Goncha siso enesia woreda trade and market development office

Goncha siso enesia woreda trade and market development office The purpose of our page is to give information for the people about trad and market development offi

04/10/2022
22/09/2022
01/07/2022
23/03/2022

ቀጣናዊ የንግድ ስምምነት ምንነትና ፋይዳው
=========================================
ሀገራት ከንግድ የሚገባቸውን ጥቅም ለማግኘትና ልማታቸውን ለማረጋገጥ የንግድ ድድር ያካሂዳሉ፡፡ ይህም ድርድር በሰጥቶ መቀበል ላይ የተመሰረተና አለም አቀፍ ስርዓት ነው፡፡ ድርድሩን የሚያካሂዱበት ዓላማም ሥራ አጥነትን ለመቀነሰ፣ የተሻለ ምርትና አገልግሎት በተሻለ ዋጋ ለማግኘት፣ ተወዳዳሪነትን በመጨመር ዘለቄታዊ እድገት ለማምጣት፣ የንግድ ሚዛን ጉድለትን ለመቀነስና ንግድን በህግ ሥርዓት ለማከናወን ነው፡፡ የድርድር ሂደቱን አልፈው ከስምምነት ላይ የደረሱ ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑ ሀገራት የሚፈጥሩት ስምምነት ቀጣናዊ ሥምምነት ወይም ትስስር/Regional Integration/ ይባላል፡፡ ቀጣነዊ ስምምነት ወይም ትስስር የሚፈጠረው ለውህደቱ የሚያስፈለጉ ተቋማትን በማቋቋምና ፕሮግራሞችንና ፖሊሲዎቸችን በማዋሀድ፣ህጎችን በማስማማትና አዳዲስ ህጎችን በመቅረፅ የንግድ፣ የኢኮኖሚ፣ የገንዘብ ብሎም የፖለቲካ ትብብር ሥርዓት የሚፈጥር በተቋምና በመዋቅር የሚመራ ሥርዓት ነው፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በአዋጅ ቁጥር 1263/2014 ሲመሰረት የወጪ ንግድን የሚመለከቱ ቀጣናዊ በተለይም ሀገራችን ከጎረቤት ሀገራት ጋር የሚኖራትን የንግድና ኢኮኖሚ ተስስርን በቀጣይነት የሚያረጋግጡ ፖሊሲዎች፣ስትራቴጂዎችና ህጎችን የማዘጋጀትና በሚመለከተው አካል ሲጸድቅም ተግባራዊ የማድረግ ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡ አግባብ ካላቸው አካላት ጋር በመተባበር የወጪ ንግድ ግንኙነቶችን የመመስረት፣የንግድ ስምምነቶችን በህግ የመፈራረምና የማስፈጸም ኃላፊነቶችም ለሚኒስቴር መ/ቤቱ የተሰጡ ናቸው፡፡

በንግድና ቀጣናዊ ትስስረ ሚኒስቴር የአካባቢያዊ ውህደት ንግድ ግንኙነትና ድርድር ዳይሬክተር አቶ ታገስ ሙሉጌታ እንደገለጹት ኢትዮጵያ የምትሳተፍባቸው ቀጣናዊ የንግድ ስምምነቶቸ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና/AfCFTA/፣የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ /COMESA/፣ በይነ-መንግስታት የልማት ድርጅት /Intergovernmental Authority for Development- IGAD/፣የኢኮኖሚ አጋርነት ስምምነት(Economic Partnership Agreement(EPA) እና የሶስትዮሽ ነጻ ንግድ ቀጣና /TFTA/ ናቸው፡፡

በአፍሪካ አገሮች መካከል የሚደረግ ክልላዊ ውህደት (Regional Integration) መሠረታዊ ፍላጎት የሚመነጨው ሰፊ የገበያ እድል፣ የመግዛት አቅም ያለው ጠንካራ ኢኮኖሚ፣ የፖለቲካና ማህበራዊ ግቦችንና ዓላማዎችን ለማሳካት መሆኖንም ዳይሬክተሩ አብራርተዋል፡፡

