Tarcha Town Municipality

Tarcha Town Municipality Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Tarcha Town Municipality, Government Organization, Dawro Zone, Tarch'a Sodo.

በታርጫ ከተማ በቤቶች ማህበር ለተደራጁ 11 ማህበር በዛሬው ዕለት መሬት ተላልፏል።መንግሥት በአነሰተኛ ቁጠባ ዘጎች የቤት ባለቤት ለማድረግ በተቀመጠው መመሪያ መሰረት ሙሉ መስፈርቶችን አሟልተ...
26/02/2026

በታርጫ ከተማ በቤቶች ማህበር ለተደራጁ 11 ማህበር በዛሬው ዕለት መሬት ተላልፏል።

መንግሥት በአነሰተኛ ቁጠባ ዘጎች የቤት ባለቤት ለማድረግ በተቀመጠው መመሪያ መሰረት ሙሉ መስፈርቶችን አሟልተው የተገኘ 154 አባላት ዛሬ የዕጣ ማስነሳት መርሀግብር ተከናውኗል።

የታርጫ ከተማ ማዘጋጀ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ባቲሳ ወንድሙ የታርጫ ከተማ ማዘጋጃ በተለያዬ ማህበራዊ መሠረት ለተደራጁ ነዋሪዎች ከሀገር መከላከያ በክብር ለተሰናበቱት አባላት፣ ለመምህራን፣ ለነዋሪዎች ከዚህ በፊት ከሶስት መቶ በላይ ማህበራት የቤት መስሪያ ቦታ ያስተላለፈ ሲሆን በዛሬ ቀን ደግሞ ለ11 ማህበራት መሬት በማዘጋጀት አስተላልፏል።

የታርጫ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፍ ወ/ሮ ብርቱካን ዘውዴ በመርሀግብሩ ላይ በመገኘት ፓርቲያችን ብልጽግና ለዜጎች ቅድሚያ የሚሰጥ ፓርቲ በመሆኑ ዘጎች የመኖሪያ ቤት እንዲያገኙ ከሁሉም የቅድሚያ ቅድሚያ በመሰጠት ያመቻቸ መሆኑን ተናግሯል።

በመጨረሻም በዛሬው ዕለት መሬት የተረከቡት የማህበሩ አባላት በበኩላቸው መሬት በማገኘት የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ የከተማ መንግሥትን አመስግነዋል ሲል የዘገበው የታርጫ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ነው።

Tarcha Town Municipality fans Southwest Communications

በታርጫ ከተማ አስተዳደር የአቶ ተሰፋዬ በለጠና ቤተሰቦቹ ኮከብ ነዳጅ ማደያ ዛሬ በይፋ ተመርቋል።ጥሪ 17/5/2018ዓ.ም በዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ አስተዳደር የአቶ ተሰፋዬ በለጠና ቤተሰቦቹ ...
25/01/2026

በታርጫ ከተማ አስተዳደር የአቶ ተሰፋዬ በለጠና ቤተሰቦቹ ኮከብ ነዳጅ ማደያ ዛሬ በይፋ ተመርቋል።

ጥሪ 17/5/2018ዓ.ም
በዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ አስተዳደር የአቶ ተሰፋዬ በለጠና ቤተሰቦቹ ኮከብ የነዳጅ ማደያ በዛሬው ዕለት የክልል፣ የዞንና የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች፣ የሀይማኖት አባቶችና ወዳጅ ቤተሰቦች በተገኘበት በይፋ ተመርቋል።

በከተማ አስተዳደሩ ሁለተኛ የሆነው ኮከብ የነዳጅ ማደያ የዞኑ ዋና አስተዳደር አቶ ዳዊት ገበየሁ እና የታርጫ ከተማ አስተዳደር ከተማ ከንቲባ አቶ አስናቀ አበበ እርባን በመቁረጥ አስመርቀዋል።

በመርሀ-ግብሩ የታርጫ ከተማ ከንቲባ አቶ አስናቀ አበበ ለአቶ ተስፋዬ በለጠና ቤተሰቦች ለወዳጅ ዘመዶችና ለመላው የከተማ ነዋሪዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፏል።

