Admin & Stu. Affairs V/President Office of MWU

Admin & Stu. Affairs V/President Office of MWU This page is created to provide up to date information about the Adminstrative and student affairs activities of Madda walabu university to the public.

02/07/2021

Beeksiisa
=========////===========
Barattoota haaraa kan bara 2013 A.L.I Yuunivarsiitii Madda Walaabuutti ramadamtan hundaaf:
Akkuma beekamu Yuunivarsiitiin Madda Walaabuu Barattoota haaraa ykn waggaa tokkooffaa kan bara 2013 A.L.I gara mooraa isaaniitti gaafa 28/10/2013 jalqabee hanga 30/10/2013 A.l.I akka galanii baruumsa eegalan waamicha dabarsuun isaa niyaadatama. Haaluma kanaan barattoonni keenya karaa irratti rakkoon akka isaan hinqunnamnee fi geejiba dhabanii akka hinrakkanneef Yuunivarsiitiin geejjiba qopheessee eeggachaa jira. Kanaafuu akkaataa ramaddii armaan gadiitti dhiyeenya keessan giddu galeessa godhachuudhaan guyyaa 29/10/2013 ganama keessaa sa’atii 12፡30 - 1፡00tti bakka isinitti dhiyaatutti argamuun akka itti fayyadamtan isin beeksifna.
1. Giddugaleessi Finfinnee kan isinitti dhiyaatu Buufata konkolaataa guddicha
2. Buraayyuufi Askoon kan isinitti dhiyaatu Buufata konkolaataa Askootti
3. Kotobeefi Laamberet kan isinitti dhiyaatu Buufata konkolaataa Laamberetitti
4. Qaallittiin kan isinitti dhiyaatu Buufata konkolaataa Qaallittiitti
5. Adaamaan kan isinitti dhiyaatu Buufata konkolaataa Adaamaa naannoo FIRAANKOOTTI

HUBACHIISA: Konkolaattonni keenya LOOGOO fi BAANERII Yuunivarsiitii Madda Walaabuu waan qabaniif addaan baasuun nama hinrakkisuYaada dabalataaf lakkoofsota bilbilaa armaan gadii fayyadamaa
1. 09-13-17-03-83
2. 09-11-91-75-21
3. 09-15-81-34-58
4. 09-10-56-57-36
5. 09-11-78-53-64
6. 09-21-50-45-82

02/07/2021

ማስታወቂያ
=============////==========
በ2013 ዓ.ም መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በሙሉ

የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ከ28/10/2013 አስከ 30/10/2013 ወደ ዩኒቨርሲቲው ገብታችሁ ትምህርት እንድትጀምሩ መጥራቱ ይታወቃል፡፡ በዚሁ መሠረት ለተማሪዎቻችን ደህንነት ሲባል ዩኒቨርሲቲዉ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ለሚመጡ ተማሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት አዘጋጅቶ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል፡፡ ስለሆነም በ29/10/2013 ዓ.ም. ከጧቱ 12፡30 – 1:00 በሚከተሉት መናኸሪያዎች እንደየቅርበታችሁ በመገኘት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንድትሆኑ በደስታ እንገልጻለን፡፡
1. ትልቁ አዉቶብስ ተራ የሚቀርባችሁ በትልቁ መናኸሪያ
2. አስኮ /ቡራዩ አካባቢ የሚቀርባችሁ በአስኮ መናኸሪያ
3. ኮቶቤ / ላምበረት የሚቀርባችሁ በላም በረት መናኸሪያ
4. ቃሊቲ የሚቀርባችሁ በቃሊቲ መናኸሪያ
5. አዳማ የሚቀርባችሁ በአዳማ መናኸሪያ/ ፍራንኮ አካባቢ/

ማሳሰቢያ፡ - አዉቶቡሶቹ ላይ የመዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ሎጎ እና ባኔር የተለጠፈ ስለሆነ ለመለየት አትቸገሩም፡፡
ለበለጠ መረጃ የሚከተሉትን ስልክ ቁጥሮች መጠቀም ይቻላል፡፡
1. 09-13-17-03-83
2. 09-11-91-75-21
3. 09-15-81-34-58
4. 09-10-56-57-36
5. 09-11-78-53-64
6. 09-21-50-45-82

