2018 ዓ.ም ዞን አቀፍ የ8ኛና የ12ኛ ክፍል አመታዊ የአሸናፊዎች አሸናፊ የጥያቄና መልስ ውድድር በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።ግንቦት 28/2018ዓ.ም...
05/06/2026

የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ የ2018 ዓ.ም ዞን አቀፍ የ8ኛና የ12ኛ ክፍል አመታዊ የአሸናፊዎች አሸናፊ የጥያቄና መልስ ውድድር በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

ግንቦት 28/2018ዓ.ም(ወልቂጤ)

የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ መብራቴ ወልደማርያም በመክፈቻ ንግግራቸው እንዳሉት የጥያቄና መልስ ውድድሩ አላማ ጎበዝ ተማሪዎች በየአመቱ ለእውቀትና ፈተና ከሚዘጋጁት ዝግጅት ባሻገር በዞን አቀፍ የጥያቄና መልስ ውድድር መሳተፍና ማሸነፍ አለብኝ የሚል ቁጭት እንዲያድርባቸው ለማድረግ ያለመ ነው።

ከዚህም ባለፈ በመንግስት ትምህርት ቤቶች በተማሪዎችና በመዋቅሮች መካከል ጤናማ የፉክክር መንፈስ እንዲኖር በማድረግ በቀጣይ ተወዳዳሪ ተማሪዎች ለመፍጠር መሆኑን ገልጸዋል።

ይህ የጥያቄና መልስ ውድድሩ ከትምህርት ቤት ጀምሮ በየደረጃው በክላስተር፣ በወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ሲካሄድ መቆየቱንም አቶ መብራቴ ተናግረዋል።

በዚህም የጥያቃና መልስ ውድድር ከሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደሮች የአሸናፊዎች አሸናፊ የጥያቄና መልስ ውድድር ላይ የተሻለ ውጤትና አቅም ያላቸው ተማሪዎች መሳተፋቸውም ገልጸዋል።

በጥያቄና መልስ ውድድሩ የዞኑ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ መብራቴ ወልደማርያም፣ የየወረዳና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽህፈት ቤት የትምህርት ቤት መሻሻል ሱፐርቪዥን ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪዎች፣ የመምሪያው የማኔጅመንት አካላትና ከሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደር የተወጣጡ የ8ኛና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ተገኝተዋል።

በወልቂጤ ከተማ በኢኒሼቲቭ ፕሮግራም የተከናወኑ የልማት ሥራዎች በኢኮኖሚያዊና በማህበራዊ ዘርፎች ጉልህና ተጨባጭ ውጤቶችን ተመዝግበዋል ሲል የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ገለፀ።‎‎ግንቦት 28/2...
05/06/2026

በወልቂጤ ከተማ በኢኒሼቲቭ ፕሮግራም የተከናወኑ የልማት ሥራዎች በኢኮኖሚያዊና በማህበራዊ ዘርፎች ጉልህና ተጨባጭ ውጤቶችን ተመዝግበዋል ሲል የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ገለፀ።

‎ግንቦት 28/2018ዓ.ም [ወልቂጤ ]

‎የለውጡ መንግስት ለከተሞች እድገትና ለውጥ በሰጠዉ ልዩ ትኩረት በወልቂጤ ከተማ የኢኒሼቲቭ ፕሮግራሙ ኮሪደር ልማት፣ የከተማ ጽዳትና ውበት፣ የሥራ እድል ፈጠራ፣ የአረንጓዴ አሻራ ሥራዎች ፣የኑሮ ውድነት ከማረጋጋት አንፃር ሊጠቀሱ የሚችሉ ውጤቶች ተመዝግቧል ።

‎የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር እንደገለፁት የለውጡ ትሩፋቶች በተገቢው በመጠቀም ከዚህ በፊት በነበረው የልማት ቁጭት በፍጥነት ህዝባችንን አሳትፈን ወደ ተግባር ገብተናል።

