Dawuro Zone Health Department የዳውሮ ዞን ጤና መምሪያ

Dawuro Zone Health Department የዳውሮ ዞን ጤና መምሪያ Dawuro Zone Health Department supports zonal health system both in preventive and curative approaches.

It is known that prevention is less prodigal than treatment that is 1 dollar to 34 dollars.

05/06/2026
ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የማህበረሰብ ሞዴል መድኃኒት ቤት ተመረቀበዳውሮ ዞን ቶጫ ወረዳ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የማህበረሰብ ሞዴ...
04/06/2026

ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የማህበረሰብ ሞዴል መድኃኒት ቤት ተመረቀ

በዳውሮ ዞን ቶጫ ወረዳ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የማህበረሰብ ሞዴል መድኃኒት ቤት በይፋ ተመረቀ።

የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ የምረቃው ፕሮግራም ላይ ተገኝተው ምረቃቱ ከምርጫ ማግስት መሆኑ ለየት ያደርገዋል በማለትና ከምርጫ ጋር የተያያዙ ሥራዎች በስኬት መጠናቀቃቸውን ተከትሎ ሁሉም መዋቅር ወደ መደበኛ የልማት ሥራው እንዲገባ አሳስበዋል።

መንግስት የህዝቡን ጤና ለመጠበቅ ጥረት ቢያደርግም የመድኃኒት አቅርቦት እጥረት ለዘርፉ ትልቅ ማነቆ ሆኖ መቆየቱን ዋና አስተዳዳሪው በመጠቀም ይህንን ችግር ለመቅረፍ የቶጫ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ያደረገው እንቅስቃሴ የሚመሰገን መሆኑን ገልጸው የዞኑ አስተዳደር አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም አረጋግጠዋል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ምትኩ የማህበረሰብ ሞዴል መድኀኒት ቤት በዳውሮ ዞን 3 ሲሆን በክልሉ 22 የማህበረሰብ ሞዴል መድኀኒት ቤት መመረቁን አስታውቀዋል።

የቶጫ ሆስፒታል በአስፈላጊ ግብዓቶችና በሰለጠነ የሰው ኃይል ተደራጅቶ ወደ ሥራ መግባቱ የአቅርቦት ቅሬታዎችን በዘላቂነት ለመፍታት ትልቅ እገዛ አለው ብለዋል።

የዳውሮ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ያዕቆብ ለንጫ እንደተናገሩት ይህ መድኃኒት ቤት ከሌሎቹ ለየት የሚያደርገው በህዝቡ ፍላጎት ላይ ተመስርቶ መደራጀቱ ነው በማለት ይህም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከመፍታት ባለፈ የህዝቡን እርካታ እንደሚያሳድግ ገልጸዋል።

የቶጫ ወረዳ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ አቶ ውበቴ ኡቴ ሆስፒታሉ የለውጡ ማግስት ፍሬ መሆኑን ጠቅሰው፣ የነበረውን የመድኃኒት እጥረት ለመቅረፍ ሞዴል ፋርማሲው መገንባቱን ገልጸዋል።

የተመረቀው ሞዴል ፋርማሲ በራሱ ራሱን የቻለ የፋይናንስ ሥርዓት (Revolving Fund) የሚተዳደር በመሆኑ መድኃኒቶች ሳይቋረጡ በቋሚነት እንዲቀርቡ ትልቅ መፍትሔ እንደሚሆን አብራርተዋል።

የዳውሮ ዞን ጤና መምሪያ የህብረተሰብ ጤና ዝግጁነትና ምላሽ ሰጭነትን የሚያጠናክሩ ከ3.4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያዎጡ የኮምፒውተርና ታብሌት ድጋፍ አደረገ፡፡---------------------...
03/06/2026

