Gurage Zone Gummer Worda Water,Mine & Energy Office የጉ/ዞ/ጉ/ወ/ው/ማ/ኢ ፅ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Wolkite
  • Gurage Zone Gummer Worda Water,Mine & Energy Office የጉ/ዞ/ጉ/ወ/ው/ማ/ኢ ፅ/ቤት

Gurage Zone Gummer Worda Water,Mine & Energy Office የጉ/ዞ/ጉ/ወ/ው/ማ/ኢ ፅ/ቤት We Strive To Give Better Service For Society

Permanently closed.
ለጉመር ወረዳ ነዋሪዎች በሙሉይህንን እድል እንዳያመልጦዎት ስናበስር በታላቅ ደስታ ነው!!!በቅድሚያ ለክልል ማዕድን ኢነርጂይ ኤጀንሲ እና የክልሉ የባዩ ጋዝ ፕሮግራም ማስተባበሪያ ዩኒቲ ለዞን...
07/10/2021

ለጉመር ወረዳ ነዋሪዎች በሙሉ

ይህንን እድል እንዳያመልጦዎት ስናበስር በታላቅ ደስታ ነው!!!
በቅድሚያ ለክልል ማዕድን ኢነርጂይ ኤጀንሲ እና የክልሉ የባዩ ጋዝ ፕሮግራም ማስተባበሪያ ዩኒቲ ለዞንና ለወረዳው ይህንን ቴክኖሎጂ ህብረተሰቡን እንዲጠቀመው አሰተዋጽኦ ለሚያደርጉ ተቋማት ሁሉ ላቅ ያለ ምስጋና እያቀረብን በሀገራችን ላይ እየተስፋፋ ያለው የባዮ ጋዝ ቴክኖሎጂ በወረዳችን እንዲስፋፋ ህብረተሰቡን በዚህ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ይሆን ዘንድ ቴክኖሎጂው እንደ ወረዳችን አዲስ እንደመሆኑ ህብረተሰቡ ቴክኖሎጂው አመኖበት ተረድቶና ተገንዝቦ በራሱ ተነሳሽነት እንደሚሰራና እንደሚጠቀመው በሙሉ እምነት ተስፋ እያደረገ የክልል የባዮጋዝ ኘሮግራም በዘንድሮ አመት በያዘው በጀት ለህብረተሰቡ ሰረቶ ማሰያ ሙሉ የግንበኛ ክፍያ በመሸፈን የቴክኖሎጂው ሙሉ እቃ አቅርቦትና የመስመር ዝርጋታን ጨመሮ ለህብረተሰቡ እያቀረበ መሆኑን እያሳወቅን ይህንን ቴክኖሎጂ ለመጠቀም ፍላጎት ያለው አርሶ አደር ቴክኖሎጂ እንዲጠቀመው እየመከረን 8 ኩንታል ሲምንቶ 3.5-4 ሜ.ኩ አሻዋ እንደ አሻዋው ጥራት 1.5ሜ.ኩ ጠጠር ማዘጋጀትና ማቅረብ የሚችል አርሶ አደር በወረዳው ባለው ውሃና ማዕድን ኢነርጂይ ፅ/ቤት እንዲመዘገቡና እድሉንም እንዳያመልጦት እያሳሰብን
ስለ ቴክኖሎጂው በጥቂቱ
✡ባዮ ጋዝ ምንድነው?
ባዩ ጋዝ ማለት ኦክሲጂን በሌለበት በባክቴሪያዎች አማካኝነት ህይወት ካላቸው ነገሮች የሚገኝ ብስባሽ እና የእንስሳት ቅሪት አካላት(organic matters) በኬሚካል ኡደት የሚለቀቅ ጋዝ ነው
ባዮ ጋዝ የተባለበት ምክንያት የሚበሰብሱ አካለት ንጥረ ነገሮች ህይወት ካልቸው ነገሮች ስለሚገኝ ነው የኦክሲጂን አልባ ኬሚካል ኡደት ተከትሎ የሚመጣውና የሚቀጣጠለው ጋዝ ባዮ ጋዝ ይባላል
1 ሜ ኩብ ባዬ ጋዝ
10 ኪ ግ ኩበት ከሚሰጠው
5 ኪ ግ እንጨት ከሚሰጠው
2 ኪ ግ የእንጨት ከሰል ከሚሰጠው ሀይል/ኢነርጂይ ጋር እኩል ሲሆን
በተጨማሪም 1ሜ ኩ ባዮ ጋዝ 1.25 ኪሎ ዋት የኤልክትሪክ ሀይል ማመንጨት ይችላል፡፡

