Gurage zone Geta woreda prosperity party office/በጉ/ዞ/ጌ/ብ/ፓ/ጽ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Wolkite
  • Gurage zone Geta woreda prosperity party office/በጉ/ዞ/ጌ/ብ/ፓ/ጽ/ቤት

Gurage zone Geta woreda prosperity party office/በጉ/ዞ/ጌ/ብ/ፓ/ጽ/ቤት "ሁላችንም አሸናፊ መሆን የምንችለው ለሁላችን የምትሆን ኢትዮጵያን መገንባት ስንችል ነው።"

26/03/2023

ብልጽግና ፓርቲ አዳጊና ተራማጅ ለሆነ አዳዲስ አስተሳሰብ የተዘጋጀ ፕራግማቲክ የፖለቲካ ፍልስፍና የሚከተል ፓርቲ ነው፡፡ ተራማጅ የዴሞክራሲ ስርዓት በሚፈልግ መሰረታዊ የፖለቲካ ኢኮኖሚ አመክንዮ መፈታት ያለባቸው ውስጣዊ ችግሮች እልፍ በሆነበት አገርና ማህበራዊ መስተጋብር ውስጥ የብልፅግና ተራማጅ እሴቶች በእርግጥም ወቅታዊና አስፈላጊ ናቸው፡፡

ብልጽግና ገና ከመነሻው የአገሩን ሰርዶ በአገሩ በሬ እንደሚባለው ለአገር በቀል ችግሮች አገር በቀል መፍትሄ ያስፈልጋቸዋል ብሎ የተነሳ ፓርቲ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ለአገር በቀል አስተሳሰብና የመፍትሄ አማራጮች ተገቢውን ትርጉም መስጠት ችሏል፡፡

ሁሉም ፖለቲካዊ ችግሮቻችን ከውጪ በሚቀዱ የፖለቲካ አስተሳሰቦች አይፈቱም የተባለ ይመስል የግድ ከአገር በቀል የመፍትሄ አማራጮች ውጭ ሙሉ ለሙሉ ከውጭ በተቀዱ ርዕዮተ አለማዊ ፍልስፍናዎች መጠመድ የለብንም ብሎ ብልፅግና አጥብቆ ያምናል፡፡

ስለሆነም የውስጥ ችግራችንን ለመቅረፍ የምንዋሰው ሌላ ባዕድ አስተሳሰብ ሳያስፈልገን እንደነገሩ ድንበር ተሻጋሪ መልካም ተሞክሮዎችን እየቀላቀልን ከችግሮች መላቀቅ እንችላለን፡፡ በዚህም በመደመር እሳቤ ሀገር በቀል ብልሀት ችግሮቻችንን መፍታትም ጀምረናል፡፡

23/03/2023

መጋቢት13/2015 ዓ.ም
==================
የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ ታላቁ የረመዳን ጾምን ምክንያት በማድረግ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላለፉ።

ዋና አስተዳዳሪው ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖች እንኳን ለ1444ኛው ታላቁ የረመዳን ፆም አደረሳቹህ ሲሉ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

ዋና አስተዳዳሪው አክለውም የረመዳን ወር ከፍቅር፣ ሰላም፣ መቻቻል እና መረዳዳት ጋር ልዩ ቁርኝት እንዳለው ገልፀው ይህ መንፈሳዊ ትሩፋትም ለመላው ዞናችን ብሎም ሀገራችን ሰላምና በረከት እንዲያመጣም ምኞታቸውን አክለዋል።

ሁልጊዜም ህዝበ ሙስሊም በእምነቱ አስተምህሮ መሰረት እንደሚከውነው ለሀገራችን ሰላም ፣ልማት እና ብልፅግናም አበክሮ ዱዐ እንዲያደርግ /እንዲፀልይ ጥሪያቸውን አቅረበዋል።

እንደ አቶ ላጫ ገለፃም ወሩ የሰላም እና መረዳዳት ወር በመሆኑ የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት ዞኑንም በሰላም እና ልማቱ የተሻለ እንዲሆን ህዝበ ሙስሊሙ እንደሁልጊዜው የበኩሉን እንዲወጣ ሲሉ መልዕክታቸውን አቅርበዋል።

በድጋሚ ሰላም ፍቅር መደረዳዳትና መቻቻል ይበልጥ የሚጎለብት ወርሀ ረመዳን እንዲሆን ምኞታቸውን ገልፀዋል።

18/03/2023

''ተባብረንና ተግተን ሰርተን ኢትዮጵያን መቀየር የሚያስችል መሰረት ላይ ማስቀመጥ ይኖርብናል። ''

