Waajjira Misooma Qonnaa Aanaa Dawaa Cafaa/የደዋ ጨፋ ወረዳ ግብርና ልማት ጽ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Kemise
  • Waajjira Misooma Qonnaa Aanaa Dawaa Cafaa/የደዋ ጨፋ ወረዳ ግብርና ልማት ጽ/ቤት

Waajjira Misooma Qonnaa Aanaa Dawaa Cafaa/የደዋ ጨፋ ወረዳ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ግብርና ከማምረትም በላይ ነው !

በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን በደዋ ጨፋ ወረዳ የተመረተ የግራንድ ናይን ሙዝ ምስል :-
22/07/2026

በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን በደዋ ጨፋ ወረዳ የተመረተ የግራንድ ናይን ሙዝ ምስል :-

በደዋ ጨፋ ወረዳ የመኸር የዘር ብዜት ክላስተር ልማት በይፋ ተጀመረበአብክመ ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ደዋ ጨፋ ወረዳ በደኖ ቀበሌ የ2019 የመኸር እርሻ የዘር ብዜት ክላስተር ልማት ሥራ ዛ...
20/07/2026

በደዋ ጨፋ ወረዳ የመኸር የዘር ብዜት ክላስተር ልማት በይፋ ተጀመረ

በአብክመ ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ደዋ ጨፋ ወረዳ በደኖ ቀበሌ የ2019 የመኸር እርሻ የዘር ብዜት ክላስተር ልማት ሥራ ዛሬ በይፋ ተጀምሯል። ይህ ተግባር የዞናችንን የዘር አቅርቦት ለማጠናከር፣ የአርሶ አደሮችን ምርታማነት ለማሳደግ እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ትልቅ አስተዋጽኦ የሚያበረክት ወሳኝ እርምጃ መሆኑ ተገልጿል።

የሥራው ማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓት በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ሃላፊ አቶ ጀማል አሊ፣ በደዋ ጨፋ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አማን ኢብራሒም፣ የወረዳው ግብርና ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ ኑሩ መሃመድ፣ የተለያዩ የዞንና የወረዳ አመራሮች፣ ባለሙያዎች እና አርሶ አደሮች በተገኙበት ተካሂዷል።

በደኖ ቀበሌ በስፋት የተጀመረው የዘር ብዜት ክላስተር ልማት በቀጣይም በሌሎች ቀበሌዎች በሰፊው እንደሚተገበር የተገለጸ ሲሆን፣ የተጀመረው ሥራ ከመሬት ዝግጅት እስከ ምርት ስብሰባ ድረስ በሙሉ ፓኬጅ ቴክኖሎጂ፣ በቅርብ ክትትልና በተቀናጀ ድጋፍ እንዲከናወን አቅጣጫ ተሰጥቷል።

በተለይም በክላስተሩ ውስጥ የሚገኙ አቅመ ደካማና የበሬ እጥረት ያለባቸው አርሶ አደሮች ከማህበረሰቡ፣ ከአመራሩ እና ከባለሙያዎች ትብብርና ድጋፍ በማግኘት ከሌሎች አርሶ አደሮች ጋር እኩል ተሳትፎ እንዲያደርጉ የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ሃላፊ አሳስበዋል።

የልማቱ ፍሬ ሁሉንም አርሶ አደር የሚጠቅም እንዲሆን ማንም ከተግባሩ ወደ ኋላ እንዳይቀር ትኩረት እንዲሰጥም አቅጣጫ ተሰጥቷል።

በመጨረሻም የተጀመረው የዘር ብዜት ሥራ የታለመለትን ውጤት እስኪያስመዘግብ ድረስ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት፣ በተጠያቂነት እና በቀጣይነት የመስክ ክትትልና ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

"የጥራት ዘር መነሻው የተጠናከረ የዘር ብዜት ነው፤ የተጠናከረ የዘር ብዜት ደግሞ የተሻለ ምርት፣ የተሻለ ገቢ እና የተረጋገጠ የምግብ ዋስትና መሰረት ነው!"

