Magaale daqaarak kabxa kee sanaqatta giti merrayti daddoosih ku/buaxh

  • Home
  • Ethiopia
  • Magale
  • Magaale daqaarak kabxa kee sanaqatta giti merrayti daddoosih ku/buaxh

Magaale daqaarak kabxa kee sanaqatta giti merrayti daddoosih ku/buaxh Government organization

08/05/2026
ጋዜጣዊ መግለጫየትራንስፖርት አገልግሎት ወደ መደበኛ ሁኔታ መመለሱን ስለማሳወቅበመካከለኛው ምሥራቅ የተከሰተው ግጭት በዓለም አቀፍ የነዳጅ ገበያ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ አሳድሮ፣ የነዳጅ ዋጋ ግሽ...
29/04/2026

ጋዜጣዊ መግለጫ

የትራንስፖርት አገልግሎት ወደ መደበኛ ሁኔታ መመለሱን ስለማሳወቅ

በመካከለኛው ምሥራቅ የተከሰተው ግጭት በዓለም አቀፍ የነዳጅ ገበያ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ አሳድሮ፣ የነዳጅ ዋጋ ግሽበትና በአቅርቦት ላይ መስተጓጎል እንዲፈጠር አድርጓል። ይህም ሁኔታ በኢትዮጵያ የናፍጣ ዕለታዊ አቅርቦትን ከ9 ሚሊዮን ሊትር ወደ 4.5 ሚሊዮን ሊትር እንዲቀንስ አድርጎ፣ በትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የሚታወቁ መስተጓጎሎችን አስከትሎ ነበር።

መንግሥት ይህንን ችግር በፍጥነት ለመቆጣጠር የታሪፍ ማሻሻያ፣ የአቅርቦት አደረጃጀት ማሻሻል እና የሎጂስቲክስ ቅንጅት ማጠናከር ጨምሮ በርካታ አስቸኳይ እና ዘላቂ እርምጃዎችን ወስዷል። ይህም የውጭ ጫናዎች ቢኖሩም የአገር ውስጥ ኢኮኖሚ መረጋጋትን በመጠበቅ እና የህዝብ አገልግሎቶች እንዳይቋረጡ በማድረግ በኩል መንግሥት የሕዝብ ጥቅምን በማስቀደም የሚከተለውን የፖሊሲ አቅጣጫ የሚያሳይ ነዉ ።

ዛሬ ሚያዚያ 21/2018 ዓ.ም የገንዘብ ሚኒስቴር በይፋ እንዳሳወቀው የነዳጅ አቅርቦት ወደ መደበኛ ሁኔታው ተመልሷል። ይህ ሁኔታ በትራንስፖርት ዘርፍ የተፈጠሩ መስተጓጎሎች በፍጥነት እንዲፈቱ ያስችላል።

በመሆኑም ከዛሬ ጀምሮ ቀደም ሲል በነዳጅ እጥረት ምክንያት የተፈጠሩ የትራንስፖርት አገልግሎት መስተጓጎሎች ሙሉ በሙሉ እንዲቀረፉ፣ ከአዲስ አበባ እስከ ክልሎች የምትገኙ ሁሉም የዘርፉ አመራሮች እና ተዋናዮች ታሪፍ በተወሰነዉ መሰረት ብቻ እንዲቀጥል በጥብቅ እንድትከታተሉ እና ትግበራዉንም በጋራ ግብረሀይል እንድታረጋግጡ እናሳስባለን፡፡

መንግሥት የህዝብ ኑሮ መረጋጋትን ማረጋገጥ፣ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ቀጣይነትን መጠበቅ እና የትራንስፖርት አገልግሎት በዘላቂ መልኩ እንዲጠናከር ያለውን ቁርጠኝነት ይቀጥላል።

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር

29/04/2026
 ''  Yanih Yan Siraglele Taqabiik Ugutak Qusba   Abtem Kasinna Takkay Ikkah Tama Tariifiy Yeyyeqenil Transport Makayinih...
26/04/2026

''

Yanih Yan Siraglele Taqabiik Ugutak Qusba Abtem Kasinna Takkay Ikkah Tama Tariifiy Yeyyeqenil Transport Makayinih Mari Madqak Amo Korak Isinnih Faxenim Nek Beetan Axcuk Akah Sahittanam Tambuliye,

👉 Laakin Isin Taaxigonu faxximtam Macaay?

Qimboh Madaqay Siinih Yeyyeqenil Taamitam Faxximtam Umattak More Sin Kinnim Ixiga

👉Kaaduk Makaayn Le Mari Madqa Asakaxxuk Madqal Tamitaanam Faxximta‼️

👉Ciggilak Safarah Yan ታሳፋሪ Taarif'ik Iroh Yan Mekla Ken Meklisiisenik Cinanam Faxximta, Makaayin Le Mari Toh Keenok Cineenik Kull Darifal Yanih Yan Tiraaf'ikih (Traffic )Warisak Madqal Ken Digalsiisanam Faxximta.