የዳውሮ ዞን ጤና መምሪያ የህብረተሰብ ጤና ዝግጁነትና ምላሽ ሰጭነትን የሚያጠናክሩ ከ3.4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያዎጡ የኮምፒውተርና ታብሌት ድጋፍ አደረገ፡፡
------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ታርጫ፤ ግንቦት 25/2018 ዓ.ም (የዳውሮ ዞን ጤና መምሪያ)
የዳውሮ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ያዕቆብ ሌንጫ በርክክቡ ወቅት መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ሃገራችን ዲጂታል ኢትዮያን እውን ከማድረግ አኳያ በጤናው ዘርፍ የዲጂታል ጤና ስርዓትን እየተገበረች ትገኛለች ብለዋል፡፡
በዚህም መሰረት የህብረተሰብ ጤና ዝግጁነት የበሽታ ቅድመ ማስጠንቀቂያና ቅኝት ስርዓትን ለማጠናከር እንዲሁም የምላሽ አቅምን ለማዘመን የዲጂታል ጤና መተግበሪያ መሳሪያዎች መሰራጨቱን ገልፀዋል፡፡
ድጋፉ ለ 10 ወረዳና 4 ከ/አሰ ጤና ጽ/ቤቶች፤ለ 4 ሆስፒታሎችና ለ 8 ጤና ጣቢያ ኮምፒውተር የተሰጠ ሲሆን የበሽታ ቅኝትና ምላሽ ስራ ለሚሰሩ የጽ/ቤት ባለሙያዎች ደግሞ 14 ታብሌት ተሰጥቷል፡፡
አቶ ያዕቆብ ሌንጫ እናዳሉት ይህ ድጋፍ በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩትና በክልል ጤና ቢሮ በኩል የተደረገ ሲሆን በአጠቃላይ 3. 4 ሚልየን ብር በላይ ወጭ ተደርጎበታል ብለዋል፡፡
ወረዳዎች የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር የልህቀት ማዕከል ለመሆን እንዲሰሩ ያሳሰቡት የጤና መምሪያው ኃላፊ ወቅታዊ የበሽታ ስርጭት መረጃን በጥራት በማስተላለፍ የመረጃ ወቅታዊነትና ሙሉነትን ማስጠበቅ አለብን ብለዋል፡፡
በመጨረሻም የተሰጡ ግብዓቶችን በአግባቡና በኃላፊነት እንዲጠቀሙ አሳስበዋል፡፡
ዳውሮ ዞን ጤና መምሪያ ነው።

በዳዉሮ ዞን በጤና ጣቢያዎች የሚሰጡ የጤና አገልግሎቶችን ለማሻሻል የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ ላይ ጥምረት ለጥራት  በሚል መሪ ቃል የ2018 በጀት ዓመት የ10 ወራት በ5ቱ መሪ ጤና ጣቢያ...
29/05/2026

በዳዉሮ ዞን በጤና ጣቢያዎች የሚሰጡ የጤና አገልግሎቶችን ለማሻሻል የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ ላይ ጥምረት ለጥራት በሚል መሪ ቃል የ2018 በጀት ዓመት የ10 ወራት በ5ቱ መሪ ጤና ጣቢያዎች የአፈጻጸም ምክክር መድረክ ተካሂዷል፡፡
ግንቦት 21/2018 ዓ/ም
ታርጫ፤
ጤና መምሪያው በተሻሻለው የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ ጥምረት ለጥራት (EPAQ) መመሪያ ላይ ያተኮረ የአፈፃፀም ምክክር መድረክ በዞን ስር በሚገኙ በአምስት መሪ ጤና ጣቢያዎች አካሂዷል ።

በጤና ጣቢያዎች መካከል ያለው ትስስርን በማጠናከር በጤና ጣቢያ ደረጃ የተሻለ አገልግሎት ለህብረተሰቡ ለመስጠት የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ ጥምረት ለጥራት መመሪያን መተግበር ወሳኝ እንደሆነ ተገልጸዋል።

በመረሃ-ግብሩ አምስት መሪ ጤና ጣቢያዎች እና 18 ተከታይ/አባል የሆኑ ጤና ጣቢያዎች የተገኙ ስሆን፣ በመሪ ጤና ጣቢያዎች የተከናወኑ የ2018 ዓ.ም የአስር ወራት አፈፃፀም ሪፖርት ለተሳታፊዎች ቀርቦ በሰፊው ዉይይት ተካሂዶበታል፡፡
የዳዉሮ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ያዕቆብ ሌንጫ እንደገለፁት ለህብረተሰቡ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ለመስጠት መመሪያውን በመተግበር ጤና ተቋማት እርስ በርስ ልምድ ልዉዉጥ ከማድረግም ባሻገር የተሻለ ተሞክሯቸዉን መማማር ያስፈልጋል ብለዋል።
መመሪያውን ሙሉ በሙሉ በመተግበር አንጻር እንደ ዞን ብዙ ስራዎች ይጠበቃል ያሉት አቶ ያዕቆብ በተለይ ከፍተኛ አመራሩ ጨምሮ የዘርፉ ባለሙያዎች በቁርጠኝነት እንዲሰሩም መልዕክት አስተላልፈዋል ።