 የግብርና ባለሙያችን እንድሪስ አብዱ አደም በደረሰበት ከባድ የሞተር አደጋ ምክንያት ከፍተኛ የአካል ጉዳት ደርሶበታል። በአሁኑ ሰዓት ቀጣይነት ያለው ሕክምና እየተደረገለት ሲሆን ለሕክምናው ...
16/07/2026


የግብርና ባለሙያችን እንድሪስ አብዱ አደም በደረሰበት ከባድ የሞተር አደጋ ምክንያት ከፍተኛ የአካል ጉዳት ደርሶበታል። በአሁኑ ሰዓት ቀጣይነት ያለው ሕክምና እየተደረገለት ሲሆን ለሕክምናው የሚያስፈልገውን ወጪ ለመሸፈን የሁላችንም ትብብር ያስፈልጋል።
"ብዙ እጆች ትንሽ ሸክም ያደርጋሉ። እያንዳንዱ የሚችለውን በማድረግ ለወንድማችን ተስፋ እንሁን። ትንሽ ድጋፍም ቢሆን ትልቅ ለውጥ ሊያመጣ ይችላል።
የባንክ ሒሳብ ቁጥር:
1000294884298
የሒሳብ ባለቤት: እንድሪስ አብዱ አደም
እባክዎ ይህን መልእክት በመለጋት (Share) ለብዙ ሰዎች እንዲደርስ ያግዙ።

 🤲 Balaa tasaa Guyyaa kaleessaa Obboleessa keenya indiris Abduu Adam irratti qaqqabeen Yaala baqaqsanii yaaluu yeroo tok...
16/07/2026

🤲
Balaa tasaa Guyyaa kaleessaa Obboleessa keenya indiris Abduu Adam irratti qaqqabeen Yaala baqaqsanii yaaluu yeroo tokkootiif baasii maallaqaa 150,000 (Kuma dhibba tokkoo fi shantamaa) ol Gaafatamee Hospitaala Xoosaatti yaalamaa jira waan taheef jaalleewwan obboleewwan qaqqaliin deeggarsa obboleessummaa keessan cimsitanii itti fufun obboleessa keenya bira dhaabbachuun jirra jedhaaniin waamicha dhaamsa obboleessummaati.
Dhugoon Shantamni nama tokkoof ba'aa dha.
Nama Shantamaaf Miidhaginaa. akkuma jedhamu jirra jedhanii.
Yaa Rabbii🤲 Yaa ilaahii🤲 Yaalli baqaqsanii yaaluu Obbolleessa keenyaa Milkiidhaan xumuramee gammachuudhaan Nutti Haa Makamuu🤲
✍️1000294884298 indiriis Abdu Adam

"የአየር ንብረት ተፅዕኖን የሚቋቋም ግብርናን መገንባት የባለድርሻ አካላት እና የማህበረሰቡ የጋራ ተልዕኮ ነው"አቶ ደረጀ ማንደፍሮ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ      ዲዛይንና ግራፊክስ...
08/07/2026

"የአየር ንብረት ተፅዕኖን የሚቋቋም ግብርናን መገንባት የባለድርሻ አካላት እና የማህበረሰቡ የጋራ ተልዕኮ ነው"

አቶ ደረጀ ማንደፍሮ
የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ





ዲዛይንና ግራፊክስ : ጌታቸው ታፈረ

08/07/2026
Gandi goboyyaa kilaastera muuziitiif hojii bolla qotuu warraaqsaan eegaleera.የጎበያ ቀበሌ የሙዝ ክላስተር ለማሳካት የጉድጓድ ቁፋሮ ንቅናቄ ጀምሯ...
08/07/2026

Gandi goboyyaa kilaastera muuziitiif hojii bolla qotuu warraaqsaan eegaleera.
የጎበያ ቀበሌ የሙዝ ክላስተር ለማሳካት የጉድጓድ ቁፋሮ ንቅናቄ ጀምሯል።

“በየደረጃው የሚገኙ የግብርና አመራሮችና ባለሙያዎች የፀረ-ድህነት ትግሉ መሐንዲሶች ናቸው”  ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር)በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አስተባባሪ      ዲዛይንና...
08/07/2026

“በየደረጃው የሚገኙ የግብርና አመራሮችና ባለሙያዎች የፀረ-ድህነት ትግሉ መሐንዲሶች ናቸው”

ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር)
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አስተባባሪ





ዲዛይንና ግራፊክስ : ጌታቸው ታፈረ

🌾🌱🌾🌱🌾🌱🌾🌱🌾🌱

08/07/2026

Address

Dewa Chefa
Kemise

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Waajjira Misooma Qonnaa Aanaa Dawaa Cafaa/የደዋ ጨፋ ወረዳ ግብርና ልማት ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share