Gargaarsa Waaqaatiin hojii gaariin hojjetameera!=========//============Waldhibdee jaarsolii Siikkoo mandoo fi Tuulamaa g...
01/07/2021

Gargaarsa Waaqaatiin hojii gaariin hojjetameera!
=========//============
Waldhibdee jaarsolii Siikkoo mandoo fi Tuulamaa gidduu jirtu guyyaa har'aa haala baay'ee namatti toluun xumurree jirra!
Jalqabbiin kun hojii itti aanuufillee haamilee guddaa Jan namatti horudha.
Namoota dhimma kana xumuruuf guyyaa fi halkan nu waliin ifaajaniin galatoomaa jechuu barbaada!!

መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ በ2013 ዓ.ም አዲስ የተመደቡ መደበኛ ተማሪዎችን የመቀበያ ጊዜ ከሰኔ 28-30/2013 ዓ.ም በመሆኑ፤ በተጠቀሰው ቀን ተገኝታቹ እንድትመዘገቡ ያሳስባል።
23/06/2021

መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ በ2013 ዓ.ም አዲስ የተመደቡ መደበኛ ተማሪዎችን የመቀበያ ጊዜ ከሰኔ 28-30/2013 ዓ.ም በመሆኑ፤ በተጠቀሰው ቀን ተገኝታቹ እንድትመዘገቡ ያሳስባል።

የግንቦት ወር ግንባር ቀደም/ምስጉን ሰራተኞቻችን!´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና ተማሪዎች ጉዳ...
16/06/2021

የግንቦት ወር ግንባር ቀደም/ምስጉን ሰራተኞቻችን!
´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´
በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና ተማሪዎች ጉዳይ ም/ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት የግንቦት ወር 2013 ዓ.ም ግንባር ቀደም ሰራተኞችን በመለየት እውቅና ሰጥቷል። ትጉህ ሰራተኞቻችንን የማበረታትና ልዩ እውቅና የመስጠት ሂደት ወደፊትም በተሻለ መልኩ በቀጣይነት ይተገበራል።

ግንባር ቀደም ሰራተኞች በመሆን እውቅና ላገኛችሁ ሰራተኞቻችን እንኳን ደስ አላችሁ!

Hojjattoota Adda duree jia'a Caamsaa ta'uun beekumtii waan argataniif baga gammaddan!

የአስተዳደርና ተማሪዎች ጉዳይ ም/ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት
[09/10/2013 ዓ.ም)

የቅጥር ማስታወቂያ-----------------------መደ ወላቡ ዩኒቨርስቲ በሶስቱም ካምፓሶች ባሉት ክፍት የሰራ መደቦች አመልካቾችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡በመሆኑም ከዚህ በታች ባለው...
15/06/2021

የቅጥር ማስታወቂያ
-----------------------
መደ ወላቡ ዩኒቨርስቲ በሶስቱም ካምፓሶች ባሉት ክፍት የሰራ መደቦች አመልካቾችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡በመሆኑም ከዚህ በታች ባለው ሰንጠረዥ የተመለከቱትን ዝቅተኛ መስፈርት የምታሟሉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10(አሰር) ተከታታይ የሰራ ቀናት ውስጥ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡

ማሳሰብያ፡-
-----------
1.የብቃት ማረጋገጫ ፈተና ለሚመለከታቸው በሌቭል የተገኙ የት/ት ዝግጅት እና የስራ መስኮች “COC” ማስረጃዎችን ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

2.የውድድር ፈተና መስጫ ግዜው በውስጥ ማስታወቂያ እና በዩኒቨርሲቲው ድረ ገፅ የሚገለፅ ሆኖ ለመቀጠር ሲያልፉ ወደ ስራ ከመግባትዎ በፊት የስራ ልምድ ለሚጠይቁ ስራ መደቦች ከቀድሞ መስሪያ ቤታችሁ መልቀቂያ እና ክሊራንስ ማቅረብ ሲኖርባችሁ 0 ዓመት የሚጠይቁ የስራ መደቦች ላይ የስራ አጥ ካርድ መቅረብ አለበት፡፡

