Agew People Force Apf/ የአገው የሰላም ኃይል አሰኃ

  • Home
  • Ethiopia
  • Sokota
  • Agew People Force Apf/ የአገው የሰላም ኃይል አሰኃ

Agew People Force Apf/ የአገው የሰላም ኃይል አሰኃ የአገው ህዝብ ሀይል

ይድረስ -ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ-ለመላው የዋግ ህዝብሹመት ጥላሁን የተባለው በአሁኑ ሰአት የዋግ ኽምራ ምክትል አስተዳዳሪ ሆኖ የዋግን ህዝብ ካላጠፋሁ አልተኛም ብሎ እየዛተ የሚገኘው ...
14/03/2026

ይድረስ
-ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
-ለመላው የዋግ ህዝብ

ሹመት ጥላሁን የተባለው በአሁኑ ሰአት የዋግ ኽምራ ምክትል አስተዳዳሪ ሆኖ የዋግን ህዝብ ካላጠፋሁ አልተኛም ብሎ እየዛተ የሚገኘው ባንዳ በ2013 ምርጫ ጊዜ የዝቋላ ምርጫ ክልል አስተባባሪ ሆኖ ከምርጫ ቦርድ ተረክቦ ሽጦ የበላውን ንብረት በዝርዝር አግኝተናል።ይህ ንብረት ደግሞ ለማንና መቼ እንደተሸጠ እዚህ መፃፉ አስፈላጊ ስላልሆነ ለሚመለከተው አካል የሚቀርብ ይሆናል።

ሹመት ሽጦ የበላው የምርጫ ቦርድ ንብረት ዝርዝር
1.28 ታብሌት
2.20 ፓወር ባንክ
3.3 ላፕቶፕ/pc
4.1ጀኔሬተር

ሹመት ሌባ ብቻም ሳይሆን የሌባ ተባባሪ ነው።አሁንም ያለ የሌለ የዞኑን ንብረት እየሰረቀ፣እያሰረቀ ሌቦች ሲያዙ በወንድሙ አምበሉ ትእዛዝ እንዲፈቱ እያስደረገ ዋግን እያወደማት ይገኛል።ይህ ሌባ ነው እንግዲ በስህተት የተሰጠውን ስልጣን ተገን አድርጎ ሃቀኛ ልጆቻችንን እያሰቃየ የሚገኘው።መላው የዋግ ህዝብ ይህን ግለሰብ ካልታገለ ዋግ ዋጋ ትከፍላለች።

የአማራ ብልፅግናዎች እውነት የዋግን ህዝብ የሚያከብሩ ቢሆኑ ኖሮ እየመጡ ለህዝብ የሚሰሩ አመራሮችን እያወረዱ መሄድ ሳይሆን መጥተው ልማት አስጀምረው ነበር መሄድ የነበረባቸው።አንድም የአማራ ...
12/03/2026

የአማራ ብልፅግናዎች እውነት የዋግን ህዝብ የሚያከብሩ ቢሆኑ ኖሮ እየመጡ ለህዝብ የሚሰሩ አመራሮችን እያወረዱ መሄድ ሳይሆን መጥተው ልማት አስጀምረው ነበር መሄድ የነበረባቸው።አንድም የአማራ ክልል መንግስት አመራር ልማት ሊያስጀመር ዋግ መጥቶ አያቅም።የሆነች ኮሽታ ካለች ከች ይላሉ።

ሰሃላም ቢሆን ህዝቡን ሰብስበው በድሮን ስለተጨፈጨፉት ወንድሞቻችን መጀመርያ ማውራት ትተው፣ህዝብ ማፅናናት ሲገባቸው ፣ስለወደመው ወረዳ እንዴት መልሶ ማልማት እንዳለባቸው ህዝብን ማነጋገር ሲገባቸው፣ህዝብ የወደደውን መሪ አጀንዳ አድርገው ውለው ሲመጡ ለዋግ ህዝብ ያላቸውን ንቀት በግልፅ አሳይተዋል።

ስለዚህ የዋግ ህዝብን ለመምራት በሁሉም ወረዳ የተቀመጣችሁ የወረዳ አመራሮችም የፈረሰን ክልል የሚመሩ ሰዎች ስለመጡ ይሄን መሽቆጥቆጡ ጥሩ አይደለም።መጀመርያ ደብረማርቆስንና ደብረታቦርን በደምብ ይምራ!

''ለኢትዮጵያዊያን ቅርቡ አርሲ ወይስ ኢራን እና እስራኤል?''ከቄስ እስከ ኡስታዝ ሳይቀር '' ክርስቲያኑ ከእስራኤል ሙስሊሙ ከኢራን'' ጎን ተሰልፈው በሚዲያ ሲጨቃጨቁ ማየት ያሳፍራል።  ሰው...
02/03/2026

''ለኢትዮጵያዊያን ቅርቡ አርሲ ወይስ ኢራን እና እስራኤል?''