በዞን ጤና መምሪያ በሽታ መከላከልና ጤና ማጎልበት ሥራ ሂደት አስተባባር አቶ ስዩም ከበደ በበኩላቸው የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ ጥምረት ለጥራት በጤና ጣቢያዎች መካከል የውድድር መንፈስን በመፍጠር የተሻሉ አገልግሎት ለህብረተሰቡ ለመስጠት ያለው ፋይዳ ጉልህ መሆኑን ገልጸዋል።
በጥምረቱ መሰረት አንድ የተሻለ ጤና ጣቢያ በስሩ አራት አባል ጤና ጣቢያዎችን በመደገፍ አፈጻጸማቸውን በየጊዜው በመገምገም የአገልግሎት ጥራታቸው ከፍ እንዲል እንደሚያግዝም አቶ ስዩም ጠቁመዋል ።

ተሳታፊዎች በበኩላቸው በየሥራ ክፍሉ የተሠሩ ሥራዎችን ተዛዋውረው በጎበኙት ወቅት አበራታች መሆኑን አንስተው በርካታ ልምድ የተገኘ መድረክ መሆኑን በአስተያየታቸው አንስተዋል ።
መርሃ ግብሩ ላይ መሪ ጤና ጣቢያዎች ፡- ኢሰራ ባሌ ጤና ጣቢያ ፡ ያሎ ጤና ጣቢያ፡ ወልደሃኔ ጤና ጣቢያ እና ዋካ ጤና ጣቢያዎች ስሆን፤ ተከታይ ጤና ጣቢያዎች ከዛባ ጋዞ ወረዳ በስተቀር ሁሉም ወረዳ ጤና ጣቢያዎች እንዲሁም ከዞን ጤና መምሪያ የተመደቡ ባለሙያዎች ፣ የወረዳው ጤና ጥ/ጽ/ቤት ማናጅመንትና ባለሙያዎች ፣ በመሪ ጤና ጣቢያዎች ስር የሚገኙ አጠቃላይ ሰራተኞች እና የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ተሳትፈዋል ።

‎ዘገባዉ፡- የዳዉሮ ዞን ጤና መምሪያ

የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን ለማሻሻል ከ2.2 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የህክምና ግብዓቶችን ግዥ መፈጸሙን አስታወቀ ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖​የድሳ ጤና ጣቢያ ለኅብረተሰቡ የሚሰጠውን የጤና...
23/05/2026

የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን ለማሻሻል ከ2.2 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የህክምና ግብዓቶችን ግዥ መፈጸሙን አስታወቀ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
​የድሳ ጤና ጣቢያ ለኅብረተሰቡ የሚሰጠውን የጤና አገልግሎት ይበልጥ ለማሳለጥና የመድኃኒት እጥረትን በዘላቂነት ለመቅረፍ፣ ከ2.2 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተለያዩ የመድኃኒት ዓይነቶች፣ የላቦራቶሪ ሪጄንትና የህክምና መሣሪያዎች ግዥ መፈጸሙን አስታወቋል ።

​የጤና ጣቢያው ኃላፊ አቶ አድማሱ ዳና እንደገለጹት፤ ተቋሙ ለተገልጋዩ ማህበረሰብ የሚሰጠውን አገልግሎት ውጤታማ ለማድረግና በየጊዜው የሚስተዋሉ የአቅርቦት ክፍተቶችን ለመሙላት በትኩረት እየሠራ ይገኛል ሲል ገልጸዋል።

ጤና ጣቢያው በወረዳው የሚገኝ ብቸኛ የጤና ተቋም መሆኑን የጠቆሙት ኃላፊው፣ በሥሩ ከ65 ሺህ በላይ ለሚሆን ተገልጋይ ሕዝብ አገልግሎት የሚሰጥ በመሆኑ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ልዩ ትኩረት እንደሚሻ አብራርተዋል።