‎የኮሪደር ልማት ስራዎች ስናስጀም በፍጥነት ወሰን የማስከበር ስራ በመስራት እና የገፅታ ግንባታ ስራ ልዩ ትኩረት ሰጥተን ሰርተናል።

‎በዋናው አስፓልት አካባቢ ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን በመልሶ ማልማትና የገፅታ ግንባታ ተግባራት አቅም ያላቸው በፍጥነት በተቀመጠው ስታንዳርድ ግንባታ እንዲፈፅሙ በማድረግ አቅም የሌላቸው በመንግሥት ቁጠባ ቤት የሚኖሩትን ደግሞ በአክሲዮን በማደራጀት ሙያዊ ድጋፍ በማድረግ ልማቱን በማፋጠን ወደ ስራ ገብተዋል።

‎የከተማው ማህበረሰብ ለልማት ያለውን ድጋፍ በከፍተኛ ሁኔታ ያሳየበት እንደነበረም ከንቲባው ጠቁመዋል።

‎በመጀመሪያው ዙር የኮሪደር ስራ 7.6 ኪሎ ሜትር በሁለቱ ክፍለከተማ መጠናቀቁን ገልፀው በህዝብና በመንግሥት ቅንጅት ተግባራዊ ሆኗል።

‎የስራ ባህላችንን ከፍ በማድረግ በከተማችን ለሚገኙ ከ700 በላይ የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን በኮሪደሩ ልማት ስራ ምክንያት የስራ እድል እንደተፈጠረላቸው አንስተዋል።

‎የሁለተኛው ዙር 6.8 ኪሎሜትር የኮሪደር ልማት ስራ በ218 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ስራው መጀመሩንም ተናግረዋል።

‎እንዲሁም በከተማችን ከተሰሩ የኢኒሼቲቭ ፕሮግራም ስራዎች ፅዱ ከተማ የኢትዮጵያ ኢኒሼቲቭ ደረጃውን የጠበቀ መፀዳጃ ቤት ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል ።

‎የአንድ ከተማ አንድ ፕሮጀክት የማህበረሰብ ፋርማሲ ቤት ግንባታ ተጠናቆ ከ4.2 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የመድኃኒት ግዢ በማድረግ አገልግሎት እየሰጠ ነው ሲሉ ከንቲባው ተናግረዋል።

‎የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት ደረጃውን የጠበቀ የገበያ ማዕከል ግንባታ ከ20ሚሊዮን ብር ወጪ እየተገነባ ነው ያሉት ከንቲባው ከሰንበት እስከ ሰንበት ገበያዎች ምርቶች በስፋት በማስገባህ ማህበረሰቡ ተጠቃሚ ለማድረግ ስራዎች በትኩረት የተሰሩ ይገኛል ብለዋል።

‎ትምህርት የሁሉም ነገር መሰረት በመሆኑ ትውልድ ላይ የሚሰሩ ስራዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉ ሲሆን አራት የመማሪያ ክፍል ግንባታ በጉብሬ ክፍለከተማ በአንድ ትምህርት ቤት እያስገነባን ነው ብለዋል።

‎እንዲሁም ኢኒሼቲቭ ፕሮግራም አንዱ የሆነውን የአንድ ማዕከል የመሶብ አገልግሎት ግንባታ በከተማችን እየተገነባ ሲሆን በአጭር ጊዜ ተመርቆ አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑንም ገልፀዋል።

‎ማዕከሉ ሲጠናቀቅ በቴክኖሎጂ በማስተሳሰር ግልፅ ጥራት ያለው አገልግሎት ለማህበረሰቡ በመስጠት ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል።



የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢንሼቲቭ ከሆኑት ግቦች መካከል ውስጥ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት አፈጻጸም የሚገኝበት ደረጃ ተገመገመ።‎‎  ...
04/06/2026

የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢንሼቲቭ ከሆኑት ግቦች መካከል ውስጥ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት አፈጻጸም የሚገኝበት ደረጃ ተገመገመ።

‎ ግንቦት 27/2018 ዓም (ወልቂጤ)

