የጨና ወረዳ ኮሙኒኬሽን Chena Woreda Communications

  • Home
  • Ethiopia
  • Wacha
  • የጨና ወረዳ ኮሙኒኬሽን Chena Woreda Communications

የጨና ወረዳ ኮሙኒኬሽን Chena Woreda Communications Chena Woreda Communications

ግንቦት 24'ን በቀን መቁጠሪያዎ ላይ አስምረውበታል?እንግዲያውስ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሊካሄድ 2 ቀናት ብቻ ቀርተዋል።ሰኞ ግንቦት 24፤ አገራችንን ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር ድምፅ የምንሰ...
30/05/2026

ግንቦት 24'ን በቀን መቁጠሪያዎ ላይ አስምረውበታል?

እንግዲያውስ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሊካሄድ 2 ቀናት ብቻ ቀርተዋል።

ሰኞ ግንቦት 24፤ አገራችንን ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር ድምፅ የምንሰጥበት ቀን ነው!

እርስዎስ የመራጭነት ካርድዎን አዘጋጅተው የድርሻዎን ለመወጣት ተሰናድተዋል?

#በምርጫብቻ

በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ:-1. 54 ሚሊዮን 57 ሺህ 871 መራጮች ተመዝግበዋል፣2.በአጠቃላይ 42 የፖለቲካ ፓርቲዎች ይወዳደራሉ፤3. 10 ሺህ 438 የፖለቲካ ፓርቲ እጩዎች እንዲሁም4. 80 የ...
30/05/2026

በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ:-

1. 54 ሚሊዮን 57 ሺህ 871 መራጮች ተመዝግበዋል፣

2.በአጠቃላይ 42 የፖለቲካ ፓርቲዎች ይወዳደራሉ፤

3. 10 ሺህ 438 የፖለቲካ ፓርቲ እጩዎች እንዲሁም

4. 80 የግል እጩዎች በምርጫው ይወዳደራሉ።

5. ፓርቲዎች በተደለደለላቸው የአየር ሰዓት 19 የክርክር መድረኮችን በአምስት ቋንቋዎች አካሂደዋል፤

6. ተፎካካሪ ፓርቲዎች ከ250 ሺህ በላይ ተወካዮቻቸውን የምርጫውን ሂደት እንዲከታተሉ ይልካሉ፤

7. ለታዛቢነት የአፍሪካ ሕብረት እና የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) ተወካዮቻቸውን ልከዋል፤

8. 59 አባላት ያሉት የአፍሪካ ሕብረት የምርጫ ታዛቢዎች ቡድን በቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት አሁሩ ኬንያታ እየተመራ ሥራውን ይሰራል፤

9. ኢጋድ 26 አባላት ያሉት የምርጫ ታዛቢዎች ቡድንን ያሰማራል፤

10. በሀገር ውስጥ የተደራጁ 55 ሲቪክ ማኅበራት ፈቃድ ወስደው ወደ ሥራ ገብተዋል፤ 55ቱ የሀገር ውስጥ ታዛቢዎች 1 ሺህ 562 የምርጫ ታዛቢዎችን አሰማርተዋል።

11. የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭትን በተመለከተ በአዲስ አበባ ለ33፣ በአፋር ለ32፣ በአማራ ለ130፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ለ22፣ በማዕካላዊ ኢትዮጵያ ለ35፣ በድሬዳዋ ለ48፣ በጋምቤላ ለ14፣ በሐረሪ ለ3፣ በኦሮሚያ ለ179፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ለ56፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ለ22 ክልሎች የምርጫ ቁሳቁስ ተሰራጭቷል።

በዋቻ ምርጫ ክልል የምርጫ ቁሳቁስ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች እየተሰራጨ መሆኑን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የክልሉ ምርጫ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።ለምርጫው በሁሉም ረገድ የተሟላ ዝግጅት የተደረገ...
29/05/2026

በዋቻ ምርጫ ክልል የምርጫ ቁሳቁስ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች እየተሰራጨ መሆኑን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የክልሉ ምርጫ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

ለምርጫው በሁሉም ረገድ የተሟላ ዝግጅት የተደረገ ሲሆን በየምርጫ ጣቢያዎችም የምርጫ ቁሳቁሶች እየተጓጓዘ መሆኑ ተገልጿል።

በምርጫ ክልል የምርጫ ቁሳቁስ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች እየተሰራጨ መሆኑን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የክልሉ ምርጫ ጽህፈት ቤት አስተባባሪ አቶ በትረአሮን መላኩ ገልጸዋል።

በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ለድምፅ አሰጣጡ ሂደት መሳካት የተሟላ ዝግጅት መደረጉን የተናገሩት አስተባባሪው፥ የምርጫ ቁሳቁሶች በመሰራጨት ላይ መሆኑን ተናግረዋል።

የድምጽ መስጫ ወረቀትን ጨምሮ ሌሎችም አስፈላጊ የምርጫ ቁሶች ወደ ምርጫ ጣቢያዎች በመሰራጨት ላይ መሆናቸውን አንስተው፥ ቦርዱ በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ እየሰራ ስለመሆኑ አንስተዋል።

የቁሳቁስ ስርጭቱ በጥንቃቄና ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ በጸጥታ ሃይል ታጅቦ ጨና ወረዳ፤ ዋቻ ከተማ አስተዳደር፤ ሺሾ እንዴ ወረዳ፤ ሺሺንዳ ከተማ አስተዳደር፤ ሼይ ቤንች ወረዳ እና ሲዝ ከተማ አስተዳደር እየተጓጓዘ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች ተደራሽ እየሆነ እንደሚገኝ ተገልጿል።

በምርጫ ክልሉ 120 የምርጫ ጣቢያዎች የፊታችን ሰኞ ድምጽ የሚሰጥ መሆኑን ገልጸው፥ዜጎች የወሰዱትን ካርድ ዋጋ በመስጠት እንዲወስኑበት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ዛሬ መተግበር የጀመረው እና ለአራት ተከታታይ ቀናት የሚቆየው የጥሞና ጊዜ መራጩ ያለ ምንም ውጫዊ ተፅዕኖ፣ ግርግርና ቅስቀሳ በሰላም አስቦ እንዲወስን ይረዳል።ኢትዮጵያ ትመርጣለች!
28/05/2026

ዛሬ መተግበር የጀመረው እና ለአራት ተከታታይ ቀናት የሚቆየው የጥሞና ጊዜ መራጩ ያለ ምንም ውጫዊ ተፅዕኖ፣ ግርግርና ቅስቀሳ በሰላም አስቦ እንዲወስን ይረዳል።

ኢትዮጵያ ትመርጣለች!

የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ መስጫ ቀን አምስት ቀናት ብቻ ቀረው!
27/05/2026

የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ መስጫ ቀን አምስት ቀናት ብቻ ቀረው!

የጨና ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተረፈ ገ/ማርያም 1447ኛውን የዒድ አል አድሐ(አረፋ) በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፤የ1447ኛውን የዒድ አል አድሐ(አረፋ) በዓል አስመልክ...
27/05/2026

የጨና ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተረፈ ገ/ማርያም 1447ኛውን የዒድ አል አድሐ(አረፋ) በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፤

የ1447ኛውን የዒድ አል አድሐ(አረፋ) በዓል አስመልክቶ አቶ ተረፈ ገ/ማርያም ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት እንደሚከተለው ቀርቧል።

"ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል አድሐ 'ዐረፋ' በዓል በሰላም አደረሰን፣ አደረሳችሁ!

ዒድ አል-አድሐ “ዐረፋ” በዓል የመታዘዝ አብነት የታየበት በመታዘዝ ውስጥ ያለ መስዋዕትነት እና የተገኘ ድንቅ በረከት የሚገልጽ ድንቅ በዓል ነው።

ኢብራሂም ልጁን በመታዘዝ መስዋዕት አድርጎ ያቀረበበት፣ ልጁም ለአባቱ የታዘዘበት እና የሙስሊሙ ማህበረሰብም ይህን ድንቅ እሴት በትልቅ አክብሮትና በመተጋገዝ የሚያከብረው በዓል ነው።

ምንም ፈተናው ከባድ ቢሆን በፈተና መታዘዝን እና መጽናትን መረጠ፤ በከባድ ቆራጥነት በመቆም የመጀመሪያ እና ብቸኛ የሆነውን ልጁን እስማኤልን መስዋዕት አድርጎ አቀረበ።