አያይዘውም ​አሁን ላይ የተፈጸመው ይሄው የህክምና ግብዓቶች ግዥ፣ በተለይም በመድኃኒት እጥረት ምክንያት ወደ ሌላ የህክምና ተቋም በሪፈር (Referral) የሚሄዱ ሕሙማንን ቁጥር ለመቀነስ እጅግ ወሳኝ ሚና እንዳለው አቶ አድማሱ ገልጸዋል።

​ከዚህ ቀደም በኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥና በነዳጅ እጥረት ምክንያት ይስተጓጎል የነበረውን የላቦራቶሪ አገልግሎት ያለምንም መቆራረጥ ለ24 ሰዓት ለመስጠት የሚያስችል የሶላር (የፀሐይ ብርሃን) ኃይል ዝርጋታ መደረጉንም ኃላፊው አብስረዋል።

ከተከናወነው የሶላር ዝርጋታ ጎን ለጎንም የተቋሙን የምርመራ አቅም ይበልጥ ለማሳደግ የሚረዱ አዳዲስ ዘመናዊ መሣሪያዎች ግዥ ተፈጽሞ ሥራ ላይ ውለዋል ሲል ተናግረው የእናቶችና ሕፃናት ሕክምና ክፍል አገልግሎት ጥራትን ለማዘመን ከዞኑ ጤና መምሪያ ​ሁለት ዘመናዊ የወሊድ አልጋዎች (Delivery Coach)፣​የእናቶችና ሕፃናት የጤና ሁኔታ መከታተያ መሣሪያ (Fetal and maternal health status monitoring machine) እና ​የፅንስ የልብ ምት መከታተያ (Sonotrax/ultrasound pocket Doppler) ዝርጋታ ተደርጎላቸው ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸውን አቶ አድማሱ ዳና ገልጸዋል።

​ኃላፊው በመጨረሻም ለተደረገው ሁለንተናዊ ድጋፍ ለባለድርሻ አካላት በተለይም ለዞኑ ጤና መምሪያ ምስጋናቸውን አቅርበው፤ ጤና ጣቢያው የህክምና ግብዓት አቅርቦትንና የአገልግሎት አሰጣጥን ይበልጥ ለማጠናከር የጀመራቸውን አበረታች ሥራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስገንዝበዋል።

ዘገባው የዲሳ ወረዳ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ነው።

የተቀናጀ የአንጀት ጥገኛ ትላትልና የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ዘመቻው በየትምህርት ቤቶች ተጠኖክሮ ቀጥሏል።‎‎ግንቦት፣10/2018 ዓ.ም ‎‎በዳውሮ ዞን ኢሠራ ወረዳና ባሌ ከተማ ...
18/05/2026

የተቀናጀ የአንጀት ጥገኛ ትላትልና የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ዘመቻው በየትምህርት ቤቶች ተጠኖክሮ ቀጥሏል።

‎ግንቦት፣10/2018 ዓ.ም

‎በዳውሮ ዞን ኢሠራ ወረዳና ባሌ ከተማ አስተዳደር ከግንቦት 7 ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት ዕዴሚያቸው ከ5-14 ዓመት ላሉ ተከታብዎች የሚሰጠው የአንጀት ጥገኛ ትላትልና የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ዘመቻ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

‎በክትባት ዘመቻውም ዕድሜያቸው ከ9-14 ለሆኑ ልጃገረዶች የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት እየተሰጠ መሆኑ ተገልጿል።

‎ክትባቱ በወረዳና በባሌ ከተማ አስተዳደር ስር ለሚገኙ በአጠቃላይ ቀበሊያት እንደሚሰጥ የተጠቆመ ስሆን በዘመቻውም የደም ግፊትን ምርመራ፣የምግብ እጥረት ያለበትንም ህጻናት ልየታና የቲቪ(TB) በሽታ ልየታ አሰሳ ስራዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ከወረዳው ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

‎በተጨማርም ጤናማ ማህበረሰብን ለመፍጠር የሚደረገው ሌሎች የጤና ተግባራት በተያያዥነት እንደሚሰሩ የኢሠራ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ተወካይ አቶ አለማየሁ ዘውዴ ገልጿል።