‎በመድረኩ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የፐፕሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ አስቴር ይርዳውና ሌሎች የዞን የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢንሼቲቭ ከሆኑት ግቦች መካከል የመሶብ አንድ ማእከል አገልግሎት አፈጻጸም የሚገኝበት ደረጃ ዛሬ በጉራጌ ዞን በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር መገምገሙ ተገለፀ።

‎የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር እንዳሉት የወልቂጤ ከተማ አንድ ማዕከል አገልግሎት ቀሪ ስራው ሲጠናቀቅ የሚኖረው ፋይዳ ከግምት ውስጥ በማስገባት የማዕከሉ ቀሪው ስራ በቀሪ ቀናት እንዲጠናቀቅ የከተማ አስተዳደሩ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

ማእከሉ በአጭር ጊዜ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችም ላይ አቅጣጫም አስቀምጠዋል።

‎ክቡር ከንቲባው አክለውም መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢኒሼቲቭ እንደሆነ እና በ2030 ዲጂታል ኢትዮጵያ እውን ከሚያደርጉ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ እንደሆነ ተጠቁመዋል ።

‎የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወልቂጤ ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ግንባታ እንደ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልልና በሌሎች ከተሞችም ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት በሆነው ልክ ባጭር ጊዜ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምርም አመላክተዋል ።

‎የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ እንዲሁም የተቋማዊ ለውጥና የአቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ አስቴር ይርዳው እንዳሉት ግንባታው ጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝና ቀሪው ስራ እንዲጠናቀቅ በልዩ ትኩረት ክትትል እየተደረገ እንደሚገኝም ጠቁመው፦

‎መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት የሚያስችል ቴክኖሎጂ እንደሆነም አመላክተዋል።

‎ወ/ሮ አስቴር ይርዳው አያይዘውም የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ተጠናቆ ስራ ሲጀምር በከተማው ቀደም ሲል አገልግሎት አሰጣጥ ሂደት የሚነሱ የመልካም አስተዳድር ችግሮችን በመቅረፍ ቀልጣፋ እና የዲጂታል አገልግሎት መስጠት እንደሚያስችልም ጠቁመዋል፡፡

የኢኮኖሚ ነጻነትና ብሔራዊ ሕልውና፤ የኢትዮጵያ ቀጥተኛ የባሕር በር ፍላጎት ስልታዊ አስፈላጊነትየአፍሪካ ቀንድ እና የቀይ ባሕር ቀጣና የኃያላን ሀገራት የጂኦ-ፖለቲካ ፍላጎት ማረፊያ በሆነበት...
04/06/2026

የኢኮኖሚ ነጻነትና ብሔራዊ ሕልውና፤ የኢትዮጵያ ቀጥተኛ የባሕር በር ፍላጎት ስልታዊ አስፈላጊነት

የአፍሪካ ቀንድ እና የቀይ ባሕር ቀጣና የኃያላን ሀገራት የጂኦ-ፖለቲካ ፍላጎት ማረፊያ በሆነበት በዚህ ወቅት፣ የኢትዮጵያ ቀጥተኛ የባሕር በር የማግኘት ፍላጎት ከሀገር ሕልውና እና ከኢኮኖሚ ነጻነት ጋር በቀጥታ የተያያዘ ታሪካዊ ጥያቄ ነው።

ከ130 ሚሊዮን በላይ የሕዝብ ቁጥር ያላት ሀገራችን፣ የወጪና ገቢ ንግዷ በአንድ የወደብ አማራጭ ላይ ብቻ ጥገኛ መሆኑ የሚያሳድርባትን ከፍተኛ የኢኮኖሚ እና የደኅንነት ሥጋት ለመቀነስ የባሕር በር ማግኘት የግድ የሚላት ሰዓት ላይ ነች።