ከቄስ እስከ ኡስታዝ ሳይቀር '' ክርስቲያኑ ከእስራኤል ሙስሊሙ ከኢራን'' ጎን ተሰልፈው በሚዲያ ሲጨቃጨቁ ማየት ያሳፍራል። ሰውነት ይቅደም!

''አያቶላ፣ኔታንያሁ፣ትራንፕ እያልክ ጎራ ለይተህ ከምትፅፍ አፍንጫህ ስር ለሚጨፈጨፉ ንፁሃን ድመፅ ብትሆን ትፀድቃለህ።''

በሚሳኤል እና በሮኬት ሀገር ተራምደው ለሚዋጉ ጥጋበኞች፣ ድጋፍም ተቃውሞም ለኢትዮጵያዊያን አያምርም

ይልቅ በማንነታቸው ለሚገደሉ ነፁሃናት አንድ መስመር መልዕክት ብትፅፍ ዋጋ አላት። በኢራን እና እስራኤል ድብድብ አንተ በአማረኛ አትድከም፣ ጎጥ እና ሀይማኖት ሳትለይ በየቦታው ለሚገደሉት በአማረኛ ፃፍላቸው።

የኢራን እና እስራኤል ግጭት አለም አውቆት እየዘገበው ነው፣ ያንተን ዘገባ አይፈልጉም፤ ''አለም ያላወቀውን የኢትዮጵያዊያንን የንፁሃን ጭፍጨፋ በማውገዝ ለአለም አሳይ፤

ትኩረት ለአርሲ ንፁሃን ግድያ

27/02/2026

የፊልሙ ርዕስ :- የወልቃይት ጉምጉምታ
ደራሲ :- ዳንኤል ክብረት
ዳይሬክተርና ፕሮዲዩሰር :- አብይ አህመድ

ተዋንያን :- በለጠ ሞላ ፣ ጌታቸው ረዳ
ካሜራ ማን :- ምርጫ ቦርድ
መብራት ያዥ :- አገኘው ተሻገር
ኮንቲኒቲ :- የተከዜ ዘብ ፣ ሃራ መሬት

ቤስት ማን :- የልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 😀

ግብፅ የኢትዮጵያን የባህር በር ፍላጎት ‘ልትደግፍ እንደምትችል’ መግለጿ አነጋጋሪ ሆኗል። ታዲያ ይህን አዲስ የሚመስለውን አቋሟን ቀረብ ብለን ስንመረምር ‘ድጋፏ’ በማያፈናፍን ቅድመ ሁኔታ የ...
25/02/2026

ግብፅ የኢትዮጵያን የባህር በር ፍላጎት ‘ልትደግፍ እንደምትችል’ መግለጿ አነጋጋሪ ሆኗል። ታዲያ ይህን አዲስ የሚመስለውን አቋሟን ቀረብ ብለን ስንመረምር ‘ድጋፏ’ በማያፈናፍን ቅድመ ሁኔታ የታጠረ መሆኑን እንረዳለን።

1. ኢትዮጵያ የባህር በር የምታገኘው በታጁራ ወደብ በኩል ይሆናል፤ ይህን ወደብ ደግሞ ግብፅ በቅርቡ ከጂቡቲ ባደረገችው ስምምነት አስፈርማለች። ይህ ማለት፣ ኢትዮጵያ ግብፅ በምትቆጣጠረው ወደብ ነው የባህር በር የሚኖራት።

1. ይባስ ብሎም፣ ግብፅ የኢትዮጵያን የባህር በር ፍላጎት የምትደግፈው፣ ኢትዮጵያ ከአባይ ወንዝ ጉዳይ የያዘችውን አቋም ካለሰለሰች ነው። ማለትም፡-

ሀ) ኢትዮጲያ ግድቡን ከግብፅ ጋር በጋራ ለማስተዳደር ከተስማማች (የግድቡን ደህንነት፣ የውሃ ፍሰት መጠን ወዘተ)
ለ) ኢትዮጵያ ከእንግዲህ በኋላ በአባይ ተፋሰስ ላይ ሌሎች ግድቦችን ላለመስራት ከፈረመች።

ይህ በግብዝነት የተሞላ የቅድመ ሁኔታ በአብይ ዘመን፣ በተለይ ባለፉት ወራት፣ የግብፅ የመደራደሪያ አቅም (leverage) ምን ያህል እንደፈረጠመ ጠቋሚ ነው።

Agew People Force Apf/ የአገው የሰላም ኃይል አሰኃ

ግብፅ  #በአብይ የዲፕሎማሲ ኩስምንና ክፍተት በመጠቀም የኢትዮጵያ ጎረቤት ሀገራትን በሙሉ ከጠቀለለች በኃላ ... ቀይ ባህር እንድትጠቀሙ ድጋፍ አደርጋለሁ ብላለች ብሎ ፋርሴቡላው እየጨፈረ ነ...
25/02/2026