✡ለምን ለምን አገልግሎት ይውላል?
❖ለመብራት/lighting -በቂ የብርሃን አገልግሎት ይሰጣል
❖ለምድጃ-የተለያዮ ምግቦች ለማብሰልና ቡና ሻይ ለማፍላት
❖ለማዳበሪያ-የተፈጥሮ- ለመሬት ለምነትና ምርታማነት የሚውል ለአፈር ማዳበሪያነት

✡ሌላኛው ጠቀሜታው?

✔የማገዶ የሚወጣውን ወጪ ይቀንሳል
✔በጭስ አማካኝነት የሚመጡ በሽታዎች ይቀንሳል
✔ለሴቶችና ልጆች የስራ ጫና ይቀንሳል ጊዜና ጉልበትም ይቆጥባል
✔ለአርሶ አደሩ ምርትና ምርታማነት ይጨምራል
✔የአፈር ለምነት ይጨምራል-ባዮስለሪ
✔ለኬሚካል የሚወጣው ማዳበሪያ ወጪ ይቀንሳል ..ሌሎች ሌሎችም

ለጉመር ወረዳ ነዋሪዎች በሙሉመቀመጫው እምድብር ከተማ ያደረገው ቪዥን ፈንድ ማይክሮ ፋይናስ ተቋም የተለያዩ የብድር አገልግሎቶች መስጠት መጀመሩ እያሳወቅን በጉ/ወ  /ው /ማ / ኢ ፅ / ቤት...
11/09/2021

ለጉመር ወረዳ ነዋሪዎች በሙሉ

መቀመጫው እምድብር ከተማ ያደረገው ቪዥን ፈንድ ማይክሮ ፋይናስ ተቋም የተለያዩ የብድር አገልግሎቶች መስጠት መጀመሩ እያሳወቅን በጉ/ወ /ው /ማ / ኢ ፅ / ቤት አማካኝነት ለህብረተሰቡ የሶላር አገልግሎት በክፍያ እያቀረበ የነበረው Import Trading ተቋም ከቪዥን ፈንድ ጋር በመነጋገር ለህብረተሰቡ የሶላር የብድር አገልግሎት መጀመሩ ስናበስር በታላቅ ደስታ ነው
ይህንን አገልግሎት መጠቀም የሚፈልግ ማንኛውንም የወረዳው ነዋሪ አቅራቢያው ባለው የቀበሌው ፅ / ቤት በመሄድ 2 ጉርድ ፎቶና የታደሰ የቀቤለው መታወቂያ በመያዝ በቀበሌው ስራ አስከያጅ 5 አለያም 3 እየሆናችሁ እርስ በርስ የጠለፋ ዋስ በመሆን መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን በመንግስት መስሪያ ቤት ላላችሁ በተመሳሳይ በየቢሮአችሁ...
የሶላሩ አይነት d light 10watt ባለ ሶስት አምፖል የእጅ ባትሪና ራድዬን ያለው ሲሆን ከሁለት አመት ዋሰትና ጋር

የብድሩ አከፋፈል ከአንድ አመት ባልበለጠ ጊዜ ሲሆን ቅድም ክፍያ 837 ሶላሩ ሲወስዱ በየወሩ 470 ለ12 ወር ሲሆን በአጭር ጊዜም ማለትም አመት ሳይጠብቁም መጨረስ እንደሚቻል እያሳወቅን የትኛውንም የሶላር ጥያቄ ካሎዎት በወረዳው ባለው ውሃና ማዕድን ኢነርጂይ ፅ / ቤት ባለሙያዎችን ያማክሩ ይጠይቁ
መልካም አዲስ አመት !!!!

Address

Gummer Arekit
Wolkite

Telephone

+251989112233

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gurage Zone Gummer Worda Water,Mine & Energy Office የጉ/ዞ/ጉ/ወ/ው/ማ/ኢ ፅ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Gurage Zone Gummer Worda Water,Mine & Energy Office የጉ/ዞ/ጉ/ወ/ው/ማ/ኢ ፅ/ቤት:

Share