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ

16/03/2023
መንግሥት ቃል በገባው መሰረት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬ ወደ መቐለ በጀመረው በረራ የተጓዙ መንገደኞችና የቤተሰቦቻቸው ስሜት በፎቶ
28/12/2022

መንግሥት ቃል በገባው መሰረት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬ ወደ መቐለ በጀመረው በረራ የተጓዙ መንገደኞችና የቤተሰቦቻቸው ስሜት በፎቶ

"ለኢትዮጵያና አፍሪካዊ ብልፅግና የሚተጋ ወጣት" የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ 1ኛ መደበኛ ጉባዔ የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ አንደኛ መደበኛ ጉባዔውን ከታኅሣሥ 21 እስከ 25 ቀን 2015...
28/12/2022

"ለኢትዮጵያና አፍሪካዊ ብልፅግና የሚተጋ ወጣት"
የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ 1ኛ መደበኛ ጉባዔ

የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ አንደኛ መደበኛ ጉባዔውን ከታኅሣሥ 21 እስከ 25 ቀን 2015 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ያካሂዳል፡፡

ለአምስት ቀናት የሚቆየው ጉባዔው "ለኢትዮጵያና አፍሪካዊ ብልፅግና የሚተጋ ወጣት" በሚል መልዕክት ይካሄዳል።

የሊጉ ፕሬዚዳንት አስፋው ተክሌ በሰጡት መግለጫ ጉባዔው የተከናወኑ ተግባራትን እንደሚገመግምና የቀጣይ ዓመት ጉዞን ጨምሮ የሊጉን መተዳደሪያ ደንብ ማሻሻል እና ማፅደቅ ላይ ይመክራል፡፡

በተጨማሪም የወጣቶች ማትጊያ ሰነድ ማፅደቅ፣ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ፣ ፕሬዚዳንትና የሌሎችም አካላት ምርጫ የሚሉ ጉዳዮች በአጀንዳነት ይቀርባሉ ብለዋል፡፡

የሊጉ ምክትል ፕሬዚዳንት አክሊሉ ታደሰ በጉባዔው ላይ በሁሉም ዘርፍ ውጤታማ የሆኑ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ በተቋማት፣ በዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች የሚገኙ ወጣቶችን ጨምሮ ሌሎችም እንደሚሳተፉ ጠቁመዋል ሲል ፋና ብሮድካስት ኮርፖሬሽን ዘግቧል፡፡

አባይ ለኢትዮጵያ የተሰጠ ፀጋ ነው።ለዘመናት ከጓዳችን ወጥቶ እየተንፎለፎለ የኖረ፣ተስፋችንን፣የተፈጥሮ ሀብታችንን ለጎረቤቶቻችን ሲለግስ የኖረ ወንዝ ነው። ኢትዮጰያ ለእልፍ ዘመናት የበይ ተመል...
28/12/2022

አባይ ለኢትዮጵያ የተሰጠ ፀጋ ነው።ለዘመናት ከጓዳችን ወጥቶ እየተንፎለፎለ የኖረ፣ተስፋችንን፣የተፈጥሮ ሀብታችንን ለጎረቤቶቻችን ሲለግስ የኖረ ወንዝ ነው።

ኢትዮጰያ ለእልፍ ዘመናት የበይ ተመልካች ሆና ከወንዟ አንዲት ቅጠል ፍሬ ማብቀል ያልቻለችበት፣ለህዝቧ የኤሌትሪክ ሀይል ብርሀንን ከአባይ ወንዝ መለገስ ያልቻለችበት ታሪክ በባለራእይ ልጆቿ ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ታሪክ ሊቀየርበት የሚችልበት ደረጃ ላይ እየደረሰ ነው።

ከአንግዲህ አባይ ለኢትዮጵያ የብርሀን፣የልማት፣የትብብር ምሳሌ እንጂ የባዳነት እና የጎምዢነት ምሳሌ ሆኖ የሚቀርብበት ጊዜ አይሆንም።

በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በተከፈለ ውድ ዋጋ አባይ ታሪኩ ተቀይሯል።

"ከሐሙስ ጀምሮ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት በመቐለ ሕገ-መንግሥታዊ ኃላፊነቱን መወጣት ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል" - አምባሳደር ሬድዋን ሁሴንበናይሮቢው የሰላም ስምምነት መሠረት ከባድ የጦር መ...
27/12/2022

"ከሐሙስ ጀምሮ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት በመቐለ ሕገ-መንግሥታዊ ኃላፊነቱን መወጣት ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል" - አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን

በናይሮቢው የሰላም ስምምነት መሠረት ከባድ የጦር መሣሪያዎችን ማስፈታት እና ከሐሙስ ዕለት ጀምሮ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት በመቐለ ሕገ-መንግሥታዊ ኃላፊነቱን መወጣት ይጀምራል ተብሎ እንደሚጠበቅ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ተናገሩ።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ሚኒስትር እና የሠላም ዐቢይ ኮሚቴ አባል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ይህንን ያሉት በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ነው።

አምባሳደር ሬድዋን በትናተናው ዕለት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ የተመራው የፌዴራል መንግሥት የልዑካን ቡድን በመቐለ የነበረውን ቆይታ አስመልክቶ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ማብራሪያ መቅረቡን ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያውን ካደመጡ በኋላ መመሪያ መስጠታቸውን ገልጸው፣ በመመሪያው መሠረትም፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቐለ የሚያደርገውን በረራ በነገው ዕለት እንደሚጀምር እና ኢትዮ ቴሌኮምም በቅርቡ አገልግሎት የሚጀምርበትን ቀን ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።

# WMCC

ታህሳስ 18/2015 ዓ.ም ወደ ህብረተሰቡ የሚደርሱ መረጃዎች ካላቸው ተጽዕኖ ፈጣሪነት አንጻር የሚኖራቸውን ፋይዳ ለማጎልበት የኮሙኒኬሽን ዘርፉ በሀላፊነት ሊሰራ እንደሚገባ ተገለጸ በደቡብ ክ...
27/12/2022

ታህሳስ 18/2015 ዓ.ም

ወደ ህብረተሰቡ የሚደርሱ መረጃዎች ካላቸው ተጽዕኖ ፈጣሪነት አንጻር የሚኖራቸውን ፋይዳ ለማጎልበት የኮሙኒኬሽን ዘርፉ በሀላፊነት ሊሰራ እንደሚገባ ተገለጸ

በደቡብ ክልል በማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና ለዘርፉ ባለሙያዎች በአርባምንጭ ከተማ እተተሰጠ ነው

የደቡብ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የመንግስት መረጃ ማዕከል እና ዲጂታል ሚዲያ አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ አቶ አይሶጼ ሂሎታ እንደገለጹት ወደ ህብረተሰቡ የሚደርሱ መረጃዎች ካላቸው ተጽዕኖ ፈጣሪነት አንጻር የሚኖራቸውን ፋይዳ ለማጎልበት የኮሙኒኬሽን መዋቅሩ በሀላፊነት ሊሰራ እንደሚገባ ተናግረዋል።

ወቅታዊ፣ ሚዛናዊና ትክክለኛ መረጃዎችን ተደራሽ ለማድረግ እስከ ወረዳ ባለው በኮሙኒኬሽን መዋቅር ላይ የሚገኙ ባለሙያዎችን አቅም መገንባት የስልጠናው ዋና ዓላማ መሆኑን የተናገሩት አቶ አይሶጼ በማህበራዊ ትስስር ገጾች አጠቃቀም እና አስተዳደር ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን መቅረፍ እንደሚያስችልም አብራርተዋል።

የማህበራዊ ትስስር ገጾች መረጃን ተደራሽ ለማድረግ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳላቸው የተናገሩት ምክትል ኃላፊው የኮሙኒኬሽን ዘርፉ ይህንን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ለህብረተሰቡ የመረጃ ተደራሽነትን በላቀ ደረጃ መፈጸም እንዳለበትም ጠቁመዋል።

በልጠናው ከክልል ሴክተር መስሪያ ቤቶች፣ ከዞን፣ከልዩ ወረዳ፣ከወረዳ እና ከከተማ አስተዳደር የተውጣጡ የኮሙኒኬሽን ኃላፊዎችና ባለሙያዎች እየተሳተፉ ሲሆን በቀጣይ ቀናት ደግሞ ለተቀሩት የኮሙኒኬሽን መዋቅሮች እንደሚሰጥ ለማወቅ ተችሏል።

ስልጠናው በደቡብ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ እና በርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት የጋራ ትብብር የተዘጋጀ ስለመሆኑም ተጠቁሟል።

27/12/2022

ታህሳስ 18/2015 ዓ.ም

ወደ ህብረተሰቡ የሚደርሱ መረጃዎች ካላቸው ተጽዕኖ ፈጣሪነት አንጻር የሚኖራቸውን ፋይዳ ለማጎልበት የኮሙኒኬሽን ዘርፉ በሀላፊነት ሊሰራ እንደሚገባ ተገለጸ

በደቡብ ክልል በማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና ለዘርፉ ባለሙያዎች በአርባምንጭ ከተማ እተተሰጠ ነው