በመልዕክቱ የሀገርን ሰርዶ በሀገር በሬ እንደሚለው ሁሉ በከተማችን ውሰጥ የሚስተዋለውን የነዳጅ ማደያ እጥረት ለማስተካከል በአከባቢው ባለሀብትና በመንግሥት አካላት በብዙ ጥረት የተሳካ በመሆኑ በዛሬው ዕለት መላው የከተማችን ህዝቦች ደስታው ወደር የለም ብሏል።

አቶ ተሰፋዬ በለጠ ሰውን በመርዳት በተለያዩ ማህበራዊ ሥራዎች ግምባር ቀደም በመሆናቸው ተጨማሪ የኢንቨስትመንት ሥራዎች ላይ እንዲሳተፉ ተጨማሪ ድጋፍ ለመሰጠት ከንቲባው ቃል ገብተዋል።
የዞኑ ዋና አስተዳደር አቶ ዳዊት ገበየሁ በዞኑ ለመሰል ኢንቨስትመንት ሥራዎች ምቹ አጋጣሚዎችን በመፍጠር የህዝብን እርካታ ለመጨመርም ያልተቆጠበ ድጋፊ እንደሚደረግ ተናግሯል።

በዛሬው ዕለት የተመረቀው ኮከብ የነዳጅ ማደያ ለህዝብ መልካም ዕድል የፈጠረና ለከተማችን ህዝብ ትልቅ ኡፎይታ የሚፈጥር በመሆኑ ለሎችም የከተማችን ባለሀብቶች ሰፊውን ማህበረሰብ የሚያማክል ሥራዎች ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።

የማደያው ባለበት አቶ ተሰፋዬ በለጠ በመድረኩ ይህ ሀብት የመላው የታርጫና የአከባቢው ማህበረሰብ ነው መሬት በማመቻቸት በተለያዩ ሁኔታዎች ያገዘንን በየደረጃው የሚገኙ የመንግሥት አካላት በማመስገን እና በነገሮች ሁሉ የተባበሩ አካላትን በሙሉ በማመስገን መድረኩ ተጠናቋል።

የታርጫ ኮሚዩኒኬሽን

15/01/2026
ኑ የታርጫ ከተማ ሁሉ ዓቀፍ ኮሪደር ልማት በጋራ እናልማ!!!              🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌👉 የታርጫ ከተማ አስ/ር ከተማዋን ለኑሮ ምቹና ቀጣዩን ትዉልድ ታሳቢ ያደረገ ከተማ ለመገንባት ...
11/01/2026

ኑ የታርጫ ከተማ ሁሉ ዓቀፍ ኮሪደር ልማት በጋራ እናልማ!!!
🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌
👉 የታርጫ ከተማ አስ/ር ከተማዋን ለኑሮ ምቹና ቀጣዩን ትዉልድ ታሳቢ ያደረገ ከተማ ለመገንባት ቆርጦ የተነሳ ሲሆን ይህንን ለማሳካት የልማት ወዳድ የሆኑ ኢትዮጵያንና ትዉልደ ኢትዮጵያን በሀሳብ፣ በገንዘብና በጉልበት እንድሳተፉ ጥሪ በማድረግ ወደ ሥራ ገብቷል፣
ሁላችንም እንሳተፋለን የተጀመረዉን ልማት ዳር እናደርሳለን!!!!!
👉 የታርጫ ከተማ አስተዳደር ኮሪደር ልማት አካዉንት 1000737424379

Daniel Desta

" የታርጫ ከተማ ዛሬ በፈጣን ልማትና ተስፋ ሰጭ እድገት ላይ መገኘቷን በግልጽ እያሳየች ሲሆን፣ ይህ እድገት የመንግስትና የሕዝብ የተባባረ ጥረት ውጤት መሆኑን በኩራት እገልጻለሁ።"      ...
06/01/2026

