መ/ሜዳ/ከአስ/ ገቢዎች ጽ/ቤት

መ/ሜዳ/ከአስ/ ገቢዎች ጽ/ቤት Welcome to the official page of the mehal meda Revenue Office.

ጥቂት ነጥቦች ስለ አዲሱ ታክስ አስተዳደር ስርዓት:-
19/05/2026

ጥቂት ነጥቦች ስለ አዲሱ ታክስ አስተዳደር ስርዓት:-

02/05/2026
የመ/ሜዳ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ፅ/ቤት በቀን 21/08/2018 የዞኑን የ9ወር ግምገማ መነሻ በማድረግ ከጠቅላላ ሰራተኛው ጋር ውይይት አድርጓል። የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ መለሰ በላይ ግዛው እ...
30/04/2026

የመ/ሜዳ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ፅ/ቤት በቀን 21/08/2018 የዞኑን የ9ወር ግምገማ መነሻ በማድረግ ከጠቅላላ ሰራተኛው ጋር ውይይት አድርጓል።
የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ መለሰ በላይ ግዛው እኖዴሉት የ9ወሩን የዕቅድ አፈፃፀምና ከዞን የተሰጠውን የማጠቃለያ ሀሳብ መነሻ በማድረግ መነሻ ሰነድ አቅርበዋል። በቀሪ ሁለት ወራቶች ውስጥ የሚከናወኑ የተንጠባጠቡ ተግባሮች ከየሂደቱ የተለቀሙ ሲሆን ሰራተኞችም በየቀበሌው ተመድበዋል። በውይይቱም የተለያዩ ሀሳቦች ተነስተው ውይይት ከተደረገባቸው በኋላ ኃላፊው ጥብቅ የስራ ስምሪት ሰጥተው ተጠናቋል።

21/04/2026

የገቢ ዘርፍ አገልግሎትና አስተዳደር ፍኖተ-ካርታ (Revenue Sector Service and Administration Roadmap) በኢትዮጵያ ያለውን የታክስና የገቢ አሰባሰብ ስርዓት ለማዘመን በስምንት ዋና ዋና ምሰሶዎች ላይ ተለይቶ ተቀምጧል።
ምሰሶ 1፦ ፍትሐዊና ተደራሽ የታክስ አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት መዘርጋት – ግብር ከፋዩ ባለበት ቦታ ሆኖ አገልግሎት የሚያገኝበትንና ፍትሐዊ አሰራር የሰፈነበትን ሁኔታ መፍጠር።

ምሰሶ 2፦ ውጤታማ የታክስ አደረጃጀትና አስተዳደር ሥርዓትን ማሳለጥ – ተቋማዊ መዋቅሩ ለስራ ቅልጥፍና በሚያመች መልኩ እንዲደራጅ ማድረግ።

ምሰሶ 3፦ የሠራተኞች የብቃት ምዘናና የማስፈጸም አቅምን ማሳደግ – የታክስና ጉምሩክ ሠራተኞች በዕውቀትና በክህሎት የታነጹ መሆናቸውን ማረጋገጥ።

ምሰሶ 4፦ ብዝኃነትንና አካታችነትን ያረጋገጠ የታክስ አስተዳደር – ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል (ሴቶችን፣ ወጣቶችንና አካል ጉዳተኞችን ጨምሮ) ያካተተ አሰራርን ማፋጠን።

ምሰሶ 5፦ ዲጂታል የታክስ አስተዳደር ሥርዓትን መገንባት – የወረቀት ንክኪን በመቀነስ አሰራሮችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ መተካት።

ምሰሶ 6፦ ነጻና ገለልተኛ የሠራተኞች አስተዳደር ሥርዓት – ሠራተኞች ከፖለቲካና ከሌሎች ተጽእኖዎች ነጻ ሆነው በሙያዊ ብቃት ብቻ የሚመሩበትን አሰራር መዘርጋት።

ምሰሶ 7፦ ገቢር ነበብ (Proactive) የታክስ አመራር እና ተቋም ግንባታ – ችግሮች ከመከሰታቸው በፊት አስቀድሞ መፍትሄ የሚሰጥ አመራርና ጠንካራ ተቋም መፍጠር።