3.ከመንግስት መ/ቤት ውጭ ለሚቀርቡ ስራ ልምድ ህጋዊ ግብር ስለመክፈልዎ ከገቢዎች ባለስልጣን ማረጋገጫ መቅረብ አለበት፤ከ6 ወር በላይ የቆዩ የስራ ልምዶች ወይም ከስራ ተገለው የቆዩበትን ህጋዊ ማስረጃ አግባብ ባለው መ/ቤት ካልታደሰ ተቀባይነት አይኖረዉም፡፡

4.የምዝገባ ቦታ አዲስ አበባ /መገናኛ ሱመያ መስጊድ ጀርባ ማጂክ ካርፔት ትምህርት ቤት አጠገብ ወይም ፊት ለፊት/ ባለው የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ጉዳይ ማስፈፀሚያ ቢሮ፣ ባሌ ሮቤ መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የሰው /ሀ/አ/ል/ደይሬክቶሬት (ዋና ግቢ አዲሱ ህንፃ G+3)ቢሮ ቁጥር 322፣ ጎባ ሪፈራል ሆስፒታል እና ሻሸመኔ ኩየራ ካምፓስ በአካል በመቅረብ መመዝገብም ሆነ ማስመዝገብ ይቻላል፡፡

5.ተመዝጋቢዎች ለምዝገባ ስትመጡ ኦርጅናል ዶክመንትና አንዳንድ በግልፅ የሚታይ ፎቶ ኮፒ የተሟላ ዶክመንት አብሮ መቅረብ አለበት፡፡

6.የፈተና ቀን በውስጥ ማስታወቂያ እና በዩኒቨርሲቲው ዌብ ሳይት ይገለፃል፡፡

መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ባሌ-ሮቤ !!

MWU Administrative & student affairs V/P  have evaluated 2014 EC  procurement plan and annual plan of the wing on 05/10/...
15/06/2021

MWU Administrative & student affairs V/P have evaluated 2014 EC procurement plan and annual plan of the wing on 05/10/2013. We have made good discussion. All our directors genuinely raised the issues, as they have overlooked the plan as previous trend and need time to back to their office and re check it.
We have great respect and thank to those came from President office and Business and development V/P office for their participation and genuine comments.

በአጭር ጊዜ ውስጥ ታስቦ በዛሬው እለት (ግንቦት 28/2013 ዓ.ም) የተዋጣለት የሰላም ኮንፍረንስ እንድናካሂድ የተቀናጀና ውጤታማ ርብርብ ላደረጋቸው የዩኒቨርሲቲያችን ግብረ-ሀይል ፅ/ቤታችን...
05/06/2021

በአጭር ጊዜ ውስጥ ታስቦ በዛሬው እለት (ግንቦት 28/2013 ዓ.ም) የተዋጣለት የሰላም ኮንፍረንስ እንድናካሂድ የተቀናጀና ውጤታማ ርብርብ ላደረጋቸው የዩኒቨርሲቲያችን ግብረ-ሀይል ፅ/ቤታችን ላቅ ያለ ምስጋና ያቀርብላቹዋል። ለቀናነታቹና ትጋታቹ እናመሰግናለን!

Guyyaa gabaabaa keessatti yaadamee Koonfiransii Nageenyaa bu'aa qabeessaa fi ho'aa ta'e akka gaggeeffamu tumsa nuuf gootan hundaaf galanni isiin haagahu!

የመወዩ አስተዳደርና ተማሪዎች ጉዳይ ም/ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት
Waajira I/Aanaa Pireezadaantii Bulchiisaa fi dhimma barattootaa Univarsiitii Madda Walaabu.

በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቱ በ6ኛው ብሔራዊ ምርጫና ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሰላም ኮንፍረስ ተካሄደ።[ግንቦት 28-2013] የሰላም ኮንፍረንሱ በአስተዳደርና ተማሪዎች ጉዳይ ም/ፕሬዝዳንት ...
05/06/2021

በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቱ በ6ኛው ብሔራዊ ምርጫና ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሰላም ኮንፍረስ ተካሄደ።
[ግንቦት 28-2013]