" የታርጫ ከተማ ዛሬ በፈጣን ልማትና ተስፋ ሰጭ እድገት ላይ መገኘቷን በግልጽ እያሳየች ሲሆን፣ ይህ እድገት የመንግስትና የሕዝብ የተባባረ ጥረት ውጤት መሆኑን በኩራት እገልጻለሁ።"
አቶ ባትሳ ወንድሙ
-------------------------------------------------------------
እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን በሰላም፣ በጤናና በደስታ አደረሳችሁ።

ይህ ታላቅ መንፈሳዊ በዓል የፍቅር፣ የአንድነትና የተስፋ መልዕክት የሚያስተላልፍ በመሆኑ፣ እኛም እነዚህን እሴቶች በሕይወታችን በመተግበር ከተማችንን በጋራ ማሳደግ ይገባናል።

ታርጫ ከተማ ዛሬ በፈጣን ልማትና ተስፋ ሰጭ እድገት ላይ መገኘቷን በግልጽ እያሳየች ሲሆን፣ ይህ እድገት የመንግስትና የሕዝብ የተባባረ ጥረት ውጤት መሆኑን በኩራት እገልጻለሁ።

በዚህ አጋጣሚ በከተማችን በሆቴልና ቱሪዝም፣ በከተማ ግብርና፣ በቤቶች ግንባታና በሌሎች የኢንቨስትመንት ዘርፎች ተሰማርታችሁ ለመስራት የምትፈልጉ ሁሉ፣ በታርጫ ከተማ በስትራቴጂክ ቦታዎች የተዘጋጀ የከተማ መሬት መኖሩን እየገለጽኩ ፣ “ኑ ኢንቨስት አድርጉ፤ ታርጫን አብረን እናልማ” የሚል ጥሪዬን በዚህ አጋጣሚ አቀርባለሁ።

መልካም በዓል! በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ! 🙏

✍️ አቶ ባትሳ ወንድሙ ‎የታርጫ ከተማ አስተዳደር
‎ማዘጋጀ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት ኃላፍ

‎ታህሳስ 28/4/2018 ዓ/ም
‎ታርጫ

የመንገድ ዳር ኮሪደር ልማት በሀገራችን አያሌ ውድ እና ውብ ዘመናዊ ከተሞችን የሚፈጥር አዲሱ የፓርቲ ኢንሼቲቭ ነው። አቶ ባቲሳ ወንድሙ በኮሪደር ልማት ከተሞች ማሕበራዊ ግንኙነታቸውን ማጠናከ...
03/01/2026

የመንገድ ዳር ኮሪደር ልማት በሀገራችን አያሌ ውድ እና ውብ ዘመናዊ ከተሞችን የሚፈጥር አዲሱ የፓርቲ ኢንሼቲቭ ነው። አቶ ባቲሳ ወንድሙ

በኮሪደር ልማት ከተሞች ማሕበራዊ ግንኙነታቸውን ማጠናከር፣ የእግረኞችን ደህንነት እንዲጠበቅ እና ንፁህ አየር እንዲነፍስ ማድረግ የሚያሰችልም ነው።

የኮሪደር ልማቱ ዘላቂ ልማት የሰፈነበት እና ለኑሮ ምቹ እንድሁም "ስሉጥ" ከተማ እውን ማድረግን ያለመ ሰፊ የከተማ ንድፍ አካል ነው። አካባቢው አረንጓዴ ገጽታ እና መንገዶቹም በእነዚህ ዛፎች ለማስጌጥ ኮሪደር ልማት ትልቅ መፍትሔ ነው።

ልማቱ ለእግረኛ ደህንነትም ቅድሚያ ይሰጣል። የብስክሌት መስመሮች ዝርጋታን እና የሕዝብ ማመላለሻ መቀላጠፍን እና የእግረኛ ደህንነትን ያስቀደመ ነው።

በከተማችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከፍተኛ የመንገድ ኮሪደር ልማት እንቅስቃሴ እየተከናወነ ይገኛል። ይህም እየተገነቡ ያሉ የኮሪደር ልማት ሥራዎች ከተማይቱን ውብ እና ሳቢ እንደሚያደርግ ይታመናል።