ለአንድ ወደብ የሚከፈለው ከፍተኛ የኪራይ ወጪ የሀገራችንን ምርቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነት የሚያሳጣ ከመሆኑም ባለፈ፤ በቀጣናው የሚከሰቱ ድንገተኛ ፖለቲካዊ መስተጓጎሎች የ130 ሚሊዮን ሕዝብ አቅርቦትን በአንድ ጀንበር አደጋ ላይ የመጣል አቅም ያለው ነው።

በመሆኑም የባሕር በር ባለቤት የመሆን ስልታዊ ግብ ኢትዮጵያ በቀጣናው ያላትን ጂኦ-ፖለቲካዊ ሚዛን ለማስከበር፣ የንግድ ወጪዋን ለመቀነስ እና ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጋር ያላትን ቀጥተኛ ትስስር ለማጠናከር ለምታደርገው ጥረት ዋነኛ አካል ሆኖ ተወስዷል።

ይህንን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር ደግሞ እርስ በርስ በመሠረተ-ልማት መተሳሰር እና ከቀጣናው ሀገራት ጋር የጋራ ዲፕሎማሲያዊ አቅም መገንባት ወሳኝ ተደርጎ ይወሰዳል።

የኢትዮጵያ የባሕር በር ፍላጎት በጋራ ተጠቃሚነት እና በኢኮኖሚያዊ ውህደት ላይ የተመሠረተ በመሆኑ፣ ኢትዮጵያ የጎረቤት ሀገራትን ሉዓላዊነት በማክበር ፍላጎቷን በጠረጴዛ ዙሪያ በማቅረብ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት ጥረት በማድረግ ላይ ትገኛለች።

ኢትዮጵያ ያላትን ሰፊ የገበያ ዕድል፣ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶችን እንዲሁም የታዳሽ ኃይል አቅርቦትን በመጠቀም በጋራ የመልማት አቅምን ማካፈል የምትችል በመሆኑ፣ የጎረቤት ሀገራትም በቀጥታ ተጠቃሚ የመሆን ዕድላቸው ከፍተኛ ይሆናል።

#ኢቢሲ

የኢትዮጵያ አሸናፊነት እና የአፍሪካ የዴሞክራሲ ፋና ወጊነትግንቦት 24 ቀን የተካሄደው 7ኛው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ፣ ሀገራችን በፈተናዎች እቶን ውስጥ አልፋ ወርቅ ሆና የወጣችበት እና አዲ...
04/06/2026

የኢትዮጵያ አሸናፊነት እና የአፍሪካ የዴሞክራሲ ፋና ወጊነት

ግንቦት 24 ቀን የተካሄደው 7ኛው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ፣ ሀገራችን በፈተናዎች እቶን ውስጥ አልፋ ወርቅ ሆና የወጣችበት እና አዲሱን የዴሞክራሲ ታሪኳን በደማቅ ቀለም የጻፈችበት ታሪካዊ ዕለት ነው።

ኢትዮጵያ የገጠሟትን ውስብስብ የውስጥ እና የውጭ ፈተናዎች በብልኃት እና በጥበብ በማለፍ፣ ሉዓላዊነቷን እና ተቋማዊ ብስለቷን ለዓለም ኅብረተሰብ በተግባር አሳይታለች።

ይህ ምርጫ የአንድ ወገን ወይም የፖለቲካ ድርጅት ድል ሳይሆን በአንድነትና በጽናት የቆመው የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ታላቅ ድል እና የሀገራችን ዘላቂ አሸናፊነት የተረጋገጠበት ማኅተም ነው።

ይህንን ታሪካዊ እውነት የዐይን እማኝ በመሆን የመሰከሩት የአኅጉራችን እና የዓለም አቀፍ ተቋማት ታዛቢዎች የሰጡት ዕውቅና የድላችንን ታላቅነት ያጎላዋል።

