የቦምቤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት Bombe Mayor City Office

  • Home
  • Ethiopia
  • Sodo
  • የቦምቤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት Bombe Mayor City Office

የቦምቤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት Bombe Mayor City Office ብልፅግና ፓርቲ ሁለንተናዊ ብልጽግናን የሚያረጋግጥ አካታች ማኅበራዊ ልማት ማረጋገጥ ነው!!

14/08/2026
14/08/2026
ከተረጂነት ለመላቀቅ የተያዘውን ግብ ለማሳካት የሚያስችሉ ውጤታማ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የቦምቤ ከተማ አስተዳደር ግብርና ዩኒቲ አስታወቀ ። #ቦምቤ፣- ነሐሴ 05/2018 ዓ.ም በወላይ...
11/08/2026

ከተረጂነት ለመላቀቅ የተያዘውን ግብ ለማሳካት የሚያስችሉ ውጤታማ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የቦምቤ ከተማ አስተዳደር ግብርና ዩኒቲ አስታወቀ ።

#ቦምቤ፣- ነሐሴ 05/2018 ዓ.ም በወላይታ ዞን ቦምቤ ከተማ አስተዳደር ከከተረጂነት ለመላቀቅ የተያዘውን ግብ ለማሳካት የሚያስችሉ ውጤታማ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የቦምቤ ከተማ አስተዳደር ግብርና ዩኒቲ አስተባባሪ አቶ አማረ አለሙ አስታውቀዋል።

የከተማው ግብርና ዩኒቲ አስተባባሪ አቶ አማረ አለሙ እንደገለጹት ግብርና የኢኮኖሚያችን የጀርባ አጥንት መሆኑን በመረዳት የምርታማነት ግብ ለማሳከት ብሎም የአርሶ አደሩ ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እየተሰራ ያለው ስራ የተሻለ እንደሆነ ገልጸዋል ።

እንደ ከተማ በዘንድሮ መኸር ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግና የአርሶ አደሩ ምርትና ምርታማነት ሊያሳድጉ የሚችሉ አዳዲስ የግብርና ኢኒሼቲፎች በማቅረብ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየተደረገ ያለው ከፍተኛ ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንደለበት አሳስበዋል።

አስተባባሪው አክሎም፣ ‎በዘንድሮው በ2018/9 በጀት ዓመት የመኸር እርሻ የሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ምላሽ ለመስጠት በከተማው እየተከናወኑ ያሉትን ተግባራት ጨምሮ የመኸር እርሻ አርሰው የዘር እጥረት ለገጠማቸው ድጋፍ ለሚሹ የማህበረሰብ ክፍሎች የዘር ድጋፍ ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር በከተማ ደረጃ የተሻለ ስራ እየተሰራ መሆኑን የገለጹት አቶ አማረ በዘንድሮ በጀት አመት ከአምና በበለጠ ውጤት ለማስመዝገብ በትኩረት እየተሰራ በመሆኑን አንስተዋል።

የማህበረሰብ አጋርነትን ለማሳየት እርሻ በሚታረስበት ወቅት በሁሉም ቀበሌዎች ወጣቶች የጉልበት አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

በመኸር ወቅት ሁሉም አርሶ አደሮች የተሻለ ምርት ለማግኘት ጠንክሮ መስራት እንዳለባቸው ያሳሰቡት አስተባባሪው በተለይም የበራስ አቅም ለአደጋ ምላሽ ለመስጠት ማሳዎች ስታረሱ ወጣቶችን በአደረጃጀት ወጥተው የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል።

‎የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ ጊፋታ በዓል መስከረም 10/2019 ዓ.ም ከመላው ኢትዮጵያዊያን ጋር በታላቅ ድምቀት በአደባባይ ይከበራል ‎‎የወላይታ ብሔር የራሱ የሆነ የዘመን መቁጠሪያ (c...
07/08/2026

‎የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ ጊፋታ በዓል መስከረም 10/2019 ዓ.ም ከመላው ኢትዮጵያዊያን ጋር በታላቅ ድምቀት በአደባባይ ይከበራል

‎የወላይታ ብሔር የራሱ የሆነ የዘመን መቁጠሪያ (calendar) አለው፡፡ በወላይታ ባህላዊ የዘመን አቆጣጠር መሠረት ጊፋታ የዓመቱ የመጀመሪያ ወር ስያሜ ነው፡፡ በካሌንደር መሠረቱ የ2019 ጊፋታ በዓል መስከረም 10/2019 ዓ.ም እሁድ ዕለት በደማቅ ሁኔታ ይከበራል።

‎የ2019 የጊፋታ በዓል ዩኒስኮ በተመዘገበበት ዓመት በመሆኑ ከወትሮ በተለየ ሁኔታ በታላቅ ድምቀት በአደባባይ ይከበራል።

‎በዓሉን ከመላው ኢትዮጵያዊያን ጋር በታላቅ ድምቀት ለማክበር አስፈላጊውን የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ ናቸው።

‎ጊፋታ በዓል ከትውልድ ወደ ትውልድ ስተላለፍ የመጣ የወላይታ ብሔር ማንነት መገለጫ የሆነው የአሮጌው ዓመት ማብቅያና የአዲሱ ዓመት የመሸጋገሪያ በዓል ነው፡፡

‎ጊፋታ ማለት፣ ከአሮጌ ወደ አዲስ፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን መሻገር የሚለውን ይገልጻል፡፡

‎የወላይታ ብሔር የራሱ የሆነ የዘመን መቁጠሪያ ያለ ስሆን ጊፋታ የዓመቱ የመጀመሪያ ወር ስያሜ ነው፡፡

‎በዓሉን ከመላው ኢትዮጵያዊያን ጋራ በታላቅ ድምቀት ለማክበር ሁሉም ሰው የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።

‎ !
‎ !

Address

Wolaita S**o
S**o
BT2017

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የቦምቤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት Bombe Mayor City Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share