የታርጫ ከተማ አስተዳደር የሁሉ አቀፉ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን የመንገድ መብራት፣ የዉሃ ፋውንተን፣ የህዝብ መዝናኛ፣ የወንዝ ዳርቻ ልማትና የአረንጓዴ ፓርኮች ሥራ የእግረኛ መንገድ (ወክ ዋይ)እና የሳይክል መንገድ ግንባታ በተቀናጀ መልኩ መላው የከተማችን ነዋሪዎችን በማሳተፍ ለማስቀጠል ጥረቶች እየተደረጉ ይገኛል።

የታርጫ ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገ/ት ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ ባቲሳ ወንድሙ የታርጫ ከተማ ኘላን የጠበቀና በአጭር ጊዜ የታለመለትን የከተማ ውቤትንና ጥራትን በጠበቀ መልኩ ለነዋሪዎች ምቹና ሳቢ ከተማ ለመገንባት የሚያስችሉ ሁኔታዎች እንዳሉ ገልጿል። በከተሞች ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚ የሚያደርግ አካታች የልማት ሥራ እንዲኖር የሚያደርግ መሆኑንም ጨምረው ገልጿል፡፡

ከኮሪደር ልማት በተጨማሪ የታርጫ ከተማን ደረጃ ለማሻሻል የሚያስችሉ የቤቶች ግንባታ ደረጃ ማሻሻልና ለሎች የተለያዩ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
እነዚህም እየተከናወኑ ያሉ የመሰረተ ልማት ሥራዎች የከተማ ገጽታ ከመቀየር ባለፈ ዜጎች በልማት ሥራዎች ላይ የሚያደርጉት ተሳትፎ እንዲነቃቃ እያደረገ መሆኑንም ነው አቶ ባቲሳ የገለጹት፡፡

ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግ የአካባቢ ነዋሪዎች እና ሰው ተኮር የኮሪደር ልማትን እየተሰራ እንደሆነና በአንሰተኛ መንገድ ዳር ሥራ ላይ የሚተዳደሩ ዜጎችም ምቹ ሁኔታ እየተፈጠረላቸው እንደሚገኝ ገልፀዋል።

በከተማ የጀመሪያ ምዕራፍ 2,085 ካ.ሜ ከወጣቶች እሰከ ሆስፒታል ድረስ የመብራት ዳር መስመር 1.1 ኪሎ.ሜትር ፣ ከላይኛው ንግድ ባንክ አሰከ ኮሬ 400 ሜትር መንገድ ዳር መብራት ፣ ከተለሀይማኖት አደባባይ እሰከ ባህል ማዕከል 1.7 ኪሎ.ሜትር መንገድ ዳር መብራት፣ አምሰት የሚዲያንን አጥር 3.2 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የተሰራ ሲሆን በቀጣይ የውሃ ፋውንተን 2400 ኪሎ ሜትር ላይ የሚያርፍ ፣ የህዝብ መናፈሻ 1500ካ.ሜ ፣በኮብልስቶን 3ሺህ ካ.ሜ ፣ዲች 300 ካ.ሜትር የወጣቶች እሰከ ሆስፒታል የእግረኛና የሳይክል መንገድ 1.18 ኪ.ሜ 6 ሄ/ር አረንጓዴና የወንዝ ዳርቻዎችን በኮሪደር ሥራ ለማልማት መታቀዱን ገልጸዋል።

ሥራውን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ በፍጥነት እየተሠራ መሆኑንም ተናግሯል ። የኅብረተሰቡን ጥያቄ ለመፍታት እና የከተሞችን የረጂም ጊዜ የእድገት ህልም ታሳቢ ያደረገ ሥራ እንደሆነም ተጠቁሟል። በመጨረሻም ኅብረተሰቡ በገንዘቡ፣ በጉልበቱ እና በዕውቀቱ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርቧል።

@የታ/ከ/አስ/ር የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን Batisa Wondimu Southwest Communications Tarcha

የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ!!በደቡብ ም/ኢ/ሕ/ክ/መንግሥት በዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ አስ/ር የታርጫ ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት ለመኖሪያና ለንግድ የሚሆን የቦታ ጨረታ አውጥቷል።የከተ...
31/12/2025

የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ!!

