Paartii Badhaadhina Magaalaa Sanbatee

Paartii Badhaadhina Magaalaa Sanbatee Prosperity Party Media

እንኳን ደስ ያላችሁ !በሰንበቴ ጤና አጠባበቅ ጣቢያየ OR ክፍል የቀዶ ህክምና አገልግሎት ተጀመረ!በሰንበቴ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ የቀዶ ህክምና አገልግሎት ዛሬ በይፋ መጀመሩ ለከተማችንና ለአካ...
17/09/2026

እንኳን ደስ ያላችሁ !

በሰንበቴ ጤና አጠባበቅ ጣቢያየ OR ክፍል የቀዶ ህክምና አገልግሎት ተጀመረ!

በሰንበቴ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ የቀዶ ህክምና አገልግሎት ዛሬ በይፋ መጀመሩ ለከተማችንና ለአካባቢው ህብረተሰብ ትልቅ የጤና አገልግሎት እመርታ ነው።

በተለይም ከወሊድ ጋር ተያይዘው የሚከሰቱ አስቸኳይ የጤና ችግሮች ሲያጋጥሙ እናቶች ለህክምና ወደ ሩቅ ጤና ተቋማት መጓዝ የሚያስከትለውን የጊዜ፣ የመጓጓዣና የወጪ እንግልት ለማስቀረት የአገልግሎቱ መጀመር ወሳኝ ሚና ይኖረዋል።

ይህም አስቸኳይ ህክምና የሚፈልጉ እናቶች በአካባቢያቸው ፈጣንና ተገቢ የህክምና ድጋፍ እንዲያገኙ በማድረግ ከመዘግየት ጋር ተያይዞ ሊከሰት የሚችለውን የጤና ጉዳትና ሞት ለመቀነስ የሚያግዝ ነው።

የአገልግሎቱ ጠቀሜታ በመጀመሪያው ቀንም ተጨባጭ ሆኗል። ሁለት እናቶች በቀዶ ጥገና ልጆቻቸውን በሰላም መገላገል ችለዋል። ይህም በአካባቢው የቀዶ ህክምና አገልግሎት መኖሩ ለእናቶችና ለሕፃናት ህይወት ጥበቃ ያለውን ትልቅ ፋይዳ ያሳያል።

የሰንበቴ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ኑረዲን አህመድ የዚህን አስፈላጊ አገልግሎት መጀመር በማስመልከት ለመላው የከተማዋ ነዋሪዎች፣ ለጤና ባለሙያዎችና ለጤና ተቋሙ አመራር የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

ከንቲባው የቀዶ ህክምና አገልግሎቱ መጀመር ከዚህ በፊት ህሙማንን ለሩቅ ጤና ተቋም ለመላክ የነበሩ እንግልቶችን በማስቀረት፣ የህክምና ጊዜን በማሳጠርና አስቸኳይ ህክምናን በቅርበት በማቅረብ የእናቶችንና የሕፃናትን ህይወት ለመጠበቅ የሚያግዝ ትልቅ ስኬት መሆኑን ገልጸዋል።

Baga gammaddan! Buufata Fayyaa Magaalaa Sanbatee Keessatti Tajaajilli Baqaqsanii Yaaluu Jalqabame! Buufata Fayyaa Magaal...
17/09/2026

Baga gammaddan!

Buufata Fayyaa Magaalaa Sanbatee Keessatti Tajaajilli Baqaqsanii Yaaluu Jalqabame!

Buufata Fayyaa Magaalaa Sanbatee keessatti tajaajilli baqaqsanii yaaluu har’a ifatti jalqabamuun, magaalaa keenyaafi hawaasa naannawaatiif tarkaanfii guddaa guddina tajaajila fayyaa ti.

Keessattuu, rakkoolee fayyaa hatattamaa yeroo da’umsa waliin walqabatan yeroo mudatan, haadholiin yaala argachuuf gara dhaabbilee fayyaa fagoo imaluun kan isaan mudatu rakkoo yeroo, geejjibaa fi baasii hambisuuf jalqabamuu tajaajila kanaa gahee olaanaa qaba.

Tajaajilli kun haadholiin yaala hatattamaa barbaadan naannoo isaaniitti tajaajila fayyaa saffisaa fi barbaachisaa akka argatan taasisuun, tursiisa yaalaa irraa kan ka’e miidhaa fayyaa fi lubbuu darbu uumamuu danda’u hir’isuuf gargaara.