ምሰሶ 8፦ የታክስ የሕግ ማስከበር ውጤታማነትን ማረጋገጥ – የታክስ ስወራንና ህገ-ወጥ ድርጊቶችን በህግ የመከላከል አቅምን ማጠናከር።

የመ/ሜዳ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች  ጽ/ቤት ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለጽ መልካም ምኞቱን ...
09/04/2026

የመ/ሜዳ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለጽ መልካም ምኞቱን ይገልፃል፡፡
በበጀት አመቱ ከመደበኛ እና ከአገልግሎት ገቢ እቅድ 135,423,148 ብር ለመሰብስብ አቅዶ እስከ አሁን 80,828,660 ብር የተሰበሰበ ሲሆን አፈፃፀሙም 59% ላይ ደርሷል፡፡ ለዚህ አፈጻጸም ከፍተኛውን ድርሻ ያበረከታችሁ ግብር ከፋዮቻችን ፣አመራሮቻችን ፣አጋርና ባለድርሻ አካላት ፣ ለገቢ ተቋሙ ባለሙያዎች እና ኃላፊ ምስጋና እያቀረብን በዓሉ የሰላም የፍቅር እና የመተሳሰብ በዓል እንዲሆንላችሁ ከልብ ይመኛል፡፡
“የመ/ሜዳ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት”

27/03/2026
18/03/2026

የመ/ሜዳ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የስምንት ወር የዕቅድ አፈፃፀም በማኔጅመንትና በጠቅላላ ሰራተኛ ግምገማ አደረገ።
የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀሙን የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ መለሰ በላይግዛው በአጭሩ ካቀረቡ በኋላ ተጨማሪ ከየሂደቱ የቀረቡ ሀሳቦችን መሠረት በማድረግ በርካታ ጥያቄና መልስ ተደርጎ ገንቢ አስተያየቶች የተሰጡበት ሲሆን:-
ከመደበኛ ገቢ 68460605 እና ከአገልግሎት ገቢ 63494397 በድምሩ 131955002 ለመሰብሰብ አቅዶ ከመደበኛ 54757018 የእቅዱን 76.12% የሰበሰበ ሲሆን አገልግሎት ገቢ 22325486 የእቅዱን 35.16% የሰበሰበ ሲሆን ከመደበኛ እና ከአገልግሎት ገቢ በድምሩ 77082504 የእቅዱን 56.91% መሰብሰብ የተቻለ በቀሪ ወራቶች ያልተሰበሰቡ ገቢዎችን ትኩረት በመስጠት መሰብሰብ እንዳለበት የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ መለሰ በላይግዛው ጥብቅ የስራ ስምሪት በመስጠት የስምንት ወሩ የስራ ግምገማ ተጠናቋል።
የግትኮ ዋና የስራ ሂደት