የሰላም ኮንፍረንሱ በአስተዳደርና ተማሪዎች ጉዳይ ም/ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት የተዘጋጀ ሲሆን፣ በዝግጅቱ ላይም በርካታ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል። በዋናነትም ከኦሮሚያ ክልል ብልፅግና ፅ/ቤት፣ የባሌ ዞንና የፌደራል ፀጥታ አካላት፣ የባሌ ዞን አስተዳደር፣ የጎባና ሮቤ ከተማ አስተዳደርና የፀጥታ አካላት፣ አባገዳዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ ወጣቶችና ሌሎች የማህበረሰብ አካላት በኮንፍረንሱ ተሳትፈዋል።

በዝግጅቱ ላይ የዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዝዳንት ዶ/ር አህመድ ከሊል ስለ ኮንፍረንሱ አላማ በመግለፅ የእንኳን ደህና መጣቹ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፣ የአስተዳደርና ተማሪዎች ጉዳይ ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዲሪባ ቀጄላ ስለመደ ወላቡ የዩኒቨርሲቲ ገፅታ ጠቅለል ገለፃ አድርገዋል።

የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ታዬ ደንደዓ በኮንፍረንሱ ላይ ተገኝተው የእለቱን Key speech (ቁልፍ ንግግር) ያደረጉ ሲሆን፣ በተጨማሪም የዩኒቨርሲቲያችን መምህር የሆኑትና በበርካታ ሚዲያዎች በፖሎቲካና የአስተዳደር ስረዓት ላይ ጠለቀ ያሉ ትንተናዎችን በመስጠት የሚታወቁት እጩ ዶ/ር ከዲር ማሞ የመወያያ ፅሁፍ ያቀረቡ ሲሆን፣ በቀረቡት ጉዳዮች ዙሪያም ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

"Excellence Through Diversity "
" ልህቀት በብዝሀነት"

የአስተዳደርና ተማሪዎች ጉዳይ ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት

ግንባር ቀደም(Model) ሰራተኞቻችንን ተዋወቋቸው!´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና ተማሪዎች...
29/05/2021

ግንባር ቀደም(Model) ሰራተኞቻችንን ተዋወቋቸው!
´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´´
በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና ተማሪዎች ጉዳይ ም/ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት የሚያዝያ ወር ግንባር ቀደም (Model) ሰራተኞችን በመለየት እውቅና ሰጥቷል።

ታታሪ ሰራተኞቹ የተመረጡት በአስተዳደርና ተማሪዎች ጉዳይ ዘርፍ ስር ያሉ ዳይሬክቶሬቶች በተዘጋጀው መስፈርት መሰረት ገምግመው ከየስራ ክፍላቸው ሁለት ሁለት ትጉህ ሰራተኞችን መርጠው እንዲያቀርቡ በማድረግ ሲሆን፤ በዚሁ መሰረት በፎቶው ላይ የምትመለከቷቸውን 15 ሰራተኞች የአስተዳደርና ተማሪዎች ጉዳይ ዘርፍ የሚያዚያ ወር 2013 ዓ.ም ግንባር ቀደም(Model) ሰራተኞች ሆነው በመመረጥ እውቅና እንዲያገኙ ተደርጓል።

ይህ አሰራር ሰራተኞችን በማረታታት፣ በሰራተኞች መካከል ቀና ፉክክርና የስራ ተነሳሽነትን በመፍጠር፣ እንዲሁም በስራቸው ደከም ያሉ ሰራተኞቻችንን በማንቃት ለዘርፋችን/ ለተቋሙ እቅድ አፈፃፀም ውጤታማነት ጉልህ አስተዋፅዎ እንደሚኖረው እሙን ነው።

ትጉህ ሰራተኞችን የማበረታትና ልዩ እውቅና የመስጠት ሂደት ወደፊትም በተሻለ መልኩ በቀጣይነት የሚተገበር መሆኑን እየገለፅን፣ የዘርፋችን ግንባር ቀደም ሰራተኞች በመሆን እውቅና ላገኛችሁ ሰራተኞቻችን እንኳን ደስ አላችሁ እንላለለን!

የአስተዳደርና ተማሪዎች ጉዳይ ም/ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት
[21/09/2013)

25/05/2021

WELCOME TO OUR PAGE! This page is created to provide up to date information about the Adminstrative and student's affairs activities of Madda walabu university to the public.

Address

Robe

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Admin & Stu. Affairs V/President Office of MWU posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share