Faayidaan tajaajila kanaas guyyaa jalqabaa irraa eegalee mul’ateera. Haadholiin lama baqaqsanii yaaluun daa’imman isaanii nagaan da’uu danda’aniiru. Kunis tajaajilli baqaqsanii yaaluu naannoo keessatti argamuun lubbuu haadholii fi daa’immanii eeguuf faayidaa guddaa akka qabu kan mul’isuudha.

Kantiibaan Bulchiinsa Magaalaa Sanbatee, Obbo Nuuraddiin Ahimad, jalqabamuu tajaajila barbaachisaa kana ilaalchisee jiraattota magaalaa hundaa, ogeeyyii fayyaa fi hoggansa dhaabbata fayyaatiif ergaa baga gammaddanii dabarsaniiru.

Kantiibaanichi, tajaajilli baqaqsanii yaaluu jalqabamuun rakkoo fi rakkina dhukkubsattoota gara dhaabbilee fayyaa fagoo erguun duraan ture hambisuun, yeroo yaalaa gabaabsuu fi tajaajila yaalaa hatattamaa bakka dhiyoo keessatti kennuun lubbuu haadholii fi daa’immanii eeguuf milkaa’ina guddaa ta’uu ibsaniiru.

🎉 Baga Gammaddan!Qajeelcha Fayyaa Bulchiinsa Saba Oromoo’n gamaggama raawwii hojii bara 2018 gaggeeffameen, Waajjirri Ee...
17/09/2026

🎉 Baga Gammaddan!

Qajeelcha Fayyaa Bulchiinsa Saba Oromoo’n gamaggama raawwii hojii bara 2018 gaggeeffameen, Waajjirri Eegumsa Fayyaa Aanaa Jiillee Dhummuugaa aanota Godinaa Oromoo jala jiran keessaa raawwii hojii gaarii galmeessuun Sadarkaa 2ffaa bahuun beekkamtii argateera.

🏆 Milkaa’inni kun bu’aa hojii cimaa, qindoominaa fi kutannoo ti!

የገቢ አቅምን በማሳደግ የልማትና የሰላም ጥያቄዎችን መመለስ ይገባል! የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት የሥራ እቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2019 በጀት ዓመት ...
17/09/2026

የገቢ አቅምን በማሳደግ የልማትና የሰላም ጥያቄዎችን መመለስ ይገባል!

የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት የሥራ እቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2019 በጀት ዓመት የሥራ እቅድ ትውውቅ መድረክ አካሂዷል።

በመድረኩ የ2018 በጀት ዓመት የገቢ አፈጻጸም በመገምገም፣ የተመዘገቡ ውጤቶችንና የታዩ ክፍተቶችን በመለየት ለ2019 በጀት ዓመት የተያዘውን ዕቅድ በተሳካ ሁኔታ ለመፈጸም የሚያስችሉ የአፈጻጸም አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ተደርጓል።

በመድረኩ የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ አሊ እንደገለጹት፣ የህዝቡን የሰላምና የልማት ጥያቄዎች በአግባቡ ለመመለስ የአስተዳደሩን የገቢ አቅም ማሳደግ ወሳኝ ነው።

በመሆኑም የገቢ አሰባሰብን ለማሻሻል፣ ያሉ የገቢ ምንጮችን በአግባቡ ለይቶ በመጠቀም የገቢ አቅምን ማሳደግ እንዲቻል ሁሉም አካላት በቅንጅትና በትጋት ሊሰሩ እንደሚገባ አቶ አህመድ አሊ አሳስበዋል።

የገቢ ተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ ወደ ዲጂታል ሥርዓት ለማስገባት የተጀመሩ ሥራዎችም ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ዋና አስተዳዳሪው ገልጸዋል። ይህም የገቢ አሰባሰብን በማዘመን፣ የአገልግሎት አሰጣጥን በማቀላጠፍና ተጠያቂነትን በማጠናከር የተቋሙን አፈጻጸም ለማሻሻል ያግዛል ብለዋል።

የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ አሚናት ሁሴን በበኩላቸው፣ በ2018 በጀት ዓመት ከ1.3 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን ገልጸዋል።

