26/05/2026
የወተት ሀብት ልማታችን ከድህነት መዉጫና የስራ ዕድል መፍጠሪያችን;- አቶ ኡስማን ሱሩር
*********
በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል በከምባታ ዞን ጸዳል ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒዬን ሀምበርቾ የወተት ማምረቻ፣ማቀነባበሪያና ግብይት ማዕከል ምረቃና ርክክብ ፕሮግራም ተካሄደ።
የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባርና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር በፕሮግራሙ መክፈቻ የብልጽግና ፓርቲ የራቀዉን በማቅረብ ፣የማይቻለዉን አስችሎ ፣የከበደዉን አቅሎ ፀጋን በማልማት የህብረተሰብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አበክረን እንሰራለን ብለዋል።
አቅሞችን በማስተባበርና በማቀናጀት፣ ወደተግባር ገብቶ በመስራቱ የአርሶ አደራችንን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ተችሏል ብለዋል።
የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገት ፀጋዎቻችንን በሚገባ ማልማት እንደሚገባም አብራርተዋል።
ግብርናን በማዘመን ምርትና ምርታማነትን በመጨመር ገበያን ለማረጋጋት የከምባታ አርሶ አደሮች ጥሩ ማሳያ እንደሆነም ተናግረዋል።
የወተት ዕሴት በመጨመር ደህንነቱና ጥራቱን የጠበቀ ምርት በማምረት ጤናማና አምራች ዜጋን ለመፍጠር እንደሚሰራ ተናግረዋል።
ልማት በማስተባበር፣ በማለቅ፣ በማስቀጠል እና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የጋራ ርብርብ እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ አቶ አቡቶ አኒቶ ግብርና በሀገራችን ለኢኮኖሚ ዕድገት መፋጠን ወሳኝ ተቋማት ዉስጥ ቀዳሚ ተቋም እንደሆነ ተናግረዋል።
የከምባታ ዞን ዋና አስተዳደር አቶ አረጋ እሼቱ በመድረኩላይ ተገኝተዉ ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጲያ በሁሉም ዘርፎች እያደገች ትገኛለች ለሀገርቱን ኢኮኖሚ እድገት የጀርባ አጥንት የግብርና ዘርፍ አማራጭ የሌለዉ ጉዳይ እንደሆነም ገልጸዋል።
ጠባብ መሬት ባለባቸዉ አከባቢዎች እንደ ከምባታ ዞን የእንስሳ ዘርፍን በሚገባ በማላቅ አርሶ አደሮች በዘርፉ ተጠቃሚ መሆን አለባቸዉ ብለዋል።
የሀምበርቾ ወተት ማምረቻ በቀን እሰከ ሁለት ሺህ ሊትር የማምረት አቅም እንዳለዉ ጠቅሰዉ ምርቱን ትርፋማ ለማድረግ ለዘርፉ ልዩ ትኩረት ሰተዉ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
በፕሮግራሙ የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አኒቶ አቡቶ፣የክልሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪ አና ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩርን ጨምሮ የፌዴራል ፣የክልል፣የዞንና የወረዳ የተለያዩ አመራሮችና አርሶ አደሮች ተሳታፊ ሆነዋል።ሲል የዘገበው ሀላባ ቲቪ ነው።