22/04/2024
በተሻሻለው የገጠር መሬት መጠቀሚያ እና የእርሻ ስራ ገቢ ግብር አዋጅ እና ደንብ ላይ ያለመ የንቅናቄ መድረክ በባቹማ ከተማ እየተካሄደ ነው
ሚያዝያ 14
ባቹማ
በምዕራብ ኦሞ ዞን በባቹማ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ዩኒት በተሻሻለው የገጠር መሬት መጠቀሚያ እና የእርሻ ስራ ገቢ ግብር አዋጅ እና ደንብ ዙሪያ አስመልክቶ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው።
በንቅናቄው መድረክ የባቹማ ከተማ አስተዳደር የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ አቶ ከድር ኮምትኬስ በእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት እንደገለፁት በተሻሻለው የገጠር መሬት መጠቀሚያ እና የእርሻ ግብር ስራ ገቢ ግብር አዋጅ እና ደንብ ላይ በመወያየት በቂ ግንዛቤ በመያዝ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ያረጋገጠ የስራ ገቢ ግብር በጋራ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ለመስራት የንቅናቄው መድረክ ዋና አላማ እንደሆነ ገልፀዋል ።
የባቹማ ከተማ አስተዳደር ዋና ከንቲባ አቶ ብርሀኑ ቡጳይ በመድረክ መክፈቻ ንግግራቸው እንደተናገሩት በከተማችን የሚገኙ የገቢ አማራጮችን ለመጠቀም ተሻሻሎ የቀረበው የግብር አዋጅ አስፈላጊ በመሆኑ የአካባቢያችንን ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ በመሆኑ በቀጣይ ተፈፃሚ ለማድረግ ከባለድርሻ በአሰራር ስርዓት ተፈፃሚ እንደሚሆን
ገልፀዋል ።
በመድረኩም የከተማው ገቢዎች ዩኒት አስተባባሪ አቶ አራጋው አሊ የ2016 ዓም የ9 ወራት አፈፃፀምና የስራ ግብር አዲሱ የግብር መክፈያ አዋጅን በሰነድ እያቀረቡ ይገኛል ።
በንቅናቄው መድረክ የባቹማ ከተማ አስተዳደር አጠቃላይ አመራሮች የሚመለከታቸው የሴክተር ባለድርሻ አካላት የ5ቱም ቀበሌ ሊቀመንበሮች ፣ ስራ አስኪያጆች ፣ የቀበሌ መሬት አስተዳደሮች ፣ የቀበሌ የግብርና ባለሙያዎች ሌሎች የቀበሌ የፊት አመራሮች ጨምሮ በንቅናቄው መድረክ እየተሳተፉ ይገኛል ።