በ2019 በጀት ዓመት ደግሞ ከ2.6 ቢሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ ዕቅድ ተይዞ ወደ ሥራ መገባቱን ያስረዱት ወ/ሮ አሚናት፣ ዕቅዱን ለማሳካት ያሉትን የገቢ ርዕሶች በግልጽ በመለየት፣ የገቢ ምንጮችን በሙሉ በማስተዳደርና ሊሰበሰብ የሚገባውን ገቢ በሙሉ በማሰባሰብ ላይ ትኩረት እንደሚደረግ ጠቁመዋል።

የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ኃላፊ አቶ አብዱ ሙሄ በበኩላቸው፣ የገቢ ሥራ የአንድ ተቋም ወይም የአንድ ዘርፍ ኃላፊነት ብቻ በመሆኑ ሊተው የሚችል ሥራ እንዳልሆነ ገልጸዋል።

በመሆኑም የገቢ አቅምን ለማሳደግ ከዕቅድ ዝግጅት እስከ አፈጻጸም ድረስ ሁሉም የሥራ ክፍሎችና ኃላፊዎች የየራሳቸውን ሚና በተገቢው ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በመድረኩ የወረዳና የከተማ የሥራ ኃላፊዎች፣ የገቢና የፋይናንስ ተቋማት ኃላፊዎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈው በ2019 በጀት ዓመት የገቢ ዕቅዱን ለማሳካት በሚያስችሉ የሥራ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት አካሂደዋል።

“በግብርናው ዘርፍ ምርታማነትን በማሳደግ ኢኮኖሚውን ማጠናከር ያስፈልጋል”አቶ አህመድ አሊበአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር “አርቆ ማየት፣ አልቆ መሥራት” በሚል መሪ ቃል ለተከታታይ ...
16/09/2026

“በግብርናው ዘርፍ ምርታማነትን በማሳደግ ኢኮኖሚውን ማጠናከር ያስፈልጋል”

አቶ አህመድ አሊ

በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር “አርቆ ማየት፣ አልቆ መሥራት” በሚል መሪ ቃል ለተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየው የ2019 በጀት ዓመት የፓርቲና የመንግሥት የሥራ ዕቅድ ትውውቅና ውይይት መድረክ ተጠናቀቀ።

የብሔረሰብ አስተዳደሩ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ አሊ በመድረኩ መዝጊያ ላይ እንደገለጹት፣ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በተደራጀ አመራርና በተቀናጀ አሠራር በርካታ የልማትና የአስተዳደር ለውጦች ተመዝግበዋል።

በቀጣይም የአስተዳደሩን የልማት አቅም ይበልጥ ለማጠናከር፣ ከክልሉ የልማት ዕቅድ ጋር በመናበብ እና የአካባቢውን ጸጋና ሀብት በአግባቡ በመለየት የሕዝቡን የልማት፣ የአገልግሎትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በተጨባጭ ሊመልስ የሚችል ዕቅድ አዘጋጅቶ በተግባር መተርጎም እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

አቶ አህመድ በተለይም በግብርናው ዘርፍ የምርታማነት ዕድገት እንዲመዘገብ በማድረግ፣ ያሉትን የአካባቢውን የግብርና ሀብቶች በአግባቡ በማልማትና የምርት አቅምን በማሳደግ የአካባቢውን ኢኮኖሚ ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸዋል።

በተጨማሪም ዘላቂና አስተማማኝ ሰላም ለልማት መሠረታዊ ጉዳይ በመሆኑ፣ በብሔረሰብ አስተዳደሩ የሰላምን ሁኔታ በማጠናከር፣ የሕዝቦችን አብሮነትና የማኅበራዊ ትስስር በማጎልበት ላይ በተቀናጀ መልኩ መሥራት እንደሚገባ አመላክተዋል።

የፓርቲና የመንግሥት ዕቅዶችን በማጣጣምና በተቀናጀ አመራር በመምራት፣ በ2019 በጀት ዓመት የተቀመጡ የልማት ግቦችን በተጨባጭ ለማሳካት አመራሩ በጋራ ዓላማ፣ በተጠያቂነትና በቁርጠኝነት መንቀሳቀስ እንዳለበትም አሳስበዋል።

