22/07/2026
ጀግንነትና መልካምነት ለካ ከቤተሰብ የሚወረስ ታላቅ እሴት ነው!
በወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ዳዊት ደሳለኝ በወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ውስጥ ያላቸው የስራ እና የህይወት ጉዞ እውነተኛ የህዝብ አገልጋይነት ምን ማለት እንደሆነ በተግባር ያሳዩበት ነው! እውቀታቸውንና አቅማቸውን ሙሉ በሙሉ ለህዝብ ጤናና ደህንነት በማዋል፣ ዘመናዊና የተቀላጠፈ የአመራር ጥበብን አሳይተዋል።
«በጤናው ዘርፍ የተማረ ተማሪ ስራ አጥ ሆኖ ቤት መቀመጥ የለበትም!» ብለው በሙሉ አቅማቸውና በቆራጥነት የተነሱ፣ ለጤና ባለሙያው የሚገባውን ቦታና ክብር ለመስጠት ሳይወዛወዙ የቆሙ የእውነተኛ ህዝባዊነትና የመልካም አስተዳደር ጀግና መሆናቸውን አስመስክረዋል።
ጀግንነት በቃል ሳይሆን በተግባር፣ በብርታትና ለህዝብ በሚደረግ እውነተኛ አገልግሎት የሚለካ መሆኑን አሳይተዋል።
እንደ አቶ ዳዊት ደሳለኝ ያሉ በጎ አሳቢ፣ አርቆ አስተዋይ እና ልበ-ቀና መሪዎች የህዝብ አለኝታ እና የዘመናችን የቁርጥ ቀን ጀግኖች ናቸው፤ ያደረጉት መልካም ነገር ሁሉ በታሪክና በሰው ልብ ውስጥ ዘላለም ሲታወስ ይኖራል።
ለሚያደርጉት የማይሰለች ጥረትና ለመልካም ስራቸው ትልቅ አክብሮትና አድናቆት ይገባቸዋል!