የደቡብ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የመንግስት መረጃ ማዕከል እና ዲጂታል ሚዲያ አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ አቶ አይሶጼ ሂሎታ እንደገለጹት ወደ ህብረተሰቡ የሚደርሱ መረጃዎች ካላቸው ተጽዕኖ ፈጣሪነት አንጻር የሚኖራቸውን ፋይዳ ለማጎልበት የኮሙኒኬሽን መዋቅሩ በሀላፊነት ሊሰራ እንደሚገባ ተናግረዋል።

ወቅታዊ፣ ሚዛናዊና ትክክለኛ መረጃዎችን ተደራሽ ለማድረግ እስከ ወረዳ ባለው በኮሙኒኬሽን መዋቅር ላይ የሚገኙ ባለሙያዎችን አቅም መገንባት የስልጠናው ዋና ዓላማ መሆኑን የተናገሩት አቶ አይሶጼ በማህበራዊ ትስስር ገጾች አጠቃቀም እና አስተዳደር ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን መቅረፍ እንደሚያስችልም አብራርተዋል።

የማህበራዊ ትስስር ገጾች መረጃን ተደራሽ ለማድረግ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳላቸው የተናገሩት ምክትል ኃላፊው የኮሙኒኬሽን ዘርፉ ይህንን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ለህብረተሰቡ የመረጃ ተደራሽነትን በላቀ ደረጃ መፈጸም እንዳለበትም ጠቁመዋል።

በልጠናው ከክልል ሴክተር መስሪያ ቤቶች፣ ከዞን፣ከልዩ ወረዳ፣ከወረዳ እና ከከተማ አስተዳደር የተውጣጡ የኮሙኒኬሽን ኃላፊዎችና ባለሙያዎች እየተሳተፉ ሲሆን በቀጣይ ቀናት ደግሞ ለተቀሩት የኮሙኒኬሽን መዋቅሮች እንደሚሰጥ ለማወቅ ተችሏል።

ስልጠናው በደቡብ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ እና በርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት የጋራ ትብብር የተዘጋጀ ስለመሆኑም ተጠቁሟል።

ዘገባው ፦ የደቡብ ክልል መንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ነው።

የጠንካራ ዲፕሎማሲ ስራ መሠረቱ ጠንካራ ውስጣዊ ሁኔታ ነው። በትናንትናው ዕለት በተጀመረው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የከፍተኛ አመራሮች እና የሚሽን መሪዎች ውይይት ላይ ይኽንኑ በአፅንኦት አንስተ...
27/12/2022

የጠንካራ ዲፕሎማሲ ስራ መሠረቱ ጠንካራ ውስጣዊ ሁኔታ ነው። በትናንትናው ዕለት በተጀመረው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የከፍተኛ አመራሮች እና የሚሽን መሪዎች ውይይት ላይ ይኽንኑ በአፅንኦት አንስተናል።

በሀገራችን በሰሜኑ አካባቢ የተፈጠረውን ግጭት በሰላም ለመፍታት የተጀመረው እንቅስቃሴም ወደ ወሳኝ ምዕራፍ ተሸጋግሯል።

በሌሎች አካባቢዎች ያለውን የሰላም ሁኔታ ለማሻሻል እና የዜጎችን ሰላም እና ደኅንነት እንዲሁም ተጠያቂነት የማረጋገጡ ጉዳይ ተጠናክሮ ይቀጥላል።

ዲፕሎማሲያችን በሀገር ውስጥ የተፈጠረውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀምና በውጭ የተጀመረውን መልካም ግንኙነት የበለጠ በማፅናት ብሔራዊ ጥቅማችንን የማስጠበቅና ተደማጭነታችንን የማሳደግ ተልዕኮ ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል።

የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ደመቀ መኮንን

"ከፊት ለፊታችን ያለውን የኢትዮጵያ ብልፅግና እያየን ወደፊት በአንድነት ለማሸነፍ እንሩጥ። ያለ ጥርጥር ኢትዮጵያ ትበለፅጋለች፤ ዜጎቿ በምቾት የሚኖሩባት ሀገር ትሆናለች አልጠራጠርም!! ይህ ...
27/12/2022

"ከፊት ለፊታችን ያለውን የኢትዮጵያ ብልፅግና እያየን ወደፊት በአንድነት ለማሸነፍ እንሩጥ። ያለ ጥርጥር ኢትዮጵያ ትበለፅጋለች፤ ዜጎቿ በምቾት የሚኖሩባት ሀገር ትሆናለች አልጠራጠርም!! ይህ የሁላችን መሻት እውን ይሆናል።"

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ

Address

Wolkite , Quante
Wolkite

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gurage zone Geta woreda prosperity party office/በጉ/ዞ/ጌ/ብ/ፓ/ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share