በመድረኩ የተሳተፉ አመራሮች በበኩላቸው፣ ባለፈው የበጀት ዓመት የታዩ ጥንካሬዎችን በማስቀጠል፣ የታዩ ክፍተቶችን በመለየትና በማረም፣ የሕዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በተሻለ ደረጃ ለመመለስ በቅንጅትና በተቀናጀ አሠራር እንደሚሠሩ ገልጸዋል።

መድረኩም የ2019 በጀት ዓመት የፓርቲና የመንግሥት የሥራ ዕቅዶችን በጋራ በመገምገም፣ የቀጣይ ዓመቱን የሥራ አቅጣጫዎች በመወሰንና በተግባር ለመተርጎም የሚያስችል የጋራ ግንዛቤና የአፈጻጸም አቅጣጫ በመፍጠር ተጠናቋል።

16/09/2026

እንኳን ለ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ!

የአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እና ለአጠቃላይ የመስተዳደሩ ነዋሪዎች እንኳን ለ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሰላም፣ በጤናና በደስታ አደረሳችሁ ይላል።

አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የአብሮነት፣ የብልፅግናና የእድገት ዓመት እንዲሆን ምኞቱን እየገለፀ፣ የወሎ ኦሮሞ ምድር ያላትን ሰፊ የኢኮኖሚ፣ የቱሪዝምና የማምረቻ አቅም በተግባር ለማልማት በርካታ የኢንቨስትመንት ዕድሎችን እያመቻቸ መሆኑን ያስታውቃል።

በተለይም በኢንዱስትሪ፣ በቱሪዝም፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በግብርናና በሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፎች መሰማራት ለሚፈልጉ ኢንቨስተሮች ምቹ የሆነ የሥራና የኢንቨስትመንት አካባቢ ለመፍጠር በትኩረት እየሰራ ይገኛል።

ስለሆነም በዚህ አዲስ ዓመት የወሎ ኦሮሞ ምድርን የተፈጥሮ፣ የሰው ኃይልና የኢኮኖሚ ሀብት በመጠቀም ለማደግና ለማልማት የሚፈልጉ የአገር ውስጥና የውጭ ኢንቨስተሮችን በሙሉ አቅማችን ለመቀበል ዝግጁ ነን።

ዕድሉን አመቻችተን፣ ለእድገት በር ከፍተን፣ ኢንቨስተሮችን በክብር እየጠበቅን ነው!

አዲሱ ዓመት የጋራ ተስፋን ወደ ተጨባጭ ውጤት፣ የኢንቨስትመንት ዕድሎችን ወደ ሥራ ፈጠራ እና የልማት ራዕያችንን ወደ ተጨባጭ እድገት የምንቀይርበት ዓመት ይሁን!

እንኳን ለ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ!

የአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር

“ሰላምን፣ አብሮነትንና አንድነትን የሚያናጉ ትርክቶችን በማረቅ፣ የሕዝቦችን ወንድማማችነት ማጽናት ይገባል”— አቶ ጀማል አሊየኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ...
16/09/2026

“ሰላምን፣ አብሮነትንና አንድነትን የሚያናጉ ትርክቶችን በማረቅ፣ የሕዝቦችን ወንድማማችነት ማጽናት ይገባል”

— አቶ ጀማል አሊ
የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ

በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር የ2018 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም ግምገማና የ2019 ዓ.ም የዕቅድ ኦሬንቴሽን መድረክ “አርቆ ማየት፣ አልቆ መሥራት” በሚል መሪ ቃል በሦስተኛ ቀኑ ቀጥሎ እየተካሄደ ይገኛል።

በዕለቱ በተካሄደው የውይይት መድረክ፣ የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጀማል አሊ፣ የሕዝብ ግንኙነት ዕቅድንና ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታን የሚመለከት ሰነድ አቅርበዋል። በሰነዱ ላይም ሰፊ ውይይትና ሃሳብ ልውውጥ ተካሂዷል።

አቶ ጀማል አሊ በአቀረቡት ሰነድ፣ ሰላምን፣ አብሮነትንና ሀገራዊ አንድነትን የሚያዳክሙ አስተሳሰቦችና ትርክቶች በማረቅ፣ በሕዝቦች መካከል ያለውን የጋራ መተሳሰብ፣ ወንድማማችነትና ትብብር ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸዋል።