‎ዘገባው፦የኢሠራ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን
‎]
የተቀናጀ የአንጀት ጥገኛ ትላትልና የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ዘመቻው በየትምህርት ቤቶች ተጠኖክሮ ቀጥሏል።

‎ግንቦት፣10/2018 ዓ.ም

‎በዳውሮ ዞን ኢሠራ ወረዳና ባሌ ከተማ አስተዳደር ከግንቦት 7 ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት ዕዴሚያቸው ከ5-14 ዓመት ላሉ ተከታብዎች የሚሰጠው የአንጀት ጥገኛ ትላትልና የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ዘመቻ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

‎በክትባት ዘመቻውም ዕድሜያቸው ከ9-14 ለሆኑ ልጃገረዶች የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት እየተሰጠ መሆኑ ተገልጿል።

‎ክትባቱ በወረዳና በባሌ ከተማ አስተዳደር ስር ለሚገኙ በአጠቃላይ ቀበሊያት እንደሚሰጥ የተጠቆመ ስሆን በዘመቻውም የደም ግፊትን ምርመራ፣የምግብ እጥረት ያለበትንም ህጻናት ልየታና የቲቪ(TB) በሽታ ልየታ አሰሳ ስራዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ከወረዳው ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

‎በተጨማርም ጤናማ ማህበረሰብን ለመፍጠር የሚደረገው ሌሎች የጤና ተግባራት በተያያዥነት እንደሚሰሩ የኢሠራ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ተወካይ አቶ አለማየሁ ዘውዴ ገልጿል።

‎ዘገባው፦የኢሠራ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን

Alemayehu Zewu, [5/18/26, 7:49 PM][🖼 Photo]Alemayehu Zewu, [5/18/26, 7:49 PM][🖼 Photo]Alemayehu Zewu, [5/18/26, 7:49 PM]...
18/05/2026

Alemayehu Zewu, [5/18/26, 7:49 PM]
[🖼 Photo]

Alemayehu Zewu, [5/18/26, 7:49 PM]
[🖼 Photo]

Alemayehu Zewu, [5/18/26, 7:49 PM]
[🖼 Photo]

Alemayehu Zewu, [5/18/26, 7:49 PM]
[🖼 የተቀናጀ የአንጀት ጥገኛ ትላትልና የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ዘመቻው በየትምህርት ቤቶች ተጠኖክሮ ቀጥሏል።

‎ግንቦት፣10/2018 ዓ.ም

‎በዳውሮ ዞን ኢሠራ ወረዳና ባሌ ከተማ አስተዳደር ከግንቦት 7 ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት ዕዴሚያቸው ከ5-14 ዓመት ላሉ ተከታብዎች የሚሰጠው የአንጀት ጥገኛ ትላትልና የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ዘመቻ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

‎በክትባት ዘመቻውም ዕድሜያቸው ከ9-14 ለሆኑ ልጃገረዶች የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት እየተሰጠ መሆኑ ተገልጿል።

‎ክትባቱ በወረዳና በባሌ ከተማ አስተዳደር ስር ለሚገኙ በአጠቃላይ ቀበሊያት እንደሚሰጥ የተጠቆመ ስሆን በዘመቻውም የደም ግፊትን ምርመራ፣የምግብ እጥረት ያለበትንም ህጻናት ልየታና የቲቪ(TB) በሽታ ልየታ አሰሳ ስራዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ከወረዳው ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

‎በተጨማርም ጤናማ ማህበረሰብን ለመፍጠር የሚደረገው ሌሎች የጤና ተግባራት በተያያዥነት እንደሚሰሩ የኢሠራ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ተወካይ አቶ አለማየሁ ዘውዴ ገልጿል።

‎ዘገባው፦የኢሠራ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን
‎]
የተቀናጀ የአንጀት ጥገኛ ትላትልና የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ዘመቻው በየትምህርት ቤቶች ተጠኖክሮ ቀጥሏል።

‎ግንቦት፣10/2018 ዓ.ም

‎በዳውሮ ዞን ኢሠራ ወረዳና ባሌ ከተማ አስተዳደር ከግንቦት 7 ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት ዕዴሚያቸው ከ5-14 ዓመት ላሉ ተከታብዎች የሚሰጠው የአንጀት ጥገኛ ትላትልና የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ዘመቻ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