በደቡብ ም/ኢ/ሕ/ክ/መንግሥት በዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ አስ/ር የታርጫ ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት ለመኖሪያና ለንግድ የሚሆን የቦታ ጨረታ አውጥቷል።

የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 መሰረት ለመኖሪያ 43 ቦታዎችን ለንግድ 15 ቦታዎችን በአጠቃላይ 58 ቦታዎችን በ2018 ዓ.ም የ1ኛ መደበኛ የሊዝ ጨረታ የወጣ መሆኑን የታርጫ ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገ/ት ጽ/ቤት ያሳውቃል።

የታርጫ ከተማ አራት ትልልቅ መግቢያ በር ያላትና ከቀን ወደ ቀን በሚያስገርም እድገት ፍጥነት ላይ የሚትገኝ ታርጫ ከተማና በተንጣለለው የታርጫ ሜዳ ላይ ለልጅ ልጅ የሚሆን ቋሚ ቅርስ ማስቀመጥ ብልህነት ነው።

የሊዝ ሰነድ ሺያጭ ለመኖሪያ ቤት 300 (ሶስት መቶ ብር) ለንግድ 400 (አራት መቶ ብር) እነደሆነ የታርጫ ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ ጽ/ቤት ም/ሀላፊና የመሬት ማኔጀመንት እና አሰተዳደር ዘርፍ ሀላፊ ይገልፃሉ።

ስለሆነም ከታህሳስ 23/2018 ዓ.ም እስከ ጥር 7/2018 ዓ.ም ደረስ ባሉ ቀናት የጨረታ ሰነድ በመግዛት የቤት ባለቤት እንድትሆኑ የታርጫ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ጥሪ ያስተላልፋል።

"እኔም የከተማዬ የጽዳት አምባሳደር ነኝ" በሚል መሪ ሀሳብ በከተማችን ታርጫ የተለመደ ሳምንታዊ የጽዳት ዘመቻ ተካሂዷል።የታርጫ ከተማ ማዘጋጀ ቤታዊ አገ/ት ጽ/ቤት ስራአስኪያጅ አቶ ባቲሳ ወ...
30/12/2025

"እኔም የከተማዬ የጽዳት አምባሳደር ነኝ" በሚል መሪ ሀሳብ በከተማችን ታርጫ የተለመደ ሳምንታዊ የጽዳት ዘመቻ ተካሂዷል።

የታርጫ ከተማ ማዘጋጀ ቤታዊ አገ/ት ጽ/ቤት ስራአስኪያጅ አቶ ባቲሳ ወንድሙ የሳምንታዊ የጽዳት ዘመቻ መርሀ-ግብር በተለያዩ መንደሮች በዛሬው ቀን ያረሰጀመሩት ሲሆን በዘመቻው ላይ የተለያዩ በጎ የፈቃደኞች፣ የከተማ አስ/ር አመራር አካላትና የተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች በመሳተፍ በተለያዩ ቦታዎች የተሰበሰበውን የደረቅ ቆሻሻ የማስወገድ ሥራ አከናውነዋል።

በተጨማሪም በማዘጋጃ ቤቱ ተሸከርካሪዎች አማካኝነት ከሚደረገው መደበኛ የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ሂደት በተጨማሪ በማህበር በተደራጁ በግል ጋራዎችም ጭምር የሚከናወነው የቤት ለቤት የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ሥራ ተሰርቷል።

በስተመጨረሻም በከተማው የሚገኙ የንግድ ተቋማትና የመኖሪያ ቤቶች 20/50 ሜትር ራድየስ ፊት ለፊታቸው ላይ ያለው ቦታ በአግባቡ በማጽዳት ቆሻሻን በተገቢው መልኩ አጠራቅመው እንዳይዙ የሚያሰገድደውን ደንብ በተገቢ መልኩ ማክበር እንዳለባቸው በማስገንዘብ ግዴታቸውን ደግሞ በማይወጡ አካላት ላይ እርምጃው ተጠናክሮ የምቀጥል መሆኑን የታርጫ ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገ/ት ጽ/ቤት የከተማ ጽዳት አስተዳደርና አረንጓዴ ልማት ሥራ ሂደት አስተባባሪ አቶ በለጠ በቀለ አሳስቧል።