ግብፅ #በአብይ የዲፕሎማሲ ኩስምንና ክፍተት በመጠቀም የኢትዮጵያ ጎረቤት ሀገራትን በሙሉ ከጠቀለለች በኃላ ... ቀይ ባህር እንድትጠቀሙ ድጋፍ አደርጋለሁ ብላለች ብሎ ፋርሴቡላው እየጨፈረ ነው 😀

ኤርትራ ፣ ሶማሊያ ፣ ጅቡቲ ከመሳሰሉ ሀገራት ጋር ኢትዮጵያ በቀጥታ ስምምነት ልታደርግ የምትችልበትን ካርድ ግብፅ ወስዳው ስታበቃ የህዳሴ ግድብን በጋራ ካስተዳደርን በኪራይ ወደብ እንድትጠቀሙ አደርጋለሁ ማለቷ ምኑ ነው የሚያስጨፍረው ??

ግብፅ በአብይ የዲፕሎማሲ ኩስምናን ምክንያት በቀይ ባህር ላይ ያገኘችው የበላይነት ፣ በከበባ ጎረቤት ሀገራትን የያዘችበት መንገድ ፣ በስምምነት የተቆጣጠረችው ወደቦች ፣ ቀይ ባህር ላይ ያገኘችው ተፅዕኖ ... ዛሬ እንደመደራደሪያ አድርጋ እያቀረበችው ነው።

ፋርሴቡላው ደግሞ ይጨፍራል። ቢያንስ #አብይ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ጥሩ ግንኙነት ቢኖረው ኖሮ ግብፅ ይህንን እድል ፈፅሞ አታገኝም ነበር። ዛሬ ላይ ቀይ ባህር ተጠቃሚ ለመሆን ግብፅ ቁልፉን ይዛለች። ጭራሽ ደግሞ በግብፅ ካርድ የአብይ ስኬት ተብሎ እየተደነሰ ነው።

ሌላው ቀርቶ ግብፅ ከሰሜን አፍሪካ ድረስ መጥታ በጅቡቲ ወደብ ተጠቃሚነት ዙሪያ እንስማማ ፣ የህዳሴ ግድብን በጋራ እናስተዳድር ስትል ፣ የባህር ሀይል ይኖረናል የሚለውን ህልም ግን ተውት ስትል ፣ ተከራይ እንጂ ባለቤት አትሆኑም ፣ የንግድ ኮንቴነር ማራገፊያ እሱንም በግብፅ ቁጥጥር ታገኛላችሁ ...

ምናምን ስትል #የአብይ የዲፕሎማሲ ውድቀትና ፣ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያለን የሻከረ ግንኙነትን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። አብይ ካሁን በኃላ በቃህ ከዚህ በላይ ማስተዳደር አትችልም ሊባል ሲገባው ... የደነዘዘው ፋርሴቡላ ግን ከግብፅ እኩል ይጨፍራል።

... ታሳፍራላችሁ 😀

አብይ ሀገር ሰላም ከሆነች ያፋሽከዋል"ታጋይ መምህር ኪሮስ ሮምሀ" የአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ አዴን ሊቀመንበር ክቡር ታጋይ መምህር ኪሮስ ሮምሀ በፌደራል መንግስት አከራካሪ ቦታዎች ተብለው ...
24/02/2026

አብይ ሀገር ሰላም ከሆነች ያፋሽከዋል"ታጋይ መምህር ኪሮስ ሮምሀ"

የአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ አዴን ሊቀመንበር ክቡር ታጋይ መምህር ኪሮስ ሮምሀ በፌደራል መንግስት አከራካሪ ቦታዎች ተብለው የተለዩ ቦታዎችን በተመለከተ የፌደሬሽን ምክር ቤት ያስተላለፈውን ውሳኔ ህገ መንግስቱን መጣስ ነው ሲል በማህበራዊ ገፁ አስፍሯል።

"ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቅንቁ" ሲል የጀመረው የሊቀመንበሩ ፅሁፍ ብልፅግናን አምነው ወደ አዲስ አበባ የሄዱ የትግራይ ተወላጅ የብልፅግና ሹማምንትንም ብልፅግናን ማመን መጨረሻው ውርደት እንደሆነም ጠቅሷል። ብልፅግና ለትግራይ ብልፅግናዎች ያለውንም ንቀት እያሳየ መሆኑንና ብዙ ጥፋቶች ቢኖሩም የዛሬው ንቀት የተለየ መሆኑን ጭምር በፅሁፉ አስፍሯል።

ሊቀመንበሩ "ምን አይነት መንግስት ነው የገጠመን" ሲል የደመደመው አጭርና ቁም ነገር አዘል እንዲሁም ብልፅግና ሀገር ሰላም ስትሆን ስልጣን ላይ መቆየት እንደማችልና አብይ ሀገር ሰላም ስትሆን እንደ ሱሰኛ እንደሚያፋሽከው ገልጿል።

Address

Waghimra
Sokota

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Agew People Force Apf/ የአገው የሰላም ኃይል አሰኃ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category