በተለያዩ ውስጣዊና ውጫዊ ተጽዕኖዎች ሳይበገር ትኩረትን በረጅም ጊዜ ዓላማዎችና በሕዝብ ጥቅም ላይ በማድረግ፣ በዞን፣ በክልልና በሀገር ደረጃ የተመዘገቡ ውጤቶችን ማጠናከርና ወደፊትም በተሻለ አፈጻጸም ማስቀጠል እንደሚገባ አመላክተዋል።

እንዲሁም በመንግሥት የሚታቀዱና የሚፈጸሙ ተግባራት ከተቀመጡ የፖሊሲና የዕቅድ አቅጣጫዎች ጋር ተጣጥመው፣ በተቀናጀና በተጠያቂነት መንፈስ እንዲፈጸሙ ማረጋገጥ የአመራሩ ቀዳሚ ተግባር መሆኑን ጠቁመዋል።

በመጨረሻም በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችና አባላት የተቀመጡ የሥራ አቅጣጫዎችን በጥልቀት በመረዳት፣ ከሚያደናቅፉ ተጽዕኖዎች በመራቅ፣ ለሕዝብ ጥቅም፣ ለሰላምና ለዘላቂ ልማት በትጋት መሥራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።

የ2018 ዓ.ም ስኬቶችን በማስቀጠል፣ ክፍተቶችን በመሙላት በ2019 ዓ.ም ተጨባጭ ውጤት ለማስመዝገብ አቅጣጫ ተቀመጠ“የ2018 ዓ.ም ስኬቶችን አስቀጥለን፣ ክፍተቶችን ሞልተን፣ በ2019 ዓ.ም...
15/09/2026

የ2018 ዓ.ም ስኬቶችን በማስቀጠል፣ ክፍተቶችን በመሙላት በ2019 ዓ.ም ተጨባጭ ውጤት ለማስመዝገብ አቅጣጫ ተቀመጠ

“የ2018 ዓ.ም ስኬቶችን አስቀጥለን፣ ክፍተቶችን ሞልተን፣ በ2019 ዓ.ም በተጨባጭ ውጤት እንሰራለን።”
— አቶ አህመድ አሊ
የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ

በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር የ2018 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም ግምገማና የ2019 ዓ.ም የዕቅድ ኦሬንቴሽን መድረክ በ«አርቆ ማየት፣ አልቆ መስራት» መሪ ቃል ተካሂዷል።

መድረኩ በ2018 ዓ.ም የተመዘገቡ የሥራ ስኬቶችን ለመገምገም፣ የታዩ ክፍተቶችንና ተግዳሮቶችን ለመለየት እንዲሁም በ2019 ዓ.ም የተሻለ የሥራ አፈጻጸምና ተጨባጭ ውጤት ለማስመዝገብ የሚያስችሉ የተግባር አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ያለመ ነው።

በመድረኩ የብሔረሰብ አስተዳደሩ የፕላን ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ሀይሌ የ2018 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም ሰነድ አቅርበዋል። በሰነዱ መነሻነትም የበጀት ዓመቱ ዋና ዋና ስኬቶች፣ ክፍተቶችና ተግዳሮቶች በስፋት ተገምግመው፣ ለ2019 ዓ.ም የሚያስፈልጉ የሥራ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።

የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ አሊ እንደገለጹት፣ 2018 ዓ.ም አመራሩ በእይታና በአስተሳሰብ ዕድገት ያሳየበት፣ በሰላምና በልማት ዘርፎች በመሬት ላይ የሚታዩና የሚዳሰሱ ውጤቶች የተመዘገቡበት እንዲሁም ሕዝቡ ተጠቃሚ የሆነበት ዓመት ነው።

ሆኖም በዓመቱ በአመራሩ ዘንድ የአስተሳሰብና የሥራ ውህደት እጥረት፣ እንዲሁም ከነባራዊ ሁኔታ ጋር በበቂ ሁኔታ ያልተጣጣሙ ዕቅዶች መኖራቸውን አመላክተዋል። እነዚህን ክፍተቶች ለ2019 ዓ.ም የሥራ ማሻሻያ መነሻ በማድረግ የተሻለ አፈጻጸም ማስመዝገብ እንደሚገባም ጠቁመዋል።