Batisa Wondimu Tarcha Town Municipality Southwest Communications

ኑ የታርጫ ከተማ ሁሉን ዓቀፍ የኮሪደር ልማትን በጋራ እናልማ!‎‎የታርጫ ከተማ አስተዳደር ከተማዋን ለኑሮ ምቹ፣ ለቀጣዩ ትውልድም ታሳቢ ያደረገች ዘመናዊ ከተማ ለመገንባት ቆርጦ ተነስቶ ወደ ...
26/12/2025

ኑ የታርጫ ከተማ ሁሉን ዓቀፍ የኮሪደር ልማትን በጋራ እናልማ!

‎የታርጫ ከተማ አስተዳደር ከተማዋን ለኑሮ ምቹ፣ ለቀጣዩ ትውልድም ታሳቢ ያደረገች ዘመናዊ ከተማ ለመገንባት ቆርጦ ተነስቶ ወደ ሥራ ገብቷል። ይህንን ታላቅ ዓላማ ለማሳካት ልማትን የሚወዱ ኢትዮጵያንና ትውልደ ኢትዮጵያን እንዲሁም በመላው ሀገርቱ የሚገኙ የዳውሮ ተወላጆች በሙሉ በሀሳብ፣ በእውቀት፣ በገንዘብና በጉልበት እገዛ በማድረግ በዚህ ሀገርን በሚያሻግር ተግባር እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርቧል።

‎ይህንን የልማት ጥሪ በደስታ በመቀበልና በፍጥነት በመቀላቀል ልማት ወዳድ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ከቅርብም ሆነ ከሩቅ የተጀመረውን ልማት ለማፋጠን ፈጣን እና አስደናቂ ምላሽ እየሰጡ ይገኛሉ። ይህ ተሳትፎ አከባቢያችንን ለማልማትና ከተማችንን ለማሳደግ የሚደረገውን ጥረት የሚያበረታታ ሲሆን በዚህ ተግባር አለኝታነታቸውን ያሳዩ ግለሰቦችም ሆነ ተቋማት ለሀገር እድገት ያለውን ፍቅርና የማይተካ ብርቱ ጥረት በተግባር የሚያመላክት ነው።

‎ለዚህ ፈጣን እና አስተማማኝ ምላሽ በታርጫ ህዝብ ስም እጅግ በጣም እያመሰገንኩ፣ አሁንም የተጀመረው ትብብር በይበልጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪዬን አስተላልፋለሁ።

‎እጅ ለእጅ ተያይዘን ከተማችንን እናለማለን፤ ወደ ከፍታ ማማ በጋራ እናወጣለን!

‎የታርጫ ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት
‎ሥራ አስኪያጅ ‎አቶ ባትሳ ወንድሙ

Tarcha Town Municipality Southwest Communications Batisa Wondimu Daniel Desta

'' በዛሬው ዕለት  የታርጫ ከተማ አስ/ር ወጣቶች የከተማውን ውቤትና ጽዳት የመጠበቅ ሥራ በቅንጅት ቀጥሏል።ከተማችን የሁላችንም መኖሪያ ናትና ጽዱ እና ምቹ ከተማ እንዲኖረን የከተማው ማህበረ...
25/12/2025

'' በዛሬው ዕለት የታርጫ ከተማ አስ/ር ወጣቶች የከተማውን ውቤትና ጽዳት የመጠበቅ ሥራ በቅንጅት ቀጥሏል።

ከተማችን የሁላችንም መኖሪያ ናትና ጽዱ እና ምቹ ከተማ እንዲኖረን የከተማው ማህበረሰብ እና ወጣቶች በአጠቃላይ በዚህ የጽዳት ዘመቻ እንዲትሳተፉ ጥሪ እናቀርባለን።''

የታ/ከ/ማ/ቤት ሥራ አስክያጅ አቶ ባቲሳ ወንድሙ

በታርጫ ከተማ የሕዝብ ውይይት መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል።"የጉባ ብስራቶች፤ የመደመር መንግስት ትሩፋቶች'' በሚል መሪ ቃል በዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ ሕዝባዊ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነ...
21/12/2025