10/03/2026

በገቢ ተቋሙ እና በየደረጃው ባለ አመራር ተከታታይ ድጋፍና ክትትል በመደረጉ ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡ ተገለፀ
የሰሜን ሸዋ ዞን ገቢዎች መምሪያ የበጀት ዓመቱ ዕቅድ 5,382,020,929 ብር ሲሆን እስከ የካቲት 30/2018 ዓ.ም ድረስ የተሰበሰበ ገቢ መደበኛ 2,951,715,066 ብር አፈፃፀም 61.45% የከተማ አገልግሎት 280.004,389 ብር አፈፃፀም 48.39% በድምሩ 3,231,719,456 ብር አፈፃፀም 60.05% ሲሆን ከ2017 ዓ.ም ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በብልጫ በ1,019,445,751 ብር ወይም 46.1% እድገት አሳይቷል ሲሉ ወ/ሮ ቀለም ተስፋዬ መምሪያ ሀላፊዋ ገልፀዋል አያይዘውም ለውጤቱ መምጣት በአመቱ መጀመሪያ ተገቢ የሆነ የእቅድ መግባባት በመፍጠር በትልቅ መድረክ የታክስ ንቅናቄ በማድረግ እና በተሰጠው ዕቅድ ላይ ከሁሉም ወረዳና ከተማ ጋር መግባባት በመፈጠር፤ ለሁሉም ወረዳና ከተማ የቀን የገቢ ዕቅድ ቆጥሮ መሰጠት፤ የመምሪያው የማኔጅመንት አባላትና ባለሙያዎች ወረዳና ከተማን በቀጠና በመከፋፈል በአካል እና በየቀኑ በስልክ መደገፍና መከታተል በመቻሉ፤ እንዲሁም በየቀኑ ለስራ የሚያነሣሣ ግብረ-መልስ በመስጠትና የተሻለ ለፈፀሙ ወረዳና ከተማ እውቅናና ማበረታቻ በመስጠት ፉክክር ውስጥ ማስገባት በመቻሉ፣ በሁሉም ወረዳና ከተማ ከፖለቲካ አመራሩ ጋር የጋራ በማድረግ ጥረት የሚጠይቁ ገቢዎችን በመለየት ግብር ከፋዮን የመቀስቀስ ስራ በየጊዜው በመሠራት፤ በየሣምንቱ ወረዳና ከተማን በዙም በመደገፍ የተደረሰበትንና የገጠሙ ችግሮችን ለይቶ መፍታት በመቻላችን የተሸለ ውጤት አስመዝግበናል፡፡ እንዲሁም ከዞን አስተባባሪዎች ጀምሮ የገቢ ስራን ከፀጥታ ስራው ቀጥሎ በመያዝ የወረዳ አስተዳዳሪዎች፣ ከንቲባዎችና ሌሎች በየደረጃው ያሉ አመራሮች ገቢ በመሰብሰብ ልማታችንን የማስቀጠል ጉዳይ ወሳኝነት በመረዳት በትኩረት ተቋሙን እየደገፉና እያገዙ ሲሆን በዋናነት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ወረዳና ከተማን በዙም ሚቲንግ ጭምር በመገምገም በትኩረት እየደግፉ ስራውን እንዲያግዙ በማድረጋቸው ለመጣው ውጤት ባለድረሻ ናቸው፡፡ አጋር አካላትም የገቢ መሰብሰብ ስራውን በሁሉም ዘርፍ በመደገፍና በማገዝ ላይ ናቸው፡፡ የንግዱ ማህበረሰብም ቢሆን በአዳዲስ አሰራሮች ላይም በሚጠሩ ውይይትና መድረኮች በመገኘት ሃሣብ የመስጠትና ግብር የምከፍለው ለራሴ እና ለሃገሬ ልማት ነው የሚለው አስተሳሰቡ በመሻሻሉ የገቢ አሰባሰቡ የተሸለ እንዲሁን አግዟል ብለዋል መምሪያ ሀላፊዋ በቀጣይም ትኩረት የሚደረግባቸውን ነጥቦች ሲያነሱ በሁሉም የገቢ አርእስት ያልተሰበሰበ ገቢን በትኩረት በለየነው መሠረት ወረዳና ከተማ ገቢውን እና ውዝፍን ቆጥሮ መሰብሰብ እንዲሁም የንግድ ትርፍ፤ የኪራይ ገቢ፤ የደረጃ “ለ” እና “ሀ” በዝርዝር ለይቶ በትኩረት መሰብሰብ በዚሁ ጎን ለጎን ሁሉም የገቢ ተቋሙ አመራሮችና ሙያተኞች ስራውን በየቀኑ እየገመገሙ መምራት፣ ጥቅል የፖለቲካ አመራሩና ባለድርሻ አካላት ገቢ መሰብሰብ የህልውና ጉዳይ ነው በማለት ተቋሙን ማገዝ፣ የከተማ አገልግሎት ገቢ በአዲሱ የታሪፍ ማሻሻያ መሠረት በትኩረት መስራት ይገባል ሲሉ ወ/ሮ ቀለም ተስፋዬ አሳስበዋል፡፡
የግብር ትምህርትና ኮሙንኬሽን ዋና የስራ ሂደት 01/07/2018 ዓ.ም

27/01/2026

Address

Mehal Meda
0000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when መ/ሜዳ/ከአስ/ ገቢዎች ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share