24/04/2026
Qafar Agatih Rakaakayih Doolatak Xiinissoh Abba Cajji Awel Arba Asaaki macsentá Awash magaalal saytun maqub leeh cugayso...
24/04/2026

Qafar Agatih Rakaakayih Doolatak Xiinissoh Abba Cajji Awel Arba Asaaki macsentá Awash magaalal saytun maqub leeh cugaysok phase two 155 milyoonuk daga takke lakqot 17.5kilo mitir Daga yakke baarisiyyi taama Qimmisiisen...

Kimaalih Ayro Qammi Baxa kee Awash Magaalah Caddol 7 Boolih Miyeeniik Daga takke Lakqot Bicseenih Yan Maqab lee Cugaysoosa Rakaakayak Naharsi Saqal Massakaxxa le Cajji Awwal Qarba kee Lee kee Elmo Malaak Dr injiner Habtaamu itafa elle geytimak Dooqayseenim tamixxige.

02/04/2026

የንግድ እና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር የነዳጅ አቅርቦት እና የዋጋ ማስተካከያን በተመለከተ የሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ዋና ዋና ነጥቦች፦
****************************

👉 ኢትዮጵያ የምትጠቀማቸውን የነዳጅ ምርቶች (ነጭ ናፍጣ፣ ቤንዚን፣ የአውሮፕላን ነዳጅ፣ ኬሮሲን እና ጥቁር ናፍጣዎች) የምታስገባቸው በዓለም አቀፍ ግልጽ ጨረታ ነው።

👉 ከኩዌት መንግሥት ጋር የ60% ነጭ ናፍጣ እና የ100% የአውሮፕላን ነዳጅ ግዥ ስምምነት ያለ ሲሆን ውሉም እስከ ዲሴምበር 31 ቀን 2026 ያገለግላል።

👉 በአሁኑ ወቅት የዓለም አቀፍ ጨረታ አሸናፊ የሆነው ቪቶል (Vitol) የተባለው ኩባንያ ለነጭ ናፍጣ እና ለቤንዚን የተወሰነ የሎጂስቲክስ ዋጋ (Premium) በማስከፈል በ360 ቀናት ዱቤ ነዳጅ እያቀረበ ይገኛል።

👉 በመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት ምክንያት የኩዌት አቅርቦት በመዘጋቱ እና የሆርሙዝ የባሕር ሰርጥ በመከልከሉ፣ ለአጣዳፊ ግዥ የሚወጣው ዋጋ እጅግ እንዲንር አድርጎታል።

👉 መንግሥት አቅርቦቱ እንዳይቋረጥ ነዳጅን በከፍተኛ ዋጋ እየገዛ ቢሆንም፣ የድጎማው ጫና ከ272 ቢሊዮን ብር በላይ በመድረሱ ድጎማውን በነበረበት መቀጠል አስቸጋሪ ሆኗል።

የድጎማ ጫናውን ለመቀነስ አዲስ የዋጋ ማስተካከያ የተደረገ ሲሆን፣ በዚህም መሠረት የችርቻሮ መሸጫ ዋጋው እንደሚከተለው ሆኗል፦

• ቤንዚን፦ 142.21 ብር
• ነጭ ናፍጣ፦ 163.09 ብር
• ኬሮሲን፦ 151.39 ብር
• የአውሮፕላን ነዳጅ፦ 150.48 ብር
• የቀጥታ ተጠቃሚዎች ነጭ ናፍጣ፦ 210.00 ብር

👉 አሁንም ቢሆን መንግሥት በአንድ ሊትር ነጭ ናፍጣ ላይ 71 ብር እንዲሁም በቤንዚን ላይ 32 ብር ድጎማ እያደረገ ባይሆን ኖሮ ከዚህ በእጅጉ ይበልጥ ነበር።

👉 የኢትዮጵያ የነዳጅ ዋጋ ከጎረቤት ሀገራት (ከኬንያ፣ ጅቡቲ እና ታንዛኒያ) ጋር ሲነፃፀር አሁንም ዝቅተኛ መሆኑ ነው።

👉 የነዳጅ አቅርቦት እና ስርጭቱን የሚመራ ቡድን የተደራጀ ሲሆን፣ ነዳጅን በቁጠባ እና በሕጋዊ የግብይት ሥርዓት ብቻ ለማሰራጨት ዝግጅት ተደርጓል።

👉 የነዳጅ አቅርቦት ቅድሚያ የሚሰጣቸው እንደ ጤና፣ ጸጥታ፣ የሕዝብ ትራንስፖርት፣ የኤክስፖርት አምራች ኢንዱስትሪዎች እና ግብርና ያሉ መሠረታዊ ዘርፎች ተለይተዋል።

👉 ኅብረተሰቡ ያለውን አስቸጋሪ ሁኔታ ተረድቶ ተገቢውን ድጋፍ እና ትብብር እንዲያደርግ መንግሥት ጥሪ አቅርቧል።

Address

Magala
Magale
015

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Magaale daqaarak kabxa kee sanaqatta giti merrayti daddoosih ku/buaxh posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share