በታርጫ ከተማ የሕዝብ ውይይት መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

"የጉባ ብስራቶች፤ የመደመር መንግስት ትሩፋቶች'' በሚል መሪ ቃል በዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ ሕዝባዊ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ ባስተላለፉት መልዕክት፦ የሕዝብን የልማት አቅሞች በማቀናጀት ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

መድረኩ የሕዝብን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመፍታትና ተግዳሮቶችን በጋራ ለማለፍ ትልቅ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።

ባለፉት የለውጥ ዓመታት በዞኑ ውጤታማ ሥራዎች መከናወናቸውን ጠቅሰው፣ በቀጣይም ሕዝብን ያሳተፉ ሰው ተኮር ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

በውይይቱ ላይ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችና አመራሮች በመሳተፍ ላይ እንደሚገኙ ከዞኑ ኮሚዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

#ዳውሮ #ታርጫ #ልማት #ኢትዮጵያ

ከቀን ግብይት በተጨማሪ የምሽት ገበያው የደመቀው አዲሱ የታርጫ ከተማ ገበያ ሶስተኛውን ሳምንት ይዟል።ከእንሰት ምርቶች እስከ እንስሳት ተዋጽኦ፣ከፋብሪካ ምርቶች አስከ ዕደ_ጥበብ ምርቶች በአን...
19/12/2025

ከቀን ግብይት በተጨማሪ የምሽት ገበያው የደመቀው አዲሱ የታርጫ ከተማ ገበያ ሶስተኛውን ሳምንት ይዟል።

ከእንሰት ምርቶች እስከ እንስሳት ተዋጽኦ፣ከፋብሪካ ምርቶች አስከ ዕደ_ጥበብ ምርቶች በአንድ ቦታ ለግብይት ምቹ ሆኖ የቀረበበት አዲሱ የታርጫ ገበያ ተመራጭ ሆኗል።

ነባሩ ገበያ ቦታ ለውጥ ከተደረገ በኃላ ሶስተኛ ሳምንቱን የያዘ ሲሆን፣ የግብይት ሂደቱ የተሻለ ተደራሽነት፣ ምቹ አከባቢና ሰፊ ቦታ በመሆኑ የገበያው እንቅስቃሴ እየተጠናከረ መቷል።

‎አዲሱ ገበያ የከተማውን ኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ከፍ የሚያደርግ፣ለህብረተሰቡ ተደራሽ የሆነና እና ለግብይቱ ምቹና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችልም ነው።

ገበያው ከቀኑ ግብይት ባሻገር በምሽት ግብይት ሳምንቱን በሙሉ የደመቀ ሲሆን ከተማ አስተደደሩ ለምሽት ገበያ ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል።

መንግስት በሰው ሰራሽና ተፈጥሮአዊ በሆኑ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ምክንያቶች የሚመጣዉን የኑሮ ውድነት ለመቀነስ የተለያዩ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ይገኛል፡፡

የምሽት ገበያ የዋጋ ግሽበትን ለመቀነስ፣ አምራችና ሸማቹን በቀጥታ በአቅራቢያው በማገናኘት፣ የዋጋ ንረትን ከማረጋጋት ባለፈ በሕገ ወጥ ደላሎች አማካይነት የሚፈጠረውን የንግድ አሻጥር በማስወገድ እና ሕጋዊ የግብይት ሥርዓትን በማስፈን ህብረተሰቡ ፍትሃዊ ተጠቃሚነቱ ይረጋገጥ ዘንድ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ከፍ ያለ ነው።

ሸማች ማህበረሰቡም የተፈጠረዉን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም አዲሱ ገበያ ተጠቃሚ እንዲሆን መልዕክታችን ነዉ።

አድራሻ :_ከታርጫ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጎን ለጎን በተለምዶ ዶሮ እርባታ መንደር

Address

Dawro Zone
Tarch'a S**o

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tarcha Town Municipality posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share