የአፍሪካ ኅብረት ታዛቢ ቡድን መሪ የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የኢትዮጵያን ሕዝብ የሰለጠነ፣ የሰከነ እና የጸና የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ሲያደንቁ፣ የኢጋድ ታዛቢ ቡድን መሪ ዶክተር ስፔሲዮዛ ዋንዲራ ካዚብዌ በበኩላቸው፣ በሂደቱ የታየውን አካታችነት፣ የሴቶች እና የአካል ጉዳተኞችን ተሳትፎ እንዲሁም ሕዝቡ ያሳየውን የላቀ ባሕላዊ መስተንግዶ እና ሰላማዊ አብሮነት በየትኛውም ሀገር አይተውት እንደማያውቁ በኩራት መስክረዋል።

የአውሮፓ ኅብረት፣ ካናዳ፣ ኖርዌይ እና ስዊዘርላንድ በጋራ ያወጡት መግለጫም የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ገለልተኝነት እና በሀገር በቀል አቅም የበለጸገውን "ምርጫዬ" የተሰኘውን የዲጂታል መራጮች ምዝገባ ቴክኖሎጂ አድንቋል።

ይህ "ለአፍሪካ ችግር አፍሪካዊ መፍትሔ" የመነጨበት እውነታ፣ ቅኝ ተገዝታ የማታውቀው የነጻነት ምልክቷ ኢትዮጵያ ዛሬም ለአኅጉሪቱ የዴሞክራሲና የሉዓላዊነት አዲስ ተምሳሌት መሆን እንደምትችል ያረጋገጠ ነው።

ምርጫው ለኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ እጅግ የላቀ ነው። ፖለቲካዊ ልዩነቶችን በኃይል ሳይሆን በሕጋዊና በሰላማዊ መንገድ በምርጫ ካርድ ለመፍታት የተደረገው ልምምድ የሀገራዊ ብስለታችን ማሳያ ነው።

ማናቸውንም ቅሬታዎች በሰለጠነ መንገድ በሕግ አግባብ ብቻ ለመፍታት የተያዘው ቁርጠኝነት ወደፊት ለሚገነባው ጠንካራ የዴሞክራሲ ሥርዓት የማይናወጥ መሠረት ጥሏል።

ምርጫው በራሱ ፍጻሜ ሳይሆን ዜጎች በሀገራቸው የወደፊት ዕጣ ፈንታ ላይ በቀጥታ የወሰኑበት እና የሕግ የበላይነት የነገሠባትን ጠንካራ ሀገር ለመገንባት የተራመድነው ታላቅ እርምጃ ነው።

አሁን ከምርጫው ማግስት የሚጠበቀው ትልቁ እና ታሪካዊው አደራ "ከመረጡ በኋላ መተባበር፣ ካረሱ በኋላ መዝራት" ነው። "አንድ ሰው ብቻውን ቢጮህ ድምፅ አይሆንም፣ አንድ እንጨት ብቻውን አይነድም" እንደሚባለው፣ ምርጫው በአሸናፊነት መጠናቀቁ የጋራ ሥራችን መጀመሪያ እንጂ ማጠቃለያ አይደለም።

በምርጫው ሂደት የታዩትን ልዩነቶች በሙሉ ወደ ጠረጴዛ በማምጣት፣ በብሔራዊ መግባባት ላይ የተመሠረተች፣ የዜጎቿን እኩልነት እና ብልጽግና ያረጋገጠች የጸናች ሀገርን በጋራ መገንባት የሁላችንም የቤት ሥራ ነው።

አሸናፊዋን ኢትዮጵያን ይበልጥ ለማጽናት፣ ሉዓላዊነቷን ለማስከበር እና የጀመረችውን የዴሞክራሲ ጉዞ ዳር ለማድረስ ሁላችንም እጅ ለእጅ ተያይዘን፣ በፍቅርና በወንድማማችነት ልንተባበር እና ልንሠራ ይገባል።

ማንም ይመረጥ ማን፣ በውጤቱ ላይ የኢትዮጵያ ታላቅነትና ሕዝባዊ አንድነት ከፍ ብሎ እንዲኖር ማድረግ የነገው ብሩህ ተስፋችን ዋስትና ነው።

ኢቢሲ

Address

Wolkite

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wolkite City Administration Government Communication Affairs Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share