ምንጭ፡- ንግድና ቀጠናዊ ትስሰር ሚኒስቴር

23/03/2022

የምግብ ዘይት አቅርቦት፣ ሥርጭትና ዋጋ ግንባታ ማስፈጸሚያ መመሪያ እየተዘጋጀ ነው
========================================
አዲስ አበባ፣13/07/2014 (ንቀትሚ) ያለቀለት የፓልም ምግብ ዘይት ለሚያስመጡ እና ከድፍድፍ ፓልም የምግብ ዘይትን ለሚያጣሩ የሀገር ውስጥ ፋብሪካዎች የምርት አቅርቦት፣ ስርጭት እና የዋጋ ግንባታ አሠራር ማስፈጸሚያ መመሪያ እየተዘጋጀ ነው፡፡
የምግብ ዘይት ፍላጎትን በዘላቂነት በሀገር ውስጥ የቅባት እህሎች እንደ ግብአት ተጠቅሞ ማምረት እስከሚቻል ድረስ የምርት ሂደቱ በከፊል የተጠናቀቀውን የፓልም ድፍድፍ ከውጪ በማስገባት እንደ ግብአት ተጠቅመው የሚያመርቱ የሀገር ውስጥ ፋብሪካዎች ወደ ሥራ እየገቡ ይገኛል፡፡በዚህ ዘርፍ የሚሳተፉ የሀገር ውስጥ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ለመምረጥ፣ የሚያስገቡትን የድፍድፍ ዘይት ምርት ወደተጣራ ዘይት ሲለወጥ የሚኖረውን መጠን ለመወሰን እና የሚሸጡበትን የፋብሪካ በር ዋጋ ለመተመን መመሪያውን ማዘጋጀት ማስፈልጉን የንግድ እቃዎች ዋጋ ጥናት ቡድን መሪ አቶ አሸናፊ ማሙዬ ረቂቅ መመሪያውን ለውይይት ባቀረቡበት ወቅት ገልጸዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ፋብሪካዎች ያመረቱትን ምርት የሚያሰራጩበት አሰራር ግልጽነት እንዲኖረው ለማድረግ እንዲሁም ክልሎች፣ ከተማ አስተዳደሮች እና በተዋረድ የሚገኙ የአስተዳደር አካላት የምርት አቅርቦት እና ስርጭት ክትትል እና ቁጥጥር ማድረግ እንደሚገባቸው ስለታመነበት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር መመሪያውን እያዘጋጀ መሆኑን አቶ አሸነፊ አስረድተዋል፡፡
በዘይት አምራችነት የሚመረጥ ፋብሪካ በቀን በትንሹ 300 ሜ.ቶን እና ከዚያ በላይ ድፍድፍ ፓልም ማጣራት የሚያስችል ማሽን ያለው፣ ድፍድፍ ዘይት ከማጣራት ውጪ በተረፈ ምርት ሌሎች የኢንዱስትሪ ምርቶችን ማቀነባበር የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችን የሚጠቀም ፣ የፋብሪካውን የተጣራ ምግብ ዘይት አሽጎ ለገበያ ማቅረብ የሚያስችለው የማሸጊያ ጀሪካኖች እና ሌሎች ግብአቶችን ማምረት የሚያስችለው ቴክኖሎጂ ያለው እንዲሁም የምግብ ዘይት በማጣራት ሂደት ውስጥ አስፈላጊውን የሰለጠነ እና ተገቢውን የሰው ሃይል በመቅጠር ለስራ አጥ ቁጥር መቀነስ አስተዋጽኦ የሚያበረክት መሆን አንዳለበት ረቂቅ መመሪያው በመስፈርትነት አስቀምጧል፡፡ አምራቹ ከድፍድፍ ፓልም የሚጣራውን ምግብ ዘይት በቫይታሚን ኤ እና ቢ አበልጽጎ ማምረት የሚያስችለው ቴክኖሎጂ ያለው መሆን አለበት ያሉት አቶ አሸናፊ ለድፍድፍ ፓልም ግብአት በመንግስት የሚመደብለትን የውጭ ምንዛሪ ሙሉ በሙሉ ለተባለው ግብአት ግዢ ብቻ መጠቀም እንዳለበትና ከድፍድፍ ፓልም ግብአት የሚመረተው ምርት የገበያ ዋጋ ከውጪ ሀገር ተጣርቶ ከሚመጣው የፓልም ምግብ ዘይት ዋጋ ወቅታዊ የዓለም አቀፍ ገበያን መሠረት በማድረግ በዋጋ የተሻለ እና ሸማቹን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆን ይገባዋልም ብለዋል፡፡
በተጨማሪም ሚኒስቴር መ/ቤቱ በሚያስቀምጠው ስታንዳርድ መሠረት ከአንድ ሜትሪክ ቶን ድፍድፍ ፓልም ማውጣት የሚገባውን የተጣራ የምግብ ዘይት ማምረት የሚያስችል ቴክኖሎጂ ያለው መሆን እንደሚገባው በመመሪያው የተጠቀሰ ሲሆን በዚህ መመሪያ እና በገባው ውል መሰረት የማይፈጽም አምራች፣ አስመጪ እና አከፋፋይ ከአምራችነት፣ አስመጭነትና አከፋፋይነት እንደሚሰረዝም ተገልጿል፡፡
ሚኒስቴር መ/ቤቱ በረቂቅ መመሪያው ላይ ከአምራች፣ አስመጭዎች፣ አከፋፋዮችና የክልል ንግድ ቢሮ ኃላፊዎች ጋር ምክክር እያደረገ ይገኛል፡፡

ምንጭ፡- ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር

Address

Motta

Telephone

+251586640225

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Goncha siso enesia woreda trade and market development office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share