ዒድ አል-አድሐ “ዐረፋ” በዓል በህዝበ ሙስሊሙ ዘንድ የመታዘዝ ጥግ የታየበት ከመሆኑም ባሻገር አንዱ ለሌላው መቆምን፣ መተጋገዝን፣ መተባበርን እና የእዝነትን የሚያሳዩበት በዓልም ጭምር ነው።

በበዓሉ ያለው ለሌለው በማካፈል፣ ያዘኑትን በማጽናናት፣ የተቸገሩትን በመጠየቅ ለሌሎች መስዋዕትነት የሚከፍሉበት መልካምነትን የሚገልጡበት በዓልም ነው።

ለሙስሊሙ በዓሉ ሙሉ የሚሆነው ያዘኑትን ደስተኞች ሲያደርግ፣ የተራቡት ሲጠግቡ፣ የታረዙት ሲለብሱ፣ በዓሉን እኩል ማሳለፍ ሲችል ነው።

በመሆኑም የተለመደውን የመተጋገዝ እና የመጠያየቅ እንዲሁም የመተባበር በጎ ተግባር ሁሉም እምነቱ በሚፈቅደው መልኩ ይወጣል የሚል እምነት አለኝ።

ኢብራሂም ምንም እንኳን በልጁ ቢፈተንም ፍላጎቱን ትቶ የተጠየቀውን በቁርጠኝነት ፈጽሟል፤ ሀገር በመገንባት ደረጃ ሀገራችንም ከዜጎቿ ቁርጠኝነትን የምትፈልግበት ጊዜ ላይ እንገኛለን።

ስለሆነም በቀጣይ ግንቦት 24 በሚካሄደው አጠቃላይ አገራዊ እና ክልላዊ ምርጫ በካርዳችን አገር የማቆም የዜግነት ኃላፊነት እና ዴሞክራሲያዊ መብታችንን የምንጠቀምበት ቀን በመሆኑ በዕለቱ በነቂስ በመውጣት የሙስሊሙም ሆነ መላው የወረዳችን መራጭ ማህበረሰብ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እንዲወጣም የከበረ ጥሪዬን አቀርባለሁ።"

በድጋሚ መልካም የዐረፋ በዓል እንዲሆን እመኛለሁ!

ዒድ ሙባረክ!!

አቶ ተረፈ ገ/ማርያም
የጨና ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ
ግንቦት 19/2018 ዓ.ም

26/05/2026
የህዝብ ማዕበል የታየበት በቦንጋ ስታዲየም ደማቅ ታላቁ የድጋፍ ሰልፍና የምረጡኝ ቅስቀሳ ማጠቃለያ መርሀግብር  አሁናዊ በፎቶ፤
26/05/2026

የህዝብ ማዕበል የታየበት በቦንጋ ስታዲየም ደማቅ ታላቁ የድጋፍ ሰልፍና የምረጡኝ ቅስቀሳ ማጠቃለያ መርሀግብር አሁናዊ በፎቶ፤

‎ከጨና ወረዳ እና ከዋቻ ከተማ አስተዳደር የተወጣጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች "ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር" በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው 7ኛው ሀገራዊ የምርጫ ቅስቀሳና ታላቅ ህዝባዊ ...
26/05/2026

‎ከጨና ወረዳ እና ከዋቻ ከተማ አስተዳደር የተወጣጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች "ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር" በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው 7ኛው ሀገራዊ የምርጫ ቅስቀሳና ታላቅ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ላይ ለመታደም የክልሉ ዋና አስተዳደርና የፖለቲካ መቀመጫ እንዲሁም የካፋ ዞን ዋና ከተማ ቦንጋ ስታዲየም ገብተዋል፤

‎በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ የ7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ጠቅላላ ምርጫ የብልጽግና ፓርቲ የይምረጡኝ ቅስቀሳ ማጠቃለያ ሕዝባዊ ሰልፍን ለመሳተፍ የጨና ወረዳ እና ዋቻ ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ፓር...
26/05/2026

‎በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ የ7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ጠቅላላ ምርጫ የብልጽግና ፓርቲ የይምረጡኝ ቅስቀሳ ማጠቃለያ ሕዝባዊ ሰልፍን ለመሳተፍ የጨና ወረዳ እና ዋቻ ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ጉዞውን በድምቀት ጀምረዋል።

Address

Chena
Wacha

Telephone

+251927220264

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የጨና ወረዳ ኮሙኒኬሽን Chena Woreda Communications posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share