‎በክትባት ዘመቻውም ዕድሜያቸው ከ9-14 ለሆኑ ልጃገረዶች የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት እየተሰጠ መሆኑ ተገልጿል።

‎ክትባቱ በወረዳና በባሌ ከተማ አስተዳደር ስር ለሚገኙ በአጠቃላይ ቀበሊያት እንደሚሰጥ የተጠቆመ ስሆን በዘመቻውም የደም ግፊትን ምርመራ፣የምግብ እጥረት ያለበትንም ህጻናት ልየታና የቲቪ(TB) በሽታ ልየታ አሰሳ ስራዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ከወረዳው ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

‎በተጨማርም ጤናማ ማህበረሰብን ለመፍጠር የሚደረገው ሌሎች የጤና ተግባራት በተያያዥነት እንደሚሰሩ የኢሠራ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ተወካይ አቶ አለማየሁ ዘውዴ ገልጿል።

‎ዘገባው፦የኢሠራ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን

የወባ በሽታ ስርጭትን በዘላቂነት ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ተግባራት በትኩረት እየተከናወኑ እንደሚገኝ ተገለጸ ‎የሎማ ቦሳ ወረዳ ጤና  ጽ/ቤት PMI evolve ከተሰኘው ...
15/05/2026

የወባ በሽታ ስርጭትን በዘላቂነት ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ተግባራት በትኩረት እየተከናወኑ እንደሚገኝ ተገለጸ

‎የሎማ ቦሳ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት PMI evolve ከተሰኘው ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር በ18 ቀበሌያት የፀረ ወባ ኬሚካል ርጭት ተደራሽ ለማድረግ ለተከታታይ አምስት ቀናት ለIRS ሠልጣኞች ሥልጠና በመስጠት ወደ ተግባር መገባቱን አስታውቋል።

በወረዳው የወባ በሽታ ስርጭት ያለባቸው በ18 ቀበሌያት ለ25 ሺህ መኖሪያ ቤቶች የኬሚካል ርጭት ተደራሽ ለማድረግ ርጭት እየተካሄደ መሆኑን የተናገሩት የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀይለማርያም ኡማ፥ የወባ በሽታ ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሚደረገው ርብርብ ውስጥ ህብረተሰቡ የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

የፀረ ወባ መከላከያ ኬሚካል ርጭት ስኬታማ እንዲሆን የኬሚካል አያያዝና ርጭት፣ የኬሚካል መርጫ መሳሪያ አጠቃቀምና ጥንቃቄዎችን እንዲሁም ኩታ ገጠም ቤት ለቤት ርጭቱን ለማከናወን የንድፈ ሀሳብና የተግባር ሥልጠና በየደረጃው ለሚገኙ ባለሙያዎች መሰጠቱን ገልጸዋል።

በተለይም በወረዳው 18 ቀበሌዎች ለወባ በሽታ ስርጭት ተጋላጭ መሆናቸውን ጠቁመው ይህንን የስርጭት መጠን ለመቀነስ የቤት ለቤት ኬሚካል ርጭት በሶስት ሳምንታት ውስጥ ተደራሽ እንደሚሆን አብራርተዋል።

ህብረተሰቡ ኬሚካል ርጭት ከተከናወነ በኃላ ለስድስት ወራት ቤቱን ቀለም እና ሌሎች ነገሮችን መቀባት እንደሌለባቸው የጥንቃቄ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

አስተያየታቸውን የሰጡን ባለሙያዎች በበኩላቸው፤ በአካባቢው የወባ ወረርሽኝ በህብረተሰቡ ጤና ላይ የሚያሳድረውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖ ለመከላከል በዘመቻው በንቃት እየተሳተፉ እንደሚገኙ ተናግረዋል ሲል የዘገበው የሎማ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።

በአንጀት ጥገኛ ትላትል/STH/ በሽታዎች አማካኝነት የሚመጡ ዘርፈ ብዙ ጉዳቶችን ለመግታት በተቀናጀ ዘመቻ የሚከናወኑ ተግባራትን በባለቤትነት መፈጸም እንደምገባ ተገለጸከጪ፣ ‎ግንቦት 06/20...
14/05/2026