በ2019 ዓ.ም አመራሩ ከየወረዳዎች ነባራዊ ሁኔታ ጋር የተጣጣመ ዕቅድ በማዘጋጀት፣ ውጤታማ ኮሙኒኬሽን በመፍጠር፣ የመፈጸም ቁርጠኝነትን በማሳደግና የመወሰን አቅምን በማጎልበት ላይ ትኩረት ሊያደርግ እንደሚገባ አቶ አህመድ አሊ አቅጣጫ ሰጥተዋል። በተጨማሪም ችግር ፈቺ ክትትልና ድጋፍን በማጠናከር ዕቅዶችን ወደ ተግባር በመቀየር የሚታይ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚገባ ገልጸዋል።

የብሔረሰብ አስተዳደሩ ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ጀማል አሊ በበኩላቸው፣ በ2018 ዓ.ም ዕቅድን መሠረት አድርጎ ለመምራት የተደረገው ጥረት አበረታች መሆኑን ገልጸው፣ የተመዘገቡ ስኬቶችን ለማስቀጠልና የታዩ ክፍተቶችን ለመሙላት በአመራሩ መካከል መደማመጥና መደጋገፍ ወሳኝ መሆኑን አስረድተዋል።

በግብርና ዘርፍ ደግሞ የሰፋፊ እርሻ አሰራርንና መካናይዜሽንን በስፋት መጠቀም፣ በእንስሳት ሀብት ልማትም በቁጥር ላይ ብቻ ከማተኮር ይልቅ ምርታማነትንና ጥራትን ማሳደግ የቀጣዩ ዓመት ዋና ትኩረት መሆን እንዳለበት አቶ ጀማል አሊ ጠቁመዋል።

የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አህመድ ሁሴን በበኩላቸው፣ በ2018 ዓ.ም ዕቅዶችን ወደ ተግባር ለመቀየር ከተለያዩ አካባቢዎች ልምድ በመቀመርና የመፈጸም ቁርጠኝነትን በማጠናከር ውጤታማ ሥራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።

በየደረጃው ያለው አመራር የአስተሳሰብ ጥራትና የአፈጻጸም ቅንጅት እንዲኖረው መደረጉ ለ2018 ዓ.ም የተገኙ ውጤቶች መሠረት መሆኑን ጠቁመው፣ በ2019 ዓ.ም ይህንን አሠራር በተጠናከረ መልኩ ማስቀጠል እንደሚገባ አስረድተዋል።

በአጠቃላይ፣ የ2019 ዓ.ም የሥራ አቅጣጫ የተመሠረተው የተገኙ ስኬቶችን በማጠናከር፣ የታዩ ክፍተቶችን በመሙላት፣ የአመራር ቅንጅትንና የውስጥ አንድነትን በማጠናከር ዕቅድን ወደ ተግባር እና ተግባርን ወደ ተጨባጭ ውጤት በመቀየር ላይ ነው።

«አርቆ ማየት፣ አልቆ መስራት» — የ2019 ዓ.ም የሥራ መርህ።

15/09/2026

በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን እና በአፋር ክልል ዞን 05 (ሀሪራሱ) አስተዳደር መካከል የጋራ የሰላም፣ የምክክር መድረክ በሰንበቴ ከተማ ተካሂዷል።

Beeksisa! Jiraattota Aanaa Jiillee Dhummuugaa fi Bul. Magaalaa Sanbatee Hundaaf! Baga Geenye Baga Geessan! Barnootni Bar...
14/09/2026

Beeksisa!

Jiraattota Aanaa Jiillee Dhummuugaa fi Bul. Magaalaa Sanbatee Hundaaf!

Baga Geenye Baga Geessan!
Barnootni Bara 2019 Guyyaa Boru 5/1/2019 Manneen Barnootaa Keenya Hunda irratti ni Jalqabama.

Kanaafu Maatiin Barattoota Dursa Idilee Irraa kaase Hanga kutaa 12ffaa jiran Gara Mana Barumsatti fiduun Ijoollee Keessan Barumsa akka jalqabsiiftan kabajaan isin Beeksifna.

Biyyi Dhalootaan Dhaloonni immo Barnootaan Ijaaraman!

Address

Senbete
Bate
0000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Paartii Badhaadhina Magaalaa Sanbatee posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Paartii Badhaadhina Magaalaa Sanbatee:

Shortcuts

Share