ዓሲምባ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ/ዓዴፓ/Assimba Democratic Party

  • Home
  • Ethiopia
  • Mekelle
  • ዓሲምባ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ/ዓዴፓ/Assimba Democratic Party

ዓሲምባ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ/ዓዴፓ/Assimba Democratic Party Political Party
(4)

Address

16 Kebeli
Mekelle

Telephone

+251991315695

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ዓሲምባ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ/ዓዴፓ/Assimba Democratic Party posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

የዓሲምባ ዴምክራስያዊ ፖርቲ ትግል እንዴት ተጀመረ

የዓሲምባ ዴምክራስያዊ ፖርቲ ትግል እንዴት ተጀመረ

ዓሲምባ በኢሮብ ወረዳ የማትገኝ በትግራይ ሁለተኛ ከፍተኛ ተራራ ሰትሆን በሳሆኛ ዓሲምባ ማለት ቀይ ተራራ ነው ። የኢትዮጵያ ላእላዊ ግዛት በቀይ ተራራ ተሰይሞዋል ይህ ብዙ ውድ የኢትዮጵያ ልጆች ደማቸውን አፍስሰው አጥንት የከሰከሱበት መሬት ያለ ነዋሪ ህዝብ ፍቃድ እንዳይነካ ዋና ዓላማ አድርጎ ሰላማዊ ትግል ለማድረግ የተመሰረተ ፓርቲ ነው ። ዓሲምባ ከዚህ በፊት የኢህአፓ ትግል የተጀመረበትና የህወሓት ሰትራቴጂክ ማእከል በመሆን ትታወቃለች ። ከዚህ በተጨማሪ ዓሲምባ መንፈሳዊ ቦታ ሆና አባ ዘወንጀል የሚባሉ ቅዱስ አባት የሚኖሩባት ተራራ ሰለሆነች ከመላው የኢትዮጵያ ክልሉች ብዙ ሰዎች ለመፈወስ የሚመጡባት ታሪካዊ ሰፍራ ናት ። በቅርቡ የተጀመረው የዓሲምባ ትግል ያሰፈለገበት ዋና ምክንያት የዚህ ፓርቲ መሰራች አባላት አብዛኛዎቹ ከህወሓት ጋር ሆነን የወሰጥ ትግል በማድረግ በሃገራችን ያሉ ማህበራዊ ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ተግዳሮቶች ለመፍታት ስደረግ የነበረው ትግል ግቡን መምታት አልቻለም ። ምክንያቱም ህወሓት የህዝቡን የልማት ፤ የመልካም አስተዳደር ፣ ሰብአዊ መብትና የዴምክራስ ጥያቄዎች መመለስ አልቻለም ። በተለይ ኢህአዴግ በኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር በሚመለከት ህዝቡን ሳያሳትፍ የሚያደርገቻው ውሳኔዎች በተለይ የአልጀርሱ ውሳኔ ሙሉ ለሙሉ መቀበሉ የድንበር አካባቢ ህዝብ ተቃውሞ በየ ግዜው በተለያዩ መልኩ ቢያሰማም የሚሰማው መንግሥት ሆነ ፓርቲ አላገኘም ። እኛ ከዛሬ ነገ ይሻላል ብለን ብንጠብቅም ነገሮች ኢየባሱ በመሀዳቸው በኢህአዴግና ህወሓት ላይ የነበረን እምነት ሰለተሟጠጠ ወደ ሰላማዊ ትግል ገባን ። ዓዴፓ ፌዴራልዝም የኢትዮጵያ ፍቱን መድሃኒት እነደሆነ በማመን፣ Social Democracy ለመከተል በመወሰን በትግራይ አንድ አማራጭ ፖርቲ ህኖ ቀርበዋል ። አንድ ሰው የፈለገውን ለመናገር ፣ ለመፃፍ ፣ የፈለገውን የፖለቲካ ፖርቲ አባል ለመሆን፣ የፈለገውን ሃይማኖት መከተል በህገ መንግስት የተሰጠው መብት ማንም ልነጥቀው እንደማይገባ ዓዴፖ በፅኑ ያምናል ። የኢትዮጵያ ህገ መንግሥት የበላይ ህግ መሆኑን በማመን መምሪያ ያደርገዋል። ማንም የኢትዮጵያ ዜጋ የዚህ ፖርቲ አባል የመሆን መብት አለው ።