በአንጀት ጥገኛ ትላትል/STH/ በሽታዎች አማካኝነት የሚመጡ ዘርፈ ብዙ ጉዳቶችን ለመግታት በተቀናጀ ዘመቻ የሚከናወኑ ተግባራትን በባለቤትነት መፈጸም እንደምገባ ተገለጸ

ከጪ፣ ‎ግንቦት 06/2018ዓ.ም (የከጪ ወረዳ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት)

በዳውሮ ዞን የከጪ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት በአንጀት ጥገኛ ትላትል/STH/ በሽታ የሚመጡ አዕምሯዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመቅረፍ የመድኃኒት ዕደላ ዘመቻ ለመጀመር የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠቱ ተገልጿል።

የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነዱን ያቀረቡት የጽ/ቤቱ የድንገተኛ አደጋ ክትትል እና ምላሽ ሥራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ደሳለዉ ሙሉ ለግንዛቤ ማስጨበጫዉ በተሰጠው ትኩረት አቅጣጫ ማህበረሰቡ ተገቢውን አገልግሎት እንዲያገኝ ባለሙያው እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተናግረዋል።

ጨምሮም አቶ ደሳለዉ ከዘመቻዉ ጋር በቅንጅት የሚሰሩ ተግባራትን የብላሃርዚያ፣ የማዕፀን በር ክትባት፣ የደም ግፊት ምርመራ፣ የዓይን ምርመራ፣ የወባ በሽታ የመከላከል እና መቆጣጠር ሥራዎች ጎን ለጎን የሚፈጸሙ ተግባራቶች እንደሆነ አስገንዝበዋል።

የወረዳው ጤና ጥ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ብዙአየሁ ዘርሁን በበኩላቸዉ የአንጀት ጥገኛ ትላትል ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ከሚሰጠዉ ከመድኃኒት ዕደላ ጎን ለጎን የሚከናወኑ ተግባራትን በማቀናጀት መሥራት ይገባል ብለዋል።

ኃላፊዉ ጨምሮም የመድኃኒት ዕደላ ለማካሄድ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች አካል የሆነዉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ዉይይት ባለድርሻዎችን እና ህብረተሰቡን በጉዳዩ ዙሪያ የማንቃት ሥራ መሥራት እንደምጠበቅበትም ገልጸዋል።

በሥልጠናው መነሻ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት፣ ከጤና ባለሙያዎችና ከቀበሌ ጤና ኤክስተንሽን ባለሙያዎች ጋር ዉይይት በተደረገበት ወቅት ከተሳታፊዎቹ የተለያዩ ግልጸኝነት ጥያቄዎች ተነስቶ ማብራሪያ ተሰጥቶ የዘመቻው ግብዓቱ እንደደረሰ ስርጭት እንደሚጀመርም ተገልጿል።

በመጨረሻም አቶ ብዙአየሁ በተሰጠው ሥልጠና የአንጀት ጥገኛ ትላትል መምጫ መንገዱን እና የሚያስከትለው ጉዳት እንደ ማ/ሰብ ከህፃን እስከ አዋቂ በአስተሳሰብ፣ በግለሰቡ ውጤታማነት፣ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ ግንኙነት እና በመሰሉ የሚያስከትለው ተፅዕኖ እጅግ ከፍተኛ መሆኑን በመገናዘብ ባለሙያው አስፈላጊውን ርብርብ በማድረግ ህዝባችንን ከዚህ በሽታ ተፅዕኖ እንዲታደግ ጥሪ አቅርበዋል።

#ዘገባዉ፣ የከጪ ወረዳ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ነው ።

ገዢ ትርክት ለሀገር መንግሥት ግንባታ !

ብዙኃነታችን ዉበታችን ነው!

አብሮነት ትርፍ አለው !

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

ለበለጠ አጋርነት አድራሻዎቻችን ያግኙን፦

facebook፦ https://www.fbkechiworeda.gov.com.et

Telegram፦ https://t.me/kwgca

Twitter፦ https://mobile.twitter.com/KechiAffairዐ

Address

Tarch'a Sodo

Telephone

+251912856886

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dawuro Zone Health Department የዳውሮ ዞን ጤና መምሪያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Dawuro Zone Health Department የዳውሮ ዞን ጤና መምሪያ:

Share